YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
🎁 #ArtLand_gifts 🎁

✿ "እማይረሱ ስጦታዎችን ለሚወዷቸው" 🎁

❤️❤️HAPPY VALENTINE'S DAY❤️❤️

✔️የወደዱትን "ፎቶ ወይም ምስል" እንጨት(MDF) እና ቆዳ(ሌዘር) ላይ እንሰራለን 👌

እንዲሁም የተለያዩ GIFT PACKAGES🎁 አዘጋጅተናል❤️

🔘☎️contact us: 0931465618
🔘For Order @Artlandgifts

🚚 ይዘዙን ያሉበት ድረስ እናደርሳለን🏍🏍

ከአዲስ አበባ ውጪ ላሉ ደንበኞቻችን በ EMS / DHL እናደርሳለን 📦

Join👇
@artlandengraving
Forwarded from YeneTube
#የኢትዮጵያ_ታሪክ_ከንግስተ_ሳባ_እስከ_አዲስ_አበባ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

የኢትዮጵያን ታሪክ ከንግስተ ሳባ እስከ አዲስ አበባ የሚቃኘውና በአማዞን የምንጊዜም የኢትዮጵያ ታሪክ መጻህፍት ሽያጭ ከፍተኛ ደረጃን የተቆናጠጠው መጽሐፍ በአማርኛ ተተርጉሞ ቀረበ፡፡

ይህ አለም በጣም ያደነቀው መጽሐፍ ኢትዮጵያን በትናንት፣ በዛሬና በነገ መነጽር የሚያሳይ የ30 ዓመታት ምርምር ውጤት የሆነ በቅጡ ሊነበብ የሚገባው መጽሐፍ ነው፡፡

የአጼ ኃይለስላሴ የልጅ ልጅ ልጅ የሆኑት ልዑል አስፋ ወሰን አስራቴ ስለመጽሐፉ እንዲህ ነው ያሉት፡-

“አንብቤ ለመጨረስ ሶስት ሌሊቶች ብቻ ነው የወሰደብኝ፡፡ ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ጥንታዊ፣ ኃይማኖታዊ ልምምድ ላይ ባልተለመደና ቀልብን በሚያነሆልል ሁኔታ የተጻፈ ነው፡፡ መጽሐፉ በአፍሪካ ምድር ከሚገኙ መሳጭ ስልጣኔዎች መካከል አንዱ ስለሆነው የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለንን ግንዛቤ የሚያፋፋ እጽ ነው፡፡”

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ መልዕክተኛ ዛሬ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ይገናኛሉ!

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ በመሆን የተሾሙት ዴቪድ ሳተርፊልድ ዛሬ ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚገናኙ ተገለጸ።ዴቪድ ሳተርፊልድ እና የኢትዮጵያ መንግስት ባለስጣናት የሚገኛኙት በአዲስ አበባ ነው ተብሏል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው ልዩ መልዕክተኛው ከመንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣ በኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ከአፍሪካ ህብረት አመራሮች፤ ከሰብዓዊ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል።

የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሐመድ ከሰሞኑ በኢትዮጵያ በአራት ክልሎች ጉብኝት በማድረግ ወደ አሜሪካ መመለሳቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የተከሰተውን ጦርነት በሰላም ለመፍታት ንግግሮች መቀጠላቸውን ገልጸው ነበር።የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛም በዚሁ የአዲስ አበባ ቆይታቸው በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ጦርነት በሰላም በሚፈታበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa
የብርን የምንዛሪ አቅም በማዳከም የውጪ ንግድን ለማሳደግ የተደረገው ሙከራ የተፈለገውን ውጤት አላስገኘም ተባለ!

የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ መንግስት የኢኮኖሚ ተሐድሶ ፕሮግራም ተግባራዊ የሆነውን የብር የምንዛሪ አቅምን በማዳከም የውጪ ንግድን የማሳደግ አሰራር ዕጣ ፈንታ ለመወሰን የዳሰሳ ጥናት እየተደረገ መሆኑን ዋዜማ ከሁነኛ ምንጮች ሰምቻለሁ ብላለች።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከፍተኛ የስራ ሐላፊ እንደተናገሩት ብርን ከሀገሪቱ የንግድ ሸሪኮች መገበያያ ገንዘብ አንጻር እየተተገበረ ያለውን ዕለታዊ ዋጋ የማዳከም አሰራር የሚገመግም የዳሰሳ ጥናት እየተሰራ ነው።በጥናቱ ላይ በመመርኮዝም ብርን በየዕለቱ የማዳከሙ ነገር “ይቀጥል” ወይንስ “አይቀጥል” የሚለው ላይ ከውሳኔ ይደረሳል።

ዕለታዊ የብርን የውጭ ምንዛሬ ተመን ከንግድ አጋር ሀገራት መገበያያ አንጻር በፍጥነት የማዳከሙ እርምጃ ከሁሉም የማክሮ ኢኮኖሚ መመዘኛዎች አንጻር የማያዋጣ ከሆነ ብሄራዊ ባንኩ ሌሎች አማራጮችን ለመከተል ይገደዳል ተብሏል።

ዝርዝሩ : https://bit.ly/34EX7jp

@YeneTube @FikerAssefa
በ2014 ግማሽ በጀት አመት ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ሙከራ በኢትዮጵያ መደረጉ ተገለጸ!

በግማሽ በጀት ዓመት ከ3 ሺህ 400 በላይ የሚደርሱ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ገልጸዋል።በበጀት ዓመቱ የሳይበር ጥቃትን የመመከት አቅም 96 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ለቆሻሻ ተብሎ የተለኮሰ እሳት በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

ቅዳሜ እና እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰ ሶስት ድንገተኛ የእሳት አደጋዎች አራት ሰዎች የመቁሰል አደጋ ሲደርስባቸው በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡አንደኛ የእሳት አደጋ የደረሰው በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት ሂርቱ ሞጆ ተብሎ በሚጠራው የጥብቅ ደን ውስጥ ነው፡፡የአደጋው ምክንያት ደግሞ ለቆሻሻ ተብሎ የተለኮሰ እሳት እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፁት በአደጋው 200 ሺህ ብር የሚደርስ ንብረት ሙሉ በሙሉ ለውድመት ተዳርጓል ብለዋል፡፡ሌላኛው አደጋ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጎማ ተራ አካባቢ በሚገኝ አንድ አነስተኛ ሆቴል ቤት ሲሆን በዚህ አደጋ ምክንያት 300 ሺህ ብር የሚጠጋ ንብረት መውድሙ አቶ ንጋቱ ተናግረዋል፡፡እንደዚሁም 10ሚሊየን ብር የሚጠጋ ንብረት ደግሞ ማዳን ተችሏልም ብለዋል፡፡

ሌላኛው አደጋ የእሳት አደጋ የደረሰው ደግሞ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በእፅዋት ማእከል ሲሆን የአደጋው አይነትም የሰደድ እሳት ነው፡፡በዚህኛው የእሳት አደጋ የተነሳም 10ሺህ ብር የሚደርስ ንብረት ለውድመት ተዳርጓል ብለዋል፡፡እንደዚሁም 10ሚሊየን ብር የሚጠጋ ንብረት ከአደጋው መታደግ እንደተቻለ የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለጣቢያችን ገልፀዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
“በዋልታ የፌስቡክ ገጽ ላይ የደረሰዉ ጥቃት ከአድሚኖች እና ኤዲተሮች ጋር የተያያዘ ነው።“:-የኢ.መ.ደ.ኤ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው

በዋልታ የፌስቡክ ገጽ ላይ የደረሰዉ ጥቃት ከአድሚኖች እና ኤዲተሮች ጋር የተያያዘ ጥቃት መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ገለጹ።

በዋናነት ለጥቃቱ ሁለት ምክንያቶችን ያስቀመጡት ዋና ዳይሬክተሩ፤ አንዱ የዋልታ የፌስቡክ ገጽ ዋና አድሚን አገር ዉስጥ ካለመሆኑ ጋር የተያያዘ እንደሆነ እና ሁለተኛዉ ምክንያት ደግሞ የሚዲያዉን የፌስቡክ አካዉንት እንዲያንቀሳቅሱ ሃላፊነት በወሰዱ አካላት ስህተት መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይም አንዱ የፌስቡክ ኤዲተር የተላከለትን አጥፊ ተልዕኮ ያለዉን ሊንክ ያለ ጥንቃቄ በመክፈት ለመረጃ ጥቃቱ መፈጸም ሚና እንደነበረዉ ዶ/ር ሹመቴ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
1👍1
በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አዋሳኝ አካባቢ የተነሳውን እሳት ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ!

የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን በሚያዋስነው አካባቢ ከሁለት ቀናት በፊት የተነሣው የእሳት ቃጠሎ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን በኦሮሚያ ደን እና ዱር አራዊት የባሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የእሳት ቃጠሎው የተነሣው በባሌ ዞን በርበሬ ወረዳ ውስጥ ልዩ ስሙ “በስመና ኦዶቡሉ” አካባቢ መሆኑን የጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ ቀነአ ዲዳ ገልጸዋል።በሕገ ወጥ ከሰል አክሳዮች፣ ማር ቆራጮች እና ለእንስሳት የግጦሽ ሳር እንዲበቅል እሳት በሚለኩሱ ግለሰቦች ቃጠሎ በተደጋጋሚ እንደሚከሰት አስታውሰዋል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የ200 ሺ ሜትሪክ ቶን የስኳር ግዢ ጨረታ የመርከብ መጫኛ ዋጋ ባለመቅረቡ ተራዘመ!

የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ያወጣው የ200 ሺ ሜትሪክ ቶን አለምአቀፍ ጨረታ ባሳለፍነው ሀሙስ የካቲት 3 እንደሚከፈት ቢጠበቅም የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት (ኢባትሎአድ) የጭነት ጠቋሚ ዋጋ ባለማቅረቡ ሊተላለፍ ችሏል፡፡ኢባትሎአድ ጠቋሚ ዋጋ ለምን እንዳላቀረበ ኮርፖሬሽኑ ማብራሪያ እንዲሰጠው የጠየቀ መሆኑን ጠቅሷል፡፡በተመሳሳይ ኢባትሎአድ ምላሽ እንደሚሰጥ ለካፒታል አረጋግጧል፡፡

በተጨማሪም የኢባትሎአድ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ለካፒታል እንዳብራሩት ድርጅታቸው የመጫኛ ዋጋ ማቅረብ የሚኖርበት ለኮርፖሬሽኑ መሆን እንደነበረበት አስታውቀው፡፡በጨረታ ሂደቱ ግን ዋጋ እንድንሰጥ የተጠየቅነው በተጫራቾች ነው ብለዋል፡፡ይህም ለድርጅቱ ጎጂ ነው በማለትም ለምን የዋጋ ጠቋሚ እንዳላቀረቡ ገልፀዋል፡፡ሆኖም የኮርፖረሽኑ ከፍተኛ አመራር ለካፒታል ችግሮችን በጋራ እንፈታለን ሲሉ ገልፀው፤ ያጋጠመውን እክል የመቅረፍ ተስፋ እንዳለ አመልክተዋል፡፡

ጨረታው በድጋሚ የካቲት 9 ቀን እንደሚከፈት የታወቀ ሲሆን ኢባትሎአድ ዋጋ ያቅርብ አያቅርብ የተባለ ነገር የለም፡፡ኮርፖሬሽኑ እያደገ የመጣውን የስኳር ፍላጎት ለመሙላት ከአገር ውስጥ ምርት በተጨማሪ በየአመቱ እስከ 350 ሺ ሜትሪክ ቶን ስኳር ከውጭ በግዢ ያስገባል፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
ባልደራስ የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባልና የትምህርት ቢሮ ሃለፊው በህግ እንዲጠየቁ ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤ አስገብቺያለሁ አለ!

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክሰራሲ ፓርቲ ለአሻም የላከው ደብዳቤ አቶ ዘላለም ሙላቱ በህግ እንዲጠየቁ ፓርቲው ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ ማቅረቡን ተመልክታለች።አቶ ዘላለም የካቲት 3 ቀን 2014 ዓ.ም በምክር ቤቱ ባደረጉት ንግግር ” በፊንፊኔ ዙሪያ የሚገኘው የኦሮሚያ ልዩ ዞን፣ አዲስ አበባ ከርሷን ሞልታ ፈርሷን የምትጥልባቸው ናቸው” በማለት አደባባይ ዘልፈዋል ሲል ባልደራስ ሃለፊውን ወንጅሏል፡፡

ይህን ተከትሎ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከምክር ቤቱ አባልነታቸው የሚነሱበትንና የማሟያ ምርጫ የሚደረግበትን እንቅስቃሴ ጀምሪያለሁ ብሏል፡፡ ”በዚህም መሠረት፣ ምርጫ ቦርድ ሂደቱን የማስጀመሪያ ህጋዊ ድጋፍ እንዲሰጠው ” ባልደራስ ጠይቋል፡፡ደብዳቤውን የፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ እና የአደረጃጀትጉዳዮች ሃለፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል በቦርዱ ዋና ፅ/ቤት ማስገባታቸውን ባልደራስ አስታውቋል፡፡

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
#ሀብት_ያለው_አእምሮህ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

የእለት ጉርስህን ለማግኘት እየተጣጣርክ ወይም ያለህ ሀብት እንዲበዛ የምታደርግበትን መንገድ እየፈለግክ ነው?

እንግዲያውስ ሀብት ያለው አእምሮህ የተሰኘው አዲሱ የዶ/ር ጆሴፍ መርፊ መጽሀፍ ይረዳሀል፡፡ መጽሐፉ “የሁሉም ሀብት መነሻ አእምሮ ነው” ይለናል፡፡

“የምትኖረው በአእምሮህ ውስጥ ነው፡፡ ሀብታም ወይም ደሀ፣ ለማኝ ወይም ሌባ የምትሆነው እዚያ ነው፡፡ በህይወት ውስጥ የምትፈልጋቸውን ነገሮች የመፍጠር ኃይል እንዳለህ ስትገነዘብ ታላቅ ዋጋ ያለው እንቁ እንዳለህ ታውቃለህ፡፡ በውስጥህ ያለው ሀብት እና ኃይል በጭራሽ የሚቀንስ ስላልሆነ አንተ ከምታስቀምጠው ገደብ በስተቀር የአእምሮህ ሀብት ገደብ አያውቅም፡፡”

ከዝቅታ ህይወት ወደ ከፍታ ህይወት ተሸጋግረህ አንገትህን ቀና ለማድረግም ሆነ፣ በሕይወትህ ውስጥ የሚገባህን ብልጽግና ለማግኘት ይህ መጽሐፍ እንዴት የድብቁን አእምሮህን ኃይል መጠቀም እንዳለብህ ያስተምርሀል፡፡

#ሀብት_ያለው_አእምሮህ መጽሐፍ
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የአገራዊ ምክክር ሂደቱ ለጊዜው ቆሞ በአካሄዱ ላይ እንደገና ውይይት እንዲደረግበት መጠየቁን የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ራሄል ባፌ ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ተናግረዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ይህንኑ ጥያቄ ያቀረበው፣ ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ባስገባው ደብዳቤ ነው። ምክር ቤቱ የአገራዊ ምክክር ሂደቱን ግልጽ እና አካታች ለማድረግ እንዲቻል ምክር ቤቱ ምላሽ ሊያገኙ ይገባቸዋል ባላቸው ጥያቄዎች ዙሪያ እንደገና ውይይት እንዲደረግ የጠየቀው፣ የምክር ቤቱ አባል የሆኑ 45 ፖለቲካ ፓርቲዎች በጉዳዩ ላይ ግምገማ ካደረጉ በኋላ እንደሆነ ተገልጧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከአፍሪካ ሀገራት ባንኮች ጋር የገንዘብ ልውውጥ ለማድረግ ስምምነት ውስጥ መግባቱን ሪፖርተር አስነብቧል።

ኢትዮጵያ አፍሪክሲም ባንክ የተባለው የፓን-አፍሪካ ባንክ በዘረጋው መርሃ ግብር ከታቀፈች የገንዘብ ተቋማትና ንግድ ድርጅቶች ለሚገበያዩዋቸው የውጭ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ብር ክፍያ መቀበል ወይም መፈጸም ይችላሉ። ባንኩ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ንግድን ማሳደግ እንዲችሉ እስከ 500 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሊሰጥ እንደሚችልም ተገልጧል። መንግሥት ባንኩ ለኮሮና ወረርሽኝ ማገገሚያ ከመደበው ገንዘብ ብድር ለማግኘት ድርድር ላይ እንደሆነም ዘገባው ጠቅሷል። አፍሪክሲም ባንክ የተቋቋመው በአፍሪካ ሀገራት መካከል የንግድ ልውውጥን ለማፋጠን፣ አፍሪካዊያን ባንኮች የንግድ ልውውጥ ክፍያ ለመፈጸም በዓለማቀፍ ባንኮች ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ለማስቀረት እና የንግድ ልውውጥ ወጭን ለመቀነስ ነው።

[Reporter/Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራሉ መንግስት ”ከክንብንቡ ወጥቶ፣ ከእንቅልፉ ነቅቶ ዐብይና ቀዳሚ” ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲል ኢህአፓ አሳሰበ!

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ(ኢህአፓ) ለአሻም በላከው መግለጫ ”መንግስት የዜጎችን በህይወት የመኖር ዋስትና ማስጠበቅ፣ መንግስታዊ ግዴታው ነው፤ እንዲሁም ቀዳሚ ተግበሩ ነው” ሲል ሃላፊነቱን አስታውሷል፡፡ይሁንና ”አሁን አሁን እንደምናስተውለው ቅድሚያ የሚያገኘው ተግባር ሌላ ሌላው እየሆነ፣፣ የዜጎች አጉል ሞትን እያለማመደን ይሆን?” የሚል ጥያቄ እንዳጨረበት ፓርቲው በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

ፓርቲው አካሄዱን ’የልጆች ጨዋታ” ሲል በመጥራት ”መንግስት ከክንብንቡ ወጥቶ፣ ከእንቅልፉ ነቅቶ፣ ዐብይና ቀዳሚ ሚናውን እንዲወጣ አሳስቧል፡፡ኢህአፓ ለአሻም በላከላት መግለጫ በአፋር ክልል በሽብርተኛ ድርጅትነት በተፈረጀው ህወሓት ”ጥቃት የተከፈተባቸው ነዋሪዎች መንግስት ድርስልን ቢሉም፤ ጩኽታቸው ሰሚ አላገኝም’ ብሏል፡፡

ፓርቲው አክሎም ” ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት አገሩንና ሕዝብን በመታደግ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደረገውን “ፋኖ” መተናኮስ መጀመራቸው እያስተዋልን ነው፡፡”ሲል ከስሷል፡፡

”ሀገር አሁን የምትሻው እንደ ክፉ ጎረቤት ሲያልክፍ ሲያገድም የሚያሽሟጥጥ አመራር ሳይሆን በስክነትና በእርጋታ፣ በመርህና በቁርጠኝነት መውጫውን የሚተልም፣ ነገን የሚያልም ሰው ነው፡፡’” ሲል መንግስትን በፅኑ ተችቷል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ሌላኛው በሽበርተኝነት የተፈረጀው ድርጅት ኦነግ ሸኔ እያደረሰ ያለውን የጅምላ ግድያ ያስታወሰው ፓርቲው ” ፈላጊ መንግስትና ዘመድ የሌላቸው ወገኖቻችን ይሄው የጅምላ መቃብራቸው እየተገኘ እንደሆነ እየሰማን ነው፡፡” ብሏል፡፡ፓርቲው በመግለጫው ”እንዲህ ያለው አካሄድ ሰነባብቶ ብልጽግናና የሚመራውን መንግሥት ከባድ ዋጋ የሚያስከፍለው መሆኑን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡’ ሲል አስጠንቅቋል፡፡

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉 https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
Forwarded from YeneTube
Kdamie.com ንግድ እና አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ፡፡
#ጅምላና ችርቻሮ ንግዶችን አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ከጨረታና ፐርፎርማ እንዲሁም የስራ ማስታወቂያዎች እና መረጃዎች ጋር፣
#በጉዞዎ መዳረሻዎችን ከነ አስጎብኚዎች እና የጉዞ ወኪሎች ጋር
#የእንግዳ ማረፊያ ሆቴልና ሪዞርቶችን ፈርኒሽድ አፓርታማዎችን ገሰት ሀውሶችን እና ፔንሲዮኖችን
ለመኖሪያ የሚሆኑ ቪላ እና ኮንዲሚኒየሞችን
#በሁሉም የገበያ ማዕከላት ለሱቅ እና ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎችን ሳይዞሩ ሳይደክሙ የሚያገኙበት Kdamie.com
#በንግድ በቱሪዝም እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ለሆኑ ድጅቶችም ኑ አብረን እንስራ ይሎታል Kdamie.com

ከኛ ጋር መስራት ንግድና አገልግሎቶን ማዘመን፣ደንበኞችዎን ባሉበት ማግኘት ነው!! Kdamie.com
#በሁሉም የማህበራዊ ገፆች
Telegrame እና whatsup - +251-911705126
Kdamie.com - https://tttttt.me/+K7sPcHhHYy44NDI0
facebook - https://www.facebook.com/Kdamie-107188781818909
Instagram - https://www.instagram.com/p/CZkVH-FAd11/?utm_source=ig_web_copy_link
Email - kdamiesells@gmail.com
phone:- +251911705126/+251916821091 ያገኙናል፡፡
Forwarded from YeneTube
#የኢትዮጵያ_ታሪክ_ከንግስተ_ሳባ_እስከ_አዲስ_አበባ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

የኢትዮጵያን ታሪክ ከንግስተ ሳባ እስከ አዲስ አበባ የሚቃኘውና በአማዞን የምንጊዜም የኢትዮጵያ ታሪክ መጻህፍት ሽያጭ ከፍተኛ ደረጃን የተቆናጠጠው መጽሐፍ በአማርኛ ተተርጉሞ ቀረበ፡፡

ይህ አለም በጣም ያደነቀው መጽሐፍ ኢትዮጵያን በትናንት፣ በዛሬና በነገ መነጽር የሚያሳይ የ30 ዓመታት ምርምር ውጤት የሆነ በቅጡ ሊነበብ የሚገባው መጽሐፍ ነው፡፡

የአጼ ኃይለስላሴ የልጅ ልጅ ልጅ የሆኑት ልዑል አስፋ ወሰን አስራቴ ስለመጽሐፉ እንዲህ ነው ያሉት፡-

“አንብቤ ለመጨረስ ሶስት ሌሊቶች ብቻ ነው የወሰደብኝ፡፡ ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ጥንታዊ፣ ኃይማኖታዊ ልምምድ ላይ ባልተለመደና ቀልብን በሚያነሆልል ሁኔታ የተጻፈ ነው፡፡ መጽሐፉ በአፍሪካ ምድር ከሚገኙ መሳጭ ስልጣኔዎች መካከል አንዱ ስለሆነው የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለንን ግንዛቤ የሚያፋፋ እጽ ነው፡፡”

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
🇭🇺የስራ ጉዞ ወደ #Hungary 🇭🇺
#Schengen_visa

👉 የሚሰራበት አገር - Budapest, Hungary
👉 የስራው አይነት - Construction work
👉 የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week
👉 የስራ ሰዓት - 8 - 10 hr/day
👉 የወር ደሞዝ - €1500 and more
👉 ፆታ - ወንድ
👉 ዕድሜ - 18 እስከ 45
👉 መኖሪያ ቤት - በነፃ
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው

#30_persons

#Requirements
👉 Passport
👉 Photo


Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
info@sabinaadvisor.com
http://Sabinaadvisor.com
https://tttttt.me/sabinavisaa
#ጅግጅጋ

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና ጅግጅጋን አስመልክቶ የክልሉ የኮሙኒኬሽን ቢሮ በተሰጠ መግለጫ!!

"በአሁኑ ወቅት ጅግጅጋ ከተማን ጨምሮ መላው የሶማሌ ክልል እንደ ወትሮው ሁሉ ሰላም እና መረጋጋት የሰፈነ ሲሆን፣ በአንዳንድ ቦታዎች ፀረ ለውጥ የሆኑና በሙስና እንዲሁም በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ለውጥ አደናቃፊ አካላት በድብቅ ግንኙነት ሲያደርጉ ተደርሶባቸው ከመንግስት መዋቅር የወጡ ሀይሎች ሰላም ለማደፍረስ ያደረጉት ሙከራ ከሰላም ወዳዱ ህዝባችን ጋር በመተባበር መክሸፉን እንገልፃለን። " ብሏል።

አመሻሹን ጅግጅጋ ከተማ ውስጥ ረብሻ፣ አለመረረጋጋትና መፈንቅለ መንግሥት እንዳለ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ግን ፍፁም ሀሰት መሆኑንም ክልሉ ገልጿል።

የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ በመግለጫ የሶማሌ ክልል መንግሥት ከሰላም ወዳዱ ህዝባችን ጋር በመሆን የህዝባችንን ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንደማይታገስና አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ እንገልፃለን ብሏል።

ምንጭ፣ የሶማሌ ክልል ኮምዩኒኬሽን ቢሮ
@Yenetube @Fikerassefa