YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተሰጣቸው

የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተሰጣቸው።

ዛሬ በተካሄደ ስነስርዓት ፥ ውጊያ ለመሩ ፣ ሀይል ለመሩ ፣ ድልና ውጤት ላስገኙ ከፍተኛ የጦሩ መኮንኖች በየደረጃው የማዕረግ ዕድገት ተሰጥቷል።

በዚህም መሰረት 1 የፍልድ ማርሻል ማዕረግ ፣ 4 የሙሉ ጀነራል ማዕረግ ፣ 14 የሌተናል ጀነራል ማዕረግ፣ 24 የሜጀር ጀነራል ማዕረግ እና 58 የብርጋዴር ጀነራል ማዕረግ ተሰጥቷል።

የጀነራል መኮንኖቹ ሹመት በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አብይ አሕመድ አቅራቢነት በርዕሰ ብሄር ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ነው የተሰጠው።

©ኤፍ ቢ ሲ
@Yenetube @Fikerassefa
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ፥ በኢትዮጵያ ቁልፍ ተቃዋሚዎችን ጨምሮ በርካታ እስረኞች ከእስር መፈታታቸውን በደስታ እቀበላለሁ ብለዋል።

ዋና ፀሀፊው ፥ ሁሉም ወገኖች ግጭት እንዲቆምና ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት በማድረግ ፣ እንዲሁም ተአማኒና ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይትና የእርቅ ሂደት እንዲጀመር በመስማማት ይህን ትልቅ የመተማመን ግንባታ ሂደት እንዲያጎለብቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል።

ጉተሬዝ ፥ በኢትዮጵያ ግጭት እንዲቆም እና ሰላምና መረጋጋትን ወደነበረበት ለመመለስ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በንቃት እሰራለሁ ሲሉም አሳውቀዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ከፍትህ ሚኒስቴር ክሳቸው ተቋርጦ በተፈቱ እስረኞች ዙሪያ የተሰጠ ማብራሪያ

መንግስት የተወሰኑ እስረኞችን ክስ በማቋረጥ ከእስር መፍታቱ የአገራዊ ምክክሩን አካታችነት እና ሰብአዊነትና ርህራሄን ታሳቢ ያደረገ ውሳኔ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር ገለጸ።

ከፖለቲካ ልሂቃን አልፈው ወደ ማህበረሰቡ እየተንጸባረቁ ያሉ ያለመግባባት ችግሮችን በአገራዊ ምክክር ከስር መሰረቱ ለመመፍታት በመደበኛ ፍትህ ብቻ ሳይሆን በተሃድሶ የሽግግር ማዕቀፍ እልባት መስጠት ያስፈልጋል ተብሏል።

የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፤ መንግስት በትናንትናው እለት የተወሰኑ እስረኞችን መፍታቱን በተመለከተ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው የተያዙ እስረኞችን በመፍታት ሂደት 'ምህረት' የሚደረገው በሕግ አውጭ አካል ሲሆን ይቅርታ ደግሞ በይቅርታ ቦርድ ጥያቄ መሰረት በአገሪቷ ፕሬዝዳንት በኩል የሚፈፀም መሆኑን አስረድተዋል።

በመሆኑም በትናንትናው እለት መንግስት ይፋ ያደረገው እስረኞችን የመፍታት እርምጃ ምህረትም ሆነ ይቅርታ ሳይሆን በፍርድ ቤት ክርክር ሂደት ላይ ያለን ጉዳይ ክስ የማቋረጥ ውሳኔ መሆኑን ገልጸዋል።

የክስ ማቋረጥ ውሳኔው የተወሰነው በሶስት መዝገቦች ሲሆን ሁሉቱ መዝገቦች በአቶ ጃዋር መሃመድና በአቶ እስክንድር ነጋ ስም ያሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በሁለቱ መዝገቦችን ክስ የማቋረጥ ውሳኔ ሁለቱ ግለሰቦች በርካታ ተከታይ ያላቸው የፖለቲካ አመራሮች በመሆናቸው ለአገራዊ ምክክር መድረኩ አካታችነትና አሳታፊነት የሚኖረውን ፋይዳ ታሳቢ ማድረጉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

'አገራዊ ምክክር በአንድ አገር ከብዙ ዘማናት አንድ ጊዜ የሚደረግ ነው' ያሉት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያም እስካሁን ሁሉን አካታች አገራዊ ምክክር ተካሂዶ እንደማያውቅ ገልጸዋል።

በዚህም እስረኞችን የመፍታት ውሳኔው 'ሁሉም ህብረተሰብ ተሳትፌበታለሁ' የሚለው አሳታፊና አካታችና ቅቡልነት ያለው የምክክር መድረክ እንዲሆን ለማስቻል መንግስት የሄደበት እርቀት ስለመሆኑ አንስተዋል።

በሶስተኛ የክስ መዝገብ ደግሞ በእነ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ስም የተካተቱ ስድስት ግለሰቦች ከጤና ችግርና ከዕድሜ መግፋት አንጻር ጉዳያቸው ታይቶ ለሰብዓዊነትና ለርህራሄ ሲባል ከእስር እንዲፈቱ መደረጉን አብራርተዋል።

በመዝገቡ የተካተቱ ተከሳሾች ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራር የሰጡ ግለሰቦቦች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ከእስር እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ስድስት ግለሰቦች የአሸባሪው ቡድን ስራ አስፈጻሚ አባል ያልነበሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በክስ መዝገቡ የተካተቱ ሌሎች ተከሳሾች የክስ ሂደቱ ግን ይቀጥላል ብለዋል።

አገር መልከ ብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ ስትገባ ችግሮቹን ለመፍታት በመደበኛ የፍትሕ ስርዓቱ መሰረት መፍትሄ ስለማያገኙ የሽግግርና የተሃድሶ ፍትህ ተመራጭ የሚደረግበት አውድ እንዳለ ጠቅሰዋል።በዚህም በኢትዮጵያ ባለው ነባራዊ ሁኔታ የአገር ህልውና ለማስጠበቅ በኢትዮጵያ ከመደበኛው ፍትህ ስርዓት ይልቅ በተሃድሶ የሽግግር ማዕቀፍ እልባት መስጠት ተገቢነት እንደለው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ አገራዊ መግባባትና መስማማት የሚያስፈልጋቸው በርካታ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር እስካሁን የተደረገ ሁሉን አቀፍ አገራዊ ምክክር አለመኖሩን ያስታወሱት ሚኒስትሩ ይህ በታሪካችን የመጀመሪያ መሆኑን ተናግረዋል።

አገራዊ ችግሮች ከፖለቲካ ልሂቃኑ አልፈው በማህበረሰቡ ዘንድ እየተንጸባረቁ በመሆኑ አገራዊ ቀውሱ ወደ ትውልድ እንዳይሻገር በበቀል ፍትህ ሳይሆን በምክክርና በውይይት መፈጸም የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ብለዋል።

ባለፉት ሶሰት ዓመታትም ሆነ ቀደም ሲል ባጋጠሙ የመብት ጥሰቶች የአገር ህልውና ታሳቢ ባደረገ መልኩ በተሃድሶ የሽግግር ማዕቀፍ መፈትሄ መስጠት እንደሚገባ ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል ነው ያሉት።

በፍርድ ቤት ክርክር ሂደት ላይ ክሳቸው እንዲቋረጥ የተደረገው አቶ ስብሐት ነጋ፣ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ፣ አቶ ዓባይ ወልዱ፣ አቶ አባዲ ዘሙ፣ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር፣ አቶ ኪሮስ ሐጎስ፣ አቶ ጃዋር መሐመድና በእርሳቸው መዝገብ የተከሰሱ እንዲሁም አቶ እስክንድር ነጋና በእርሳቸው መዝገብ የተከሰሱ መሆኑ ይታወቃል።

[ኢዜአ]
@YeneTube @FikerAssefa
በመዲናዋ በነገው ዕለት ሊካሄድ የነበረው የ “በቃ” ሰልፍ ለቀጣይ ሳምንት ተላለፈ!

በአዲስ አበባ በነገው ዕለት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የ “በቃ” ወይም #Nomore ሰልፍ በዳያስፖራው ጥያቄ መሰረት ለቀጣይ ሳምንት መተላለፉ ተገለፀ፡፡በርካታ የዳያስፖራው ማህበረሰብ አሁንም ወደ አገሩ እየገባ በመሆኑ ሰልፉ ቀጣይ ሳምንት የሚካሄድ መሆኑን ነው ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላከተው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በዛሬው እለት የማዕረግ እድገት ያገኙ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ዝርዝር

የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተሿሚ
1. ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ገለልቻ

የጀነራል ማዕረግ ተሿሚዎች
1. ሌ/ጀነራል አበባው ታደሰ አስረስ
2. ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ ቡታ
3. ሌ/ጀነራል ሐሰን ኢብራሂም ሙሳ
4. ሌ/ጀነራል ጌታቸው ጉዲና ሰልባና

የሌ/ጀነራል ማዕረግ ተሿሚዎች
1. ሜ/ጀነራል አለምሸት ደግፌ ባልቻ
2. ሜ/ጀነራል አጫሉ ሸለመ መረጋ
3. ሜ/ጀነራል ጥጋቡ ይልማ ወንድምሁነኝ
4. ሜ/ጀነራል መሐመድ ተሰማ ገረመው
5. ሜ/ጀነራል አብዱራህማን እስማዔል አሎ
6. ሜ/ጀነራል በላይ ስዩም አከለ
7. ሜ/ጀነራል ዘውዱ በላይ ማለፊያ
8. ሜ/ጀነራል መሰለ መሰረት ተገኝ
9. ሜ/ጀነራል ሹማ አብደታ ህካ
10. ሜ/ጀነራል ብርሀኑ በቀለ በዳዳ
11. ሜ/ጀነራል አሰፋ ቸኮለ እንዳለው
12. ሜ/ጀነራል ደሳለኝ ተሾመ አብተው
13. ሜ/ጀነራል ሰለሞን ኢተፋ ለሙ
14. ሜ/ጀነራል ይልማ መርዳሳ ኛጳ

የሜ/ጀነራል ማዕረግ ተሿሚዎች
1. ብ/ጀነራል አማረ ገብሩ ሀይሉ
2. ብ/ጀነራል ኢተፋ ራጋ ሜኮ
3. ብ/ጀነራል ተስፋዬ ወ/ማሪያም ሀብቱ
4. ብ/ጀነራል አዳምነህ መንግስቴ ገብሬ
5. ብ/ጀነራል አብዱ ከድር ከልዩ
6. ብ/ጀነራል ሙላቱ ጀልዱ ዋቅጅራ
7. ብ/ጀነራል ሙሉዓለም አድማሱ ካህሱ
8. ብ/ጀነራል ግርማ ከበበው ቱፋ
9. ብ/ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን በርሄ
10. ብ/ጀነራል አድማሱ አለሙ ወ/ሰንበት
11. ብ/ጀነራል ታገሰ ላምባሞ ድምቦሬ
12. ብ/ጀነራል ፍቃዱ ጸጋየ እምሩ
13. ብ/ጀነራል አለማየሁ ወልዴ ጅሎ
14. ብ/ጀነራል ሰለሞን ቦጋለ መኮንን
15. ብ/ጀነራል ሻምበል ፈረደ ውቤ
16. ብ/ጀነራል ግዛው ኡማ አብዲ
17. ብ/ጀነራል ደምሰው አመኑ ፋፋ
18. ብ/ጀነራል ጀማል መሃመድ ይማም
19. ብ/ጀነራል አለሙ አየነ ዘሩ
20. ብ/ጀነራል ሰይድ ትኩዬ አበጋዝ
21. ብ/ጀነራል አብድሮ ከድር በናታ
22. ብ/ጀነራል ናስር አባዲጋ አባዲኮ
23. ብ/ጀነራል ተስፋዬ አያሌው አለሙ
24. ብ/ጀነራል ነገሪ ቶሊና ጉደር

የብ/ጀነራል ማዕረግ ተሿሚዎች
1. ኮ/ል ሙሉ ሞገስ መኮንን
2. ኮ/ል ደረጀ ደመቀ ማሞ
3. ኮ/ል ተሾመ ይመር አበጋዝ
4. ኮ/ል ያዴታ አመንቴ ገላን
5. ኮ/ል አዱኛ ዴሬሳ ሆሬሳ
6. ኮ/ል ሹመት ጠለለው እንዳሻው
7. ኮ/ል ደስታ ተመስገን አራጋው
8. ኮ/ል ደርቤ መኩሪያ አዲሱ
9. ኮ/ል አበበ ዋቅሹም ተሬሳ
10. ኮ/ል እሸቱ አስማማው አስፋው
11. ኮ/ል አበባው ሰይድ ይመር
12. ኮ/ል ተመቸው ተስፋዬ አበራ
13. ኮ/ል አማረ ባህታ በርሄ
14. ኮ/ል ጌታቸው አሊ መሃመድ
15. ኮ/ል ማርየ በየነ አስናቀ
16. ኮ/ል ካሳ ደምሌ አቡነህ
17. ኮ/ል ሻምበል በየነ ንጉሴ
18. ኮ/ል አምሳሉ ኩምሳ ሮሮ
19. ኮ/ል ተሾመ አናጋው አያና
20. ኮ/ል ተመስገን ማሎሬ ግዶሬ
21. ኮ/ል ገዛኽኝ ፍቃዱ በቀለ
22. ኮ/ል ጀማል ሻሌ ዱሌ
23. ኮ/ል ከማል አቢሶ እንተሌ
24. ኮ/ል ጀማል ቱፊሳ ጭቃቂ
25. ኮ/ል በስፋት ፈንቴ ተገኝ
26. ኮ/ል ሃይሉ መኮንን ምስክር
27. ኮ/ል አዲሱ መሐመድ ፀዳል
28. ኮ/ል ማርየ ምትኩ አለሙ
29. ኮ/ል ናስር አህመድ እራስ
30. ኮ/ል ጌታሁን ካሳዬ ሳህሉ
31. ኮ/ል አበባው መንግስቴ ሰራጨ
32. ኮ/ል አብርሀም ሞሶሳ ጋጀ
33. ኮ/ል ንጉሴ ሚዔሶ ጅባ
34. ኮ/ል ተስፋየ ከፍያለው አስፋው
35. ኮ/ል ታየ አለማየሁ ገዛኽኝ
36. ኮ/ል አዘዘው መኮንን አበራ
37. ኮ/ል ዱሬሳ ደገፋ ኤኙኒ
38. ኮ/ል እሸቴ አራጌ ሞገስ
39. ኮ/ል ወርቅነህ ጉዴታ ደበሉ
40. ኮ/ል ሶፊያን ሸክመሀመድ ከሊፋ
41. ኮ/ል መሀመድ ሁሴን እንድሪስ
42. ኮ/ል ሰይፈ ኢንጊ ጉራሮ
43. ኮ/ል ሁሉአገርሽ ድረስ እንዳሻው
44. ኮ/ል መካሽ ጀምበሬ አምባው
45. ኮ/ል ዝናቡ አባቦር አባጊሳ
46. ኮ/ል ሞሲሳ ቶሎሳ ገርባ
47. ኮ/ል እሸቱ መንግስቱ መንገሻ
48. ኮ/ል እርቃሎ ዱካቶ ጋጌ
49. ኮ/ል ዋለልኝ ታደሰ አዛል
50. ኮ/ል ተስፋዬ ለገሰ ዲያና
51. ኮ/ል ጌታቸው ሀብታሙ ቸኮል
52. ኮ/ል ሐሺም መሐመድ ጭቆላ
53. ኮ/ል ከበደ ገላው ጅማማ
54. ኮ/ል መላኩ ገላነህ ዘለቀ
55. ኮ/ል ተክሉ ሁርሳ ጅንካ
56. ኮ/ል ሐሽም ኢብራሂም አዋሌ
57. ኮ/ል በላይ አየለ ማሞ
58. ኮ/ል ሀብታሙ ምህረቴ በየነ

@YeneTube @FikerAssefa
የእሸቴ ሞገስ እና የልጃቸው የይታገሱ እሸቴ የቀብር ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው!

የጀግንነት ታሪክ ሰርተው የተሠውት የእሸቴ ሞገስ እና የልጃቸው የይታገሱ እሸቴ የቀብር ሥነ ሥርዓት በሸዋሮቢት ከተማ እየተካሄደ ነው።ከአንድ ወር በፊት ሳላይሽ በተባለ ቦታ 16 የአሸባሪው የህወሓት ቡድን አባላትን በመግደል ለሀገር ሲሉ የተዋደቁት አባት እና ልጁ አስከሬናቸው ከወደቀበት ቦታ ተነሥቶ በክብር ወደሚያርፍበት ቦታ አሸኛኘት እየተካሄደ ነው።ጸሎተ ፍትሐት ከተደረገ በኋላም በተዘጋጀው የቀብር ቦታ አስከሬናቸው በክብር የሚቀመጥ ይሆናል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኬፕ ቨርዴ ብሔራዊ ቡድን ጋር ምሽት 4፡00 ላይ ላለበት ጨዋታ የመጀመሪያው አሰላለፍ ይህንን ይመስላል፦

ግብ ጠባቂ

22 ተክለማርያም ሻንቆ

ተከላካዮች

15 አስቻለው ታመነ
16 ያሬድ ባየህ
20 ረመዳን ዩሱፍ
2 ሱሌይማን ሀሚድ

አማካዮች

8 አማኑኤል ዮሐንስ
3 መስዑድ መሀመድ
7 ሱራፌል ዳኛቸው

አጥቂዎች

11 አማኑኤል ገብረ ሚካኤል
10 አቡበከር ናስር
9 ጌታነህ ከበደ (አምበል)

[EFF]
@YeneTube @FikerAssefa
ተበዳይ ፍትህ ሳያገኝና ሳይካስ በዳይን ነፃ ማውጣት በፍትህ ስርዓቱ መቀለድ ነው- ኢዜማ

“በጥድፊያ የሚደረጉ ውሳኔዎች ፍትህን በመጨፍለቅ በተቋማቱ ላይ ያለንን እምነት በሂደት የሚሸረሽሩ ናቸው. . . ተበዳይ ፍትህ ሳያገኝ እንዲሁም ሳይካስ በዳይን ነፃ ማውጣት በፍትህ ስርዓቱ መቀለድ፣ የሕዝባችንን ጉዳትም ማቃለል ነው።” በማለት የኢትዮጽያ ዜጐች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

‘ሁልጊዜ ወገንተኛነታችን ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ጋር ይሁን’ በሚል ባወጣው መግለጫ ፍትህ የአብሮ መኖር ማስተማመኛ ውል ነች ያለው ፓርቲው ታህሳስ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. በመንግሥት የተወሰደው እርምጃም ከሕዝብ ጋር ምክክር የጎደለው ግብታዊ እርምጃ እንዲሁም አመፀኝነትን የሚያበረታ እና መከፍፈልን የሚያጠነክር እጅጉን አሳሳቢ ተግባር ነው ብሏል።

በአሁኑ ሰዓት ትልቁ የሀገራችን አጃንዳ ከገባንበት ቅርቃር መውጫችን ሃገራዊ ምክክር ነው በማለትም የኢትዮጽያ ዜጐች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ አሳስቧል።

ስለዚህም መንግስትና የመንግስት ሚድያዎች ለጉዳዩ እጅግ ከፍተኛ ትኩረት አለመስጠታቸው ለታይታ ከሚደረጉ ነገሮች በዘለለ መላውን ህዝብ ያሳተፈ እዉነተኛ ምክክር እንዲደረግ ቆራጥነት እንደሚጎድል ማሳያ ነው በማለት የፓርቲው ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በዘመቻ ለህብረ ብሄራዊ አንድነት ከፍተኛ ድል ያስመዘገቡ እና ጀብዱ የፈፀሙ መሰረታዊ ወታደሮች እና የጦር መኮንኖች የሜዳልያና የጥቁር አምበሳ ከፍተኛ ብሔራዊ ሽልማት ተበረከተላቸው።

በዘመቻ ለህብረ ብሄራዊ አንድነት የተሰጣቸውን ግዳጅ በላቀ ብቃት ለፈፀሙ መሰረታዊ ወታደሮች፤ ክፍለ ጦሮች እና የተዋጣለት የጦር አመራር ለሰጡ ወታደራዊ መኮንኖች  የጦር ሜዳ ጀብዱ ሜዳይና የላቀ ስራ ውጤት ሚዳሊያ ተሰጥቷል።ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠው "የአድዋ ድል መታሰቢያ የጀግና ከፍተኛ ሜዳልያ" ለስምንት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተሰጥቷል።

የአድዋ ድል መታሰቢያ የጀግና ከፍተኛ ሜዳልያ የተሰጣቸው ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ሜዳልያውን ተሸልመዋል።

የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ምክትል ኢታማዦር ሹሙ ጄኔራል አበባው ታደሰን ጨምሮ ጄኔራል ባጫ ደበሌ እና ሌትናንት ጄነራል ዓለምሸት ደግፌ ደግሞ "ወደር የሌለው የጥቁር አምበሳ ከፍተኛ ብሔራዊ ሽልማት" ተበርክቶላቸዋል።ሽልማቱ የተሰጠው አዲሱ የመከለከያ ሚኒስቴር ዋና መስርያ ቤት ህንጻ ምረቃ በተከናወነበት መርሃግብር ላይ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
ክስ አቋርጦ የተወሰኑ እስረኞችን የመፍታቱ ውሳኔ የተገኘውን ዘላቂ ድል ለማዝለቅ በማሰብ የተሰጠ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል ባሉት ውሳኔ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፤ በአዲሱ የመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ አዲስ ህንጻ የማስመረቂያ ስነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፡፡

ዘላቂ ድልን ማረጋገጥ ማሸነፍ ብቻም ሳይሆን ይቅር ብሎ ምህረት ማድረግን ይሻል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁጣው ጭር ሲል ከማይወድና የት እንዳለ ከማይታወቅ ቡድን እና በዜናው ድንገተኛነት ከደነገጠ ጠላትን አምርሮ ከሚጠላ “የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ” መሰማቱን ተናግረዋል፡፡

ይህን የሚረዳው መንግስት “እኛንም መጀመሪያ አስደንግጦን ነበር” ስላሉት ውሳኔ ለማስረዳት ጥረት እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡“እየመረረን የዋጥነው ነው” ሲሉም ነው ስለ ውሳኔው ያስቀመጡት፡፡ ሆኖም ውሳኔው ለኢትዮጵያ የሚበጅና ጠላትን የሚቀንስ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ኢትዮጵያን በጠንካራ ዓለት ላይ ለማቆም በማሰብ የተወሰነ መሆኑን አውቃችሁ ለሃገር አሸናፊነት ስትሉ ውሳኔውን እንድትቀበሉ እጠይቃለሁም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

ተጨማሪ:
https://am.al-ain.com/article/pm-abiy-calls-for-ethiopians-to-accept-government-s-decision-to-release-prisoners

@YeneTube @FikerAssefa
ኢቢሲ 33ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን በቀጥታ ያስተላልፋል!

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ኢትዮጵያ የምትካፈልበትን 33ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን በዜና እና በመዝናኛ ቻናሎቹ በቀጥታ እንደሚያስተላልፍ ገልጿል።

ዛሬ በይፋ በተጀመረው 33ኛው አፍሪካ ዋንጫ ሀገራችን የምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ዛሬ ምሽት 4:00 ላይ ከኬፕ ቨርድ ጋር ታደርጋለች።የመክፈቻ ጨዋታውን አስተናጋጇ ካሜሩን እና ቡርኪና ፋሶ ምሽት 1:00 ላይ ጀምረዋል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ክሳቸው ተቋርጦ ስለተፈቱ እስረኞች የሰጡት ማብራሪያ

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኮቪድ ምክንያት 11 ተጫዋቾች እንኳን ቢቀሩ ጨዋታ እንደማይሰረዝ ካፍ ገለጸ!

በአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፉ ሃገራት የኮቪድ1-9 ወረርሽኝ ቢያጋጥማቸውና 11 ተጫዋች ብቻ ቢቀራቸው እንኳ ጨዋታው እንደማይሰረዝ ካፍ ገልጿል።የአፍሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪው ካፍ ከአስራ አንዱ ተጫዋቾች አንዱም ግብ ጠባቂ ባይሆን ጨዋታው እንደማይሰረዝ አስታውቋል።ይህንን ማሟላት የማይችል ቡድን በተለምዶ ፎርፌ በሚባለው ሕግ መሠረት የ2-0 ሽንፈት ይጣልበታል ይላል ካፍ።

ካፍ ይህንን ትዕዛዝ ያስተላለፈው ዛሬ ምሽት [እሑድ] ከሚጀምረው ውድድር በፊት በርካታ ሃገራት ተጫዋቾቻችን በኮቪድ ተይዘዋል ብለው ካማረሩ በኋላ ነው።ካፍ አክሎም "ለየት ያለ ምክንያት" ላላቸው ሃገራት የውድድሩ አጋጅ ኮሚቴ "አስፈላጊውን ውሳኔ ይሰጣል" ብሏል።

ከሁሉም ቀድማ ካሜሩን የገባችው ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት የተወሰኑ ተጫዋቾቿ በኮቪድ ተይዘውባት እንደነበር ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቦ ነበር።ተጫዋቾችን ጨምሮ የአሠልጣኝ ቡድን አባላት በኮቪድ ተይዘው ለቀናት ካገገሙ በኋላ መመለሳቸውን ድረ-ገፁ ዘግቧል።

BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በክልሉ በተከሰተው ድርቅ በሰውና በእንሰሳት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለማድረግ በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ የሶማሌ ክልል መንግሥት አስታወቀ፡፡

የሶማሌ ክልል መንግሥት ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በክልሉ አከባቢዎች የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ፥ ድርቁ በሰውና በእንስሳት ህይወት ላይ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ለዜጎች አስቸኳይ እርዳታ እያቀረበ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በሸበሌ ዞን ቤር-አኖ ወረዳ የሚገኙ የቆራህዳ፣ የገላ-መዶቦ ቀበሌ ነዋሪዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ እና የእንስሳት መኖ ማድረሱን የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል።

በተጨማሪም የቤር-አኖ ወረዳ አስተዳደሪ አቶ መሀመድ አብዱላሂ እንደተናገሩት ፥ በወረዳው ሥር የሚገኙ 15 ቀበሌ ነዋሪዎች የአስቸኳይ እርዳታ ከማድረጉ በተጨማሪ ከደናንና ከጎደይ ወረዳዎች እንዲሁም ከአጎራባቹ ኖጎብ ዞን ወረዳዎች የተፈናቀሉ ዜጎችም የአስቸኳይ እርዳታ እየቀረበላቸው ነው ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የድርቁ ሁኔታ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ከሆነ የዞኑን ነዋሪ ከድርቁ ለመታደግ፣ የሸበሌ ወንዝ ዳርቻን ለግብርና ልማት እንዲጠቀሙ ሰፊ የእርሻ መሬት እንደሚዘጋጅም አስተዳደሪው መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሰርቢያዊዉ የአለም ጥቁር 1 የቴኒስ ተጫዋች ኖቫክ ጆኮቪች ከአውስትራሊያ እንዲወጣ የተወሰነበትን ውሳኔ በፍርድ ቤት ተከራክሮ አስቀየረ።

ጆኮቪች ለአውስትራሊያ ኦፕን የሜዳ ቴኒስ ውድድር ወደ ሜልቦርን ቢያቀናም በሀገሪቱ ባለስልጣናት የኮቪድ መከላከያ ክትባት አልወሰድክም በሚል ከሀገሪቱ እንዲወጣ መወሰኑ ከሰሞኑ ትልቅ ዜና ሆኖ ነበር።

ይህንንም ተከትሎ ጆኮቪች የተቋረጠበትን የአውስትራሊያ ቪዛ ለማስመለስ ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን ይግባኙ ተቀባይነት አግኝቶለታል ሲል የዘገበው አርቲ ነዉ።

@YeneTube @FikerAssefa
በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት ከዳያስፖራው ጋር ውይይት እየተደረገ ነው።

ውይይቱ አሸባሪው የህወሓት ወራሪ ቡድን ጉዳት ባደረሰባቸው የአማራ እና የአፋር ክልል አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት የሚረዳ ምክክር በስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ነው።በመድረኩ ሚኒስትሮች ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ፣ ዳያስፖራዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት በነ አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር መዝገብ ከ45 በላይ የዓቃቢህግ ምስክሮችን የሰማው ፍርድ ቤቱ ቀሪ ምስክሮችን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።

ቀሪ ምስክሮችን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

የቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀመድ ኡመርን : የቀድሞ ሱማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ፈርሐት ጣሂር : የበርከሌ ዞን ፖሊስ አዛዥ አብዱላሃ አህመድ ኑርን ጨምሮ 17 ተከሳሾች በ2010 ዓ/ም ከሀምሌ 26 እስከ ሀምሌ 30 በጂጂጋ ከተማ እና በተለያዩ ዞንና ወረዳዎች የሄጎ ቡድን በማደራጀት ግጭት በመቀስቀስ በክልሉ የሚኖሩ የሌላ ብሔር ተወላጆችን እንዲፈናቀሉ በማድረግ : በሴቶች ላይ ጾታዊ ጥቃት በማድረስ :59 ሰዎች ህይወት እንዲያልፍ በማድረግ: የኦርቶዶክስ ዕምነት ተቋማት እና የግለሰብ የንግድና የመንግስት ተቋማትን በማቃጠል :ንብረት በማውደም ከ412 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል ብሎ ዓቃቢህግ በየተሳትፎ ደረጃ የሽብር ወንጀል ክስ መስርቶባቸው እንደነበር ይታወሳል።

ተከሳሾቹ ወንጀሉን አልፈጸምንም ብለው የሰጡትን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዓቃቢህግ ወንጀሉን ለመፈጸማቸው የሚያስረዱ 213 ምስክሮች እንዳሉት ለፍርድ ቤቱ አስረድቶ ነበር።

ፍርድ ቤቱ ከ213 የዓቃቢህግ ምስክሮች ውስጥ 26 በላይ የዓቃቢህግ ምስክሮችን ቃል የሰማ ሲሆን ዓቃቢህግ ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል ባላቸው ሁለት ምስክሮች ለደህንነታቸው ጥበቃ እንዲደረግላቸው ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ መጠየቁን ተከትሎ ይግባኙ ዕልባት እስኪያገኝ የመደበኛው ችሎት የምስክር የመስማት ሂደቱ ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል ።

በድጋሚ ከታሳስ 12 ቀን ጀምሮ እስከ ታሳስ 27 ቀን 2014 ዓ/ም በነበረ ቀጠሮ መደበኛው ችሎት ተቋርጦ የነበረውን የምስክር የመስማት ሂደት ቀጥሏል።በዚህም ፍርድ ቤቱ አጠቃላይ ከ45 በላይ የምስክሮችን ቃል አዳምጧል።ሌሎች ስድስት የዓቃቢህግ ምስክሮች ደግሞ ፖሊስ በቀጠሮ ቀን ባለማቅረቡ ምክንያት እንዲታለፉ ተደርጓል።ሆኖም ቀሪ ምስክሮችን ለመስማት ከየካቲት 1 ቀን እስከ የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

Via Tarik Adugna
@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት በፍርድ ሂደት የነበሩ ሰዎችን ክስ በማቋረጥ ከእስር እንዲለቀቁ ማድረጉ ሕዝቡን ለከፍተኛ ግራ መጋባት ያጋለጠ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ በቂ ማብራሪያ እንዲሰጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ለኢትዮጵያ አሳሰበ፡፡

ውሳኔው በህዝቡ ዘንድ ግርታን ከመፍጠሩ ባሻገር የተለያዩ አገራትን አሰላለፍ ጭምር ሊቀይር የሚችል በመሆኑ መንግስት ተጨማሪ ማብራሪያዎችን መስጠት ቀዳሚ ስራው ሊሆን እንደሚገባ ነው ያሳወቀው፡፡ውሳኔው አገርንና ህዝብን የሚያሳጣው አንዳች ነገር እንዳይኖርም መንግስት መጠንቀቅ ይኖርበታል ሲሉ ለአሐዱ የገለፁት የጥምረቱ ፕሬዝዳንት ጋሻው ሽባባው ናቸው፡፡

ፕሬዝዳንቱ አገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የአሁኑ ውሳኔ ለሌላ ችግር የሚዳርግ እንዳይሆን ጥንቃቄዎች መደረግ እንደሚገባቸውም አመላክተዋል፡፡መንግስት በቂ መረጃዎችን ለህዝቡ እንዲደርስ በማድረግ ሊደርሱ የሚችሉ ስጋቶችን ከወዲሁ መቀነስ ይኖርበታል ሲሉም አክለዋል፡፡

መንግስትም ይሁን ሌሎች ወገኖች በየትኛውም አኳኋን የህዝብን ቁጣ ከሚቀሰቅሱ ማናቸውም ደርጊቶች መቆጠብ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል፡፡መንግስት የፖለቲካ ምኅዳሩን ለማስፋትና ለአካታች አገራዊ ምክክር ሲል እስረኞቹን በምሕረት መፍታቱን ማሳወቁ አይዘነጋም፡፡

[አሐዱ]
@YeneTube @FikerAssefa
የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽነርነት ጥቆማን እስከ ጥር 6 መቀበሉን እንደሚቀጥል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አስታወቀ!

የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መቋቋሙን ተከትሎ የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማን ከታህሳስ 26 ቀን 2ዐ14 ዓ/ም ጀምሮ እየተቀበለ የሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እስከ መጪው ጥር 6 ቀን 2014 ዓ.ም ጥቆማ መቀበሉን እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡

በሂደቱ ጠቋሚዎች የሚያነሷቸው እና እንዲብራሩላቸው የሚፈልጓቸው ጉዳዮችን አስመልክቶ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጥያቄዎችን እየጠየቁ ይገኛሉ ያለው ምክር ቤቱ ፣ዜጎች ለጉዳዮ ትኩረት ሰጥተው መከታተላቸውንና ጥያቄ ማቅረባቸውን አድንቋል፡፡

የሚጠቆሙት ዕጪዎች ከሚኖራቸው ከፍተኛ ሃገራዊ ኃላፊነት አንፃር ጠቋሚዎች ስለሚጠቁሙት ሠው የተሟላና ተጨባጭ ዕውቀት መኖር እጅግ አስፈላጊ በመሆኑና በዚህ ደረጃ ታስቦበትና ዝግጅት ተደርጎበት መጠቆም እንደሚኖርባቸው አሳስቧል።ከዚሁ ጋር ተያይዞ አንድ ጠቋሚ መጠቆም የሚችለው አንድ ግለሰብ ብቻ መሆኑን ም/ቤቱ ገልጿል።

በተጨማሪም አንድ ዕጩ በስንት ሰዎች ተጠቆመ የሚለው አሃዝ ለዕጩ ኮሚሽነሮች መረጣ እንደ መሥፈርት ያልተቀመጠ በመሆኑ አንድን ግለሰብ ደጋግሞ መጠቆም ተቀባይነት እንደሌለውም አሳውቋል፡፡በዚሁ መሠረት በተዘጋጀው ቅጽ መሠረት ብቻ በመጠቀም ጥቆማውን መስጠት የሚቻል መሆኑን ም/ቤቱ አስቀምጧል፡፡

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል የሚተገበር የ4.5 ቢሊዮን ብር የመልሶ ግንባታ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ!

የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) በአማራ ክልል የሚተገበር የአምስት ዓመታት ፕሮጀክት ስምምነት ተፈራርሟል።የድርጅቱ ዳይሬክተር ዶክተር አለማየሁ ዋሴ ዛሬ ከልዩ ልዩ ተቋማት የሥራ ኀላፊዎች ጋር ስምምነቱን ተፈራርመዋል።አመልድ ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ አደጋ በሚያጋጥም ጊዜ የዕለት ደራሽ ድጋፍ በማድረግ፣ በመልሶ ማቋቋም እና በልዩ ልዩ የልማት ሥራዎች አማራ ክልልን የሚደግፍ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው።

ይህ ድርጅት ከለጋሽ አካላት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ አማካኝነት ለአምስት ዓመታት የሚተገበር የ4.5 ቢሊዮን ብር ስምምነት ዛሬ ተፈራርሟል። የፕሮጀክቱ መዳረሻ የኅብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል ነው።ትኩረቱንም የመተዳደሪያ አቅምን በማሳደግ፣ የአመጋገብ ስርዓትን በማሻሻል እና የተቋማትን አቅም በማጎልበት ላይ አድርጎ ይሠራል ተብሏል።ተግባራዊ የሚደረገው ደግሞ በሰሜን ወሎ ዞን እና በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች ነው።በ207 ቀበሌዎች 217 ሺህ 879 ሰዎች ቀጥተኛ ተጠቃሚ እንደሚሆኑም በፊርማ ሥነርስዓቱ ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa