YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ቻይና በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ እንደምትሾም አስታወቀች!

ቻይና በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ እንደምትሾም የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ አስታወቁ።የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በኬንያ የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ይህንን ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።ቻይና የምትሾመው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ በቀጠናው ያሉ ሀገራት የሚያጋጥሟቸውን የፀጥታ እና ደህንነት ስጋቶችን ለመቀልበስ የሚያደርጉትን ጥረት ለመደገፍ መሆኑንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ያሉ ሀገራ በሀገራቸው ውስጥ ያሉ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ተወያይተው ሊፈቱ ይገባል ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ በቀጠናው ሰላማዊ ድርድሮች እንዲካሄዱም ቻይና ሁኔታዎችን የሚያመቻች ተጠሪነቱ ለሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆነ ልዩ መልዕክተኛ በቅርቡ ተልካለች ብለዋል።ከኬንያ አቻቸው ጋር በወደብ ከተማዋ ሞምባሳ የተወያዩት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ፤ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የቀጣናውን እጣ ፈንታ በእጃቸው ማስገባት አለባቸው ብለዋል።

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
በሰሜን ሸዋ ደገም ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ!

በዛሬዉ እለት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደገም ወረዳ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት አልፏል።አደጋዉ የደረሰዉ መነሻዉን አዲስ አበባ በማድረግ የእርዳታ እህል ጭኖ ወደ ጎጃም ሲጓዝ የነበረ ኮድ3 26181 ኢቲ የሆነ ተሽከርካሪ መንገዱን ለቆ ከገርበ ጉራቻ ወደ ፊቼ 13 ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ3 39274 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪን ገጭቶ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የደገም ወረዳ የትራፊክ ደህንነት ቢሮ አስተባባሪ ዋና ሳጅን ታደሰ ዉሪሳ በተለይ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

በተጨማሪም በሚኒባሱ ተሳፍረዉ ከነበሩ 13 ሰዎች መካከል ሌሎች 7 ሰዎች ከባድ አደጋ የደረሰባቸው ሲሆኑ ለህክምና ወደ አዲስአበባ እና ፊቼ መወሰዳቸውን ጨምረዉ ተናግረዋል።ዋና ሳጅን ታደሰ ዉሪሳ እንደተናገሩት በአካባቢው የትራፊክ ምልክቶች አለመኖራቸው በተለይም ለእንደዚህ አይነት የትራፊክ አደጋዎች መንስኤ ሊሆኑ አንደሚችሉ አክለዉ ለብስራት ተናግረዋል።

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
የገና ስጦታ ሎተሪ ወጣ!

የገና ሥጦታ ሎተሪ ሀሙስ ታህሳስ 28/ 2014 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል፡፡

👉🏻 1ኛ. 10,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 1977732
👉🏻 2ኛ. 5,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር 0341880
👉🏻 3ኛ. 2,500,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 0929042
👉🏻 4ኛ. 1,500,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 1357756
👉🏻 5ኛ. 1,000,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 1288620
👉🏻 6ኛ. 500,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር 0614488
👉🏻 7ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው 20,000 ብር የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 18052
👉🏻 8ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 10,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 05609
👉🏻 9ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 5,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 4599
👉🏻 10ኛ. 200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 6941
👉🏻 11ኛ. 2,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 500 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 883
👉🏻 12ኛ. 2,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 250 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 904
👉🏻 13ኛ. 20,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 100 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 22
👉🏻 14ኛ. 200,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 50 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር (የማስተዛዘኛ ዕጣ) ደግሞ 4 ቁጥር በመሆን መውጣቱን ብሄራዊ ሎተሪ አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!
በላሊበላ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ገና ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የእምነቱ መሪዎችና ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

@YeneTube @FikerAssefa
በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ የልደት በዓል በሰላም ተጠናቋል- የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን

የኢየሱስ ክርስቶስና የቅዱስ ላሊበላ የልደት በዓል ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ፣ ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እና ምዕምናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።የልደትን በዓል መሰላም መጠናቀቅ አስመልክቶ በላሊበላ መግለጫ የሰጡት የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ የልደት በዓል በሰላም መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

በዚህ ዓመት የልደት በዓል በላሊበላ በልዩ ሁኔታ እንዲከበር ጥሪ ተለላልፎ እንደነበርም አስታውሰዋል።በተደረገው ጥሪ መሠረት በታላቅ ድምቀት መከበሩንም አስታውቀዋል።አካባቢው በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ተወርሮ የነበረ ቢሆንም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት መከበሩንም ገልፀዋል።በዓሉ በሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች በዓሉ በፀጥታ ኃይሎች ጥመረት፣ በወጣቶች እና በሰላም ወዳዱ ሕዝብ የጋራ ትብብር በሰላም መጠናቀቁን ነው የተናገሩት።የፀጥታ ችግር እንዳይኖር ላደረጉት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የነበሩት ጄፍሪ ፊልትማን ከኃላፊነታቸው መመነሳታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አስታወቁ።

አንቶኒ ብሊንከን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ እንደገለጹት፤ ጄፍሪ ፊልትማን ተነስተው በምትካቸው አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ተሹመዋል።

ፊልትማን ላለፉት ዘጠኝ ወራት በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

አሁን የተሾሙት አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ በሳውዲ ዓረቢያ፣ ሊባኖስ፣ ቱኒዚየ እና ሶሪያ በዲፕሎማትነት ያገለገሉ ሲሆን የአሜሪካ የመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ከፍተኛ ዲፕሎማት ሆነውም አገልግለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሰበር ዜና!

እስክንድር ነጋን ጨምሮ ታስረው የነበሩ የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች ከእስር ተለቀቁ!


እስክንድር ነጋን ጨምሮ ታስረው የነበሩ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ (ባልደራስ) የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት ከእስር ተለቀቁ።የፓርቲውን ሊቀመንበር እስክንድር ነጋን ጨምሮ ስንታየሁ ቸኮልን መሠል የፓርቲው አመራሮች ከእስር መፈታታቸውን ባልደራስ በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል።

ጀዋር መሃመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ አመራሮች ይፈታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የአል ዐይን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል።

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
የአገር መከለከያ ሠራዊት ሲጠቀምበት በቆየው የማዕረግ ምልክት ላይ ማሻሻያዎችን አደረገ፡፡

ማሻሻያውን ተከትሎ ሠራዊቱ ተከታዩን መግለጫ አውጥቷል፡-

ማሻሻያው የተደረገበት ምክንያትም የሠራዊቱ ማዕረግ አገራዊም ይሁን ወታደራዊ ታሪካዊ ይዘት ያለውና የሠራዊቱንም ባህሪ ሊገልፅ የሚችል ሆኖ እንዲዘጋጅ በማስፈለጉ ነው።

በዚህም መሠረት በሠራዊታችን የማዕረግ ምልክቶች ውስጥ ጋሻና አንበሳ በዋናነት ጥቅም ላይ ውለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
እነእስክንድር ነጋና ጃዋር መሐመድን ጨምሮ በእስር ላይ የነበሩ የፖለቲካ መሪዎች ተፈቱ!

መንግሥት በእነ እስክንድር ነጋና ጃዋር ሲራጅ መሐመድ መዝገብ የተከፈቱትን ክሶች እንዲቋረጡ መወሰኑን ተከትሎ እስረኞቹ ከማረሚያ ቤት እንዲወጡ ሆኗል፡፡

ከእሥር በምሕረት እንዲፈቱ የተወሰነላቸው

1. አቶ ስብሐት ነጋ
2. ወሮ ቅዱሳን ነጋ
3. አቶ ዓባይ ወልዱ
4. አቶ አባዲ ዘሙ
5. ወሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር
አቶ ኪሮስ ሐጎስ
6. አቶ ጁሐር መሐመድና በእርሱ መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ
7. አቶ እስክንድር ነጋና በእርሱ መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ

@YeneTube @FikerAssefa
የእነ ጃዋር መሐመድ፣ እስክንድር ነጋ እና ስብሐት ነጋ ክስ እንዲነሳ የተደረገው በቀጣይ የሚደረገውን ሃገራዊ የምክክር መድረክ ሂደት ውጤታማነት እና አካታችነት ከፍ ለማድረግ በማሰብ መሆኑን የፍትሕ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ በእነ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል መዐሾ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ውስጥ እነ ስብሐት ነጋ የጤና እና የዕድሜ ሁኔታን ከግምት በማስገባት ክሱ ተነስቶላቸዋል ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
ክሳቸው የተነሳላቸው እነ ጃዋር መሀመድ ከማረሚያ ቤት ወጥተዋል!

አቶ ጃዋር መሀመድ ፣አቶ በቀለ ገርባ ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ አቶ ሀምዛ አዳነ እና ሸምሰዲን ጣአን ጨምሮ በነጃዋር መዝገብ የተካተቱ ሁሉም እስረኞች ከማረሚያ ቤት ወጥተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
TOP book series 📚ቶፕ የተማሪዎች አጋዥ መፅሀፍት

📌ከ 1-12 ክፍል በ ተለያዩ ቋንቋ የተዘጋጀ
📌በ ኦሮምኛ
📌በ አማርኛ
📌በ እንግሊዘኛ በሁሉም አይነት ትምህርት የተዘጋጀ
- maths chemistry biology physics ...
📌ለ 8 እና 12ኛ ክፍል ፈተና የሚያዘጋጁ
📌ለ ልጆችም 20 አይነት ተረት መጽሀፍት ታትሞዋል

❗️❗️በሁሉም መፅሀፍት ቤት ይጠይቁ
 
ዋና አከፋፋይ : ኤደን መጽሀፍት ቤት  
* * መገናኛ ሀይሌ ህንፅ ፊት ለ ፊት
📞 0911238057
0912732493

@TOPBOOkSERIES