YeneTube
115K subscribers
31.7K photos
485 videos
79 files
3.94K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሐማስ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ሊያደርጉ ይችላሉ ተባለ!

አንድ የሐማስ ከፍተኛ ባለሥልጣን በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት የጋዛ ታጣቂዎችና የእስራኤል ባለሥልጣናት የተኩስ አቁም ስምምነት ሊፈርሙ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጡ። ከዚህ አስተያየት በተቃራኒ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታንያሁ ትናንት ረቡዕ "ለእስራኤል ዜጎች ሰላምና ደኅንነት እስኪመለስ ድረስ ጥቃቱን እንቀጥልበታለን" ብለዋል።

ሐሙስ ከቀትር በፊት ብቻ ከመቶ በላይ የእስራኤል የአየር ጥቃቶች በሐማስ ወታደራዊ መዋቅር ላይ እንደተተኮሱ ተዘግቧል። በምላሹ የፍልስጤም ታጣቂዎች ወደ እስራኤል ሮኬት ተኩሰዋል። የጋዛው ግጭት የተጀመረው በእስራኤልና ፍልስጤማዊያኑ መሀል እስራኤል በኃይል በያዘቻቸው የምሥራቅ ኢየሩሳሌም አካባቢ በረመዳን ወር ለቀናት ውጥረት ከነገሠ በኋላ ነው።

ሙስሊሞችና አይሁዳዊያን ቅዱስ ቦታችን ነው በሚሉት አል አቅሳ የደማስቆ በር መግቢያ ላይ የእስራኤል ወታደሮች ክልከላ በማድረጋቸው ጋዛን የሚቆጣጠረው ሐማስ ቁጣውን ሲገልጽ ቆይቷል። ፍልስጤማዊያንም በእስራኤል ወታደሮች የሚደርስባቸው እንግልት እያየለ መምጣቱ ግጭቱን ወደከፋ ደረጃ እያደረሰው መምጣቱ ይታወሳል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መንግስት መረጃን ለህዝብ በማቅረብና ተአማኒ በመሆን ረገድ ያለብኝን ችግር ይፈታል ያለውን የተግባቦት ሰነድ አዘጋጅቶ ወደ ስራ ገብቷል ተባለ።

በጠቅላይ ሚንስትሩ ፅህፈት ቤት የተዘጋጀውና ዋዜማ ራዲዮ አገኘሁት ያለችው “የኢፌዴሪ የተግባቦት ሰነድ” ከተለያዩ የመንግስት አካላት፣ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ፅህፈት ቤት ቅርብ በሆኑ ጋዜጠኞች፣ በመረጃና ደህንነት ተቋሙና በክልል መስተዳድር አካላት ሀሳብ የተሰጠበት እንደሆነ በመግቢያው ላይ ያትታል።

ዝርዝሩን ለማንበብ :-

https://bit.ly/3u5lzRP

@YeneTube @FikerAssefa
ይመሰረታል የተባለዉ አገር አቀፍ ገለልተኛ አማካሪ ቡድን

የነበረው የፀጥታ አወቃቀር “ግራ የተጋባ፣ ስርዓቱ የተዛባና አስተሳሰቡ ልክ ያልሆነ ስለነበር ህዝቡ በእጅጉ ሰላም ርቆት ቆይቷል ” ሲል የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ!

አገር አቀፍ ገለልተኛ አማካሪ ቡድንና የህብረተሰብ ደህንነት ቅኝት በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚቋቋምም ሚኒስቴሩ አመልክቷል፣ አደረጃጀቱ ቅርበትን ሰለሚፈጥር ውጤታማ እንደሚሆን አንድ የግጭት መከላከልና አፈታት ባለሙያ ተናግረዋል፡፡አገር አቀፍ ገለልተኛ አማካሪ ቡድንና የህብረተሰብ ደህንነት ቅኝት ለመመስረት በሰላም ሚኒስቴርና በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ ባሕር ዳር ላይ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ፍሬዓለም ሽባባው እንዳሉት ከዚህ በፊት የነበሩት የፀጥታ ተቋማት አደረጃጀታቸው ግራ የተገባና የተዛባ ነበር፡፡

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ በምታካሂደው በመጭው ሃገራዊ ምርጫ 36 የሚደርሱ ዓለም አቀፍና የተለያዩ ሀገራት ሲቪክ ተቋማት ምርጫውን ለመታዘብ ዝግጁ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ::

ሀገራዊ ምርጫው የተሳካና ቅቡልነቱ የተሻለ እንዲሆን ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ስለመሆኑ የጠቆሙት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሚካሄደው ምርጫ በታዛቢነት ለመሳተፍ የሚቀርቡ ጥያቄዎች እየጨመረ መሆኑን ገልፀዋል::እስካሁን ባለው ሂደትም 36 የሚደርሱ ዓለም አቀፍና የተለያዩ ሀገራት የሲቪል ተቋማት ተጠባቂ ምርጫውን ሂደት ለመታዘብ ዝግጁ ሆነዋል ብለዋል አምባሳደር ዲና::ተቋማቱ በዋናነትም ከአፍሪካ ህብረት ከአሜሪካ ሁለት እውቅ ሲቪክ ማህበራት የሚወጣጡ መሆናቸውንም አስታውቀዋል::

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
በቅርቡ ከዚህ አለም በሞት የተለየውን ደራሲ መስፍን ጌታቸውን የሚዘክር ፕሮግራም ዛሬ በብሔራዊ ቲያትር ተዘጋጅቷል፡፡

የሕይወት ታሪኩን የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልምን ጨምሮ ሌሎችም ጥበባዊ ዝግጅቶች ተሰናድተዋል፡፡አበበ ባልቻ፣ ማህደር አሰፋ፣ ሰሎሞን ዓለሙ፣ ሀና ዮሀንስ፣ ሰሎሞን ቦጋለ፣ ሳምሶን ታደሰ- ቤቢ፣ ሸዊት ከበደ፣ ይገረም ደጀኔ፣ ሄለን በድሉ፣ ሱራፌል ተካ በመድረኩ እንደሚሳተፉ ተነግሯል፡፡ፕሮግራሙ ዛሬ ከ7 ሰአት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡መግቢያው በነጻ ነው፡፡

[@AddisZeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
አማራ ልማት ማኅበር ለተፈናቃዮች ከአጋር አካላት የሰበሰበውን 30 ሚሊዮን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አስረከበ፡፡

የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) በሰሜን ሽዋ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ለተፈናቀሉ ወገኖች ከአጋር አካላት የሰበሰበውን 30 ሚሊዮን ብር የሚገመት ልዩ ልዩ ቁሳቁስ አስረክቧል፡፡ የተሰበሰበውን የቁሳቁስ ድጋፍ በሰሜን ሽዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ ተገኝተው ያስረከቡት የአልማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፋንታ እንዳሉት የተሰበሰበው ቁሳቁስ ለ1 ሺህ 500 ቤቶች ግንባታ ይውላል ብለዋል፡፡ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና ያቀረቡት የአልማ ሥራ አስፈፃሚ መላኩ ፋንታ ሌሎች አጋር አካላትም ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት አጋዥ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት 20 ሚሊዮን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡ የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ቴዎድሮስ ቦጋለ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡በላይነህ ክንዴ ግሩፕ 15 ሺህ ሊትር ዘይት እና ሴንቸሪ ካምፓኒ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል ተብሏል፡፡

[AMC]
@YeneTube @FikerAssefa
አባይ ባንክ በ10 ዓመት ውስጥ ተቀማጭ ገንዘቤ 23.5 ቢሊየን ብር ደርሷል አለ።

የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል 4.2 ቢሊየን ብር መድረሱን ተሰምቷል።የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 29 ቢሊየን ብር ደርሷል።አባይ ባንክ ከ 10 የአየር መንገዶች ጋር የበረራ ትኬት መቁረጥ የሚቻልበትንም መላ ወደ ስራ ማስገባቱን ተናግሯል።ዲጂታል ባንኪንግ ላይ በብርቱ እየሰራሁ ነው ብሏል።ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን የበረራ ትኬት መቁረጥ የሚቻልበትን የዲጂታል የክፍያ አገልግሎት ዛሬ መጀመሩን ተሰምቷል።የክፍያ አገልግሎቱ ጉዞ ጎ የተሰኘ የድጅታል ክፍያ መተግበርያ ነው።አገልግሎቱ 3 አማራጮችን ይዞ ወደ ስራ ገብቷል።

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ ፍርድ ቤት ምርጫውን አሳልፎ ከሁለት አመት በኋላ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጥ ጠየቁ!

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ የሚያካሂደውን ምርመራ አቋርጦ ምርጫው ካለፈ በኋላ ለ2015 እና 2016 ቀጠሮ እንዲሰጣቸው አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባ ጠየቁ። ተከሳሾቹ ጥያቄውን ያቀረቡት ዛሬ ሐሙስ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በነበራቸው መደበኛ የክስ ሂደት የችሎት ውሎ ላይ ነው።

በመጀመሪያ ተቃውሟቸውን ያሰሙት አቶ በቀለ ገርባ ቀጠሮ ምንም ፋይዳ ስለሌለው ፍርድ ቤቱ ግንቦት 18 ቀጠሮ ከሚሰጥ ይልቅ ከሁለት ዓመት በኋላ ለ2015 ወይም 2016 ቢሰጥ ይሻላል ብለዋል።“ሰው በአደባባይ በሚረሸንበት አገር ፍርድ ቤት መቅረብ እድለኝነት ነው” ያሉት አቶ በቀለ ገርባ፤ ይህም ሆኖ ግን ምንም ፍትህ ለማይገኝለት ነገር ፍርድ ቤት መመላለስ እንደሌለባቸው ጠቅሰዋል።

ይሄንኑ ተቃውሞ ደግፈው የተናገሩት አቶ ጃዋር መሐመድ “እናንተ ነፃ ናችሁ ብትሉንም እነሱ ግን አይለቁንም” በማለት ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።በተጨማሪም መንግስት የሚፈልገው የእኛን መታሰር ስለሆነ የፍርድ ቤቱንም የእኛንም ጊዜ ከምንገድል ከሁለት አመት በኋላ ቀጠሮ ቢሰጥልን ይሻላል ሲሉ ተደምጠዋል።

[ኢትዮጵያን ኢንሳይደር]
@YeneTube @FikerAssefa
ሰበር ዜና!

6ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ለሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲካሄድ መወሰኑን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

በዛሬው ዕለት በሆቴል ዲሊኦፖል እየተሰጠ በሚገኘው መግለጫ ላይ የቦርዱ ኮሚኒኬሽን ኃላፊ ሶሊያና ሽመልስ ተናግረዋል ።

የመራጮች ምዝገባ ላይ ቅሬታ ያለባቸው ቦታዎች ላይ ግን ሰኔ 14 ቀን እንደማይካሄድ ገልፀዋል ።

@Yenetube @Fikerassefa
በትግራይ ክልል የከፋ ረሃብ ሊያጋጥም ይችላል ሲሉ ዩኤስኤድ ዋና የስራ ሀላፊ ሳማንታ ፓወር ተናገሩ!

የአሜሪካ ከፍተኛ የረድኤት የስራ ሀላፊ በኢትዮጲያ ትግራይ ክልል የከፋ ረሃብ ሊያጋጥም ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።የዩኤስኤድ ዋና የስራ ሀላፊዋ ሳማንታ ፓወር የምግብ የአስቸኳይ ክትትል ኤጀንሲ መረጃ ሁኔታው ደረጃ አምስት አፋጣኝ ምድብ ላይ ያሳያል ደረጃ ስድስት የሚባል የለም ሲሉ ተናግረዋል።

ፓወር በክልሉ ያለው ግጭት እንዲያበቃና ለረድኤት ሰራተኞች ድጋፉ የሚያደርጉበት ሁኔታ እንዲመቻች ጥሪ አቅርበዋል።የአለም የምግብ ፕሮግራም(WFP)5.2 ሚሊዮን የክልሉ ነዋሪዎች የምግብ ድጋፍ እንደሚያሻቸው ማስታወቁ አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ መንግስት ለዜጎቹ ድጋፍ እንዲያገኙ በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሆነና ከዓለም አቀፍ ተቀማት ጋር ተባብሮ እንደሚሰራ በተደጋጋሚ ማሳወቁ አይዘነጋም።

✍️ዳጉ ጆርናል
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተባባሩት አረብ ኢሜሬትስ መንግስት ድጋፍ አማካኝነት ዋዲ አልሲደር ኮሜርሻል ኢንቨስትመንት ሊያቢሊቲ ሊሚትድ ኩባንያ ጋር በከተማዋ 30 ሺህ ወጪ ቆጣቢ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተባባሩት አረብ ኢሜሬትስ መንግስት ድጋፍ አማካኝነት በዋዲ አልሲደር ኮሜርሻል ኢንቨስትመንት ሊያቢሊቲ ሊሚትድ ኩባንያ ተወካዮች ጋር በቀጥታ የቪዲዮ ኮንፈረንስ የውል ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነቱ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት በከተማዋ የሚታየውን የመኖርያ ቤት ፍላጎት እና አቅርቦትን ለማጣጣም በተለያዩ አማራጭ የቤት ልማት ፕሮግራሞችን በመንደፍ እና ተግባራዊ በማድረግ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩም እንደአንድ አማራጭ ካስቀመጣቸው ተግባራት መካከል ከውጭ ባለሀብቶች ጋር በሽርክና በመስራት ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን በአጭር ጊዜ በመገንባት ለተጠቃሚዎች ማድረስ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም በሚቀጥሉት 5 ዓመታት የቤት ፍላጎቱን ለሟሟላት በሀገር ውስጥ እና ከውጪ ሀገር ኩባንያዎች ጋር በመቀናጀት በከተማዋ ከአንድ ሚሊዮን በላይ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት እቅድ መያዙን ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

በዚሁ መሰረት የከተማ አስተዳደሩ በተባባሩት አረብ ኢሜሬትስ መንግስት ድጋፍ አማካኝነት ከዋዲ አልሲደር ኮሜርሻል ኢንቨስትመንት ሊያቢሊቲ ሊሚትድ ኩባንያ ጋር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በ68.4 ሄክታር መሬት ላይ በመጀመሪያ ዙር 30 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የውል ስምምነት ሰነድ መፈራረሙን ምክትል ከንቲባዋ መግለፃቸውን ኸፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ ሴኔት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ጉዳይ ላይ ምን አለ?

ምክር ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ ሐሳብ ላይ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 10 ነጥቦችን ዝርዝሯል።በመጀመሪያ ሴኔቱ በትግራይ ክልል ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቋል በንሑሃን ዜጎች ላይ የሚደርስ ጥቃት በጽኑ ይወገዛል ብሏል።በሴኔቱ የውሳኔ ሃሳብ ላይ የቀረበው ሦስተኛው ሃሳብ ደግሞ፤ የኤርትራ ጦር በአስቸኳይ ከኢትዮጵያ እንዲያስወጣ ይጠይቃል።

ጨምሮም በትግራይም ሆነ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል በኤርትራ ሠራዊትም ሆነ በየትኛውም አካል የተፈጸሙ ማናቸውም አይነት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ ግድያዎች፣ ዘረፋዎች፣ የመድፈር ወንጀሎች በጽኑ ይወገዛሉ ብሏል።ሴኔቱ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የፖለቲካ ውጥረቱ ወደ ወታደራዊ ግጭት መግባቱን ተቀባይነት የለውም ብሏል።

በመላው ትግራይ የኤሌክትሪክ፣ የባንክ፣ የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በአፋጣኝ እና ሙሉ በሙሉ መመለስ አለባቸው ብሏል።ሴኔቱ በውሳኔ ሃሳቡ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ይጠበቅበታል ያለውን ሦስት ነጥቦች ዘርዝሯል።እነዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንክ እና ለዓለም የምግብ ፕሮግራም ቃል በገባው መሠረት የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን ለማሻሻል ተጨባጭ እርምጃዎችን ይውሰድ ብሏል።የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙትን ተጠያቂ ማድረግ ይኖርበታልም ብሏል።

በቁጥጥር ሥር የሚውሉ የህወሓት አባላትን በተመለከተም የኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፍ ሕጎች መከበር አለባቸው ብሏል ሴኔቱ።የኤርትራ ጦር በአስቸኳይ እና ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ እንዲወጣት የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲጠይቅ ሴኔቱ ጠይቋል።በፖለቲካ አመለካከታቸው የታሰሩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ደጋፊዎች፣ ማኅበራዊ አንቂዎች እንዲሁም ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን ተጠቅምው የታሰሩ ጋዜጠኞች በብሔራቸው፣ በሚያራምዱት ርዕዮተ ዓለም እና የፖለቲካ ወገንተኝነታቸው ሳይለዩ ከእስር ይለቀቁ ጠይቋል።

በመላው አገሪቱ ተዓማኒነት ያለው እና ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ ብሔራዊ ውይይት እንዲካሄድም ጠይቋል።ሴኔቱ በተጨማሪም በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በሙሉ ግጭት እንዲያቆሙ፣ ያሉ ልዩነቶችን ለመፍታት የፖለቲካ መፍትሄ እንዲሰጥ፣ በዓለም አቀፍ ሕግጋቶች እንዲገዙ፣ በንሑሃን ዜጎች ላይ ተጨማሪ ጉዳት ሊያስከትሉ ከሚችሉ ተግባራት እንዲቆጠቡ ጠይቋል።

ሴኔቱ በመጨረሻ ምክረ ሃሳቡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር፣ የገንዘብ ሚንስትር፣ የዩኤስኤይድ አስተዳደሪ ከሌሎች የአሜሪካ የፌደራል መስሪያ ቤቶች ጋር በመቀናጀት የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የኤርትራ መንግሥት እና ህወሓት ጋር በመገናኘት ግጭት እንዲቆም፣ የኤርትራ ጦር እንዲወጣ፣ የሰብዓዊ ቀውስ መፍትሄ እንዲሰጡ ጠይቋል።ሴኔቱ የአሜሪካ መንግሥት ፌደራል አካላት የዲፕሎማሲ፣ የልማት እና የሕግ አማራጮችን በመጠቀም ተጨማሪ ብሔር ተኮር የሆኑ ግጭቶች እንዳይከሰቱ እና በኢትዮጵያ መድበለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲያብብ ጠይቋል።ሴኔቱ በመጨረሻም የአሜሪካ መንግሥት ከዓለም አቀፍ አገር አገራት እና የተመድ የጸጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የቅርብ ትስስር በመፍጠር በትግራይ እና በተቀረበው የአገሪቷ ክፍል ለሚከሰቱ ግጭቶች መፍትሄ እንዲሰጡ አሳስቧል።

የሴኔት የውሳኔ ሐሳብ የሕግ ተፈጻሚነት የላቸውም። ምክረ ሐሳቦች በአንድ ጉዳይ ላይ የሴኔቱ አባላት የጋራ አቋምን የሚያንጸባርቁባቸው ናቸው።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ኦነግ በዘንድሮው ምርጫ መሳተፍ አይችልም ሲል ምርጫ ቦርድ አስታወቀ!

ኦነግ በውስጥ ችግሩ ምክንያት ጠቅላላ ጉባዔ ሳያካሂድ በመቆየቱ “የምርጫና የዕጩ ምዝገባ ጊዜ አልፎብናል” በማለት ቦርዱ ችግሩን ግምት ውስጥ በማስገባት የምልክት መረጣና የዕጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዲያደርግ እንዲፈቅድለትና ጠቅላላ ጉባኤውንም እንዲያጸድቅለት ቦርዱን በደብዳቤ ጠይቆ ነበር።ቦርዱም የቀረቡትን ሰነዶች በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና በፓርቲው ህገ ደንብ መሰረት መርምሮ ባሳለፈው ውሳኔ፤ አዲስ የተመረጡትን የኦነግ አመራሮች እና የተካሔደውን ጉባኤ እንደማይቀበል አስታውቋል፡፡

በዚህ መሰረት ኦነግ የቦርዱን ውሳኔ ተቃውሞ ወደ ፈረድ ቤት ወስዶ ሲከራከር ቆይቶ ፍርድ ቤትም የቦርዱን ውሳኔ ውድቅ አድርጓል።የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ያደረገውን የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ እና በስብሰባው ያሳለፈውን ውሳኔ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲቀበለው ወስኖ ነበር።

የቦርዱ ኮሙንኬሽን ሀላፊ ወይዘሪት ሶልያና ሽመልስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ የኦነግን የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዴት ልታስኬዱት ነው ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።ኦነግ በምርጫው መወዳደር የሚያስችለውን የምርጫ ስራዎች የጊዜ ሰለዳዎች ስላለፉት በዘንድሮው ምርጫ ላይ መወዳደር እንደማይችል ወይዘሪት ሶልያና ተናግረዋል።ኦነግ በፍርድ ቤት ተወስኖልኛል እና በምርጫው ልሳተፍ ብሎ ቦርዱን እንደጠየቀ ወ/ሪት ሶልያና ተናግረዋል።

ይሁንና ፓርቲው ለምርጫ ፉክክር የሚያበቁ ስራዎች ስላለፉት ፓርቲው በምርጫው ለመሳተፍ የሚያበቃ ጊዜ ስለሌለው እንዳይሳተፍ ቦርዱ መወሰኑን ተናግረዋል።ለአብነትም ፓርቲው የመራጮች ምዝገባ፤ የእጩ ተፎካካሪዎች ምዝገባ እና ሌሎች በምርጫው እንዲሳተፍ የሚያበቁ ስራዎችን አልፈውታል ብለዋል።የኦነግ የፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ ቦርድ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠይቆ ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውንም ወ/ሪት ሶልያና ተናግረዋል።

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ነገ በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኢምባሲን ጨምሮ በተለያዩ ኢምባሲዎች ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ጥሪዎች በመቅረባቸው የአሜሪካ ኢምባሲ ቆንስላ ቢሮ ለደኅንነት ጥንቃቄ ሲል በዕለቱ አገልግሎት እንደማይሰጥ ቢሮው በትዊተር ገጹ ማምሻውን አስታውቋል። አገልግሎት ፈላጊዎች ወደ ኢምባሲው አካባቢ እንዳይጠጉም ቢሮው አስጠንቅቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሊት በተያዘለት ጊዜ እንደሚካሄድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

በጎረቤት አገራትና ታላላቅ ሃይቆች ክልል የሚገኙ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲዮኖች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ጋር በመተባበር "የናይል ፍትሃዊ አጠቃቀም፣ የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ለክልላዊ ትብብር ያለው ሚና" በሚል ርእስ በተዘጋጀው የበይነ መረብ ውይይት ላይ ተሳትፈዋል።የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሊት በሶስቱ አገራት የሳይንቲስቶች ብሄራዊ ቡድን በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደሚካሄድ አቶ ደመቀ መኮንን ገልፀዋል።

የሶስትዮሽ ድርድሩ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ መርህ መሰረት ውጤታማ እንዲሆን የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ያላቸውን እምነት አረጋግጠዋል።ግብፅና ሱዳን ጉዳዩን ዓለም አቀፋዊ በማድረግ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ጥረት እያደረጉ ስለ መሆኑ አውስተዋል።

በስብሰባው ተሳታፊ የነበሩት የደቡብ ሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ጉዳዮች ሚኒስትር ደንግ ዳው ደንግ በበኩላቸው ታላቂ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ የሰላም ፕሮጀክት መሆኑን ገልፀዋል ፤ የሀገራቸው ፓርላማ በቅርቡ የናይል ስምምነት ማዕቀፍን እንደሚያፀድቅ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የሶሰትዮሽ ድርድር ሁሉን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ላይ በመድረስ እልባት እንደሚያገኝ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

በወቅቱም የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋውና ሌሌች የዘርፉ ባለሙያዎች የውይይት መነሻ ፅሑፍ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ በደብረ ብርሃን ከተማ የአፄ ዘርዓያዕቆብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጧል።

ፋብሪካው ትምህርት ቤቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ከአማራ አቀፍ ልማት ማህበር እና ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ እንደሚሰራ ታውቋል።

ለትምህርት ቤቱ ግንባታ 20 ሚሊየን ብር ወጪ ይደረጋል ተብሎ የተገመተ ሲሆን፣ ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚሸፍን ተጠቁሟል።

የትምህርት ቤቱ ግንባታ በአንደኛ ደረጃ ብቻ ተወስኖ የነበረውን የዘርዓያዕቆብ ትምህርት ቤት ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትነት ከፍ እንደሚያደርግ ዋልታ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ያሉ የታጠቁ አካላት “የሰብዓዊ እርዳታ ሰራተኞችን ህይወት” እንዲጠብቁ አሜሪካ ጥሪ አቀረበች!

ከህዳር ወር ወዲህ በትግራይ ሰባት የሰብዓዊ እርዳታ ሰራተኞች መገደላቸውን የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት ድርጊቱን የፈፀሙ አካላትን ወደ ሕግ እንዲያቀርብ ኤምባሲው ጠይቋል፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የውጭ ሀገር መንግስታት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙ የሚገልፅ ደብዳቤ ለማስገባት አለመቻሉ ተገለጸ!

የውጭ ሀገር መንግስታት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆሙ የሚገልፅ ደብዳቤ ዛሬ ማለዳ መቀመጫቸውን በኢትዮጵያ ላደረጉ ኤምባሲዎች ለማስገባት ታቅዶ የነበረው መርሐግብር ኤምባሲዎቹ በእለቱ ዝግጁ ባለመሆናቸው መከናወን አለመቻሉ ተገለፀ።በዚህም በሚቀጥለው ሳምንት ከኤምባሲዎቹ ጋር ይፋዊ ቀጠሮ በመያዝ ደብዳቤዎቹን ለማድረስ መታቀዱ ተገልጿል።

ሆኖም የውጭ ሀገር መንግስታት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት የሌለው መሆኑንና እጃቸውን እንዲያነሱ የሚጠይቀው መርሐግብር ግን በተያዘለት ጊዜ ይከናወናል ተብሏል።በዚህም ዜጎች በያሉበት ቦታ ሆነው ይህ መልዕክት በተለያዩ መንገዶች እንዲያስተላልፉ የመርሐግብሩ አስተባባሪዎች ጠይቀዋል።ከሀገራት ጋር የሚኖረውን ወዳጅነት ላይ ጥላ በማያጠለሽ መልኩና የሀገርን ገፅታ እንዳያበላሽ ጥንቃቄ በማድረግ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ህዝቡ ድምፁን እንዲያሰማም ጥሪ አቅርበዋል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ2.8 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የሥራ እድል ተፈጠረላቸዋል ሲል የፌዴራል የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከክልል ስራ እድል ፈጠራ አካላት ጋር በመሆን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀሙንና የመረጃ ጥራት ዳሰሳ ጥናት ግምገማ በሀዋሳ እያካሄደ ነው፡፡ኮሚሽኑ ይፋ እንዳደረገው የተፈጠረው የሥራ እድል የአመቱን አቅድ 94 በመቶ ያሳካ ነው ተብሏል፡፡በግብርና፣ ኢንዱስትሪ እና አገልግሎት ዘርፍ ከተፈጠረው የሥራ እድል ውስጥ 64 በመቶ ቋሚ ሲሆን ቀሪው ጊዜያዊ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ዘንድሮ በገጠርና በከተማ በተደረገው እንቅስቃሴ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል 35 በመቶ ሴቶች ናቸው ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ጅምራቸው ጥሩ የሆነ ውጤት ያስገኘ ቢሆንም፣ በሌላ መንገድ አገሪቱ ዕድልም ዕዳም ያለበት ምዕራፍ ላይ እንደምትገኝ ተገለጸ፡፡

ይህ የተገለጸው የሰላም ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሽግግር ሒደት፣ ብሔራዊ መግባባት፣ ምርጫ 2013 እና ከዚያ ባሻገር በተሰኙ ርዕሰ ጉዳዮች የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚገኙበት ለአራት ቀናት የሚቆይ አገራዊ የምክክር መድረክ ሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2013 ዓ.ም. በሐያት ሬጀንሲ ሆቴል በተከፈተበት ወቅት ነው፡፡

በመድረኩ የተገኙት የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያ ካሚል፣ ‹‹አገር በተወሰነ አካል ፍላጎትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ብቻ ማቆም እንደማይቻል ሁሉም ሊያውቀው የሚገባ አውነታ ነው ብለን እናምናለን፤›› ብለዋል፡፡ ሚኒስትሯ አክለውም፣ ‹‹ዘላቂ የሰላም ግንባታ ሥራችን ከግለሰብ የሚጀምር፣ በቤተሰብ የሚመነዘር፣ በኅብረተሰብ ደረጃ የሚተገበር፣ የእሱም ድምር ውጤት አገራዊ ቅርስ ሆኖ የሚያዝ እንደሆነ ይታመናል፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

via reporter
@Yenetube @Fikerassefa