ባለፈው 1 ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ በዓለም ዙሪያ ቢያንስ 225 ሚሊዮን ሰዎች ከቋሚ ሥራቸው ተፈናቅለዋል ተባለ።
በሌላ በኩል፣ የዓለማችን 10 የናጠጡ ከበርቴዎች ሀብት በዚሁ 1 ዓመት ውስጥ በ500 ቢሊዮን ዶላር መጨመሩ ተሰምቷል።እነዚህን ሪፖርቶች ያወጡት፣ በቅደም ተከተል ዓለምአቀፉ የሥራ ድርጅት (ILO) እና በፀረ-ድህነት ተግባሩ የሚታወቀው የእንግሊዙ ኦክስፋም ናቸው።የድርጅቶቹን ሪፖርት ጠቅሶ ዋሽንግተን ፖስት እንዳስነበበው፣ በመላው ዓለም በመቶ ሚሊዮኖች የተቆጠሩ ሰዎች ከቋሚ ሥራቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት የሆነው የኮረና ወረርሽኝ ጦስ ነው።
የዓለምአቀፉ የሥራ ድርጅት ሪፖርት፣ በዓለም በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ብቻ ባለፈው 1 ዓመት ሥራ ያጡ ሰዎች ቁጥር፣ እ.አ.አ. በ2009 በተከሰተው ዓለምአቀፍ የፋይናንስ ቀውስ ሳቢያ ካገጠመው በአራት እጥፍ የላቀ ነው ብሏል።በሌላ በኩል፣ የዓለማችን አሥሩ ቱጃሮች ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ ያጋበሱት ከ500 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት፣ ለመላው የዓለም ህዝብ ክትባት ለማዳረስ የሚያስችል አቅም ያለው እንደሆነ የኦክስፋም ጥናት በንጽጽር ማመልከቱን ዘገባው አውስቷል።
✍Sheger
@YeneTube @FikerAssefa

በፈለጉበት ቦታ ሆነው የፈለጉትን ይማሩ!
www.yenecademy.com ላይ በመግባት የፈለጉትን ኮርሶች መማር ይችላሉ::
አሁኑኑ ገብተው ይማሩ
@yeneacademy

ኢዜማ በቀጣዩ ምርጫ ከየትኛውም ፓርቲ ጋር ሳይዋሀድ ብቻውን በመላው የሃገሪቱ የምርጫ ወረዳዎች እንደሚወዳደር አስታወቀ።
የኢትዮጲያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሳወቀው ለቀጣዩ ስደስተኛ ዙር ሃገራዊ ምርጫ በመላ ሃገሪቱ ባሉት 435 የምርጫ ወረዳዎች ዕጩዎችን ያቀርባል፡፡ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ እንደተናገሩት ፓርቲያቸው በአዲሰ አበባ በሚገኙ 23 የምርጫ ወረዳዎች ለመሳተፍ ከፍተኛ ዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
[Ethio FM]

ለሠርግ ማድመቂያ በሚል በተተኮሰ ጥይት የሁለት አጃቢዎች ህይወት አለፈ!
በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ለሠርግ ማድመቂያ
በሚል በተተኮሰ ጥይት የወንድ ሙሽራው ሁለት አጃቢዎች ህይወታቸው ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መሳፍንት አባይ ለኢዜአ
እንደተናገሩት አጃቢዎቹ ህይወታቸው ያለፈው በወረዳው ጭህራ ማንጠርኖ በተባለ የገጠር ቀበሌ ውስጥ ነው፡፡
ጥር 16/2013 አመሻሽ የተከሰተው አደጋ ሙሽራው ከወንድ አጃቢዎቹ ጋር
በመሆን ሴት ሙሽራዋን ከቤተሰቦቹዋ ቤትና ከመንደሩዋ ይዟት በመውጣት ላይ
እያለ መሆኑን ን ገልጸዋል፡፡
ለሠርጉ ማድመቂያ ተብሎ በአንድ ግለሰብ በተተኮሰው ጥይት ሁለቱ የሙሽራው አጃቢዎች ክፉኛ ቆስለው ወደ ህክምና በመወሰድ ላይ እያሉ ህይወታቻው ማለፉን ዋና ኢንስፔክተር መሳፍንት አስታወቀዋል፡፡
ፖሊስ የሙሽራውን አጃቢዎች አሟሟት በህክምና በማረጋገጥ አስከሬናቸውን
ለቤተሰቦቻቸው ማስረከቡንና የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸውም ትናንት መፈጸሙን
ተናግረዋል፡፡
በሠርጉ እለት ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ ለጊዜው ከአካባቢው ማምለጡን ያመለከቱት ዋና ኢንስፔክተሩ ፖሊስ ለመያዝ የተጠናከረ ፍለጋ እያካሄደ እንደሚገኝም አስረድተዋል፡፡
በሠርግና ቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይ ጥይት በመተኮስ በንጹሃን ሰዎች ላይ በየጊዜው የሚደርሰውን አደጋ ለመከላከል ማህበረሰቡ ከፖሊስ ጋር ተባብሮ ሊሰራ እንደሚገባም ዋና ኢንሰፔክተር መሳፍንት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
Via Bisrat FM

ከድንበር ድርድር በፊት የኢትዮጵያ ቅድመ ሁኔታ
ሱዳን ቀድማ ወደነበረችበት ቦታ ሳትመለስ በድንበሩ ጉዳይ ድርድር እንደማይኖር ኢትዮጵያ አስታወቀች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳምንታዊ መግለጫው ኢትዮጵያዊ በትግራይ ሕግ የማስከበር እርምጃ ላይ ባተኮረችበት ወቅት ሱዳን ድንበር አልፋ የኢትዮጵያን መሬት መያዟን አስታውሷል።
ሆኖም ለድንበር ውዝግቡ እልባት ማግኘት የሚቻለው በሰላማዊ የውይይት መድረክ ብቻ ነው የሚለው የኢትዮጵያ አቋም ዛሬም የፀና ነው ብሏል።
ቃል አቀባዩ ዲና ሙፍቲ በጉዳዩ ላይ እናደራድራችሁ ለሚሉ አገራትና ወገኖች ክብር አለን ያሉም ሲሆን፤ ከየትኛውም ድርድር በፊት ግን መቅደም ያለበት ቅድመ ሁኔታ እንዳለ ነው የገለፁት።
ይኸውም ሱዳን መጀመሪያ ወደነበረችበት ቦታ መመለስና የያዘችውን መሬት መልቀቅ አለባት የሚል እንደሆነ ነው ያሰመሩበት።
[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @Fikerassefa

በአዲስ አበባ ከ21 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በህገወጥ መንገድ ተይዘው መገኘታቸውን ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ በህገወጥ መሬት ወረራ ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።
ወይዘሮ አዳነች በዚህ ጊዜ እንዳሉት በአዲስ አበባ በህገወጥ መንገድ 21 ሺህ 695 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በህገወጥ መንገድ ተይዘው መገኘታቸውን ተናግረዋል።
ከዚህ ቤቶች ውስጥ 15 ሺህ 891 ቤቶች የባለቤትነት መረጃ አልቀረበባቸውም።
850 ቤቶች ደግሞ ዝግ ሆነው ሲገኙ 4 ሺህ 530ዎቹ ደግሞ ባዶ ሆነው መገኘታቸውን ገልጸዋል።
እንደ ምክትል ከንቲባዋ በአዲስ አበባ ካሉ121 ወረዳዎች ውስጥ በ88ቱ ወረዳዎች በተፈጸመ የመሬት ወረራ 1 ሺህ 338 ሄክታር መሬት የተወረረ ሲሆን በተደረገው የህንጻ ቆጠራ 322 ህንጻዎች እና ቤቶች ባለቤት አልባ መሆናቸውን ወይዘሮ አዳነች ተናግረዋል።

ኢዜማን ጨምሮ 5 ፓርቲዎች የምርጫ ምልክቶቻቸውን ቀይረው እንዲያቀርቡ ቦርዱ አሳሰበ!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የፓርቲዎች የምርጫ ምልክት መረጣ እየተከናወነ እንደሆነ አስታውቋል።
በዚህም መሰረት እስከአሁን ድረስ 45 ያህል ፓርቲዎች ምልክቶቻቸውን ያስገቡ ሲሆን አምስት ፓርቲዎች የመረጧቸው ምልክቶች በተለያዩ ምክንያቶች ቀይረው እንዲያቀርቡ ጥሪ ተደርጎላቸዋል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ( ኢዜማ) የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ፤
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ፤
የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ- የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ፤
የምእራብ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ – ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በሆኑ፤
የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያቂ ንቅናቄ- ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በመሆኑ የምርጫ ምልክቶቻቸውን ቀይረው እንዲያቀርቡ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
በተጨማሪ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር -ህጋዊ ሃላፊነት በተሰጠው አካል ምልክታቸውን እንዲመርጡ ተጠይቆ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ የምርጫ ምልክት አስገብተዋል ብሏል የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ።
በዚህ መሰረት የምርጫ ምልክቶቻቸውን ያላስገቡ፣ እንዲቀይሩ የተገለፀላቸው ወይም መቀየር የሚፈልጉ እስከ ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንዲያጠናቅቁ ቦርዱ እያሳስቧል።የጸደቁ ምልክቶችን እና የፓርቲዎችን ዝርዝር ሂደቱ ሲጠናቀቅ ይፋ እንደሚያደርግ ቦርዱ አስታውቋል።

በመቐለ "ቤንዚን በሊትር እስከ 50 ብር በህገ-ወጥ መልኩ እየተሸጠ" መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያቋቋመውን ኮሚቴ በመላክ ማረጋገጡን አስታወቀ። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ባደረገው ክለሳ በአዲስ አበባ ቤንዚን በሊትር 23 ብር ከ67 ሳንቲም ይሸጣል።ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እንደሚለው በመቐለ ነጭ ጤፍ 45 ብር፣ ቀይ ጤፍ 38 ብር፣ ሠርገኛ ጤፍ 38 ብር፣ ስንዴ 28 ብር፣ ሽንኩርት 15 ብር፣ ቲማቲም 10 ብር፣ ድንች 20 ብር በኪሎ እንደሚሸጡ የኮሚቴው አባላት አረጋግጠዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የሐዋሳ የኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ችግር ላይ መሆኑ ተገለጸ!
በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ቡድን አባላት በኢሚግሬሽን እና ወሳኝ ኹነቶች ኤጄንሲ የሐዋሳውን ቅርንጫፍ በጎበኙበት ወቅት የቅርንጫፉ ሠራተኞች በበርካታ ችግር ላይ እንደሚገኙ መገንዘባቸውን ለምክር ቤቱ ገልጸዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ቡድን የሐዋሳ የኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ምን እንደሚመስል እና በምን አይነት ቁመና ላይ እንደሚገኝ ተዘዋውሮ ከተመለከተ በኋላ ትዝብቱን ለቅርንጫፉ ማኔጅሜንት ዘርዝሯል።
[Addis Maleda]

በወላይታ ሶዶ አንዲት እናት አራት ልጆችን በሰላም ተገላገለች!
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ኦቶና ማስተማሪያና ሪፌራል ሆስፒታል አንዲት እናት አራት ልጆችን በሠላም ተገላግላለች። በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ዎሺዎቻ ዳቃያ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወይዘሮ ወርቅነሽ ብርሃኑ ካገባች ዓመት ያለፋት ሲሆን የመጀመሪያዋ እርግዝናዋ መሆኑን ገልጻለች።
Via FBC

ማይንድ ኢትዮጵያ ለብሄራዊ ውይይት የሚያግዙ አጀንዳዎችን እየሰበሰብኩ ነው አለ!
ከነሐሴ ወር 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ ዘርፎች የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በተለያዩ መድረኮች ሲያወያይ የቆየው የሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ምክክር ኢኒሼቲቭ ኢትዮጵያ (Multi-stakeholder Initiative for National Dialogue Ethiopia (MIND - Ethiopia))፣ ለምክክሮቹ የሚረዱ አጀንዳዎችን እየሰበሰበ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡
ከምርጫ በፊት ሊፈቱ የሚገባቸው ተብለው የተለዩት ለምርጫ አስቻይ ሁኔታዎች መኖር አለመኖራቸው፣ የምርጫ ሒደትን የተመለከቱ የታዛቢና መሰል ጉዳዮች፣ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድና የሌሎች አስፈጻሚ አካላት ገለልተኝነት፣ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችና የመንግሥት ኃላፊነትና ተጠያቂነት፣ የብሔረሰቦች የማንነት ጥያቄዎችና የምርጫ ክልል ተያያዥ ጉዳዮች፣ ሰላምና ፀጥታ፣ ከውጤት በኋላ ሊነሱ የሚችሉ ቀውሶችና ተጠያቂነት፣ የፀጥታ አካላት ተጠያቂነት፣ ሚዲያና ሚዛናዊነት፣ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎዎችን የተመለከቱ ናቸው፡፡
ከምርጫ በኋላ በረዥም ርቀት እንዲታዩ የተባሉት ሕገ መንግሥት፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ገለልተኝነት፣ የአገረ መንግሥት ግንባታ፣ የታሪክና ትርክቶች ንባቦች አረዳዶችና የብሔራዊ ዕርቅ ጉዳይ ናቸው፡፡
[Reporter]

የአውሮጳ ኅብረት የሰብአዊ ጉዳዮች ልዑክ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው!
በትግራይ ክልል ስላለው ሁኒታና በኢትዮጳያና ሱዳን የደንበር ውዝግብ ላይ ለሚኒስትሮቹ ማብራሪያ ሰጥቻለሁ በማለት ሁኒታውን በቅርብ ለማየትና ከሚመለከታቸው አክላት ጋር ለመወይየትም የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሚስተር ፔካ ሀቪስት የአውሮጳ ህብረትን ከፍተኛ ልኡክ በመምራት በዚህ ወር መጨረሻ ወደ አካባቢው የሚሄዱ መሆኑን ቦሬል አስታውቀዋል።
[DW]

በደቡብ ክልል የሚገኙ አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ 11ኛ የፌደራሉ መንግስት አካል ሆነው ለመደራጀት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን አስታወቁ።
የጋራ ክልላዊ መንግሥት ለመመስረት የተስማሙት የከፋ፣ የሸካ ፣የቤን ሸኮ፣የምዕራብ ኦሞና የዳውሮ ዞኖች እንዲሁም የኮንታ ልዩ ወረዳ፣ክልል ለመሆን የሚያበቃቸውን ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን የደቡብ ክልል መንግሥት አስታውቋል። የደቡብ ምዕራብ ክልል ህዝበ ውሳኔ አስተባባሪ ኮሚቴ ፣ለዶቼቬለ እንዳሳወቀው ህዝበ ውሳኔውን ከሚያስፈጽመው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ ነው።የህዝበ ውሳኔው ውጤት መሠረት የሚዋቀረውን ክልላዊ መንግስት፣ ህገ መንግስትና አስተዳደራዊ መዋቅርም ከወዲሁ እንደሚያዘጋጅ የኮሚቴው ምክትል ስብሳቢ አቶ ፀጋዬ ማሞ ተናግረዋል።ኩታ ገጠም የሆኑት እነዚህ አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ ፣ባለፈው ዓመት ነበር አንድ የጋራ ክልላዊ መንግሥት ለማቋቋም በየምክር ቤቶቻቸው የወሰኑት።ውሳኔያቸውም የኢትዮጵያ ፌደሬሽን ምክር ቤትን ይሁንታ አግኝቶ ጥያቄው ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድበት መወሰኑን የDW ዘገባ ያስታውሳል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የተከሰተው የጸጥታ ችግር ውስብስብ የሆነው ከቀበሌ ጀምሮ በየደረጃው ባሉ የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉ አመራሮች የተሳተፉበት በመሆኑ እንደሆነ የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ ገለፁ።
አፈጉባኤው አቶ ታደለ ተረፈ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ በክልሉ ከመጋቢት 2011 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ የፀጥታ ችግሮች ተከስተዋል። ባለፉት ስድስት ወራት ደግሞ ችግሩ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር።
የክልሉ ምክር ቤት ይህንን ችግር ከመሰረቱ ለመፍታት በህግና ዴሞክራታይዜሽን ቋሚ ኮሚቴ አማካኝነት ልዩ ልዩ ጥረቶችን ቢያደርግም በአካባቢው በነበሩ የፀጥታ ችግሮች የተነሳ ኮሚቴው ታች ድረስ ወርዶ ችግሩን ለማየትና ለመገምገም እንዳልቻለ አመልክተዋል።
በምክር ቤት ደረጃ በጉዳዩ ላይ ምክክርና ውይይት ከተደረገ በኋላ በተደጋጋሚ አቅጣጫዎች ተቀምጠው እንደነበርም አስታውቀዋል።
ችግሩ ከምክር ቤቱም ሆነ ከክልሉ አቅም በላይ በመሆኑ የፌዴራል መንግስት ከአንድም ሶስት ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማውጣት ችግሩን ለመቆጣጠር ሙከራ አድርጓል ያሉት አቶ ታደለ፤ ይህም ቢሆን ስኬታማ ሊሆን እንዳልቻለ ጠቁመዋል ። ለዚህም ዋነኛ ምክንያቱ የውስጥና የውጭ ኃይሎች በአካባቢው ላይ ያላቸው የተለየ ፍላጎት እንደሆነም ገልጸዋል።
ክልሉ ሰፊ የእርሻ መሬት፣ በርካታ ማዕድናትና ጥሬ ሃብት አለው ያሉት አቶ ታደለ፤ ይህም የራሳቸውን ሃብት ለማካበት የሚፈልጉ ኃይሎች ልዩ ፍላጎት እንዲያድርባቸው ምክንያት መሆኑን አመልክተው፣ ከዚህም ባሻገር ክልሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሚገነባበት ስፍራ በመሆኑ የውጭ ኃይሎች በአካባቢው ላይ ልዩ ትኩረት ማድረጋቸውን ገልጸዋል ።
በነዚህና ሌሎች ችግሮች የተነሳ ክልሉ የግጭት መናኸሪያ ሆኖ መቆየቱን ጠቁመዋል።
እንደ አቶ ታደለ ገለፃ፤ በየደረጃው ያሉት የመንግሥት መዋቅሮች ለችግሩ መባባስ የራሳቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል። በተለይ የቀበሌ፣የወረዳ እና የዞን አመራሮች ሆን ብለው ወይም ተገደው የችግሩ አስተሳሰብ ተሸካሚ ሆነዋል ፤ ከዚያ በላይ ያሉ ከፍተኛ አመራሮችም በአብዛኛው ሆን ብለው የችግሩ አራማጅ እንደነበሩ አስታውቀዋል።
በተለይ የቀበሌና የወረዳ አመራሮች በህብረተሰቡ ውስጥ የሚገኙ በመሆናቸው እነዚህን ኃይሎች ከህብረተሰቡ በመነጠል እርምጃ ለመውሰድ አዳጋች እንደነበር የጠቆሙት አቶ ታደለ፤ ይህ ደግሞ ችግሩን ውስብስብ አድርጎት እንደቆየ አመልክተዋል።
በዚህ ውስጥ የሚሳተፉ የታችኛው መዋቅር ውስጥ ያሉ አመራሮችን ሁኔታ ስንመለከት አንዳንዱ ሆን ብሎ የሃሳቡ ደጋፊና ተጋሪ ሆኖ ሲሆን ከፊሉ ደግሞ ተገዶ በጫና የነዚያ የፀረ ሰላም ኃይሎችን እቅድ የሚያስፈጽም ነው።
ወደ ከፍተኛ አመራሩ ሲመጣ ደግሞ በአብዛኛው የአስተሳሰቡ ተሸካሚ ሆኖ ነው። ይህ ደግሞ ከግል ጉዳይ ወይም ከስልጣን ጥማት ጋር ተያይዞ ሊሆን ይችላል። በዚህ የተነሳ የሃሳቡ ተጋሪ የሚሆንበት ሁኔታ አለ።በአጠቃላይ ግን በታችኛው መዋቅር ውስጥ ችግሩ በጣም ሰፊ እንደሆነ አስታውቀዋል።
Via EPA

ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ሀሰተኛ ደረሰኝ ተገኘ!
የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ባደረገው የኦዲት ምርመራ ግምታቸው ከ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ ሀሰተኛ ደረሰኞች ማግኘቱን ለአዲስ ዘይቤ ገልጿል፡፡“የተጭበረበሩ ደረሰኞችን በማዘጋጀት፣የታክስ እዳውን ለመቀነስ ወይም ተመላሽ ለመጠየቅ ሆን ተብሎ እንደተደረገ በኦዲት ስራ ተጋልጧል።
እንዲህ አይነት ህገወጥ ተግባር ደግሞ የ100 ሺህ ብር የገንዘብ እና ከሰባት እስከ አስር አመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ቅጣት እንደሚያደርሰ ህጉ ላይ በግልፅ ተቀምጧል።” በማለት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሀመድ ተናግሯል።በመጨረሻም አሁን ላይ መስሪያቤቱ የህግ ማስከበር ስራን በስፋት አጠንክሮ እየሰራ እንደሚገኝ ዋና ዳይሬክተሩ ጠቅሶ የኦዲት ስራን የሚሰሩ ባለሞያዎች ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው ብሏል፡፡
[@addiszeybe]

ዳሞት ባንክ የወረቀት ተኮር ስራን በማስቀረት በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎትን ይዞ ሊመሰረት ነው!
ዳሞታ ባንክ አክሲዮን ማህበር በኢትዮጵያ ያለውን የባንክ አገልግሎትና የህዝብ ቁጥር አለመመጣጠን ታሳቢ አድርጎ ሊመሰረት መሆኑን አስታወቀ።የባንኩ የትኩረት አቅጣጫ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ ሰፋፊ የስራ እድል መፍጠር በመሆኑ ከተከፈለ ካፒታል ውስጥ 10 በመቶ የሚሆነውን ከድርጅቶችና ከግለሰብ ጋር በጋራ በመሆን ለኢንቨስትመንት አገልግሎት ያውለዋል።ዘመናዊ አሰራርን ይከተላል የተባለው ባንከ ወረቀት ተኮር የሆነውን አሰራር የሚያስቀር የባንክ ቴክኖሎጂ ይዞ ወደ አገልግሎት እንደሚገባም ዳሞት ባንክ አስታውቋል።
የመንግስት መመሪያ ከተሻሻለ ከፍተኛ ለሀገር ጠቀሜታ ያላቸውን ግለሰቦች እና ድርጅቶች የብድር አገልግሎት መስጠት፣ለዲያስፖራው ከ 10-20% ተቀማጭ በሆነ የአጭር፣የመካከለኛ እና የረዥም ጊዜ የቤት መግዣ ብድር ይሰጣል።ከሌሎች ባንኮች ጋር በመተባበር ግዙፍ ፕሮጀክቶችን የብድር አገልግሎት መስጠት እና በአንድ ላይ መስራት የሚያስችሉ አገልግሎቶችን እንደሚያስተዋውቅ የባንኩ አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኤልያስ ሎሃ ለትብስራ ሬድዮ ተናግረዋል።
የአንድ አክሲዮን ዋጋ አንድ ሺህ ብር ሲሆን መግዛት የሚቻለው ዝቅተኛ የአክሲዮን ብዛት 50 ወይም 50 ሺህ ብር ነው።የአክሲዮን ግዢ ሲፈጽሙ የጠቅላላ አክሲዮን ዋጋ 50% ከፍለው ቀሪውን በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ በሶስት ዙር ከፍለው ማጠናቀቅ እንደሚቻል ዳሞት ባንክ አስታውቋል።
[Bisrat FM]

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አስመልክቶ የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባላት፣መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት አመራሮችና የሚዲያ ተቋማት በተገኙበት ወርክ ሾፕ አካሂዷል።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ቻናሎች ወደ ኢትዮ ሳት መቀየራቸው ተከትሎ የዲሽ ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል፡፡
ከሰሞኑ በርካታ የቴሌቪዥን ቻናሎች ወደ ኢትዮ ሳት መቀየራቸው ተከትሎ የዲሽ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ ነው የተነገረው፡፡ኢትዮ ኤፍ ኤም በተለያዩ የዲሽ እቃ መሸጫ ሱቆች ተዘዋውሮ በተመለከተበት ሰአት በዲሽ እቃዎች ላይ ከፍተኛ ጭማሪ መኖሩን ታዝቤያለው ብሏል፡፡
እንደማሳያ ከአንድ ወር በፊት ኤች ዲ ላይፍ ስታር ከ650 እስከ 700 ይሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ እስከ 1000 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡እንዲሁም ሱፐር ስታር ኢሮ ቦክስ እና ኤል ኢጂ 700 የነበረ ሲሆን አሁን እስከ 1 ሺህ 100 ድረስ እየተሸጠ ይገኛል፡፡
የዲሽ ዋጋ በተመለከተም ባለ 60 ሳህን 600 ብር የነበረ ሲሆን አስከ 850 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡ባለ 90 ሳህን ደግሞ 700 የነበረ ሲሆን አሁን ላይ እስከ 1 ሺህ አንድ መቶ ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ኢትዮ ኤፍ ኤም መታዘብ ችሏል፡፡እንደዚሁም የዲሽ ዋጋም በተመለከተ ከዚህ በፊት 20 ሜትሩ አንድ መቶ ብር የነበረ ሲሆን አሁን በሜትር እስከ 600 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ በተከሰተ የእሳት አደጋ የ ሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ።
የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በትላንትናው እለት በደረሰ ድንገተኛ የእሳት አደጋ የሁለት ሰው ህይወት ማለፉን ገልጿል፡፡አደጋው የደረሰው በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ቦኖ ውሃ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ በቀበሌ መኖሪያ ቤቶች ላይ ነው፡፡በተከሰተው ድንገትኛ የእሳት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ታውቋል፡፡
ህይወታቸው ያለፈው አንድ አረጋውያንና አንድ ወጣት ናቸው፡፡እንደዚሁም አንድ ወጣት ህክምና ተሰጥቶት ወደ ቤት መመለስ መቻሉንና በአደጋውም ሁለት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መቃጠላቸውንም ነው ያስታወቀው፡፡የአደጋው መንስኤ በፖሊስ በመጣራት ላይ የሚገኝ ሲሆን በአደጋው ምን ያህል ንብረት ለውድመት እንደተዳረገ እና ምን ያህል ንብረት ደግሞ ማዳን እንደተቻለ በመጣራት ላይ ነው፡፡

የእነ አቶ ጃዋርን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ፍርድ ቤቱ በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ!
የእነ አቶ ጃዋር መሀመድን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ፍርድ ቤቱ በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስትና የጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ዛሬ በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ተሰይሞ የነበረው የተጠርጣሪዎችን የእምነት ክህደት ቃል ለመመልክት ነበር።ይሁንና ተከሳሾቹ ቤተሰቦቻቸን ችሎት ስላልታደሙ የእምነት ክህደት ቃላቸንን መስጠት አንችልም ሲሉ አቤቱታ አሰምተዋል።
አቃቢ ህግም ጊዜው በተገፋ ቁጥር የተከሳሾችም ሆነ የኛንም ጊዜ እየተወሰደ ይሄዳል ስለዚህ ጊዜው ታሳቢ ቢደረግ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።አቶ ጃዋርም የፍርድ ቤቱን ጊዜ ለመውስድ አይደለም ቤተሰቦቻችን መግባት ስላለባቸው ነው ሲሉ በፍርድ ቤቱ ያላቸውን እምነት ጥሩ እንደሆነ ገልጸዋል።አቤቱታውን ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመመልከት ለጥር 27 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ኢቢሲ ዘግቧል።