ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት 6 ወራት ከ25 ቢሊየን በላይ ብር ማግኘቱን አስታወቀ።
የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ በተቋሙ ግማሽ ዓመት አፈጸጸም ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።ወይዘሪት ፍሬህይወት በዚህ ጊዜ እንዳሉት ባለፉት 6 ወራት 25 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል።
ገቢው ካለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጸጸር በ12.3 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።ተቋሙ በአጠቃላይ 50.7 ሚሊየን ደንበኞች እንዳሉት ተገልጿል።ካሉት ደንበኞች ውስጥ 48.9 ሚሊዮኖቹ የሞባይል ደንበኞች ሲሆኑ 23 ነጥብ 5 ሚሊዮን ደግሞ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ናቸው።
[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa

ውቅሮ ፣አዲግራት እና ደገ ሀሙስ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎት መጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።
የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ እንዳሉት በትግራይ ክልል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት የቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደገና ለማስጀመር ጥረቶች ቀጥለዋል ብለዋል።
በአዲግራት፣ውቅሮ እና እደጋ ሀሙስ አካባቢዎች ኔትወርክ አገልግሎት ተጀምሯል ብለዋል።
በሌሎች አካባቢዎችንም የስልክ አገልግሎት ለማስጀመር የጥገና ስራዎችን እየሰራን ነውም ብለዋል።የሳይበር ጥቃት ሙከራ በስራችን ላይ ችግር ሆኖብን ነበር ነገር ግን ኔትዎርካችን ሳይነካ መክተን አልፈናል ሲሉም ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል።

አዲሱ የኢትዮ ቴሌኮም ማቋቋሚያ ደንብ ማሻሻያ ኢትዮ ቴሌኮም የተፈቀደለት ካፒታል ከ40 ቢሊዮን፣ 400 ቢሊዮን እንዲሆን ያስችለዋል።
እንዲሁም ደንቡ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪው በሞባይል ገንዘብ እና በሌሎች ተዛማጅ የፋይናንስ አገልግሎቶች ውስጥ እንዲሰማራ ያስችለዋል ፡፡
[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
እንዲሁም ደንቡ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪው በሞባይል ገንዘብ እና በሌሎች ተዛማጅ የፋይናንስ አገልግሎቶች ውስጥ እንዲሰማራ ያስችለዋል ፡፡
[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
በስድስት ተከታታይ ወራት የወጪ ንግድ አፈፃፀም ከፍተኛ ድርሻ ካላቸው አምስት ዘርፎች መካከል ወርቅ በአንደኝነት መቀመጡ ተገልጿል።
በዚህም መሰረት
1. ወርቅ 335 ነጥብ 54 ሚሊየን ዶላር
2. ቡና 304 ነጥብ 46 ሚሊየን ዶላር
3. አበባ 213 ነጥብ 37 ሚሊየን ዶላር
4. ጫት 187 ነጥብ 82 ሚሊየን ዶላር
5. የቅባት እህሎች 150 ነጥብ 72 ሚሊየን ዶላር ገቢ ያስገኙ ሲሆን የጥራጥሬ ሰብሎች፣ጨርቃጨርቅና አልባሳት እንዲሁም ኤሌክትሪክ ከስድስት እስከ ስምንት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
ምግብና መጠጥ፣የስጋ ወተትና ኢንዱስትሪ ዘርፍ፣አትክልትና ፍራፍሬ፣ የቁም እንስሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች እና ኤሌክትሮኒክስ እንደየቅደም ተከተላቸው ያለውን ደረጃ መያዛቸውም ነው የተገለጸው።
Via FBC

የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች የድጋፍ ፊርማ እንዲያቀርቡ የሚደነግገው የህግ ክፍል ለዘንድሮው ምርጫ ብቻ እንዲታገድ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ለፓርላማ ቀረበ።
በኮቪድ 19 ምክንያት የወረቀት ልውውጥን ለመቀነስ፤ ባለው የተጣበበ የምርጫ ሰሌዳ ፊርማ ለማሰባሰብ በቂ ጊዜ ባለመኖሩ እንዲሁም ፓሪቲዎች ቅሬታ እያቀረቡበት በመሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ 1162/2011 አንቀፅ 32(2) ለ6ኛው ምርጫ ብቻ እንዲታደግ ተጠይቋል።
[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
በኮቪድ 19 ምክንያት የወረቀት ልውውጥን ለመቀነስ፤ ባለው የተጣበበ የምርጫ ሰሌዳ ፊርማ ለማሰባሰብ በቂ ጊዜ ባለመኖሩ እንዲሁም ፓሪቲዎች ቅሬታ እያቀረቡበት በመሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ 1162/2011 አንቀፅ 32(2) ለ6ኛው ምርጫ ብቻ እንዲታደግ ተጠይቋል።
[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
ባይደን በተሾሙ ማግስት ቻይና በ28 የአሜሪካ የቀድሞ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ጣለች!
በዘመነ ትራምፕ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩት ማይክ ፖምፒዮ እና ሌሎች 27 ባለስልጣናት ላይ ቻይና ማዕቀብ መጣሏን የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ባለስልጣናቱ በቻይና ላይ ጭፍን ጥላቻ በማራመድ ሉዓላዊነቷን በመዳፈራቸው እና በውስጥ ጉዳይዋ ጣል ቃ በመግባታቸው ነው ማዕቀቡ እንደተጣለባቸው የተገለጸው፡፡ 28ቱ የትራምፕ ሹማምነንት ወደ ቻይና እና የሀገሪቱ አካል ወደሆኑት ሆንግ ኮንግ ፣ እና ማካኦ እንዳይገቡ እገዳ ተጥሎባቸዋል ሲል ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መንግሥት ሁሉንም የቤት ሰራተኞች ቀጣሪ ኤጀንሲዎችን ሊዘጋ ነው፡፡
የቤት ሰራተኞች አስመጪ ኤጀንሲዎቹ በመጋቢት ወር ሙሉ በሙሉ እንደሚዘጉ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡በአገሪቱ 250 የቤት ሰራተኛ አስቀጣሪ ኤጀንሲዎች እንዳሉ መረጃው አስታውሷል፡፡አብዛኞቹም በሕገ-ወጥ መንገድ በቱሪስት ቪዛ ወደ አገሪቱ የቤት ሰራተኞችን የሚያስገቡ ናቸው ተብሏል፡፡ነባሮቹ የግል ኤጀንሲዎች በመጋቢት ወር ሙሉ በሙሉ ሲዘጉ ለዚሁ ዓላማ የተቋቋሙ 58 የመንግሥት ማዕከላት የቤት ሰራተኞችን ቅጥር እና አስተዳደር እንደሚያቀላጥፉ ተነግሯል፡በመንግሥት ስታትስቲካዊ አሃዝ መሰረት በኢሚሬትስ ከሚኖሩ ሰዎች ከ88 በመቶ በላይ የውጭ አገራት ዜጎች ናቸው፡፡
[ሚድል ኢስት ሞኒተር/ሸገር]

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለትግራይ ክልል 18.3 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ እህል ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር አብረሃም በላይ የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ አስረክበዋል።ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት እንደገለጹት ድጋፉ በጁንታው እኩይ ተግባር ምክንያት ለተለያዩ ችግሮች ለተጋለጡ የትግራይ ወገኖች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ያለመ ነው።የትግራይ ህዝብ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ዲሞክራሲ ህይወቱን የሰዋ ህዝብ በመሆኑ በነሱ የደረሰው ጉዳት የኛም ጉዳት ነው፤ በቀጣይ ክልሉን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የከተማ አስተዳደሩ ከተለያዩ አካላት ጋር በመሆን የድጋፍ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል።

በትግራይ ክልል በልዩ ልዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ባለሙዎች በትግራይ ክልል በቀጣይ ትምህርት ለማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከክልሉ ጊዜያዊ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር መክረዋል።ለናሙናነት በተካሄዱ የመስክ ምልከታዎች እንደተረጋገጠው በክልሉ የሚገኙ የትምህርት መሠረተ-ልማትና ግብዓቶች በህወሃት የጥፋት ቡድን ጉዳት እንደደረሰባቸውና እንደተዘረፉ ለመመልከት መቻሉን ሚንስቴር መስሪያቤቱ በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል።የመማር-ማስተማር ሥራው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ነበረበት እንዲመለስ የክልሉ መንግሥትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ክትትል የሚያደርግ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ሁሪያ አሊ አረጋግጠዋል።

አቶ በላይነህ ክንዴ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከመተከል ዞን ተፈናቅለው በቻግኒ-ራንች ጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ800 ኩንታል ዱቄት ድጋፍ ማድረጋቸውን በቻግኒ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
በከታማዋ በጊዜያዊነት የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ጀምበሩ ደሴ እንደገለፁት ባለሃብቱ በላይነህ ክንዴ ያደረጉት ድጋፍ ለተፈናቃዮች ጊዚያዊ እፎይታ የሚሰጥ እና ለወገን ደራሽነታቸውን ያሳዩበት ነው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በቻግኒ ከተማ ራንች በተባለው ጊዜያዊ መጠለያ ከ40 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ አብመድ ዘግቧል።

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎችን ጥር 20 እና 21 በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ኹሓ ካምፓስ ተቀብሎ እንደሚያስተምር አስታወቀ።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ገብረእየሱስ ብርሃነ የመማር ማስተማር ሂደትን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ “በትግራይ ክልል እየተወሰደ ባለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ተቋርጦ የነበረው የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደት በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ኹሓ ካምፓስ ይጀመራል” ብለዋል።ዩኒቨርሲቲው ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በተደረገ ውይይት ተመራቂ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።ተማሪዎችም ሆኑ ወላጆች የደህንነት ስጋት ሳይገባቸው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተመራቂዎቹ መገኘት እንዳለባቸው በመግለጽ ጥሪ አቅርበዋል።
በቀጣይም ሌሎች ተመራቂ ላልሆኑ ተማሪዎች ጥሪ በማድረግ ዩኒቨርሲቲው የሚያስተምር መሆኑንም ነው የገለጹት።የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና የመሰረተ ልማት ጉዳዮች ዳይሬክተር ሰለሞን አብርሃም፤ መንግስት በትግራይ ክልል ባካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማር ሂደት ተስተጓጉሎ እንደነበር አስታውሰዋል።በዋናነት በአክሱም እና በአዲግራት ዩኒቨርሰቲ የመማር ማስተማር ሂደቱን ማስቀጠል እንዳልተቻለም አንስተዋል።የመቀሌ እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቃቸውን ፕሬዚዳንቱ አስታውሰዋል።በአክሱም እና አዲግራት ተቋርጦ የነበረው ትምህርት በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ እንዲቀጥል የማመቻቸት ስራ መስራቱን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በትግራይ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በጤናው ዘርፍ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል የጤና ባለሞያዎች ቡድን መላኩን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ!
በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በጤናው ዘርፍ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል የተለያዩ የጤና ባለሞያዎች ቡድን ወደ ክልሉ መላኩን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የጤና ሚኒስቴር ከተለያዩ ኤጀንሲዎች እና የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ከሰብአዊ ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል ድጋፍ እና መልሶ ማቋቋም ላይ በስፋት እየሠራ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ በትግራይ በተጎዱ አካባቢዎች ያለው የኅብረተሰብ ጤና እና ደህንነት ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው በመሆኑ መንግሥት በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ድንገተኛ ምላሽ እየሰጠ እና ወሳኝ የጤና አገልግሎቶችን ለማድረስ ካለፉት በርካታ ሳምንታት ወዲህ እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
በክልሉ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንዲቻልም የተለያዩ የጤና ባለሞያዎች ቡድን መላኩንም ሚኒስቴሩ አመልክቷል፡፡
እስካሁንም ከ71 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው መድኃኒቶች እና የሕክምና ግብዓቶችን በክልሉ ለሚገኙ የመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ማእከላት ተልከው ለሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ ይገኛሉም ብሏል፡፡
ጤና ተቋማት የሚሰጡት መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለማስቀጠል ከሕክምና አቅርቦቶች እና መድኃኒቶች በተጨማሪ አምቡላንሶችን ጨምሮ የቴክኒክ እና የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝም በሚኒስቴሩ መግለጫ ተመልክቷል፡፡
በማኅበረሰቡ ውስጥ የበሽታ ቅኝት እና የተንቀሳቃሽ ክሊኒከ አገልግሎቶችም በአንዳንድ አካባቢዎች ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር እየተሰጠ እንደሚገኝ የገለጸው የጤና ሚኒስቴር፣ እየሰጠ ያለውን የጤና አገልግሎት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡
Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa

ለትግራይ ክልል 71 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው መድኃኒቶችና የህክምና ግብዐቶች ተልከዋል!
በትግራይ ክልል ለደረሰው አስቸኳይ ሁኔታ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እስካሁን ከ71 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው መድኃኒቶችና የህክምና ግብዐቶችን በክልሉ ለሚገኙ የመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ማዕከላት በመላክ ለሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።
ለደረሰው አስቸኳይ ሁኔታ ፈጣን ምላሽ ለመስጠትም የተለያዩ የጤና ባለሙያዎች የያዘ ቡድን ወደ ትግራይ መላኩን ጠቅሷል።
ሚኒስቴሩ፣ ተጠሪ ኤጀንሲዎቹ እና የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ከሰብዓዊና ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል ድጋፍ እና መልሶ ማቋቋም ላይ በስፋት እየሰሩ እንደሚገኙም በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አመልክቷል።
“በተጎዱ አካባቢዎች ያለው የህብረተሰብ ጤና እና ደህንነት ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ሲሆን መንግስት በተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች የድንገተኛ ምላሽ እየሰጠና ወገኖች ወሳኝ የጤና አገልግሎቶች እንዲያገኙ ለማድረግ ላለፉት በርካታ ሳምንታት እየሰራ ይገኛል” ሲል ሚኒስቴሩ አስታውሷል።

ፌስቡክ የትራምፕን አካውንት ለማገድ ያሳለፈውን ውሳኔ ለተቆጣጣሪ ቦርድ አቀረበ!
ፌስቡክ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አካውንትን ላልተወሰነ ጊዜ ለማገድ ያሳለፈውን ውሳኔ ገለልተኛ ለሆነው የተቆጣጣሪ ቦርዱ መምራቱን አስታውቋል፡፡ ይዘትን በተመለከተ የካምፓኒውን ውሳኔ ሊሽር የሚችለው በቅርቡ የተመሰረተው ቦርድ ወሳኔውን እስኪመረምረው ድረስ የትራምፕ አካውንት እንደታገደ ይቆያል ተብሏል፡፡ የትራምፕ አካውንት የታገደው ደጋፊዎቻቸውን በማስተባበር በካፒቶል ችግር ፈጥረዋል የሚል ውግዘት ከደረሰባቸው በኋላ ነው፡፡የፌስቡክ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኃላፊ ኒክ ክሌግ በበኩላቸው “በእኛ ጉዳይ ላይ በጣም እምነት አለኝ” ብለዋል ፡፡ “ያንን ውሳኔ የወሰንንበትን ሁኔታ የሚመለከት እና አሁን ያሉትን ፖሊሲዎቻችንን የሚመለከት ማንኛውም ምክንያታዊ ሰው እንደሚስማማ በጣም እርግጠኛ ነኝ” ብለዋል፡፡
✍Al-ain

የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትን የሚያስተባብር ምክትል ርዕሰ መምህር በሁሉም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲኖር የሚያስችል የአደረጃጀት መመሪያ እየተዘጋጀ ነው::
Via :- ትምህርት ሚንስትር
@Yenetube @FikerAssefa
Via :- ትምህርት ሚንስትር
@Yenetube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን በተቀሰቀሰ የኩፍኝ ወረርሽኝ የሁለት ሕጻናት ሕይወት ሲያልፍ ሌሎች ከ80ያ በላይ የሚሆኑት መታመማቸውን የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ተቋም አመለከተ።
ተቋሙ እንዳስታወቀው የኩፍኝ ወረርሽኙ ከባለፈው ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ የተቀሰቀሰው በዞኑ ካራትና ሰገን ዙሪያ ወረዳዎች ውስጥ ነው።በወረዳዎች በተለያየ የዕድሜ ደረጃ ላይ የሚገኙ 81 ሕጻናት በወረርሽኙ ተይዘው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ነው የተቋሙ ምክትል ዳይሬክተር አቶ እንዳሻው ሽብሩ ዛሬ ለዶቼ ቬለ (DW) የገለጹት። በወረርሽኙ ከተያዙት መካከል በካራት ሆስፒታል በህክምና ላይ የነበሩ ሁለት ህጻናት ህይወታቸው ማለፉን ምክትል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።ወረርሽኙ በወረዳዎቹ ሊከሰት የቻለው ከወራት በፊት በክልል ደረጃ የተከናወነው መደበኛ የሕጻናት ክትባት ዘመቻ በስፍራው በሚታየው የጸጥታ ችግር የተነሳ ሳይካሄድ በመቅረቱ መሆኑን አቶ እንዳሻው አመልክተዋል።በአሁኑ ወቅት የወረርሽኙን መከሰት ተከትሎ ከኮንሶ ዞን ጤና መምሪያና ከደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በተውጣጣ የባለሙያዎች ግብረ ሀይል አማካኝነት ክትባት የመስጠት ሥራ መጀመሩንም ገልጸዋል።ለአንድ ሳምንት በሚካሄደው የመከተብ ሥራ ከ24 ሺህ በላይ ሕጻናት ይከተባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ምክትል ዳይሬክተሩን የጠቀሰው የዶይቼ ቨሌ ዘገባ ያመለክታል።

ፍርድ ቤቱ እነ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ የ18 ተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ!
ነገር ግን ዐቃቤ ሕግ ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት ማመልከቻ አቅርቧል።
የማመልከቻው ይዘት በእነ ጃዋር የክስ መዝገብ አምስት ክሶች በተለይም ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት ጋር በተያያዘ አዋጁን ጠቅሶ ዋናው ክስ ላይ የጠቀሰውን የክስ ጭብጥ ፍርድ ቤቱ እንዲያሻሽል ትእዛዝ ቢሰጥም ማሻሻል እንደማይችል የተለያዩ ምክንያቶች ጠቅሶ ማመልከቻ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።
ችሎቱም የተወሰነ ጊዜ ወስዶ የዐቃቤ ሕግን ማመልከቻ መርምሯል። በመሆኑም ከጦር መሣሪያ አዋጅ ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል የሰጠው ትእዛዝ አሳማኝ መሆኑን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ ከጦር መሣሪያ ጋር ተያየዝ በተከሳሾች ላይ ያቀረበውን ክስ የማያሻሽል መሆኑን በመገንዘብ እንዲቋረጥ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ይህንንም ተከትሎ ፍርድ ቤቱ የእምነት ክህደት ቃል እንዲሰጡ ተከሳሾችን ጠይቋል፤ ነገር ግን የተከሳሽ ጠበቆች ተሻሽሏል የተባለውን ክስ በአግባቡ ለመረዳት ጊዜ ስለሚያስፈልግ እና ከደንበኞች ጋር ለመመካከር ስለሚያስፈልግ አሁን ባለንበት ሁኔታ የእምነት ክህደት ቃል ለመስጠት ያስቸግራል፤ ስለዚህ አጭር ቀጠሮ ይሰጠኝ በማለት አመልክተዋል።
ተከሳሾችም በዛሬው ቀጠሮ የእምነት ክህደት ቃል ለመስጠት ዝግጁ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።
ይህንን ግምት ውስጥ ያስገባው ችሎቱ ተከሳኞች ጠበቆች ከጠቀሱት ወሳኝ በሚባለው የእምነት ክህደት ቃል መስጠት ጋር በተያያዘ በቂ ዝግጅት አድርገው እንዲመጡ ለመጪው ረቡዕ ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
[ዳጉ ጆርናል]

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰላም እና ብሔራዊ መግባባት ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጠ!
በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለሰላም እና ብሔራዊ መግባባት መሠረት ናቸው ባሏቸው ጉዳዮች ያደረጉትን ውይይት አስመልክተው ጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም መግለጫ ሰጥተዋል።በተያዘው ዓመት የሚደረገው 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲያልፍ ከምርጫ በፊት፣ በምርጫ ሂደትም ሆነ ከምርጫ በኋላ ሁሉም ፓርቲዎች እና ባለድርሻ አካላት ሊያደረጉ የሚገቡ ጉዳዮችን የሚዳስስ ውይይት ከጥር 02-04 ቀን 2013 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ባደረጉት ውይይት የጋራ መግባባት ላይ የደረሱባቸውን ነጥቦች በዝርዝር አቅርበዋል።
በቀረበው መግለጫ ከምርጫው በፊት እና በኋላ ሀገራዊ ሰላም እንዲጠበቅ ይበጃሉ ባሏቸው ጉዳዮች ላይ በጥልቀት መወያየታቸውን አስገንዝበዋል።በሀገራዊ ሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ፣ የሰብአዊ መብት መከበር ጉዳይ ፣ የመንግስት ሓላፊነት እና ተጠያቂነት ላይ የጋራ መግባባት መደረሱ ተገልጿል፡፡በተጨማሪም የብሔረሰብ የማንነት ጥያቄ እና የምርጫ ክልል ተያያዥነት፣ በምርጫው ውጤት ሊነሡ ስለሚችሉ ጉዳዮች እና ተጠያቂነት፣ የፀጥታ አካላት ገለልተኝነት፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ገለልተኝነት ‹የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና የተቋማት ገለልተኝነትም መግባባት ከተደረሰባቸው መካከል መሆናቸውን ከሠላም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ የሚዲያ ተቋማት ገለልተኝነት፣ ምርጫው ፍትሐዊ እና ተአማኒ እንዲሆን የፖለቲካ ምኅዳሩን ስለማስፋት፣ የሀገረ መንግሥት ግንባታ፣ የታሪክ እና ትርክት ጉዳይ፣ ብሔራዊ ዕርቅ በሚሉ ጉዳዮች ውይይት እንዳካሄዱባቸው እና የጋራ መግባባት ላይ እንደደረሱባቸው በመግለጫ አትተዋል።

የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ!
የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ የሱዳን ጉብኝታቸውን አጠናቀው ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡ ዶሚኒክ ራብ በካርቱም ቆይታቸው በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበርና በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ፣ከሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት አባላትና ከጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክና ከካቢኔ አባሎቻቸው ጋር ፣ ውይይት ማድረጋቸውን የሱዳን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡በኢትዮጵያ ቆይታቸውም ዛሬ አመሻሽ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ይወያያሉ፡፡
[Al-ain]

(January 24 ) የፊታችን እሁድ በመዲናች አዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ የመኪና ውድድር ይካሄዳል።
ከጠዋቱ አንድ ሰዐት ጀምሮ የሚካሄደውን የመኪና ውድድር አስመልክቶ ሜክሲኮ ቶታል አካባቢ ለገሀር እንዲሁም ብሄራዊ አካባቢ መንገዶች ዝግ እንደሚሆኑ አዘጋጅ ክፍሉ ጠቁሞናል።
የውድድሩ አዘጋጅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሞተር ስፖርት አሶሴሽን ነው።