የአምባሳደር ድንበሩ ዓለሙ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ!
የአምባሳደር ድንበሩ ዓለሙ የቀብር ስነ ስርአት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና እና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በተገኙበት በኮልፌ የሙስሊም መቃብር ተፈፅሟል።አምባሳደር ድንበሩ ዓለሙ በዱባይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት በዲፕሎማትነት በማገልግል ላይ እያሉ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ጥር 09 ቀን 2013 ዓ.ም ሕይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው።አምባሳደር ድንበሩ አለሙ ባለትዳርና የሁለት ሴቶች እና የ አንድ ወንድ ልጅ አባት ነበሩ፡፡
@YeneTube @FikerAssefa

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ሌተናል ጀነራል አልቡርሃን ምላሽ ሰጠ።
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
አምባሳደር ዲና በዚህ ጊዜ እንዳሉት “አጥፊ ሐይሎች የእናተን ድንብር ተጠቅመው ወደ እኛ እንዳይገቡ ማለት እናንተ ግቡ ማለት አይደለም” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ለሱዳን መሪዎች እኛ ወደ ሰሜን ህግ የማስከበር ስራ ላይ በመሆናችን የእናተን መግቢያ ድንበሮች ጠብቁ ነው ያሉት ብለዋል አምባሳደር ዲና።
ሱዳንን ለማረጋጋት ኢትዮጵያ በርካታ ስራዎችን ሰርታለች ፣ በሁለቱ ሀገራት የከፋ የነቆራ ታሪክ የለም ሲሉም አክለዋል አምባሳደሩ።
በሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው መሬቱን ውሰዱ ተብልናል የሚለው ሀሳብ ትክክል አይደለም አሁንም አቋማችን የሱዳን ጦር ወደ ቀድሞ ቦታው ሲመለስ እንነጋራለን ብለዋል አምሳደር ዲና።
[Ethio FM]

YeneTube
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ሌተናል ጀነራል አልቡርሃን ምላሽ ሰጠ። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ። አምባሳደር ዲና በዚህ ጊዜ እንዳሉት “አጥፊ ሐይሎች የእናተን ድንብር ተጠቅመው ወደ እኛ እንዳይገቡ ማለት እናንተ ግቡ ማለት አይደለም” ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ…
የኤርትራ ሰራዊት ከኢትዮጵያ መከላከያ ጋር ተደርቦ ሕወሓትን ወግቷል የተባለው ጉዳይ መሰረተ ቢስ ወሬ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአገር ውስጥ አልፎ ሰላም ለማስከበር የሚያስችል አቋም አለው ሲሉም ተናግረዋል።
[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
ሀገረ አሜሪካንን ላለፉት አራት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ነጩን ቤተ መንግስት ለተተኪው ፕሬዝዳን ጆ ባይደን ለቀው ወጥተዋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያን ከኤርትራ የአሰብ ወደብ ጋር የሚያስተሳስረው የሜሎዶኒ መገንጠያ - ማንዳ - ቡሬ መንግድ ፕሮጀክት ሊገነባ ነው።
በነገው ዕለትም ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ፕሮጀክቱን በይፋ የማስጀመር መርሃ ግብር ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በዕለቱ በሚኖረው መርሃ -ግብርም ግንባታው የተጠናቀቀው የዲቾቶ - ጋላፊ የሲሚንቶ ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትም ይመረቃል።
የሜሎዶኒ መገንጠያ - ማንዳ - ቡሬ መንገድ ሲጠናቀቅ ወደ አሰብ ወደብ የሚዘልቅ መንገድ እንደመሆኑ ለኢትዮጵያ የተሻለ የወጪ ገቢ ንግድ እንቅስቃሴ መሳለጥ አይነተኛ ሚናውን ይጫወታል፡፡
71.65 ኪ. ሜ የሚረዝመውን ይህን ፕሮጀክት በብር 2,085,985,162.6 በሆነ ወጪ ጨረታውን አሸንፎ ግንባታውን የሚያከናውነው ሻንዶንግ ሊኪኖ ግሩፕ የተባለ የውጭ የስራ ተቋራጭ ድርጅት ነው።
የግንባታውን የማማከርና የቁጥጥር ስራ ደግሞ ስሜክ ኢንተርናሽናል እንዲሁም ቫሊዩ ኢንጅነሪንግ በንዑስ ተቋራጭነት ይሳተፋል ።
ለፕሮጀክቱ ግንባታ ማስፈጸሚያ ወጪም የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት መሆኑን ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልፈጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ፎቶ:የዲቾቶ - ጋላፊ መገንጠያ - ኤሊዳር - በልሆ የመንገድ ገጽታ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ለሽሬ ቅርንጫፍ ለሁለተኛ ዙር የሚሆን ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን ሕይወት አድን መድኃኒቶች እያጓጓዘ መሆኑን አስታወቀ።
ከ3 ሚሊዮን 96 ሺህ 657 ብር ዋጋ ያላቸውን ሕይወት አድን መድኃኒቶች ከጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እያጓጓዘ መሆኑ የመ/ሕ/መ/ክምችትና መጋዘን አያያዝ እስተዳደር ዳይሬክተር ወ/ሮ ገዳምነሽ አስፋው ገልጸዋል፡፡
ለቅርንጫፉ የተላኩት በዋናነት ለእናቶችና ህፃናት የሚዉሉ ህይወት አድን መድሀኒቶችና ህክምና ግብዓቶች እንድሁም ለፀረ ወባና ሳንባ ነቀርሳን ለማከም የሚረዱ መድሀኒቶች ናቸው፡፡
መድኃኒቶች እና ሕክምና ግብዓቶቹም ሽሬ ቅርንጫፍ ሲደርሱ ለጤና ተቋማት እንደሚከፋፈሉ ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በሀገር ዐቀፉ ምርጫ ዙሪያ ለሚነሱ ቅሬታዎች ችሎቶች እየተደራጁ እንደሆነ ሸገር ዘግቧል፡፡ በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ለችሎቶች የሚቀርቡ ጉዳዮች፣ ከመራጮች እና ከዕጩዎች ምዝገባ፣ ከስነ ምግባር ደንቦች ጥሰት፣ ድምጽ አሰጣጥ፣ ከድምጽ ቆጠራ እና ከምርጫ ውጤት አገላለጽ ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ፍርድ ቤቶች የሚያዩት በምርጫ ክልል ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች ምላሽ ያላገኙትን ቅሬታዎች ይሆናል፡፡ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች የስነ ምግባር ጥሰትን የሚመለከቱ ሲሆን፣ ድምጽ ቆጠራ እና ውጤት አገላለጽን ደሞ ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ያያሉ፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዴሪ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል፡፡
ምክር ቤቱ በውሎው የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች ምክር ቤት ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በመተከል ዞን እና በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች የተፈጸመውን የግፍ ግድያ አስመልክቶ ከተወያየ በኋላ በሰጠው አቅጣጫ መሰረት ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ የውሳኔ ሀሳቡን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል የዳኝነት አስተዳደር ለመወሰን የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አዋጁን ማጽደቅ፣ የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አዋጁን ማጽደቅ እና የኢፌዴሪ የካፒታል ገበያ ረቂቅ አዋጅን መመርመር የእለቱ የምክር ቤቱ ውሎ ተግባራት መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
ምንጭ፡- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው በዋሽንግተን ዩኤስ ካፒቶል ተሰየሙ።
ከእርሳቸው ጋር ምክትል ፕሬዚዳንት ካሚላ ሀሪስ የተገኙ ሲሆን፣ የመጀመሪያዋ ሴት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።በበዓለ ሲመቱ ላይ የቀድሞዎቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እና ባለቤታቸው ሚሼል ኦባማ፣ ጆርጅ ዎከር ቡሽ እና ባለቤታቸው ላውራ ቡሽ እንዲሁም ቢል እና ሂላሪ ክሊንተን ተገኝተዋል፡፡የትራምፕ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ማይክ ፔንስም በበዓለ ሲመቱ ተገኝተዋል፡፡አዲሱ ተመራጭ ጆ ባይደን ቃለ መሀላ እስኪፈጽሙ ድረስ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገው ማንኛውም በረራ እንደሚቋረጥ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን "ልዩ ወረዳ እንመሰርታለን" በሚሉና ጥያቄውን በሚቃወሙ ቡድኖች መካከል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን እየተናገሩ ይገኛሉ።
ነዋሪዎቹ ባለፈው ሳምንት በዞኑ ሰገን ዙሪያ ወረዳ የተነሳውን ግጭት በመሸሽ ወደ ደራሼ ልዩ ወረዳ ገብተው ቢጠለሉም አስከአሁን ምግብና መጠለያ ጨምሮ የእለት ደራሽ ድጋፍ አንዳልቀረበላቸው ገልጸዋል።በተጠለሉበት ስፍራ በመገኘት ያናገሯቸው የክልሉ ባለስልጣናት የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ወደ ቀያቸው ሲመለሱ እንደሚያገኙ ነግረውናል የሚሉት ተፈናቃዮቹ ባለው የጸጥታ ስጋት የተነሳ ጥያቄውን ሳይቀበሉት መቅረታቸውን ተናግረዋል።የክልሉ ባለስልጣናት በበኩላቸው በዞኑ ግጭቱን የቆሰቆሱና የተሳተፉ ቡድኖች በህግ ጥላ ስር እየዋሉ ፣አካባቢውም እየተረጋጋ ይገኛሉ ብለዋል።
[ዶይቼ ቨሌ]

አቶ ልደቱ አያሌው ከተመሠረተባቸው "ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት" የሚል ክስ ፍርድ ቤት ነጻ ናቸው ብሎ እንደፈረደላቸው ተሰማ፡፡
የድምጻዊ ሐጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በቢሾፍቱ በተቀሰቀሰ ሁከት ላይ ሁከቱን አስተባብረዋል፣ በገንዘብም ረድተዋል በሚል በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው፣ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ከቀረበባቸው "ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት" የሚል ክስ ፍርድ ቤት ነጻ ናቸው ብሎ እንደፈረደላቸው ተሰማ፡፡
ዛሬ ዕለተ ረቡዕ ጥር 12፣2013 በነበራቸው የፍርድ ቤት ቀጠሮ የውሳኔ ሂደት፦
1ኛ መሣሪያው በሌላ ሕገ ወጥ መንገድ ያልተገኘና የመንግሥት ንብረት ስለመሆኑ በፖሊስም በአቃቤ ሕግም መረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ፤
2ተኛ ተከሳሹ መሣሪያውን የታጠቁት ያለ ፈቃድ መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል መሆኑን የሚደነግገው አዲሱ አዋጅ ከመውጣቱ ከብዙ ዓመታት በፊት እና የፓርላማ አባል በነበሩበት ወቅት መሆኑ ስለተረጋገጠ፣ ክሱ ውድቅ ተደርጎ ፍርድ ቤቱ በነፃ እንዳሰናበታቸው ተሰምቷል፡፡
Via Sheger FM

የትግራይ ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደና ጓደኛው በመቐለ ከተማ ተገደሉ!
የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የሚያስተዳድረው ቴሌቭዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ የነበረው ዳዊት ከበደ እና ጓደኛው ትናንት በመቐለ ከተማ በጥይት ተመተው ተገደሉ።የሟች ቤተሰቦች እና ጓደኞች ለዶይቼ ቬለው የመቐለ ዘጋቢ እንደተናገሩት ጋዜጠኛ ዳዊት እና አንድ ሌላ ጓደኛው በከተማው በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ ላይ ሳሉ ከጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል። በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ ታስረዋል። በመቐለ ከተማ የሰዓት ዕላፊ ታውጇል። የዶይቼ ቨሌ የመቐለ ዘጋቢ እንዳለው ኩነቱ የተፈጸመው በከተማው መንቀሳቀስ በተከለከለበት ወቅት ነው።የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን እና ከጊዜያዊው አስተዳደር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የተደረገው ጥረት እንዳልሰመረ ጠቅሶ የዘገበው ዶይቼ ቨሌ ነው።

አንዳንድ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ለመጭው ምርጫ የምርጫ ክልል እና የምክር ቤት መቀመጫ ለውጦችን እንደማይቀበል ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ሰሞኑን የምርጫ ክልል ወይም የምክር ቤት መቀመጫ ብዛት ላይ ለውጥ ማድረጋቸውን ለቦርዱ ያሳወቁት አፋር፣ ጋምቤላ እና ደቡብ ክልሎች እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንደሆኑ ቦርዱ ጠቅሷል፡፡ ሆኖም የተጠቀሱትን ለውጦች ማድረግ የሚፈቀደው ከመራጮች ምዝገባ 6 ወራት በፊት እንደሆነ በመጥቀስ፣ ጥያቄውን ወድቅ እንዳደረገ ቦርዱ አስታውቋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ዋስትና የተፈቀደላቸው የኦነግ አባላት እንዳልተፈቱ ጠበቃቸው ተናገሩ!
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አባላት የሆኑ ፖለቲከኞች ድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ከተገደለ በኋላ በተቀሰቀሰ ኹከት ተጠርጥረው ከታሠሩ በኋላ ፍርድ ቤት ዋስትና ቢፈቅድላቸውም እስከዛሬ አልተፈቱም። ጠበቃቸውን ቱሊ ባይሳ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ዋስትና ተፈቅዶላቸው ሳይፈቱ ከቀሩት መካከል ለሚ ቤኛ፣ ዳዊት አብደታ እና ኮሎኔል ገመቹ አያና ይገኙበታል።
[DW]

መንግሥት ከዶላርና መሰል የውጭ ምንዛሪ መገበያያዎች አንፃር የብር ምንዛሪ ዋጋን እንዲዳከም ማድረጉ፣ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ያስከትላል የሚል ሥጋት እንዳላቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ተናገሩ።
የብር ዋጋ መዳከሙ የፋብሪካዎች ጥሬ ዕቃ መግዣ ዋጋ እንዲጨምር በማድረጉ፣ አገር ውስጥ እየተመረቱ ያሉ ምርቶች እንዲወደዱ ምክንያት ሆኗል። ጭማሪው እንደ ዘይት ባሉ ከውጭ ሙሉ ለሙሉ የሚገቡ ምርቶች ላይ የባሰ ሲሆን፣ ይህም የኑሮ ውድነት እያስከተለ መሆኑን ማውቅ ተችሏል።
በአንድ ዓመት ውስጥ እስከ ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ ብቻ ብር ከዶላር አኳያ በ24 በመቶ፣ ከዩሮ አኳያ 34 በመቶ፣ እንዲሁም ከፓውንድ አኳያ ደግሞ 28.6 በመቶ ተዳክሞ የመሸጫና የመግዣ ዋጋው ወርዷል፡፡
ዘገባው የሪፖርተር ነዉ ተጨማሪ ለማንበብ: https://bit.ly/2Y1kRY4

ኢትዮጵያ ድሮኖችን በአገር ውስጥ ማምረት ልትጀምር መሆኑን አስታወቀች።
የኢትጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖኖሊጂ ኢንስቲትዩት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ የድሮን ቴክኖሎጂ ላይ ለመስራት ድሮኖችን ለማምረት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብሏል፡፡የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር የሽሩን አለማየሁ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ አገሪቱ በራሷ አቅም ድሮኖችን ማምረት የሚያስችል ስራዎች ተጀምረዋል ነዉ ያሉት፡፡ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን ወደ ስራ ለመግባት ስምምነት ላይ መደረሱም ተነግሯል፡፡
አሁን ላይ ኢትዮጵያ የምትጠቀማቸዉ ድሮኖች ከዉጭ በማስገባት እንደሆነ የተናገሩት ዶክተር የሽሩን ከቅርብ ጊዜ በኋላ ግን አገር ዉስጥ ይመረታሉ ብለዋል፡፡ኢትዮጵያ በተላያዩ ዘርፎች ላይ የምትጠቀማቸዉ ድርኖች በተበታተነ መልኩ የሚገኙ ከመሆናቸዉ ባለፈ በከፍተኛ ዉጪ የተገዙ ናቸዉ፡፡የድሮን ቴክኖሎጂ በአገር ዉስጥ ተግባራዊ መደረጉም ወጪን ከመቆጠቡ በተጨማሪ ዘርፉን ያሳድገዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡በኢትጵዮጵያ የድሮን ቴክኖሎጂ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ያስረዱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በተለይም በግብርናዉ እና በጤናዉ ዘርፍ የሚታዩ የተደራሽነት ችግሮችን ለመፍታት ይረዳል ተብሏል፡፡

የህወሓትን ታጣቂ ሃይል በመምራትና በማዋጋት የተሳተፉት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴል ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ እጃቸውን ሰጡ!
የመከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩትና በጡረታ በክብር የተሰናበቱት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴል ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ እጃቸውን በሰላም መስጠታቸውን የአገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ።የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ እጃቸውን የሰጡት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የህወሓትን ታጣቂ ሃይል በመምራትና በማዋጋት ላይ የነበሩ ናቸው።መኮንኖቹ በጡረታ ከተገለሉ በኋላ ህወሓትን በመቀላቀል የጦርነት ዝግጅት ሲያደርጉ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።የአገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ ህወሃት ጥቃት በፈጸመበት ወቅትም ዋና አስተባባሪ የነበሩ ናቸውም ተብሏል።

በትግራይ 92 የምግብ ማሰራጫ ማዕከላት መቋቋሙ ተገለጸ።
በትግራይ ክልል ለ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎችን እርዳታ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉም ተገልጿል።በትግራይ ህግ ከማሰከበር ዘመቻ በፊት 1.8 ሚሊየን ዜጎች እርዳታ የሚፈልጉ ነበሩ።የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ እና በቤንሻጉል ጉምዝ መተከል ዞን በክልሉ ስላለው የሰብዓዊ ዕርዳታ ለዜጎች ለማድረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ እና አጠቃላይ በተመለከተ መግለጫ እየሰጡ ነው።የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ የማቋቋም እና ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፍ በቅንጅት እየተሰራ ነው።በመቀሌ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ተቋቁሟል በትግራይ 92 ምግብ ማሰራጫ ጣቢያ አለ።አጠቃላይ የሰብዓዊ የረድኤት ተቋማትን ጨምሮ ሁሉም አካላት ስራቸውን ከፌደራል መንግስት ጋር ተቀናጅተው እንዲያከናውኑ እና ከውጭ ድርጅቶችም ጋር እየተሰራ ነውም ተብሏል።በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች በትግራይ ክልል 4.5 ሚሊየን እርዳታ የሚፈልግ ዜጋ አለ እያሉ የሚለቁት መረጃዎች በፌዴራል መንግስት ያልጸደቀ ቁጥር እንደሆነም በመግለጫው።

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት 6 ወራት ከ25 ቢሊየን በላይ ብር ማግኘቱን አስታወቀ።
የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ በተቋሙ ግማሽ ዓመት አፈጸጸም ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።ወይዘሪት ፍሬህይወት በዚህ ጊዜ እንዳሉት ባለፉት 6 ወራት 25 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል።
ገቢው ካለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጸጸር በ12.3 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።ተቋሙ በአጠቃላይ 50.7 ሚሊየን ደንበኞች እንዳሉት ተገልጿል።ካሉት ደንበኞች ውስጥ 48.9 ሚሊዮኖቹ የሞባይል ደንበኞች ሲሆኑ 23 ነጥብ 5 ሚሊዮን ደግሞ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ናቸው።

ውቅሮ ፣አዲግራት እና ደገ ሀሙስ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎት መጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።
የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ እንዳሉት በትግራይ ክልል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት የቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደገና ለማስጀመር ጥረቶች ቀጥለዋል ብለዋል።
በአዲግራት፣ውቅሮ እና እደጋ ሀሙስ አካባቢዎች ኔትወርክ አገልግሎት ተጀምሯል ብለዋል።
በሌሎች አካባቢዎችንም የስልክ አገልግሎት ለማስጀመር የጥገና ስራዎችን እየሰራን ነውም ብለዋል።የሳይበር ጥቃት ሙከራ በስራችን ላይ ችግር ሆኖብን ነበር ነገር ግን ኔትዎርካችን ሳይነካ መክተን አልፈናል ሲሉም ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል።