YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በሱዳን ደቡብ ዳርፉር ግዛት በሪዜይጋት እና ፈላታ ጎሳዎች መካከል ትናንት ሰኞ ዕለት ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም ግጭት መቀስቀሱን የሱዳን ዜና ወኪል ዘግቧል፡፡

በአካባቢው አንድ እረኛ መገደሉን ተከትሎ በሁለቱ ጎሳዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በአስሮች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን የደቡብ ዳርፉር አስተዳዳሪ ሙሳ ማህዲ ገልጸዋል፡፡

ከእረኛው ግድያ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ዳርፉር ዋና ከተማ ንያላ 85 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው አል ጣዊል መንደር ፣ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ነው ሰዎች የተገደሉት እና የቆሰሉት፡፡

ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል ግጭቱ ወደተከሰተበት አካባቢ ተጨማሪ የጸጥታ ኃይሎች መላካቸውንም የግዛቱ አስተዳዳሪ ተናግረዋል፡፡

በአንድ በኩል በፈላታ እና በማሳሊት ጎሳዎች ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በፈላታ እና በሪዜይጋት ጎሳዎች መካከል ከአንድ ወር በፊት ግጭቶች መከሰታቸውን ተከትሎ የደቡብ ዳርፉር ግዛት ወደ ስፍራው በርካታ ወታደሮችን ልኮ እንደነበር ዘገባው ያመለክታል፡፡

Via Al-ain
@YeneTube @FikerAssefa
የዋልድባው መነኩሴ ተሸለሙ!

የዋልድባ ገዳም በስኳር ልማት ሰበብ ፈተና ላይ በወደቀበትና ለችግር በተዳረገበት ወቅት ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉት አባ ገብረየሱስ ኪዳነማርያም ሽልማትና እውቅና ተሰጣቸው።የማዕከላዊ ጎንደር ሀገር ስብከት፤ አባ ገብረየሱስ ለከፈሉት መስዋዕትነት በወርቅ የተሰራ ማህተም፣ ምስክር ወረቀት አበርክቶላቸውል፤ ካባ አልብሷቸዋል።የዋልድባን ገዳም ሲነካ ከፍተኛ መስዋዕት የከፈሉ መሆናቸው ተጋድሎውም ፍሬ ያፈራ መሆኑ በጎንደር ባህረ ጥምቀት ላይ በነበረው ሥነ ስርአት ላይ ተገልጿል።አባ ገብረየሱስ በገዳሙ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ብሎም ህዝቡ እንዲረጋጋ ከፍተኛ መስዕዋት መክፈላቸው በመድረኩ ላይ ተወስቷል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የከተራና የጥምቀት በዓል በሠላም መጠናቀቁን አስታወቀ።ህብረተሰቡ ለበዓሉ በሠላም መጠናቀቅ ላበረከተው አስተዋፅኦ ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል 2.5 ሚሊዮን የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ!

በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ እየቀረበ ሲሆን 2.5 ሚሊዮን የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን የሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል።ሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል የህግ ማስከበር ሂደት ከተጠናቀቀ ወዲህ ምግብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች እና የሕክም አቅርቦቶችን የያዘ የሰብዓዊ ድጋፍ በትግራይ ክልል ለሚገኙ 1.8 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች መድረሱን ነው የገለፀው።በአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል የሚኒስትሮች ኮሚቴ መሪነት አፋጣኝ ፍላጎቶችን ለማሟላት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ ከክልል ቢሮዎች፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅቶችና ከአለም ዓቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተውጣጡ የቴክኒክ ቡድኖችን ያካተተ የአስቸኳይ ጊዜ ኦፕሬሽን ማስተባበሪያ ማዕከል (ኢ.ኦ.ሲ.) በመቀሌ ከተማ መቋቋሙም ተገልጿል።

ተጨማሪ ፍላጎቶችን ለመለየት ባለ አራት ደረጃ የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበር ሥርዓት (የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና የምግብ ማከፋፈያ ቦታዎችን ያካተተ) ተደራጅቶ ወደ ስራ መገባቱንም ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የገለፀው።ተለይተው ለታወቁ ተጠቃሚዎች የድጋፍ ሽፋንን ለማሳደግ እንዲሁም በፍጥነት አቅርቦትን ለማዳረስ የኢትዮጵያ መንግሥት ከልማትና ከሰብዓዊ አጋሮች ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።በመግለጫው ብሄራዊ የመከላከያ ሠራዊት ደህንነቱ የተጠበቀ የሰዎችና የአቅርቦቶች እንቅስቃሴን በማመቻቸት የሰብአዊ ዕርዳታውን ቅንጅት በከፍተኛ ደረጃ በመደገፍ ላይ ይገኛልም ነው የተባለው።

ስርጭቱ በብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ በአለም ዓቀፍ ሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ (ዩ.ኤን.ኦቻ) አስተባባሪነት በዓለም ዓቀፍና በሀገር በቀል መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም በሴፍቲኔት መርሃ-ግብር (ፒ.ኤስ.ኤን.ፒ) እየተከናወነ ይገኛል። ስርጭቱ የሚከናወነው ከአክሱም፣ አዲግራት፣ አላማጣ፣ መቀሌ ዙሪያ፣ ሽሬ እና መቀሌ ከተማ ከሚገኙ የማሰራጫ ጣቢያዎች መሆኑ ተገልጿል።በሂደቱ ለሴቶች፣ ሕፃናት፣ አረጋውያንና የአካል ጉዳተኞች ለምግብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስና የሕክምና አቅርቦቶች ስርጭት ቅድሚያ እየተሰጠ እየተሰጠ እንደሚገኝም ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አስታውቋል።የተጠቃሚዎችን ብዛት በትክክል ለመለየት የጋራ የፍላጎት ዳሰሳና ግምገማ በማካሄድ ላይ ናቸው ያለው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለወገኖቻችን የሰብዓዊ ድጋፍ ለማዳረስ ትኩረት ተሰጥቶ በቁርጠኝነት ርብርብ እየተደረገ መሆኑንን ጠቁሟል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የጥምቀት በዓል በመቀሌ ከወትሮው በተለየ መልኩ ቀዝቀዝ ብሎ መከበሩን ነው ለመረዳት ችለናል።

ዶይቼ ቨሌ እንደዘገበው ታቦታት ከየቤተ ክርስቲያኑ ሳይወጡ ምዕመኑ በየአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን ተገኝቶ በሃይማኖታዊ ሥርዓቱ ተሳትፏል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሁለት የብሔራዊ ዘብ ወታደሮች በባይደን በዓለ ሲመት ላይ እንዳያገለግሉ ታገዱ

ኤፍቢአይ ከውስጥ ጥቃት ሊፈፀም ይችላል በሚል ስጋት ለአሜሪካው ዕጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዓለ ሲመት ጥበቃ የተመደቡ 25 ሺ የብሔራዊ ዘብ ወታደሮችን በመፈተሽ የማጣራት ስራ እየሰራ መሆኑን በትናንትናው ዕለት መግለፁ ይታወሳል። አሁን ሲኤንኤን በሰበር ዜና እንደዘገበው ታዲያ ሁለት የብሔራዊ ዘብ ወታደሮች እምነት ታጥቶባቸው በዝግጅቱ ላይ የፀጥታ ስራ እንዳይሰሩ ተከልክለው ተቀንሰዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባይደን ለበዓለ ሲመታቸው ከዴላዋር ወደ ዋሺንግተን አቅንተዋል።

Via:- Alian
@YeneTube @FikerAssefa
የትራምፕ አስተዳደር በስም ያልተጠቀሱ የታንዛኒያ ባለስልጣናት ላይ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የቪዛ ማዕቀብ ጣለ!

አሜሪካ በታንዛኒያ ባለስልጣናት ላይ የቪዛ ክልከላ ማዕቀብ የጣለችው በወርሃ ጥቅምት በተደረገው ምርጫ ምዝበራ እና በሰብዓዊ መብት ረገጣ እጃቸው አለበት በተባሉ ላይ ነው፡፡በጥቅምት በታንዛኒያ በተደረገው ምርጫ ጆን ማጉፉሊ ከ 80 በመቶ በላይ የመራጮችን ድምፅ አግኝቼ አሸነፍኩ ቢሉም የተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎችን ወደ እስር በመወርወር ነበር፡፡ምርጫው አግባብነት የሌለው ፣ ፍትሀዊ ፣ ገለልተኛ አልነበረም የሚሉ ክሶች ይደመጣሉ፡፡የትራምፕ የ24 ሰዓት ሙሉ የስራ ቀን በዋይት ሀውስ በትላንትናው እለት የተጠናቀቀ ሲሆን ፣ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዛሬ በዓለ ሲመታቸው ይፈፀማል፡፡

ብስራት ሬድዮ
@YeneTube @FikerAssefa
በሱዳን ዳርፉር ግዛት በተቀሰቀሰው ግጭት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 155 ደረሰ!

በዳርፉር የተቀሰቀሰውን ደም አፍሳሽ ግጭት ተከትሎ የሱዳን ጦር በአካባቢው የተሰማራ ሲሆን ከተገደሉት 156 ሰዎች በተጨማሪ በርካቶች ክፉኛ ቆስለዋል። ባሳለፍነው ቅዳሜ በአረብ ዘላኖች እና አረብ አይደለንም በሚሉት የማሳሊት ጎሳ አባላት መካከል በምዕራባዊ ዳርፉር ግዛት መዲና ኢል ገኒና ግጭት መቀስቀሱን የግዛቲቱ ገዢ ሞሃመድ አል ዶዩማ ተናግረዋል።

50 ሺ ያህል ዜጎች ግጭቱ ለስደት መዳረጉን ዓለም አቀፋዊው የረድኤት ድርጅት የልጆች አድን(Save The Children) አስታውቋል።ከካርቱም እና ከሌሎች ግዛት የተውጣጡ የፀጥታ አካላት ወደ ምዕራባዊ ዳርፉር ግዛት ያቀኑ ሲሆን በግዛቲቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል።

@YeneTube @FikerAssefa
በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት በወታደራዊ ኃይል ጥንካሬ ዝርዝር ውስጥ ከገቡት የአፍሪካ አገራት መካከል ኢትዮጵያ የስድስተኛነትን ቦታ ስትይዝ በዓለም 60ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣላች።

የተለያዩ መረጃዎችን መሠረት በማድረግ በየዓመቱ የአገራትን ወታደራዊ ጥንካሬ የሚያሳይ ደረጃን የሚያወጣው 'ግሎባል ፋየር ፓወር' የተባለው ተቋም ለዚህ ዓመት ባወጣው ዝርዝር ውስጥ 35 የአፍሪካ አገራት የተካተቱ ሲሆን ኢትዮጵያ የ6ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በደረጃው ሰንጠረዥ መሠረት ግብጽ ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ስትሆን፣ በመከተል ደግሞ አልጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ሞሮኮና ኢትዮጵያ በቅደም ተከተል ተቀምጠዋል። የኢትዮጵያ ጎረቤት ሱዳን ደግሞ በ10ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የአፍሪካ መሪዎች የዘንድሮውን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ ላይመጡ ይችላሉ ተባለ።

የአፍሪካ ህብረት መሪዎች በዓመት ሁለት ጊዜ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ እና በተመረጡ ሌሎች ከተሞች ዓመታዊ የመሪዎች ጉባኤውን ያካሂዳል።በአሁን ሰዓትም የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኞች ዓመታዊ ስብሰባ በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።ሕብረቱ ዓመቱን “የባህል፤ኪነ ጥበብ እና ቅርስ ጥበቃ ለምንፈልጋት አፍሪካ” በሚል ትኩረት እንደሚሰጥ ገልጿል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም ከህብረቱ ኮሙንኬሽን የስራ ክፍል ሰምቻለው እንዳለው ከሆነ የዘንድሮው የ2021 ዓመት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ያለበት ቢሆንም መሪዎቹ በአካል ወደ አዲስ አበባ ላይመጡ ይችላሉ።የኮሮና ቫይረስ ደግሞ መሪዎቹ ወደ ሕብረቱ መዲና አዲስ አበባ በአካል እንዳይመጡ ምክንያት መሆኑ ተሰምቷል።ይሁንና እስካሁን ዓመታዊ የመሪዎች ጉባኤ በገጽ ለገጽ ወይስ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ይካሄድ? የሚለው ጉዳይ አለመወሰኑ ተገልጿል።

ከዛሬ ጀምሮ በሚካሄዱ የቪዲዮ ውይይቶች ላይ ጉዳዩ ውሳኔ እንደሚያገኝ ተገልጿል።ከቀናት በፊት ወደ ተግባር የተቀየረው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና፣ሽብርተኝነት፣ኮሮና ቫይረስ እና ሌሎች ጉዳዮች ደግሞ መሪዎቹ የሚወያዩባቸው አጀንዳዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ የትምህርት ዞን እንዲሆን መወሰኑ ይደርስ የነበረውን እንግልት በማስቀረት ትክክለኛ የተቋም መረጃን በአንድ ስፍራ ለማግኘት እንደሚያስችል ተገለጸ፡፡

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶክተር አንዱአለም አድማሴ ለአሀዱ እንደተናገሩት በትምህርት ዘርፉ የተበጣጠሱ የአገልግሎት ሴክተሮችን ወደ አንድ ለማምጣት ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮሜዳ ባለዉ አካባቢ የትምህርት ዞን ብሎ በመሰየም በትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ ዉስጥ ተቋማቱ አገልግሎት እንዲሰጡ ሊደረግ ነው። የተገልጋይን እንግልት ለመቀነስ ሚናው ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

በኤጀንሲዉ ዉስጥ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚደረጉት እነዚህ ተቋማት የትምህርት ጥራት ተጠያቂነትና ተደራሽነት እንዲሁም ስለ ትምህርት ተቋማት ትክክለኛ እና የተሟላ አገልግሎት እንዲገኝ በማድረግ አኳያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸዉ።

[አሐዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
የገቢዎች ሚኒስትር በታህሳስ ወር ከ22 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

በወሩ 21 ቢሊየን 338 ሚሊየን 652 ሺህ 82 ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 22 ቢሊየን 375 ሚሊየን 335 ሺህ 266 ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው አስታውቀዋል፡፡

ይህም የእቅዱን 105 በመቶ መሆኑንም ሚኒስትሩ የገለጹ ሲሆን ገቢው ከሀገር ውስጥ ገቢ፣ ከወጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ እና ከሎተሪ ሽያጭ የተሰበሰበ ነው ተብሏል፡፡

የዘንድሮው ገቢ ካለፈው በጀት አመት አንፃር በ23 በመቶ ዕድገት እንዳለውም ከሚኒስትሩ የፌስቡክ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ14,000 በላይ እናቶች በወሊድና ከወሊድ ጋር በተያያዘ የጤና ችግር ህይወታቸው ያልፋል ተባለ!

የጤና ሚንስቴር መረጃ እንደሚያሣየው ፣ በኢትዮጵያ በየዓመቱ በአማካይ ከ14 ሺህ በላይ እናቶች በወሊድና ከወሊድ ጋር በተገናኘ ችግር ህይወታቸው ያልፋል፡፡በአለም ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው እናቶች ከእርግዝና እና ከወሊድ ጋር በተያያዙ ችግሮች ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ፣ ከእዚህ ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑት እናቶች ለህልፈት የሚዳረጉት በደም መፍሰስ ሳቢያ መሆኑን በጤና ሚኒስቴር የእናቶች ፣ ሕጻናትና ስርዓተ ምግብ ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም በተለይም ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሯ ገለፃ ፣ ወደ ጤና ተቋማት ሄደው የማይወልዱ እናቶች መኖር ፣ የመሰረተ ልማት እና የህክምና ግብዓቶች እጥረት እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ስነ-ምግባር ችግር ለእናቶች ሞት በምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡

አሁን ላይ 51 በመቶ የሚሆኑ እናቶች ወደ ጤና ተቋማት እንደሚሄዱ ዶ/ር መሰረት የተናገሩ ሲሆን ይሁን እንጅ አሁንም ቢሆን ከእርግዝና እና ከወሊድ ጋር ተያይዞ በርካታ እናቶች ህይወታቸው ያልፋል ሲሉ አንስተዋል፡፡የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሊረባረቡ ይገባል ተብሏል።የጤናማ እናትነት ወር ዘመቻ ከጥር አንድ ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ በደም መፍሰስ ምክንያት እናት ለምን ትሙት በሚል መሪ መልዕክት እየተከበረ ይገኛል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክልል የበረሃ አንበጣ ዳግም መከሰቱን የክልሉ እርሻ፣ አርብቶ አደርና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የበረሃ አንበጣ መከላከል ግብረ-ሃይል አስተባባሪ ዶክተር አያሌው ሹመት ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ አፋምቦ፣ ዱብቲና አይሳኢታ ወረዳዎች ጥር 9 ቀን 2013 ዓ.ም የአንበጣ መንጋው ዳግም ተከስቷል።መነሻውን ከጅቡቲና ሱማሌ ያደረገው የአንበጣ መንጋ በሌሎችም የክልሉ ወረዳዎች እየተስፋፋ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ ሚሌ፣ ጭፍራ፣ ጉሊናና ቴሩ ወረዳዎች የአንበጣ መንጋው የተስፋፋባቸው መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።አሁን ላይ በክልሉ የግብርና ስራዎች የሚከናወኑበት ወቅት በመሆኑ የአንበጣ መንጋው ከእንስሳት መኖ በተጨማሪ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ህብረተሰቡን በማሳተፍ በባህላዊ መንገድ የመከላከል ስራ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

መንጋው እስካሁን ያደረሠውን ጉዳት ለማወቅ መረጃ እየተሰበሰበ መሆኑንም ገልጸው፤ መንጋውን ለመቆጣጠር በሰውና በተሽከርካሪ ኬሚካል ለመርጨት አስቸጋተሪ በመሆኑ አካባቢዎች ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር በአውሮፕላን የታገዘ ርጭት ለማካሄድ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስተባባሪው አስታውቀዋል።በክልሉ ካለፉት ሁለት አመት ወዲህ በተደጋጋሚ የበረሃ አንበጣ ተከስቶ በሰብል፣ በእንስሳት መኖና ቁጥቋጦዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሶማሊ ክልል ምክትል ርዕሰ መሰተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ኡመር ደጋህቡር ከተማን ከአዋሬ ወረዳ የሚያገናኘው መንገድ ላይ ለሚገነባውን ድልድይ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

በ 45ሚሊዮን ብር ወጪ የሚገነባው ድልድዩ 26 ሜትር ርዝመት እና 20 ሜትር የጎን ስፋት እንደሚኖረው የክልሉ የኮንስትራክሽን እና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አብዱልፈታህ ቢሂለ ተናግሯል።

የድልድዩ ግንባታ ሲጠናቀቅ በደጋህቡርና አዋሬ ወረዳ መሀከል የሚገኙና በኢኮኖሚ ተዳከመው የነበሩ አከባቢዎችን ድጋሚ እንደሚነቃቁ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግሯል።

[@addiszeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላላ ጉባኤ ያላደረጉ ፓርቲዎች 6ኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ በተጠናቀቀ በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ እንዲያካሂዱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ አሳለፈ።

ቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ምዝገባ ሂደት በሚያከናውንበት ወቅት የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ዓ.ም. እና በመመሪያ ቁጥር 3 መሠረት ጠቅላላ ጉባኤ በማድረግ እስከ ጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ እንዲያቀርቡ የተገለፀላቸው ፓርቲዎች እንደነበሩ አስታውሷል።

ቦርዱ በ2012 ዓ.ም. ሊያካሂድ የነበረው 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ተላልፎ እንደነበር ያስታወሰው ቦርዱ በአሁኑ ወቅት የምርጫው የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ሆኖ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ነገር ግን ጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱ የተገለፀላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች በተጠቀሰው ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄዱ በሚያደርጉት የምርጫ ዝግጅት እንቅስቃሴ ላይ ጫና እንደሚፈጥርባቸው ገልፀው ምርጫው ከተጠናቀቀ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱ እንዲፈቀድላቸው ለቦርዱ ጥያቄ ማቅረባቸው ነው የተነገረው፡፡

ቦርዱም ጥር 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የፖለቲካ ፓርቲዎች እስከ ጥር 30 ቀን 1013 ዓ.ም. ድረስ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱ ያሳለፈውን ውሣኔ እንዲራዘምላቸው ያቀረቡትን ጥያቄ መርምሯል፡፡

በዚህም ቦርዱ የ6ኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የገባ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ ቢያካሂዱ ጫና የሚፈጠርባቸው መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት 6ኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ በተጠናቀቀ በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ አካሂደው መተዳደሪያ ደንባቸው ላይ ማስተካከያ በማድረግ እንዲያቀርቡ ወስኗል፡፡

በመሆኑም የምርጫ ተሳትፎ ዝግጅት ምክንያት ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ ያልቻሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በተጠናቀቀ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን በማከናወን ማሻሻያዎቻቸውን ለቦርዱ እንዲያቀርቡ አሳስቧል።ይህ ውሳኔ ተግባራዊ የሚሆነው በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ የሚሳተፉ ፓርቲዎች ላይ ብቻ መሆኑን ቦርዱ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአምባሳደር ድንበሩ ዓለሙ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ!

የአምባሳደር ድንበሩ ዓለሙ የቀብር ስነ ስርአት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና እና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በተገኙበት በኮልፌ የሙስሊም መቃብር ተፈፅሟል።አምባሳደር ድንበሩ ዓለሙ በዱባይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት በዲፕሎማትነት በማገልግል ላይ እያሉ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ጥር 09 ቀን 2013 ዓ.ም ሕይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው።አምባሳደር ድንበሩ አለሙ ባለትዳርና የሁለት ሴቶች እና የ አንድ ወንድ ልጅ አባት ነበሩ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ሌተናል ጀነራል አልቡርሃን ምላሽ ሰጠ።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

አምባሳደር ዲና በዚህ ጊዜ እንዳሉት “አጥፊ ሐይሎች የእናተን ድንብር ተጠቅመው ወደ እኛ እንዳይገቡ ማለት እናንተ ግቡ ማለት አይደለም” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ለሱዳን መሪዎች እኛ ወደ ሰሜን ህግ የማስከበር ስራ ላይ በመሆናችን የእናተን መግቢያ ድንበሮች ጠብቁ ነው ያሉት ብለዋል አምባሳደር ዲና።

ሱዳንን ለማረጋጋት ኢትዮጵያ በርካታ ስራዎችን ሰርታለች ፣ በሁለቱ ሀገራት የከፋ የነቆራ ታሪክ የለም ሲሉም አክለዋል አምባሳደሩ።

በሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው መሬቱን ውሰዱ ተብልናል የሚለው ሀሳብ ትክክል አይደለም አሁንም አቋማችን የሱዳን ጦር ወደ ቀድሞ ቦታው ሲመለስ እንነጋራለን ብለዋል አምሳደር ዲና።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ሌተናል ጀነራል አልቡርሃን ምላሽ ሰጠ። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ። አምባሳደር ዲና በዚህ ጊዜ እንዳሉት “አጥፊ ሐይሎች የእናተን ድንብር ተጠቅመው ወደ እኛ እንዳይገቡ ማለት እናንተ ግቡ ማለት አይደለም” ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ…
የኤርትራ ሰራዊት ከኢትዮጵያ መከላከያ ጋር ተደርቦ ሕወሓትን ወግቷል የተባለው ጉዳይ መሰረተ ቢስ ወሬ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአገር ውስጥ አልፎ ሰላም ለማስከበር የሚያስችል አቋም አለው ሲሉም ተናግረዋል።

[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
ሀገረ አሜሪካንን ላለፉት አራት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ነጩን ቤተ መንግስት ለተተኪው ፕሬዝዳን ጆ ባይደን ለቀው ወጥተዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa