YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በትግራይ የሚገኙ ጡረተኞች ክፍያቸውን በንግድ ባንክ በኩል እንዲያገኙ ተደረገ!

በደደቢት ብድር እና ቁጠባ ተቋም በኩል የጡረታ ክፍያ ይከፈላቸው የነበሩ በትግራይ ክልል የሚገኙ ጡረተኞች የጡረታ ክፍያቸውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲከፈላቸው መደረጉን የመንግሥት ሠራተኞች ማሕበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ የልዩ ኃይል አባላትን አስመረቀ!

የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ በብር ሸለቆ መሰረታዊ የውትድርና ትምህርት ቤት ያሰለጠናቸውን የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላትን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ክልል ሰላምና የህዝብ ደህንነት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ፣ የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙና ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በአፍደር 13 ማዳበሪያ አደንዛዥ እፅ ተያዘ!

በሶማሌ አፍደር እና ቆራሄይ ዞኖች ኬላ ላይ ትናንት ታህሳስ 27፣2013 ዓም ከቀኑ 6፡30 ገደማ በተደረገ ፍተሻ 14 ማዳበሪያ አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ።በገልባጭ መኪና ላይ ተጭኖ የተገኘው አደንዛዥ ዕፁ ከላይ ሽንኩርት ለብሶ እንደነበር የአፈደር ዞን ወንጀል መከላከል ዋና የስራ ሒደት አስተባባሪ ሳጅን አብዱሰላም አህመድ ተናገሯል።የተያዘው አደንዛዥ ዕፅ አሽከርካሪውም በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን አክሏል።

[@addiszeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በታላቅ የነጃሺ መስጅድ ላይ በደረሰው ጥቃት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለፀ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በታላቁ የነጃሺ ታሪካዊ መካነ ቅርስ መስጅድ ላይ የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።ምክር ቤቱ የዓለም ቅርስ በሆነው የነጃሺ ታሪካዊ መስጅድና የቀብር ቦታ ላይ በከባድ ጦር መሳሪያ በደረሰ ጥቃት በቅርሱ መስጅድ ላይ ጉዳት ደርሷል ብሏል።እንዲሁም የአገልግሎቶ መስጫ ተቋማት እና የመገልገያ ቁሳቁሶች ለዝርፊያ መጋለጣቸውንም ገልጿል፡፡የታላቁ ንጉስ ነጃሺ እና የነብዩ መሐመድ (ሰዐወ) ባልደረቦች መቃብር እና በስሙ የተሰየሙ በዓለም የሚገኙ ቀደምት መስጂዶች አንዱ የሆነው ታሪካዊ ቦታ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ቅርስ ነውም ብሏል ምክር ቤቱ።

መንግስት እና ህብረተሰቡ በመቀናጀት ይህን የወንጀል ድርጊት የፈጸሙ አካላትን በአፋጣኝ ለህግ እንዲያቀርቡም ጠይቋል ምክር ቤቱ፡፡በዚህ ታላቅ ታሪካዊ ቅርስ እና መስጅድ ላይ በደረሰው ጉዳት የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ሙስሊሞች ልብ ተሰብሯል ብሏል።ምክር ቤቱ ይህንን ፍፁም ፀያፍና አሳፋሪ የወንጀል ድርጊት በጽኑ እንደሚያወግዝም አስታውቋል።መንግስት እና ህብረተሰቡ በመቀናጀት ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈፀሙ አካላትን በአፋጣኝ ለፍትህ እንዲቀርቡም ጥሪ አቅርቧል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም ይህንን የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ትክክለኛውን መረጃ እና ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚመለከታቸው  የመንግስት አካላት ጥያቄ ማቅረቡንም ነው ያስታወቀው።እንዲሁም ቅርሱ የደረሰበትን ትክክለኛ ጉዳት እና የጉዳቱን መጠን የሚያጣራ ቡድን ከሚመለከታቸው የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣንና የምክር ቤቱ ባለሙያዎች ቡድን ወደ ቦታው ተልኮ ቡድኑ ሪፖርቱን በአጭር ጊዜ እንዲያቀርብ እየሰራ እንደሚገኝ ነው የተገለፀው፡፡ጠቅላይ ምክር ቤቱ ጥቃት የደረሰበት መስጅድና ቅርስ የሚመለከታቸውን አካላት በማስተባበር በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠግኖ የቀድሞ አገልግሎቱን እንዲሰጥ እንደሚያደርግና ለዚህም ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካው የግምጃ ቤት ኃላፊ ስቴቨን ምኑቺን ካርቱም ገብተዋል!

በትናንትናው ዕለት ከግብጽ ፕሬዝዳንት ጋር በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የተወያዩት ምኑቺን ከአል ቡርሃን እና ከሀምዶክ ጋርም በግድቡ እና በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ይወያያሉ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያና ሱዳን የድንበር ስምምነት በሱዳን በኩል መጣሱን የድንበር ኮሚሽኑ ገለጸ!

እ.ኤ.አ የ1972ቱ ስምምነት የጋራ መፍትሄ እስኪገኝ መሬት ላይ ያለው ነባራዊ ሁኔታ እንዲቀጥል ያስገድዳል፡፡ሱዳን ወደ ቀድሞ ይዞታዋ ተመልሳ ድርድሩ እንዲቀጥል ኢትዮጵያ ለሀገሪቱ መግለጿን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ትናንት አስታውቋል፡፡

[አል ዐይን]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ።

@YeneTube @FikerAssefa
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትላንት ሌሊት በደረሰ የእሳት አደጋ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።

የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢዜአ እንደገለጹት የእሳት አደጋው የተከሰተው በክፍለ ከተማው ወረዳ 11 መኮንኖች ክበብ በሚባለው አካባቢ ከሌሊቱ 8 ሰዓት ገደማ ነው።በአደጋው 2 ሚልዮን 300 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት የወደመ ሲሆን በሰው ህይወት ላይ ግን የደረሰ ጉዳት የለም ብለዋል።የእሳት አደጋው በአንድ እንጨት ቤት፣ ጋራዥ ቤት እና በቶርኖ ቤት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንም ገልጸዋል።

በጋራዡ ውስጥ ከነበሩት 5 መኪኖች መካከል ሁለቱ ሙሉ ለሙሉ ሲወድሙ ሶስቱ ከፍተኛ ጉዳት ደረሶባቸዋልም ብለዋል።የአደጋው መንስኤ ገና በመጣራት ላይ መሆኑን የገለጹት አቶ ጉልላት፤አደጋውን ለመቆጣጠር 9 የእሳት ማጥፊያ መኪኖች አገልገሎት መስጠታቸውንም ጠቅሰዋል።እሳቱን ለማጥፋት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በተደረገ ርብርብ 26 ሚልዮን ብር የሚገመት ንብረት ለማዳን ተችሏልም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።በነገው እለት በሚከበረው የገና በዓልም የእሳት አደጋ እንዳያጋጥም ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አቶ ጉልላት አሳስበዋል።

[ENA]
@YeneTube @FikerAssefa
“የተፃፈበትን የብር ኖት አትቀበሉ ” በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ መሠረተ ቢስ ነው-የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የብር ኖት አሳትሞ ሥራ ላይ አውሏል።ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም በመላ አገሪቱ የብር ኖት ቅያሪ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡የብር ኖት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚታተም የሕዝብ ሀብት ነው።

በመሆኑም በጥንቃቄ ተይዞ ሕብረተሰቡ ለረጅም ጊዜ ሊገለገልበት ይገባል።ከዚህ አንፃር ሆን ተብሎ ወይም በቸልተኝነት በብር ኖት ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት እንዲሁም ብዛት ያለው ገንዘብ ሕግን ባልተከተለ መልኩ ያለአግባብ እንዳይከማች ለማድረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር CMD/01/2020 ማውጣቱ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም፣ የብር ኖቱ ረጅም ጊዜ እንዲያገለግል በማስብ፡

1) በብር ኖቱ ላይ መፃፍ፣ መቅደድና በቀለም ማበላሸት፣ የትኛውንም ዓይነት ጉዳት ማድረስና ምልክቶቹን ያለፈቃድ ማባዛት የተከለከለና በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን፣

2)ለማስታወቂያ ሥራ ከተፈለገ ግን ለማባዛት የባንኩን ፈቃድ ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን፣

3) በጣም የተጎዱ የብር ኖቶች ሲያጋጥሙ ከዝውውር ስለሚወጡበት ሁኔታ ዝርዝር መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን፣እና

4) ባንኩ መመሪያውን ወደ አማርኛ በማስተርጎምና በማብራራት ስለብር ኖት አጠቃቀም በየጊዜው ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ የሚሠራ መሆኑን፣ እየገለፅን “የተፃፈበትን የብር ኖት አትቀበሉ” እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ መሠረተ ቢስ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን ብሬን መትረየስን ጨምሮ 153 የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች፣ ከ17 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች እና ሌሎች ለወንጀል ተግባር የተዘጋጁ ቁሳቁሶች ጋር በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ ፖሊስ አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል እና የአካባቢ ሰላም ማስከበር ምክትል ዳይሬክተር ዋና ኢንስፔክተር ተሬሳ ዴሬሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የጦር መሣሪያዎቹ እና ሌሎች ሕገ ወጥ ቁሳቁሶች በቁጥጥር ሥር የዋሉት በዞኑ 13 ወረዳዎች እና ሦስት የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ ነው።

ባለፉት 20 ቀናት በተደረገ ድንገተኛ የጎዳና እና የቤት ለቤት ፍተሻ በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ሰባት ብሬን መትረየስ፣ 19 ክላሽንኮቭ እና 127 ሽጉጦች ይገኙበታል ብለዋል።

በተጨማሪም 17 ሺህ 451 ተተኳሽ ጥይቶች፣ አራት ቦምቦች፣ የተለያዩ የሬዲዮ መገናኛዎች እና የጦር ሜዳ መነጽሮች መገኘታቸውንም አስረድተዋል።

ከእነዚህ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች እና ቁሳቁሶች ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ 56 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ለማቅረብ እየተሠራ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ተሬሳ ገልጸዋል።

ባለፉት ሦስት ወራት 48 ተጠርጣሪዎች ላይ በሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር በፍርድ ቤት ተከስሰው እስከ 11 ዓመት በሚደርስ እስራት እና እስከ 50 ሺህ ብር እንዲቀጡ የተወሰነባቸው መሆኑንም አውስተዋል።

"ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመግታት የኅብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው" ያሉት ዋና ኢንስፔክተሩ፣ እነዚህን መሣሪያዎች በቁጥጥር ሥር ለማዋል ሕዝቡ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

[ኢብኮ]
@YeneTube @FikerAssefa
«የህዝብና ቤት ቆጠራ መርሃ-ግብር በ2014 ዓም ይካሄዳል» የማዕከላዊ ስታትስቲክ ጽህፈት ቤት 

ለሦስት ጊዜያት የተራዘመው የኢትዮጵያ የህዝብና የቤቶች ቆጠራ በሚቀጥለው ዓመት እንደሚካሄድ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። የኤጀንሲው ዋና ሃላፊ አቶ ቢራቱ ይገዙ የቆጠራው መርሃ ግብር በ2014 ዓም በሚመሰረተው አዲስ መንግሥት ተፈጻሚ እንደሚሆን ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

የህዝብ ቆጠራው በያዝነው 2013 ዓም በግንቦት መጨረሻ ላይ ይካሄዳል ተብሎ ከሚጠበቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ አስቀድሞ ቢደረግ ይመረጥ እንደነበር ሃላፊው ተናግረዋል።ሆኖም የቤት ለቤት ቆጠራው ባይከናወንም የህዝብ ቆጠራ ትንቢያን በመጠቀም ሊያጋጥሙ የሚችሉትን ችግሮች ማቃለል ይቻላል ብለዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ዋሽንግተን የሚገኘውን የአሜሪካን ኮንግረስ መሰብሰቢያ ጥሰው ገብተዋል። የትራምፕ ደጋፊዎች ይህንን ያደረጉት ኮንግረሱ የ2020 የምርጫ ውጤትን ሊያፀድቅ እየተሰናዳ ባለበት ወቅት ነው። ይህ ከተከሰተ በኋላ ዶናልድ ትራምፕ በርካታ ውግዘት እየደረሰበት ሲሆን፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ በትዊተር ማህበራዊ ትስስር ገፅ ትራምፕን መከተል አቁመዋል( unfollow አድርገዋል)። ከዚህ ሁሉ በኋላ ትራምፕ 'ይህ አይነቱ ድርጊት መቆም አለበት' ሲሉ ተናግረዋል። 'ምንም እንኳን ምርጫው ቢጭበረበርም ለሀገራችን ስንል እንደዚህ አይነት ነገር ከማድረግ መቆጠብ አለብን' ያሉ ሲሆን 'አሁን ወደየ ቤታችሁ ሂዱ' ሲሉም ተደምጠዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ለክርስትና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች፣ እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ! መልካም በዓል ይሁንላችሁ!
መልካም ገና ይሁንላችሁ - ዴሊቨሪ ሀዋሳ

ከተማችን ላይ ከሚገኙ ሁሉም ሬስቶራንቶች ጋር አብረን እንሰራለን በቤቶ ሆነው የሚያስፈልጎትን ይዙዙን።

ስልክ :- 0952626262 / 0462126282
ሀዋሳ ላይ ብቻ ነው የምንሰራው
#deliveryhawassa #Hawassa
ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራፕ ከፌስቡክ እና ትዊተር ታገዱ

ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዋነኛዎቹ የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጾች እንዲታገዱ ሆነዋል።ይህ እርምጃ የተወሰደባቸው ደጋፊዎቻቸው የካፒቶል ሂል ግቢን መውረራቸውና አደጋ ማድረሳቸውን ተከትሎ ነው።ዓለምን ባስገረመውና በአሜሪካ ምድር ይሆናል ተብሎ ባልተጠበቀ ነውጥ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የታችኛውና የላይኛው ምክር ቤት መሰብሰቢያ የሚገኝበትንና የመንግሥት መቀመጫ የሆነውን ካፒቶል ሒልን ጥሰው በመግባት አደጋ ያደረሱት ከሰዓታት በፊት ነው።

https://telegra.ph/trump-01-07
@Yenetube @Fikerassefa
የፌስቡክ ስራ አስኪያጅ ማርክ ዙከርበርግ የዶናልድ ትራምፕ የፌስቡክ ገጽ ቢያንስ ለ2 ሳምንት ከፌስቡክ ታግዶ እንደሚቆይ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በዛሬው እለት በደረሱ ሁለት የእሳት አደጋዎች ከ3.5 ሚሊየን ብር በላይ የተገመተ ንብረት ወደመ!

የመጀመሪያው የእሳት አደጋ በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው መሻለኪያ ቄስ ሰፈር ዛሬ ረፋድ ላይ ደርሷል።መሿለኪያ ቄስ ሰፈር በደረሰው የእሳት አደጋ 3 ሚሊየን አምስት መቶ ሺ ብር የሚያወጣ ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቃል፡፡የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከፌደራል ፓሊስ፣አዲስ አበባ ፓሊስ እና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን እሳቱን መቆጣጠር የቻለ ሲሆን 30 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ንብረት ከውድመት መታደግ መቻሉን በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

አደጋው በሱቆች እና በመኖሪያ ቤት ላይ ውድመት ያደረሰ ሲሆን መነሻ ምክንያቱ ግን በውል አልታወቀም፡፡አደጋውን በቁጥጥር ስር ለማዋል 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ወስዷል። 109 የእሳት አደጋ ሰራተኞች 24 ተሽከርካሪዎች እና 145 ሺ ሊትር ውሀ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የደረሰው ሁለተኛው የእሳት አደጋ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው 93 ቁጥር ማዞሪያ ነው፡፡አደጋው የተነሳው በተለኮሰ ሻማ ምክንያት እንደሆነ ሲገለፅ 50ሺ ብር የሚያወጣ ንብረት ማውደሙን አቶ ጉልላት ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባለሙያዎች ባደረጉት ርብርብ 2 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ንብረት በእሳት እንዳይወድም ማድርግ ችለዋል፡፡

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa