ፈረንሳይ በቅርቡ በዩናይትድ ኪንግደም ተገኘ የተባለውና ከነባሩ በጣም ተላላፊ በሆነው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ የተያዘ የመጀመሪያውን ሰው ማግኘቷን አረጋገጠች።
የፈረንሳይ የጤና ሚኒስቴር እንዳለው ግለሰቡ የፈረንሳይ ዜጋ ሲሆን ከሰባት ቀናት በፊት ከለንደን ወደ አገሪቱ የገባ ነው።በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠውም ከአምስት ቀናት በፊት በሆስፒታል ምርመራ ከተደረገለት በኋላ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።ሚኒስቴሩ እንዳለው ግለሰቡ የበሽታው ምልክት ያልታየበት ሲሆን አሁን ላይ በቤቱ ውስጥ ራሱን ለይቶ ይገኛል።በቫይረሱ የተያዘው ግለሰብ ነዋሪነቱን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገ ፈረንሳዊ ሲሆን በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አክሏል። ስለግለሰቡ የጤና ሁኔታ ግን በዝርዝር ያለው ነገር የለም።
[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa

የፌዴራል መንግስት በጀመረው ሕግ የማስከበር ሥራ የተደመሰሱ ከፍተኛ የሕወሓት አመራሮች መኖራቸውን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርኃኑ ጁላ አስታወቁ፡፡
በተደረገው ሕግ የማስከበር ሥራ የሞቱ አመራሮች መኖራውን ለኢሳት ቴሌቪዥን የገለጹት ጄኔራል ብርሃኑ ይህም ወደፊትለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በተደጋጋሚ እያጋጠመ ያለውን የዜጎች ጭፍጨፋ ለማስቆም የመከላከያ ሠራዊት በሽፍታዎች ላይ ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ ነው ብለዋል፡፡ እንደ ጄኔራል ብርሃኑ ገለጻ ሌ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮም ወደ መተከል የሄዱት ለዚሁ ተግባር ነው፡፡ እስካሁንም በርካታ ጸረ ሰላም ኃይሎች እርምጃ እንደተወሰደባቸው ጄኔራሉ ገልጸዋል፡፡
ይሁንና ይህ ሥራ በጸጥታ ኃይል ብቻ የሚሰራ እንዳልሆነና የፖለቲካ ስራ እንደሚጠይቅ ነው ያብራሩት፡፡ በአመራሮች መካከል ያለው የፖለቲካ ሽኩቻ ፣ መሬትህ ሊነጠቅ ነው በማለት የጉሙዝ ሽፍቶችን ማደራጀት እንዲሁም የውጭ ኃይሎች ተሳትፎ ለአካባቢው ቀውስ ዋነኛ ምክንያቶች እንደሆኑም አንስተዋል፡፡ ይህም ነገሮችን እንዳወሳሰበ ነው ጄኔራሉ ያነሱት፡፡ ሽፍቶቹ እርምጃ ሲወሰድባቸው ጎረቤት ሀገር ጭምር እየሄዱ እንደሚሸሸጉም ጄኔራል ብርሃኑ ተናግረዋል፡፡
✍ Al ain

አዲሱን የላፍቶ አትክልትና ፍራፍሬ መገበያያ ማዕከል ግልጋሎት ለማወክ የሚሠሩ ጥቂት ግለሰቦች ቦታው ላይ እሳት የመለኮስ እና ሱቆቹን የማፍረስ ሙከራ ሲያደርጉ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሰክሬታሪያት አስታወቀ።
በጊዜያዊነት በጃንሜዳ እንዲቆይ የተደረገው የአትክልት ተራ ጃንሜዳን ወደቀደመው ማኅበራዊ ግልጋሎት ለመመለስ እና ለጥምቀት በዓልም ለማስለቀቅ 1 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ዘመናዊ የንግድ ማዕከላት መገንባታቸውን ፕሬስ ሰክሬታሪያቱ ገልጿል። ከእነዚህ ማዕከላት መካከል አንዱ የሆነው የላፍቶ የአትክልት ገበያ በውስጡ በቂ የመኪና ማቆሚያ እና ምቹ የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ 556 ጥራታቸውን የጠበቁ ሱቆች፣ የምግብ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች እና የንፅህና መጠበቂያ ስፍራ ተገንብቶለት ወደ ሥራ መግባቱን ነው የገለጸው። ነገር ግን "ከጃንሜዳ መነሳት የለብንም" የሚሉ እና "ወደ ፒያሳ እንመለስ" በሚሉ ጥቂት በኅቡዕ የተደራጁ ነጋዴ እና ከነጋዴ ውጪ ባሉ አካላት የተለያዩ ጥፋቶች (እሳት የመለኮስ እና ሱቁን የማፈረስ) ሙከራ ሲያደርጉ መያዛቸውን ነው ያስታወቀው።
ይህንን የሕዝብ ሀብት ያፈሰስንበትን ዘመናዊ የንግድ ማዕከል በአግባቡ በመጠቀም ለጤናማው ነጋዴ እና ስለብዙኃኑ የሸማች ማኅበረሰብ ስንል ንፅህናውና የጥራት ደረጃውን የጠበቀ ግልጋሎት እንዲሰጥ ማድረግ ይኖርብናል ብሏል።ፕሬስ ሴክሬታሪያቱ፣ ሌሎች ተመሳሳይ ማዕከላት እየገነባን ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ እንሰራለን እንጂ ወደኋላ መመለስ የለብንም ያለ ሲሆን፣ ኅብረተሰቡም ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚከናወኑ ማንኛውንም ሕገ-ወጥ ድርጊቶች በመከላከል እና ለሚመለከተው አካል በመጠቆም አብሮት እንዲሰራ እና እንዲያጋልጥ ጥሪውን አቅርቧል።

ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተሰጠ ማሳሰቢያ:
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ የጥገና ሥራ ስለሚያከናውን እሁድ ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከጥዋቱ 12፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በምስራቅ ኢትዮጵያ ማለትም በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ በአሰበተፈሪ፣ በጅግጅጋ፣ በፊቅ ፣ በደገሃቡር፣ በአዋሽ ሰባት ኪሎ፣ በአዲጋላ፣ በሁርሶ፣ በአሰላ፣ አዳማ፣ አዳሚ ቱሉ እና ሻሸመኔ እንዲሁም በምስራቅ ኢንዱስትሪ ዞን በኖሪያ፣ ደብረዘይት፣ በኢላላገዳ፣ በጆርጅ ጫማ ፋብሪካ፣ በሞጆ፣ በራም፣ በጎዴ፣ በኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር እና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡ ስለሆነም ደንበኞች ይህን በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደረጉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳስቧል፡፡

ግምቱ ከ1.6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ 93 ኩንታል ባእድ ነገር የተቀላቀለበት ቅቤ ወደ ገበያ ሊቀርብ ሲል በቁጥጥር ስር ዋለ!
በደቡብ ክልል ከፋ ዞን ዋቻ ከተማ አስተዳደር ቁሉሽ ቀበሌ ከተለያዩ ባለድርሻ አካለት ጋር በመተባበበር ግምታዊ ዋጋው 1.6 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ ከባእድ ነገር ጋር የተቀላቀለ ቅቤ በገበያ ላይ በተደረገ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የደቡብ ምዕራብ ቅ/ጽ/ቤት አስታውቋል።የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የደቡብ ምዕራብ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ በቃሉ አረጋ እንደገለጹት በኦፕሬሽኑ ቅ/ጽ/ቤቱ ከከፋ ዞን ጤና መምሪያ፣ ከደቡብ ከልል ልዩ ሀይል፣ ከከፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ፣ ከዋቻ ወረዳ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ምርቱ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉ ተገልጿል።
በዓላት በሚደርሱበት ወቅት በህብረተሰቡ በስፋት በሚፈለጉ ምርቶች ላይ ባዕድ ነገሮችን በመቀላቀል አላግባብ የሆነ ትርፍ ለማጋበስ የሚሮጡ የህብረተሰቡንም ጤና ለጉዳት የሚዳርጉ ግለሰቦች እየተስተዋሉ መሆኑም ተጠቁሟል።እነዚህን ህገወጦች ለማስቆም ማንኛውም የህገወጥ የምግብና መድኃኒት ንግድ፣ ዝውውር እንዲሁም ምግብን ከባድ ነገር ጋር የሚደባልቁ በጋራ ለመከላከል ህብረተሰቡ አቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቆጣጣሪ፣ ለፍትህ አካለት አሊያም በነጻ ስልክ መስመር በ8482 በመጠቆም የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ጥሪ አቅርቧል።
[EBC]

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 533 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 6,709 የላብራቶሪ ምርመራ 533 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,901 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 670 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 108,269 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 122,413 ደርሷል፡፡

በቅርቡ በአመክሮ ነጻ የተባሉት የቀድሞው መንግሥት ባለሥልጣናት ሌ/ጄኔራል አዲስ ተድላ እና ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ ከሰኞ ጀምሮ ባሉት ጥቂት ቀናት ለ30 ዐመታት በጥገኝነት ከተጠለሉበት ጣሊያን ኢምባሲ እንደሚወጡ ማረጋገጡን አዲስ አድማስ ጋዜጣ አስነብቧል። ጋዜጣው ሁለቱን ግለሰቦች በስልክ ማነጋገሩንም አክሎ ገልጧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የመተከል ዞን በፌዴራል የፀጥታ መዋቅር ሥር መሆን አለበት አለ!
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በመተከል ዞን እየደረሰ ያለው የሰብዓዊ መብት ቀውስ፣ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መንግሥት ሕግ የማስከበር አቅም በላይ በመሆኑ፣ የዞን አስተዳደሩን በጊዜያዊነት በፌዴራል የፀጥታ መዋቅር ሥር በማድረግ ሁኔታውን ማረጋጋት እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
[ሪፖርተር]

በኦሮሚያ ክልል ባሕላዊ ፍርድ ቤት ሊቋቋም ነው!
የኦሮሞ ሕዝብ በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ የሚገጥሟቸውን እክሎች ማለትም የቤተሰብ እና የጎረቤት፣ እንዲሁም የጎሳ ግጭትን ከዘመናዊ ሕግ በተጨማሪ በሽምግልና ይፈታል።ሽማግሌም ግራ ቀኙን ካዳመጠ በኋላ ጉዳዩን መዝኖ ያጠፋው እንዲቀጣ፣ የተጎዳው ደግሞ እንዲካስ ይወስናል።የኦሮሚያ ክልልም ይህንን ማኅበረሰቡን ግጭቶችንና ችግሮችን ሲፈታበት የቆየውን እሴት የሕግ እውቅና ባለው መንገድ እንዲሰራ ለማድረግ ባሕላዊ ፍርድ ቤት እያቋቋመ መሆኑን የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ገልጿል።በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኮሙኑኬሽን ጉዳዩች ዳይሬክተር አቶ ጎንፋ አቶማ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ይህ የሚቋቋመው ባሕላዊ ፍርድ ቤት በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ላይ ያለውን ጫና የሚያቃልል ይሆናል።"ባሕላዊ ፍርድ ቤት ማለት በማኅበረሰቡ ውስጥ ያለውን ባሕላዊ እሴት በመጠቀም ግጭቶቹን በፍርድ ቤት መፍታት ማለት ነው።ፍርድ ቤቱ የሚጠቀማቸው የመደበኛ ፍርድ ቤቶችን ሕግ ሳይሆን ባሕላዊ ሕጎችን ነው።"የዚህ ባሕላዊ ፍርድ ቤት አመሰራረትም የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልልን ሕገ መንግሥትንና እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች ምሥረታ እና ሥልጣን ድንጋጌ 216/11 መሰረት ያደረገ መሆኑን አክለው ገልፀዋል።

“በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ትምህርት ለማስጀመር እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል” -ትምህርት ሚኒስቴር
በፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርት ባልተጀመረባቸው አካባቢዎች ላይ
ለማስጀመር እየሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ሚኒስቴሩ በኮሮና ወረርሽኝ ዙሪያ ተገቢ ጥንቃቄ እየተደረገ በአብዛኛው አካባቢዎች ትምህርት ቢጀመርም በወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት ትምህርት ያልጀመሩ አካባቢዎች እንዳሉ አስታውቋል።በአሁኑ ሰዓት ሁሉም አካባቢ በሚባል ደረጃ ትምህርት ተጀምሯል ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢፕድ የሰጡት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ገረመው ሁሉቃ በተለይ በገጠሙ የጸጥታ ችግሮች ምክንያት በትግራይ ክልል እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ትምህርት እንዳልተጀመረ ተናግረዋል።
በመሆኑም በአካባቢዎቹ ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል እንደ ሚኒስትር ዴዔታው ገለጻ።ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በተለይ በትግራይ ክልል ትምህርት ለመጀመር የህወሓት ቡድን ከተመደሰሰ በኋላ ነባራዊ ሁኔታን የሚገመግም ኮሚቴ አዋቅሮ ወደ አካባቢው ልኳል።ሆኖም ቡድኑ ትምህርት ቤቶችን በማውደሙ ምክንያት የመጠገን ሥራ ይሰራል፡፡ ይህም ጊዜ መውሰዱ አይቀርም።በመተከልም የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር ተመሳሳይ ሥራ የሚሰራ ይሆናል።

በቀጣዩ ሃገር አቀፍ ምርጫ የጸጥታ እቅድ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው!
በቀጣዩ ሃገር አቀፍ ምርጫ የጸጥታ እቅድ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ ውይይቱ የሚካሄደው ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በተዘጋጀ ዕቅድ ላይ ነው፡፡ዕቅዱ የምርጫውን ፍትሃዊነት፣ ተዓማኒነት፣ ሠላማዊነት እና ዴሞክራሲያዊነት ለማስጠበቅ የሚያስችል ነው ተብሏል።የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ቀነዓ ያደታ (ዶ/ር) በሚመሩት በውይይቱ ላይ የፌዴራል እና የክልል ባለድርሻ አካላት ታድመዋል እንደ ኢዜአ ዘገባ።ሀገራዊ ምርጫውን እና የደቡብ ምዕራብ ሕዝበ ውሳኔን ግንቦት 28 ለማድረግ የሚያስችል የጊዜ ሰሌዳ ከሰሞኑ በቦርዱ ይፋ መደረጉ ይታወሳል፡፡የጊዜ ሰሌዳው ትግራይን አይመለከትም የተባለ ሲሆን የአዲስ አበባ እና የድሬደዋ ከተማ መስተዳደሮች ድምፅ መስጫ ቀን ሰኔ 05 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሆን መወሰኑም አይዘነጋም። ትግራይ ክልልን በተመለከተም የሁኔታዎች አመቺነት ታይቶ የጊዜ ሠሌዳ እንደሚወጣለት ተገልጿል።
[ENA/Al-ain]

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ የሆነው የዘይት መጭመቂያ ፋብሪካ ሊገነባ እንደሆነ ተገለጸ።
አማ ቢዝነስ ግሩፕ ለሚያስገነባው ፕሮጀክት የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።
@YeneTube @FikerAssefa
አማ ቢዝነስ ግሩፕ ለሚያስገነባው ፕሮጀክት የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ከ17ሺህ በላይ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ ቅስቀሳና ምዘገባ እየተካሄደ ነው ... የክልሉ ትምህርት ቢሮ
በአፋር ከ17ሺህ በላይ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ የቤት ለቤት ቅስቀሳና ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ሃላፊ አቶ መሀመድ ሐመዱ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ ከ1ሺህ በላይትምህርት ቤቶች ከ166 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብለው ኮሮናን በመከላከል ማስተማር ጀምረዋል።
“ይሁን እንጂ በክረምት ወቅት የጎርፍና አንበጣ ክስተት በስፋት በተስተዋለባቸው ገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩ ከ17 ሺህ በላይ የመጀመሪያ ደረጃ መጀመሪያ ሳይክል ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ሳይመለሱ ቀርተዋል” ብለዋል ።
የጎርፍና አንበጣ ክስተት ከአርብቶ አደሩ የኑሮ ዘይቤ ጋር ተደምሮ ለተማሪዎቹ ከትምህርት ገበታ መራቅ ተጠቃሽ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ ርእሰ መስተዳድር የሚመራ የከፍተኛ አመራሮች አብይ ኮሜቴ ተዋቅሮ እስከታችኛው የአስተዳደር እርከን ድረስ በመውረድ ህብረተሰቡን በማነሳሳት ተማሪዎቹን ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
የትምህርት ስራ የአንድ ሴክተር ሳይሆን የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ንቁ ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ከመንግስት መዋቅሩ በተጨማሪ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም እስከቀበሌ ድረስ አደረጃጀት ያሏቸውን የጤና ኤክስቴንሽንና የግብርና ባለሙያዎችን ባሳተፈ መልኩ የቤት ለቤት ቅስቀሳና የተማሪዎች ምዝገባ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
ከትምህርት ገበታ ውጭ የሚገኙ 17ሺህ በላይ ተማሪዎች በመጭው ሳምንት ውስጥ ወደ ትምህርት እንዲመለሱ እንደሚደረግ ሃላፊው አስታውቀዋል።
ምንጭ -ኢዜአ
@YeneTube

በሶማሊ ክልል ሲቲ ዞን አፈደም ወረዳ ደን ለሄለይ ቀበሌ በንፁሃን ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶ ከሶማሊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ!!
የሶማሊ ክልላዊ መንግስት ሲቲ ዞን በአፈደም ወረዳ ደን ለሄለይ ቀበሌ ንፁሃን ሰዎች ላይ በተፈፀመው ግድያ፣ በደረሰው የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል።
የአካባቢው አርብቶ አደር ነዋሪዎች የተፈጠረው ግጭት ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ የሚያጋጥመው አይነት መስሏቸው ራሳቸው ለመከላከል ሙከራ ያደረጉ ቢሆንም የህወሓት ርዝራዦች ፣ ኡጉጉሞ የሚባሉት የአፋር አማፂያንና የአፋር ክልል ልዩ ሀይል ተቀናጅተው ቀደም ሲል ጁንታው ያስታጠቃቸውን ከባድ የጦር መሳሪያ በመጠቀም ንፁሐን ዜጎች ላይ የደረሰው ጉዳት ከባድ እንዲሆን አድርጓታል።
ማንኛውም በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የሚደርስ የጥፋት ድርጊት ወንጀል ተብሎ የሚፈረጅ ቢሆንም የዘር ማጥፋት ወንጀል ግን በቀጥታ ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ንፁሃንን ሰለባ የሚያደርግ በመሆኑ ከወንጀሎች ሁሉ የከፋ ወንጀል መሆኑ በተለያዩ የአገራችን እንዲሁም አሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ህጎች ላይ በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል።
ሰዎችን በቋንቋ፣ በዘር ፣ ወይም በማንኛውም በሚያመሳስላቸው ምክንያት ለይቶ መግደልን ጨምሮ አካላዊም ሆነ ስነልቦናዊ ጉዳት ማድረስ ደግሞ የዘር ማጥፋት ወንጀል ዋነኛ መገለጫ ነው።
ስለሆነም የአፋር ክልል የተነሳው አጥፊ ቡድን ወደ ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ቀበሌዎች ዘልቆ በመግባት ጉዳዩ የማይመለከታቸው ንፁሐን ዜጎችን ሶማሊ በመሆናቸው ብቻ በማንነታችው ለይቶ የፈፀመው ጅምላ ጭፍጨፋ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመሆኑ ሌላ ማረጋገጫ የሚጠይቅ ጉዳይ አይደለም።
የሶማሊ ክልላዊ መንግስት በተደጋጋሚ ሲያጋጥም የቆየውን ግጭትና ግጭቱን ተከትሎ የሚመጣውን የንብረት ውድመትና የንፁሃን ሞት ለማስወገድ ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ በመነጋገር መፍትሔ ለመስጠት ያልተቆጠበ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።
ይሁን እንጂ ሰላም በአንድ ወገን ፍላጎት የሚመጣ አይደለምና በተደጋጋሚ ያደረግነው ጥረት ፍሬያማ ሊሆን ባለመቻሉ ዛሬም በአፋር ክልል የመሸገው አጥፊ ቡድን በፈፀመው ጨካኝ ጭፍጨፋ የንፁሃን ሰዎች ደም በከንቱ ሊፈስ ችሏል።
በመሆኑም አጥፊ ቡድኑ ከመሸገበት አፋር ክልል እየተነሳ በተደጋጋሚ ንፁሃንን እየገደለ፤ የሶማሊ ክልላዊ መንግስት ብቻውን ስላም ፈላጊ ሆኖ መቀጠል ስለማይችል ፤ የክልሉ መንግስት በቀጣይ ህግና አሰራርን ተከትሎ የክልሉ ነዋሪ የሆኑ ንፁሃን ሰዎችን ህይወት ለመታደግና የንብረት ውድመትን ለመከላከል ማንኛውንም አስፈላጊ እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
የሱማሌ ክልላዊ መንግስት ንፁሃን የአካባቢው ነዋሪዎች በማንነታቸው ተለይተው በክፉዎች ምክንያት አልባ ጨካኝ እርምጃ ህይወታቸው በማለፉ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በድጋሚ እየገለፀ ለሟቾቹ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመድ ሁሉ ፈጣሪ መፅናናቱን እንዲሰጥ ይመኛል።
የሶማሊ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
ታህሳስ 18/2013 ዓ.ም
ጂግጂጋ

በአማራ ክልል አዊ ዞን ቻግኔ ከተማ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ለተፈናቀሉ ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስተባበር የአስቸኳይ ጊዜ ተግባራት ማስተባበሪያ ማዕከል ተቋቋመ።
በሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎች ወ/ሮ ፍሬአለም ሽባባው እና አቶ ሃይላይ ብርሃነ የተመራ የልዑካን ቡድን በአማራ ክልል አዊ ዞን በቻግኔ ከተማ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በደረሰው ጥቃት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስተባበር የአስቸኳይ ጊዜ ተግባራት ማስተባበሪያ ማዕከል አቋቁሟል።
በቻግኒ ከተማ የማስተባበሪያ ማዕከሉን ስራ በይፋ ያስጀመረው የልዑካን ቡድን ትኩረት የሚያሻቸው ጉዳዮችን ለይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
ተፈናቃዮች የሚያስፈልጋቸውን አስቸኳይ ድጋፍ መለየት፤ የደረሰውን ጉዳት ዓይነትና መጠን መለየት፤ ከሰብዓዊ ድጋፍ ስራ ባሻገር ተፈናቃዮችም ሆኑ ነዋሪዎች ምንም ዓይነት አደጋ እንዳይገጥማቸው ደህንነታቸውን ማረጋገጥ፤ የፀጥታ አካሉን ቁርጠኝነት ማረጋገጥ፤ ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት ካሉ ማረጋገጥና ለወደፊት እጣፈንታቸው መወሰን እንዲቻል ባፋጣኝ መለየት፤ ተፈናቃይ ሆነው ይበልጥ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ህፃናት፣ ነብሰጡር ሴቶች፣ የሚያጠቡ እናቶች እና አቅመ ደካሞችን ቅድሚያ በመስጠት ሰብዓዊ ድጋፍ ባፋጣኝ እንዲያገኙ ማድረግ የአስቸኳይ ጊዜ ተግባራት ማስተባበሪያ ማዕከሉ ዋና ዋና ተግባራት እንደሚሆኑ የሰላም ሚኒስቴር እታውቋል ፡፡
የማዕከሉ ዋና አላማ ፈጣን ምላሽ መስጠት ነው፡፡ ለተፈናቃዮች ለተጠቂዎች ጥያቄ ፈጣን ምላሽ መስጠት ነው ተብሏል፡፡
ቀጠዩ እርምጃ የሁኔታ ዳሰሳ በማድርግ ተጎጂ ወገኖችን አወያይቶ ወደቀያቸው የመመለስ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ነው ተብሏል፡፡ህግ ማስከበርና ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብም ቀዳሚ ተግባር ነው ተብሏል፡፡
Via FBC

በገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ 75 ሚሊዮን 574 ሺህ 275.46 ብር የሚገመት ዕቃ ከታኅሣሥ 9-15/2013 ዓ.ም ባለው አንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ መያዙን ገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
ከዚህ ውስጥ ወደ ሀገር ለማስገባት ሲሞከር የተያዘው 63 ሚሊዮን 704 ሺህ 85.18 ብር የሚገመት ዋጋ ያለው ሲሆን 11 ሚሊዮን 870 ሺህ 190.28 ብር የሚገመተው ደግሞ ከሀገር ሊወጣ ሲል የተያዘ ነው ተብሏል።በተጠቀሰው ጊዜ ከተያዘው የኮንትሮባንድ ዕቃ ውስጥ ከሀገር ሊወጣ የነበረ 312 ኩንታል ቡና፣ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣ አደንዛዥ እፆች፣ መድኃኒቶች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ የመለዋወጫ ዕቃዎች፣ የተለያዩ አልባሳት እና የቀንድ ከብቶች እንደሚገኙበት ተገልጿል።ዕቃዎቹን ሲያጓጉዙ የነበሩ 19 ተጠርጣሪ ግለሰቦች ደግሞ በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል ነው የተባለው።የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙት በፍተሻ፣ በብርበራ እና በተሽከርካሪ በመከታተል ሲሆን የጉምሩክ ሠራተኞች እና አመራሮች ከፌዴራል እና ክልል ፖሊስ አባላት ጋር በቅንጅት በመሥራት እነዚህን የኮንትሮብንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል ብሏል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ በነገው እለት ታህሳስ 20 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አለምነሽ ይባስ አስታውቀዋል።
ምክትል አፈ-ጉባኤዋ ለኢዜአ እንዳሉት ምክር ቤቱ በነገው ዕለት በአሶሳ ከተማ አስቸኳይ ጉባኤውን ያካሂዳል።የመተከል ዞን የሠላምና ጸጥታ ችግር ዋነኛው የምክር ቤቱ ትኩረት እንደሚሆን ምክትል አፈ-ጉባኤዋ አስታውቀዋል።እንዲሁም ሌሎች ክልላዊ እና ሃገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮችን የውይይቱ አጃንዳ አድርጎ እንደሚወያይም ምክትል ወይዘሮ አለምነሽ አስታውቀዋል።

ሮይተርስ የካሜራ ባለሙያዬ ኢትዮጵያ ውስጥ ታስሮብኛል አለ።
ሮይተርስ ኩመራ ገመቹ የተባለው የካሜራ ባለሙያ ከሰሞኑን በኢትዮጵያ ፖሊሶች መታሰሩን ያስታወቀ ሲሆን፣ ለእስር የተዳረገበት ምክንያት እስካሁን አይታወቅም ብሏል። በተጨማሪም ከ12 ቀናት በፊት የጣቢያው ጋዜጠኛ ጢቂሳ ነገሪ በ2 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ድብደባ እንደተፈፀመበት ገልጿል።

በደቡባዊ ዳርፉር የጎሳ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ሱዳን በአካባቢው ወታደሮቿን ማስፈሯ ተሰማ!
በደቡባዊ ዳርፉር ግዛት ጎሳን መሰረት ያደረገ ግጭት ተቀስቅሶ ቢያንስ 15 ንፁሃን መገደላቸውን ተከትሎ መንግስት ከፍተኛ ቁጥር አላቸው የተባሉ የፀጥታ አካላትን በአካባቢው ላይ አስፍሯል፡፡
የዳርፉር ግዛት ከ 2003 አንስቶ ከፍተኛ ግጭት ያስተናገደ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በውሃ የተነሳ የማሳሊት እና ፎልአታ ጎሳ አባላት በተደጋጋሚ ወደ ግጭት ውስጥ ይገባሉ፡፡
በዳርፉር ግጭት 300ሺ የሚጠጉ ሰዎች ሲገደሉ 2.5 ሚሊዮን ሰዎች ለስደት ተዳርገዋል፡፡
Via Bisrat FM

በትግራይ ክልል ውድመት ለደረሰባቸው ፋብሪካዎች ወትሮ ከሚመደበው ውጪ 45 በመቶ የውጪ ምንዛሪ በብሔራዊ ባንክ በኩል እንደተዘጋጀላቸው ተነገረ!
በትግራይ ክልል በነበረው ህግ የማስከበር ዘመቻ ወቅት በርካታ ፋብሪካዎች ለውድመት መዳረጋቸውን ባለሃብቶች አሳውቀዋል፡፡በርካታ ቁጥር ያላቸው ፋብሪካዎቹ ከ50 በመቶ እስከ 90 በመቶ የሚጠጋው ክፍላቸው ለውድመት መዳረጉን ለሚመለከተው አካል ያሳወቁ ሲሆን በአፋጣኝ ወደ ስራ የምንገባበትን መንገድ መንግስት ያመቻችልን ብለዋል፡፡
ጉዳዩን የሚመለከተው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በነበረው ህግ የማስከበር ዘመቻ ውድመት ደርሶባቸዋል የተባሉትን ፋብሪካዎች ለመገምገም መሞከሩ ተገልጿል፡፡
የንግድና ኢንዱስትር ሚኒስትር ድኤታው አቶ ዮሃንስ ድንቃየሁ እንደተናገሩት መንግስት ችግሩን ለመቅረፍ ፋብሪካዎቹ ከእዚህ ቀደም ይፈቀድላቸው ከነበረው የውጭ ምንዛሬ አሁን ላይ 45 በመቶ ጭማሪ ተደርጎላቸው እንዲያገኙ ለማድረግ ከብሔራዊ ባንክ ጋር መግባባታቸውን ገልፀዋል፡፡
ከእዚህ ባሻገር የጥሬ አቅርቦት እቃ እና ሌሎች መሰረታዊ ጉዳዮችን ለማሟላት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በክልሉ የሚገኙ እና በከፍተኛ ደረጃ ውድመት ደርሶባቸዋል ከተባሉት ፋብሪካዎች መካከል ዘኒት ገብስ እሸት ፤ አይካ ንግድና ኢንዱስትሪ ፤ ሼባ ሌዘር ፤ አክሎክ ጄነራል ትሬዲንግ ፤ ሳባና እርሻ እና AJJ የወተት ፋብሪካ እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡
የፋብሪካዎቹ ተወካዮች እና ባለቤቶች ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር ያደረጉትን ውይይት ብስራት ሬድዮ ከስፍራው ተገኝቶ የተከታተለ ሲሆን እነዚህ ኢንዱስትሪዎች በአጭር ጊዜ ወደ ስራ መመለስ የሚችሉበት እድል ጠባብ መሆኑን ለመታዘብ ችሏል፡፡
[Bisrat FM]