YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ከጥቂት ሰዓት በኋላ የምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳውን ይፋ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያደረጋቸውን ዝግጅትና የፈፀማቸውን ዋና ዋና ተግባራት ለፖለቲካ ፓርቲ ኃላፊዎች እያስረዳ ነው።

የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ እያቀረቡ ባሉት ማብራሪያ ከፓርቲዎች በኩል እየተነሱ ያሉት የምርጫ የፀጥታ ጉዳይ ቦርዱንም የሚያሳስበው ስለመሆኑ ጠቅሰዋል።ሆኖም በመንግሥት በኩል የፀጥታውን ጉዳይ የሚከታተል ግብረ ኃይል መቋቋሙን በበጎው አንስተውታል። ቦርዱ የምርጫ ፀጥታን የተመለከቱ ስጋትና መረጃዎችን ታዛቢና ተሳታፊም ጭምር ለሆነበት ግብረ ኃይል እያቀረበ መሆኑን ነው ያስረዱት።ቦርዱ በሰሞነኛው ውሳኔው 43 ፓርቲዎችን በሕጋዊነት የመዘገበ ሲሆን 12 ፓርቲዎች የሚቀሯቸው መረጃዎች ስላሉ ውሳኔ ያላገኙ በሚል ይዟቸዋል።

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በኮንሶ ዞን አካባቢ ባገረሸ ግጭት መነሻነት ከኅዳር 1 እስከ ኅዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ 66 ሰዎች መገደላቸውን የደቡብ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮን ጠቅሶ አስታወቀ፡፡

ለዓመታት የተገነቡ ቀበሌዎችም በስድስት ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ወደ አመድነት መቀየራቸውን ነው ባወጣው ሪፖርት የገለጸው፡፡

ኮሚሽኑ በሪፖርቱ 39 ሰዎች መቁሰላቸውን እንዲሁም 132 ሺህ 142 ሰዎች መፈናቀላቸውን ጠቅሷል፡፡

ከኅዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ኅዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ወደ አካባቢው የክትትል ቡድን ልኮ ምርምራ ማድረጉን የገለጸው ኮሚሽኑ የክትትል ቡድኑ በሀይበና እና በአይዴ ቀበሌዎች እንዲሁም በአርባምንጭ፣ በጊዶሌ እና በካራት ከተሞች በመገኘት ተጎጂዎችንና ቤተሰቦቻቸውን፣ የዓይን ምስክሮችንና የተለያዩ የመንግስት አካላትን ማነጋገሩን ነው የጠቀሰው፡፡

በርካታ ሰዎች በጥቃት ፈጻሚዎች በጭካኔ እና በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፣ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ እንዲሁም በርካታ ቀበሌዎች ውስጥ መኖሪያ ቤቶች፣ የተሰበሰበን እህል ጨምሮ ንብረት እና የእርሻ ቦታዎች መሉ በሙሉ እና በከፊል በእሳት መውደማቸውን ነው ያስረዳው።

ከጥቃቱ መሸሽ ያልቻሉ አቅመ ደካማ ሰዎች ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ ተቃጥለው ለህልፈት መዳረጋቸውን ጠቅሶ ግጭቱ መጠነ ሰፊ የሆነ ሰብአዊ ቀውስ አስከትሏልም ነው ያለው፡፡

የችግሩ መሰረታዊ ምክንያት ወይም የስር መንስዔ ገና እልባት ያላገኘና ግጭቱ መልሶ ሊያገረሽ የሚችል በመሆኑ ዘላቂ መፍትሄ የመፈለጉ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በአሁኑ ወቅት በግጭቱ ለተፈናቀሉና በተለያዩ አካባቢዎች ተጠልለው ለሚገኙ ሰዎች አስፈላጊውን ሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ ጊዜ ሊሰጠው የማይገባ ቀዳሚው ስራ መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቅሷል።

የመንግስትን መዋቅር ይዘው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ግጭቱን የሚያነሳሱ፣ የሚደግፉና የሚያባብሱ ወይም ግጭቱን ባለመከላከል ኃላፊነታቸውን በማይወጡ ሰዎች ላይ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ የእርምት እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባም ምክረ ሃሳብ አቅርቧል።

በአካባቢው እየተስፋፋ እንደመጣ የሚነገረው የሕገወጥ መሳሪያ ዝውውር ላይ የሚደረገውን ቁጥጥር ማጠናከርም በኮንሶ ዞንና በአካባቢው በየጊዜው የሚያገረሹ ግጭቶችን ለማስቀረት የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ መሆኑንም በሪፖርቱ አንስቷል።

ጥቃቱ የደረሰው ኮንሶ ዞን አካባቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከጥቅምት 21 ቀን ጀምሮ አካባቢውን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ መሆኑንም ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የደምቢዶሎ ከተማ ነዋሪዎች ኦነግ ሸኔን የማደን ዘመቻ አካሂደዋል ተባለ!

በቄለም ወለጋ ዞን በደምቢዶሎ ከተማ የሚኖሩ የተለያዩ የህብረተሰብ አካላት ኦነግ ሸኔን የማደን ዘመቻ አድርገዋል፡፡ዘመቻው ለ3 ቀናት የተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የደምቢዶሎ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙላቱ ሌሊሳ፣ ህብረተሰቡ ኦነግ ሸኔን በመታገል ከየትኛውም ጊዜ በላይ ለሰላሙና ለደህንነቱ ዘብ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ገመቹ ጉርሜሳ በበኩላቸው፣ ጽንፈኛው የህወሃት ቡድን ላይ ዘምተን ቡድኑን እንደቀበርን ሁሉ የኦነግ ሸኔን በማጥፋት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እየሰራን ነው ማለታቸውን የደምቢዶሎ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤትን ጠቅሶ ብስራት ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የሙለር ሪልስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ ፍርድ ቤት በዋስ እንዲወጡ ፈቀደ!

የሕወሓት እና የኦነግ ሸኔ የጥፋት ቡድኖች የፋይናንስ ምንጭ ናቸው ተብለው በሕግ ቁጥጥር ስር የዋሉት የሙለር ሪልስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ በዋስ እንዲወጡ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት ፈቅዷል።በዋስ እንዲወጡ ከተወሰነላቸው ከባለሀብቱ የሙለር ሪልስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ በተጨማሪ ኃይላይ መዝገበ እና ሳሙኤል አባዲ የተባሉ ተጠርጣሪዎችም ይገኙበታል።በዋስ የወጡት ተጠርጣሪዎች ከአገር ሳይወጡ ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉም ወስኗል።ግለሰቦቹ ትላንት ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት የሕወሓት እና የኦነግ ሸኔ የጥፋት ቡድኖች የፋይናንስ ምንጭ ስለመሆናቸው የሚያስረዳ ማስረጃ ማግኘቱን በመጥቀስ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ቢሮ ተከራክሮ ነበር።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ 100 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ።

የብድር ስምምነቱ  በጥቃቅንና አነስተኛ ስራ ዘርፍ ለተሰማሩ ሴት ስራ ፈጣሪዎች የሚውል ነው ተብሏል።

የስምምነት ፊርማውን የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ያስሚን ወሀብሬቢ እና በኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና ኤርትራ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ናቸው።

ፕሮጀክቱ የገንዘብ እጥረት ያለባቸውን ጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ብድር የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት እና የኮቪድ ወረርሽኝ ስራቸው ላይ ጉዳት ላደረሰባቸው ሴቶች የሚውል መሆኑንም ሚኒስትር ዲኤታዋ ተናግረዋል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ግንቦት 28 እንዲካሄድ ሃሳብ ቀረበ!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም የድምጽ መስጫ ቀን እንዲሆን ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።የቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫን የጊዜ ሰሌዳ አስመልክቶ ቦርዱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በአዲስ አበባ ራዲሰን ብሉ ሆቴል ተወያይቷል፡፡በዚህ ስብሰባ በ2013 የሚደረገው ምርጫ አጠቃላይ የትግበራ መርሃ ግብር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች የህክምና አገልግሎት ለመስጠት የተቀናጀ የህክምና ባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው ማቅናቱን የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታውቋል።

ወደ ሥፍራው ያቀናው የህክምና ቡድኑ ከአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል የተወጣጡ የተለያዩ የሙያ ስብጥር ያላቸው ሲሆኑ፣ 1 ዶክተርን ጨምሮ 3 ነርሶች፣ 2 ላብራቶሪ ባለሙያዎች፣1 የድንገተኛ ቀዶ ህክምናና ለሎች ባለሙያዎችም ይገኙበታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ ፣ ከ157 ሚሊየን ብር በላይ ሰበሰብኩ አለ!

ኢንተርፕራይዙ በ2013 በጀት ዓመት አምስት ወራት ውስጥ በአዲስ-አዳማ እና በድሬዳዋ-ደወሌ የክፍያ መንገዶች ከመቶ ሃምሳ ሰባት ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታውቋል፡፡

በበጀት ዓመቱ በክፍያ መንገዶቹ ከ 4 ሚሊየን በላይ የትራፊክ ፍሰት ለማስተናገድ ታቅዶ 3.5 ሚሊየን ማከናወን መቻሉንም የክፍያ መንገዶች የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ሮቤል አያሌው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡ክንውኑም 90 በመቶ ሆኖ መዝግቡን ገልፀዋል፡፡

ከክፍያ መንገድ አገልግሎት ከ 161 ሚሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ 147 ሚሊየን 55 ሺህ ብር መሰብሰቡን ለማወቅ ችለናል፡፡

እንዲሁም ከልዩ ልዩ ገቢዎች፣ከማስታወቂያ ቦታዎች ኪራይ፣ ከወደሙ የመንገድ ሃብቶች ካሳ ክፍያ፣ ከተሽከርካሪ ማንሻና መጎተቻ ከአስር ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አቶ ሮቤል ጨምረው ነግረውናል፡፡

በሁለቱ አገልግሎቶችም 157 ሚሊየን ብር በላይ በ5 ወራት ውስጥ መሰብሰብ ተችሏል፡፡የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ያልተቋረጠ የ24 ሰዓት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
ሰረገላ ሜትር ታክሲ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል።

በሴቶች ብቻ አገልግሎት የሚሰጠው ሰረገላ በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመርቋል።ሴቶች የመኪና አደጋን የማድረስ አጋጣሚያቸው አነስተኛ በመሆኑ እና ሴቶች አቅም ስላላቸውም ነው ሴት አሽከርካሪዎችን የመረጥነው ሲሉ የሰረገላ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቤተልሄም ነጋሽ ተናግረዋል፡፡

ሰረገላ ደንበኞቹን አክብሮ በጥንቃቄ ና በጥራት የሚሰራ እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡የሰረገላ መስራች አቶ ኤልያስ ነጋሽ በበኩላቸው ሰረገላ ከአሽከርካሪዎቹ በተጨማሪ የማኔጅመንት አባላት አብዛኛዎቹ ሴቶች ናቸው ብለዋል፡፡

የትራንስፖርት ዘርፉ ሴቶችን ያገለለ መሆኑ ከጥንቃቄ አንጻር ብዙ ጉድለቶች ነበሩበት ያሉት አቶ ኤልያስ ሰረገላም ይሄን ችግር ለመቅረፍ ሀ ብሎ ጀምሯል ሲሉ አክለዋል፡፡የምንጠቀማቸው መኪኖችም ከቴክኖሎጂና ከደህንነት አንጻር በሚገባ ተዘጋጅተንበታል ብሏል ሰረገላ፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን ታጣቂዎችና ሚሊሻዎች ከሰሞኑ የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው ጥቃት መፈፀማቸውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ፡፡

ሚሊሻዎቹ እና ታጣቂዎቹ የገበሬዎችን ማሳ በመዝረፍ እና በማፈናቀል በርካታ ህገ ወጥ ድርጊት መፈጸማቸውን አምባሳደር ዲና ከዋልታ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ከሱዳን አመራሮች ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የገለጹት አምባሳደር ዲና፣ በሀለቱ ሀገራት መካከል ልዩነትን ለመፍጠር የሚፈልጉ አካላትና ወደ ሱዳን የሸሸው የጁንታው ቡድን ሁኔታው እንዲባባስ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

የመሬት ይዞታ ባለቤትነት ጥያቄ በአንዳንድ የሱዳን ፖለቲከኞችም ይስተዋላል ያሉት ቃልአቀባዩ፣ ድርጊቱን በመደገፍ በሱዳን የሚገኙ መገናኛ ብዙኃንም ሲያራግቡት መቆየታቸውን አንስዋል፡፡ከሰሞኑ በሱዳን በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይም ብሔርን መነሻ ያደረገ ማጎሳቆል እንደደረሰባቸውም ተናግረዋል፡፡ኢትዮጵያ በህግ ማስከበር ሂደት ውስጥ መሆኗን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የሀገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ የሚጥሩ አካላት ሁኔታዎችን ለማባባስ እየሰሩ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡

[ዋልታ]
@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ያሉ መስሪያ ቤቶች በሙሉ ተዘግተው እንደሚገኙ አል ዐይን ዘግቧል!

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሕብረት መረጃ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌ/ጄ አስራት ዴኔሮ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰንና ከምክትላቸው ጌታሁን አብዲሳ ጋር በዝግ እየተወያዩ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

በግልገል በለስ ከተማ ውስጥ ስታር ሆቴል እየተካሄደ ባለው ዝግ ስብሰባ የዞን አመራሮች እንዲወጡ መደረጉን ለማወቅ ችለናል፡፡ የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ውጭ እንዲሆኑ መደረጉን አል ዐይን ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: https://am.al-ain.com/article/ethiopian-military-officials-are-holding-secret-talks-with-ashadli-hassan-and-his-deputy

@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 207 መድረሱን ወረዳው አስታወቀ።

የጉምዝ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የተገደሉ 207 ሰዎች መሆናቸው በወረዳው ኮማንድ ፖስት፣ የክልሉ መርማሪዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተቆጥሮ መረጋገጡን የቡለን ወረዳ አስታውቋል።ሕጻናት፣ አረጋውያን እና ሴቶች ጨምሮ "ሟቾች የተለያየ ኃይማኖት ተከታዮች በመሆናቸው የአካባቢው ሰው በተስማማበት" በጅምላ በአንድ ጉድጓድ ተቀብረዋል። የሽናሻ፣ አገው፣ አማራ ብሔር አባላት መሆናቸው ከጅምላ መቃብሩ በመቃ በቆመ ወረቀት ተከትቧል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ለሰብአዊ ድጋፍ የሚሆን ተጨማሪ የምግብ እህልና ሌሎች ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ክልል እየተጓጓዙ ነው ተባለ!

ለሰብአዊ ድጋፍ የሚሆን ተጨማሪ የምግብ እህልና ሌሎች ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ክልል እየተጓጓዙ መሆናቸው ተገለጸ።የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር መኮንን ሌንጂሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ተጨማሪ የምግብና ሌሎች ቁሳቁስ ወደ ስፍራው እየተጓጓዙ ነው።

በትናትናው እለት ድጋፉን የጫኑ ዘጠኝ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ መቐሌ መጓዛቸውን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሩ፣ በዚህም 2 ሺህ 900 ኩንታል ዱቄት፣ 280 ኩንታል መኮሮኒ፣ 438 ካርቶን የዱቄት ወተትና 200 ኩንታል ሩዝ አዳማ ከሚገኘው የኮሚሽኑ የእህል ማከማቻ መጋዘን ተጭኖ ወደ ስፍራው በመጓጓዝ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በሰብአዊ እርዳታው እስካሁን ከ129 ሺህ ኩንታል በላይ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ወደ ስፍራው መጓጓዙንም ጠቅሰዋል።“የሚደረገው ሰብአዊ ድጋፍ ቀጣይነት ይኖረዋል” ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ፤ በአገሪቱ ለ7 ወር የሚሆን የመጠባበቂያ የእህል ክምችት እንዳለም ተናግረዋል።

[ኢዜአ]
@YeneTube @FikerAssefa
በጋምቤላ ክልል ዋንተዋር ወረዳ 36 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ቱት ኮር ገለጹ።

ከጦር መሣሪያዎቹ መካከል18 ታጣፊ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ባለሰደፍ ክላሺንኮንቭ መሆናቸውን ተናግረዋል።ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎቹን ሲያዘዋወሩ የተደረሰባቸው ግለሰቦች ተኩስ ከፍተው ለማመለጥ ሲሞክሩ እርምጃ እንደተወሰደባቸውም ገልጸዋል።እርምጃው የተወሰደው ግለሰቦቹ ትናንት ምሽት አራት ሰዓት አካባቢ ከጠረፍ ወደ ዋንተዋር ወረዳ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎችን በሸክም ለማስገባት ሲሞከሩ ነው።

አዘዋዋሪዎቹ ለማምለጥ ሲሞክሩም በተካሄደው የተኩስ ልውውጥም ሁለቱ መገደላቸውን አስታውቀዋል።አራት የሚሆኑ አዘዋዋሪዎች ደግሞ ለጊዜው ሸሽተው ቢያመለጡም፣ ሳይቆስሉ እንዳልቀረ ጠቁመዋል።ያልተያዙትን አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ሥር ለማዋል ክትትል እያደረገባቸው እንደሚገኝም አመልክተዋል።በተለይም ክልሉ ከደቡብ ሱዳን ሰፊ የድንበር ወሰን ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር እየተስፋፋ መሆኑን ጠቁመው፣ “ኅብረተሰብን በማሳተፍ ለመከላከል ጥረት እየተደረገ ነው” ብለዋል።ለመከላከል እየተደረገ ባለው ጥረት በተለይ የኑዌር ዞን የፀጥታ አካላት እና ኅብረተሰቡ እያሳዩ ላሉት ትብብር ምክትል ኮሚሽነሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የሙለር ሪልስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ ፍርድ ቤት በዋስ እንዲወጡ ፈቀደ! የሕወሓት እና የኦነግ ሸኔ የጥፋት ቡድኖች የፋይናንስ ምንጭ ናቸው ተብለው በሕግ ቁጥጥር ስር የዋሉት የሙለር ሪልስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ በዋስ እንዲወጡ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት ፈቅዷል።በዋስ እንዲወጡ ከተወሰነላቸው ከባለሀብቱ የሙለር ሪልስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ በተጨማሪ ኃይላይ መዝገበ…
በዋስትና እንዲወጡ ተወስኖላቸው የነበሩት የሙለር ሪልስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው አዲስ የምርመራ መዝገብ ተከፈተባቸው!

ተጠርጣሪው አዲስ በተከፈተባቸው የምርመራ መዝገብ በመጪው ሰኞ ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው ይታያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ከእርሳቸው ጋር የዋስትና መብታቸው የተከበረላቸው ኃይላይ መዝገበ እና ሳሙኤል አባዲ ላይ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ ይግባኝ መጠየቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡ግለሰቦቹ የሕወሓት እና የኦነግ ሸኔ የጥፋት ቡድኖች የፋይናንስ ምንጭ ሆነዋል በሚል ወንጀል ተጠርጥረው ጉዳያቸው በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ሲታይ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

[ኢብኮ]
@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ከጭፍጨፋዉ የተረፉ ሰዎች የምግብና የመጠጥ ውኃ ችግር እንዳጋጠማቸው ተናገሩ፡፡

ሰሞኑን በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በብኩጂ ቀበሌ ዘርን ለይቶ በተፈጸመው ጭፍጨፋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁኃን ሰዎች መገደላቸውን ከጥቃቱ የተረፉ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የፌድራል የጸጥታ ኀይል ጥበቃ እያደረገላቸው እንደሚገኝ የተናገሩት ነዋሪዎቹ ጥቃቱን ሲያስፈጽሙብን የነበሩ ኀላፊነት የጎደላቸው የክልሉ አመራሮች ናቸው ብለዋል፡፡

በወቅቱ መሰብሰብ የነበረባቸዉን ሰብል በሠላም እጦት መሰብሰብ እንዳልቻሉና በጥፋት ኀይሎች መቃጠሉን የተናገሩት ነዋሪዎቹ በየቦታው ተፈናቅለን ለምንገኝ ወገኖች መንግሥት ሊደርስልን ይገባል ብለዋል፡፡

ቁጥራቸዉ በውል ያልታወቁ ተፈናቃዮችም በቡለን አዳራሽና በትምህርት ቤቶች ተጠልለው እንደሚገኙና የምግብና የመጠጥ ውኃ ችግር እንዳጋጠማቸው ተናግረዋል፡፡ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረ ጊዜ ድረስ ተፈናቃዮችን የጎበኘ የመንግሥት አካላት እንደሌለም ተናግረዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቅድመ ማስጠንቀቂያና የአደጋ ስጋት ቅነሳ ዳይሬክተር ሰሎሞን ነጋሽ ለተፈናቃዮች ለመድረስ ከብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የተላኩ 5 ተሽከርካሪዎች እስከ ተሳቢያቸው የዕለት ደራሽ ምግብ ጭነው ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን አስረድተዋል።

የክልሉ መንግሥት በሁለት ተሽከርካሪዎች ምግብና ሌሎች ቁሳቁሶችን ይዞ ወደ ስፍራዉ እየተጓዘ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

[አብመድ]
@YeneTube @FikerAssefa
ከመቐለ አላማጣ የመኪና መጓጓዣ 800 ብር ሆኗል።

ከጦርነቱ በፊት በመኪና ለመጓዝ ዘጠና ብር የሚያስከፍለው የ177 ኪሎ ሜትሩ የመቀሌ አለማጣ መንገድ 800 ብር እየተከፈለበት ነው።

በትግራይ የነበረው ጦርነት የፈጠረው አለመረጋጋት ትራንስፖርት ዘርፉን አንዳሻቸው ለሚጨምሩ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ክልሉን ዳርጎታል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ በተመራጭ ፎቶና በቴክኖሎጂ የታገዘ እንደሚሆን ተገለፀ!

ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ መራጭ የሚያውቀውን ሰው በትክክል አውቆ እንዲመርጥ በፎቶ የተደገፈ መረጃ እንደሚሰጠውና ሙሉ ምርጫው በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሁም የመረጃ ማስገቢያ ባለሙያ የተመደበበት ሆኖ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለፀ።ስድስተኛው አገራዋ ምርጫ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ በጊዜያዊነት ቀን ተይዞለታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተወያየበት ወቅት እንደተገለፀው፤ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲካሄድ ጊዜያዊ የቀን ቀጠሮ የተያዘለት በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በርካታ አዳዲስ አሠራሮችና ቴክኖሎጂዎች ይተገበራሉ።

ከእነዚህ መካከልም መራጭ ማንነቱንና ምንነቱን እየለየ እንዲመርጠው የሚያስችል ተመራጭ እንዲኖረው ለማድረግ በፎቶ የተደገፈ ምርጫ መሆኑ ተጠቃሽ ሲሆን፤ ሌላው በባለሙያ የተደገፈ መረጃ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ላይ እንዲኖር ለማድረግ የመረጃ ማስገቢያ ባለሙያ ለምርጫው ዝግጁ መሆናቸው ነው።

አጠቃላይ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ተግባሩ የዘንድሮው ምርጫ ለየት የሚያደርገው እንደሆነ የገለፀው ቦርዱ፤ ከምርጫ ምዝገባ እስከ ውጤት ድረስ ያሉ ተግባራት በቴክኖሎጂው አማካኝነት የሚከናወኑ እንደሆነም አስታውቋል። የምርጫ ምልክቶችም ቢሆኑ በሚገባ እንዲመረመሩ የሚያስችል አሠራር መዘርጋቱንም ጠቁሟል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀንና በማታ ያሰለጠናቸውን 4 ሺህ 87 ተማሪዎቹን ዛሬ ያስመርቃል፡፡

ከተመራቂዎቹ መሀከል 48ቱ በ3ኛ ዲግሪ በቀን ያሰለጠናቸውን ናቸው፡፡በመጀመሪያ ዲግሪ በማታ ፕሮግራም 809፣ በቀን 3039 እንዲሁም በርቀት 18 ተማሪዎቹን ለምርቃት አብቅቷል፡፡በህክምና ስፔሻሊቲም 26 ተማሪዎቹ ዛሬ ከሚመረቁት መሀከል መሆናቸው ተነግሯል፡፡ዛሬ ከሚመረቁት መሀከል 2635 ወንዶች ሲሆኑ 1452 ሴቶች ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በአመቱ በአጠቃላይ 10561 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡ከእነዚህ መሀከል 5045 በመጀመሪያ ዲግሪ ፣ 313 በ3ኛ ዲግሪ እና 2226 በማታ ፕሮግራም ያሰለጠናቸው መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡እንዲሁም በርቀት 180፣ በክረምት 2252፣ በስፔሻሊቲ 265፣ ከፍተኛ ዲፕሎማ በመምህርነት ፕሮግራም 269 ናቸው፡።በአመቱ የዛሬውን ጨምሮ በአጠቃላይ 7350 ወንዶችን እና 3211 ሴቶች ተማሪዎቹን ለምረቃ አብቅቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ፈረንሳይ በቅርቡ በዩናይትድ ኪንግደም ተገኘ የተባለውና ከነባሩ በጣም ተላላፊ በሆነው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ የተያዘ የመጀመሪያውን ሰው ማግኘቷን አረጋገጠች።

የፈረንሳይ የጤና ሚኒስቴር እንዳለው ግለሰቡ የፈረንሳይ ዜጋ ሲሆን ከሰባት ቀናት በፊት ከለንደን ወደ አገሪቱ የገባ ነው።በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠውም ከአምስት ቀናት በፊት በሆስፒታል ምርመራ ከተደረገለት በኋላ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።ሚኒስቴሩ እንዳለው ግለሰቡ የበሽታው ምልክት ያልታየበት ሲሆን አሁን ላይ በቤቱ ውስጥ ራሱን ለይቶ ይገኛል።በቫይረሱ የተያዘው ግለሰብ ነዋሪነቱን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገ ፈረንሳዊ ሲሆን በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አክሏል። ስለግለሰቡ የጤና ሁኔታ ግን በዝርዝር ያለው ነገር የለም።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa