YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
 ጋዜጠኛ፣ አርቲስት እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ዕድገት ውስጥ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተው ኢብራሂም ሀጂ አሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

ኢብራሂም ሀጂ አሊ ካለፈው ክረምት ጀምሮ ባጋጠመው የጤና እክል ሳቢያ የህክምና ክትትል ሲደረግለት ቆይቶ ድጋፍ ሲደረግለት ቆይቶ ትናንት ሌሊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡የቀብር ስነስርዓቱ ዛሬ 9፡00 ሰዓት ላይ በኮልፌ በሚገኘው የሙስሊም መቃብር ይፈጸማል፡፡ጋዜጠኛ፣ አርቲስት እና የቋንቋ ተመራማሪው በሙዚቃ ህይወቱ በርካታ ነጠላ ዜማዎችን ያበረከተ ሲሆን፣ አራት ዓይነት የሙዚቃ መሳሪያዎችን መጫወት ይችል ነበር፡፡

ኢብራሂም ሀጂ አሊ ሙዚቃን የጀመረው ተወልዶ ባደገባት በድሬዳዋ ሲሆን በ1967/68 የአርፈን ቀሎ ባንድ 2ኛ ትውልድ በመባል በሚጠራው ከአዱ ቢራ ባንድ መስራቾች ከሚባሉት የክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ፣ ሂሜ የሱፍ፣ አብዱ ሸኩር፣ መሀመድ ጠዊል ጋር በመሆን አንደኛው መስራች ነበር፡፡

ከዚያን ጊዜ በኋላ የጋዜጠኝነት ህይወትን እስከሚቀላቀል የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃን በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች ለማስተዋወቅ እድል አግኝቶ ተጠቅሞበታል፡፡በ1968 ዓ.ም በሪሳ ጋዜጣ ስራ ሲጀምር ኢብራሂም ሀጂ አሊ አንዱ ጋዜጠኛ ነበር፡፡ኢብራሂም የግጥም እና ዜማ ደራሲ እንደነበርም በቅርብ የሚያውቁት እና የእሱን ስራዎች የተጫወቱ ይመሰክሩለታል፡፡

በ1987 ዓ.ም ሬዲዮ ፋና ሲመሰረት ፋናን ከተቀላቀሉት አንጋፋ ጋዜጠኞች መካከልም አንዱ ሲሆን ተወዳጅ የሆነውን ፋና አፋን ኦሮሞ ፕሮግራምን አዘጋጅቶ በማቅረብም ይታወቃል፡፡
ኢብራሂም በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እስከ ኤዲተርነት ያገለገለ ሲሆን ህይወቱ እስክታልፍ ድረስም የስፖርት ጋዜጠኛ ነበር፡፡አፋን ኦሮሞ በጥናት ላይ ተመስርቶ እንዲያድግም ጥረት ካደረጉ ታላላቅ ሰዎች መካከል አንዱ ነው፡፡

[ፋብኮ]
@YeneTube
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተወሰኑ የግል ንግድ ባንኮችን የጨረታ ማስያዣ ቦንድ (ቢድ ቦንድ) እና የሥራ መፈፀም አቅምን የሚያረጋግጥ (ፐርፎርማንስ ቦንድ ) እንዳይሰጡ እንዳገዳቸው ተሰምቷል።

የቢድ እና የፐርፎርማንስ ቦንድ እንዳይሰጡ የታገዱት ባንኮች 8 መሆናቸውን ሸገር ዘግቧል።ንብረታችንን አስይዘን የጨረታ ማስያዣ ቦንድ ለመውሰድ የግል ባንክ ስንጠይቅ ብሔራዊ ባንክ ስላገደ ልናስተናግዳችሁ አልቻልንም ተብለናል ያሉ ደንበኞች ቅሬታ እንደገባቸው ነግረዋል።ደንበኞች በዚህ ሁኔታ ሥራቸው እንደተደናቀፈባቸው አስረድተዋል።

ይህንኑ ለማረጋገጥ የተወሰኑ የግል ባንክ የስራ ሀላፊዎች ተጠይቀዋል በዚህም ከባንኮቹ መካከል የታገዱ እና ያልታገዱ አሉ።ከዚህ ውስጥ 8 የግል ባንኮች የጨረታ ማስያዣ እና የሥራ የመፈፀም አቅምን የሚያረጋግጥ ሰነድ እንዳይሰጡ ብሔራዊ ባንኩ እንዳገዳቸው ታውቋል።

ሸገር ይህን መረጃ በተመለከተ ከብሔራዊ ባንክ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሞክሮ አልተሳካለትም።

የፐርፎርማንስ እና የቢድ ቦንድ እንዳይሰጡ የታገዱት የግል ባንኮች ብሔራዊ ባንክ መስጠት ካለባቸው ጣሪያ በላይ አልፈው ስለሄዱ መሆኑን ተሰምቷል።

ነገር ግን የተጠየቁት እና ለግዜው ስማቸውን ያልተገለፁ የግል ባንኮች የሚመለከታቸው የአብዛኛዎቹ እግዶች ምክንያት ማስያዣዎችን ከፍርድ ቤት በማሳገድ ሳቢያ በክፍያ ላይ ከተፈጠረ ችግር ጋር የተያያዘ መሆኑ ታውቋል።የሌሎች የግል ባንኮች እገዳ ሌላ ምክንያት ሊሆን ይችላል።በጉዳዩ ላይ የታገዱት የግል ባንኮች ለብሔራዊ ባንክ እግዱ እንዲነሳ ደብዳቤ መፃፋቸውን እና ከ ባንኩ ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ መያዛቸውንም ተሰምቷል።

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
ብሔራዊ ባንክ የደቡብ ግሎባል ባንክ የትርፍ ድርሻ ክፍፍልን አገደ!

በተጠናቀቀው የ2012 የሒሳብ ዓመት የትርፍ ምጣኔያቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ካሳደጉት ጥቂት ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው ደቡብ ግሎባል ባንክ፣ የትርፍ ድርሻ ክፍፍልን ተፈጻሚ እንዳያደርግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕገዳ አደረገበት፡፡

የደቡብ ግሎባል ባንክ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ ብሔራዊ ባንክ የሒሳብ ዓመቱ የትርፍ ክፍፍል ድርሻ ታግዶ እንዲቆይ ውሳኔ ያስተላለፈው፣ ከውጭ ምንዛሪ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ መጣራት ያለበት ሒሳብ በመኖሩ እንደሆነ ታውቋል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2017 የሒሳብ ዓመት ጀምሮ ባንኩ ከሰጠው የውጭ ምንዛሪ ብድር ጋር ተያይዞ ያልተወራረደና ያልተጣራ ሒሳብ በመኖሩ፣ እስኪጣራ ድረስ የሒሳብ ዓመቱን የትርፍ ድርሻ ክፍፍል ማከፋፈል የማይችል መሆኑ ተገልጾለታል፡፡

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
የመተከልን የጸጥታ ችግር ለመፍታት የሚያግዝ ህዝባዊ ውይይት በአሶሳ ተጀመረ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከልን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ያግዛል የተባለለት ህዝባዊ ውይይት ዛሬ በአሶሳ ከተማ ተጀምሯል።በውይይት መድረኩ ከክልሉ የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።ውይይቱ የሀገር አቀፉ የማህበረሰብ ምክክር መርሃ ግብር አንዱ አካል እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ዓላማው የመተከልን ሠላም መመለስ በሚቻልበት ዙሪያ ለመምከር መሆኑን የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ የሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሳ ሃሚድ ተናግረዋል።ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ ቀርቦ የመድረኩ ተሳታፊዎች ለመተከል ጸጥታ ችግር ምክንያት በሆኑና መፍትሄው ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።ለሁለት ቀናት በሚቀጥለው የውይይት መድረክ ክልሉና ሠላም ሚኒስቴር በጋራ ያዘጋጁት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በባሕሬን የኢትዮጵያ ቆንስል በይፋ ሥራውን መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም መሰረት ቆንስል ጄኔራል ሆነው የተመደቡት አምባሳደር ጀማል በከር ስራቸውን ባሕሬን ማናማ ደርሰው ከባሕሬን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አደራጅ ኮሚቴ አባላት ጋር ትውውቅ ማድረጋቸውም ተገልጿል፡፡አምባሳደሩ ባሕሬን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተወካይና በሀገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አቀባበል አድርገውላቸዋል ተብሏል።ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በዱባይ ውይይት ባደረጉበት ወቅት በባሕሬን ሚስዮን እንዲከፈት አቅጣጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ነው ሚሲዮኑ የተከፈተው፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
"በተለያዩ ስያሜዎች የተከፈቱና ስድብን ትጥቅ አድርገው የሚንቀሳቀሱ 43 የሚደርሱ የፌስቡክ ገጾችና አካውንቶች አሁን አየር ላይ የሉም፣ ድርጊቱም 45 በመቶ ቀንሷል!"

በሀገርና በህዝብ ላይ ጉዳት የሚያስከትል፣ ሌላውን አካል የሚጎዳ፣ የሚያስከፋ ወይም የሚያስቀይም ሐሰተኛ መረጃ ማሰራጨት ወይም መስጠት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በሁሉም ብሔረሰቦች የሚያጸየፍ ተግባር ነው፡፡

የመረጃውን ትክክለኛነት ከማጣራትና ከማሰራጨት አንጻር የብሮድካስት ሚዲያው ሳይበለጽግ በማህበራዊ ሚዲያ ሐሰተኛ መረጃዎች በፍጥነት የሚሰራጩበትና በሰዎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚፈጥሩበት አጋጣሚዎች ይስተዋላሉ፡፡

በተቋማት ድረ-ገጽ ላይ ገብተው ሀሳብ ከሚሰጡት አካላት አብዛኞቹ ተቺዎች፣ ተሳዳቢዎችና ግጭት ቀስቃሾች መሆናቸውን የገለጹት የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዱዓለም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የህግ ማስከበር ዘመቻ ከተጀመረ ወዲህ ይህ ድርጊት 45 በመቶ መቀነሱን በማህበራዊ ሚዲያ የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ ብለዋል፡፡

አቶ ወንድወሰን አያይዘውም ሀሳባቸውን ጨዋነት በተሞላበት መንገድ መግለጽ እየቻሉ ብሔር፣ ሀይማኖት፣ ማንነት፣ የኋላ ታሪክ እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች እያነሱ ከሚሳደቡ ግለሰቦች አብዛኞቹ በውጭ ሀገር የሚኖሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የህግ ማስከበር ዘመቻውን ተከትሎ በተለያዩ ስያሜዎች የተከፈቱና ስድብን ትጥቅ አድርገው የሚንቀሳቀሱ 43 የሚደርሱ የፌስቡክ ገጾችና አካውንቶች አየር ላይ እንዳልነበሩም ተናግረዋል፡፡

Via Ethiopian Broadcast Authority/Ethio Check
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል በተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች እጃቸው እንዳለበት በመረጋገጡ 711 አመራሮች ከሓላፊነት ተነሱ!

የደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሓላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን በክልሉ ላለፉት ሁለት ቀናት የተካሄደውን የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት አፈጻጸም ግምገማ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶች ቢኖሩም ክልሉ በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ ማለፉን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ በጉራፈርዳ፤ በወላይታ በኮንሶ ዞን እና በዙሪያው ባሉ ልዩ ወረዳዎች ጽንፈኛው የህወሓት ጁንታ ሓይል ለግጭት አመቺ የሆኑ ቦታዎችን በመጠቀም እና የአደረጃጀት እና የወሰን ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግ ህብረተሰቡ ያልተገባ ዋጋ እንዲከፍል ማድረጉን ወ/ሮ ሰናይት ተናግረዋል፡፡በብዝኃነቱ የሚታወቅና ለሌሎች አካባቢዎችም ተምሳሌት የሆነውን የደቡብ ክልል ጽንፈኛው ሓይል ለእኩይ አላማ ሲጠቀምበት እንደነበር በዝርዝር መገምገም እንደተቻለም ሓላፊዋ ገልጸዋል፡፡

በተፈጠረው ችግር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጃቸው መኖሩ የተረጋገጠ 711 አመራሮች ከሓላፊነት እንዲነሱ ተደርጓል ብለዋል፡፡ 918 የሚሆኑት ከቦታቸው እንዲሸጋሸጉ ሲደረግ 1 ሺህ 966 ደግሞ በማስጠንቀቂያ መታለፋቸውን ገልጸዋል፡፡ጽንፍ ይዘው የጸጥታ ችግሩን ሲመሩ እና ሲያስተባብሩ የነበሩ አመራሮች ደግሞ በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል ሲሉ መናገራቸውን በከደቡብ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ለ12ኛ ክፍል ፈተና የሚውሉ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ ከውጭ እንደሚገቡ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

በኦንላይን የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ለመስጠት እቅድ መያዙን ሚኒስቴሩ ገለጿል።ሚኒስቴሩ ከአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ጋር በመሆን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ዝግጅት በማስመልከት ማብራሪያ ሰጥቷል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ በትምህርት ቤቶች ላይ ተተክለው ከሚኒስቴሩና የፈተናዎች ኤጀንሲ ሰርቨሮች ጋር የሚገናኙ 1 ሺህ 500 ቪሳት ቴክኖሎጂ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

መሳሪያዎቹን የሚተክሉ 250 ባለሙያዎች ስልጠና ወስደው ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።12 ሺህ ላፕቶፖች ደግሞ ለፈታኞች ለማከፋፈል ዝግጁ እንደሆኑ ያብራሩት ሚኒስትሩ፤ 450 ሺህ ታብሌቶች ደግሞ እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ ከውጭ እንደሚገቡ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በማይካድራ በጅምላ ለተገደሉ መታሰቢያ መሰረት ድንጋይ ተቀመጠ!

በማይካድራ ከተማ ቁጥራቸው ከ600 እስከ 1000 ሺሕ እንደሚደርስ የተነገሩ በጅምላ የተገደሉ ነዋሪዎችን እየዘከረች መሆኗን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስታወቀች::

በማይካድራ በጅምላ የተቀበሩ ሰዎች ፀሎተ ፍትሃት ተደርጎላቸው አስክሬናቸው ቤተክርስቲያ ውስጥ በተዘጋጀ የመቃብር ሥፍራ እንዲያርፍ ተደርጓል።በከተማው መሃልም የመታሰብያ ሃውልት መሰረተ ድንጋይ ተቀምጦላቸዋል::

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ዛሬ ማለዳ በንጹሓን ዜጎች ላይ ጥቃት ተፈጽሟል!

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዛሬ ታኅሳስ 14/2013 በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን አዲስ ማለዳ ከወረዳው ኗሪዎች ተረድቻለው ብሏል።በቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ የሚገኙ ኗሪዎች ላይ የታጠቁ ኃይሎች ከማለዳው 11 ስዓት ጀምሮ በአራት ማዕዘን ከበው ጥቃቱን እንደፈጸሙት ገልጸዋል፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ዛሬ ማለዳ በንጹሓን ዜጎች ላይ ጥቃት ተፈጽሟል! በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዛሬ ታኅሳስ 14/2013 በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን አዲስ ማለዳ ከወረዳው ኗሪዎች ተረድቻለው ብሏል።በቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ የሚገኙ ኗሪዎች ላይ የታጠቁ ኃይሎች ከማለዳው 11 ስዓት ጀምሮ በአራት ማዕዘን ከበው ጥቃቱን እንደፈጸሙት ገልጸዋል፡፡ Via Addis Maleda…
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ በተባለች ቀበሌ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ከ90 በላይ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀረ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።

[በዶይቼ ቨሌ]

ጥቃቱ በቀበሌዋ ዛሬ ማለዳ መፈጸሙን የተናገሩት ነዋሪዎቹ ከሀምሳ በላይ የመኖርያ ቤቶችም መቃጠላቸውን ገልጸዋል። ዛሬ ሲነጋጋ አሰራ አንድ ሰዓት አካባቢ ተጎጂዎች ተኝተው ባሉበት ቤታቸው ከውጭ እየተዘጋ እንዲቃጠልባቸው እና ሌሎች ደግሞ ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ መገደላቸውን ከአካባቢው መስማታቸውን አንድ የቡለን ወረዳ ነዋሪ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። በጥቃቱም ሕጻናትን ጨምሮ 96 ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀረም ገልጸዋል።

«በዓይኔ እንኳን አላየሁም ቢያንስ ጥዋት 11 ሰዓት አካባቢ ሰዎች ተኝተው ባለበት ሰዓት ቡለን ወረዳ በኪጂ በምትባል ቀበሌ ማኅበረሰቡ በድንገት ታፍኖ ብዙ ጥቃቶች ደርሷል። ሰዎች ሳር ቤት ውስጥ በተኙበት በራቸው ከውጭ እየተቆለፈ ሕጻናት፣ እናቶች እና ብዙዎች ሞተዋል። እስካሁን ባይረጋገጥም እስከ 96 ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀሩ መረጃዎች አሉን።»በመተከል ዞን የግልገል በለስ ከተማ ነዋሪ እና መምህር እንደሆኑ የተናገሩት ፣ ሌላው ምስክር ደግሞ የጥቃቱ ሰለባዎችን ቁጥር 106 ያደርሱታል። በተጨማሪም በጥቃቱ ከተገደሉት ውጭ ከ50 በላይ መኖርያ ቤቶች መቃጠላቸውንም ይገልጻሉ።

«በመተከል ዞን ዋና ከተማ ግልገል በለስ ነው ያለሁት።በአንድ ወረዳ ከ106 በላይ ሰው ነው የታረደው እና የተገደለው።እና በጣም ዘግናኝ እና በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ እና ተሰምቶ የማይታወቅ ድርጊት ነው የተፈጸመው። በተጨማሪም ከ50 በላይ ቤቶችም ተቃጥለዋል።በዚህ ድርጊት እስከ ስድስት ሰዓት ድረስ 96 ሰዎች ነበር አሁን እየተፈተሸ እየተፈተሸ ሄዶ ወደ 106 ሰዎች ደርሷል።»

ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅትም የመከላከያ ሠራዊትም ሆነ ሌሎች የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በአቅራቢያ እንዳልነበሩ እና ዘግይተው መድረሳቸውንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።በመተከል ዛሬ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት በተመለከተ የክልሉን መንግሥት አስተያየት ለማካተት ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጋሹ ዱጋስ ቢደወልም ስልካቸውን ባለማንሳታቸው አልተሳካም። የክልሉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ ደግሞ ስብሰባ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በመተከል ዞን ተገኝተው በአካባቢው ባለው የጸጥታ ሁኔታ ላይ የነዋሪዎች ተወካዮችን ያነጋገሩት ትናንት ማክሰኞ ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ትምህርት ተዘግቶባቸው በነበረባቸው ወቅቶች ፤ ከ 5ሺ በላይ እድሜቸው ለጋብቻ ያልደረሱ ህጻናት ተድረዋል ተባለ!

በኮቪድ-19 ወረርሽኙ ምክንያት የመማር ማስተማሩ ተቋርጦ በነበረበት ወቅት ፤ በአማራ ክልል ከሚገኙ 92 ወረዳዎች ውስጥ ብቻ 5,763 እድሜቸው ለጋብቻ ያልደረሱ ህጻናት መዳራቸውን የክልሉ ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል፡፡

በክልሉ በ9 ወራት ውስጥ ጋብቻ ከፈጸሙት 5,763 ሕጻናት መካከል አንድ ሺህ ስልሳ አንዱ ወንዶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ አራት ሺ ሰባት መቶ ሁለቱ ሴቶች መሆናቸውን በቢሮው የሴቶች ንቅናቄ ተሳትፎ ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ስማቸው ዳኜ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

የ2013 የትምርት መርሀ ግብር ሲጀመር በወረዳዎቹ ከተዳሩት 3,919 የሚሆኑት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው አለመመለሳቸውን ለማወቅ ችለናል፡፡

በሌሎች 100 ወረዳዎች እስካሁን ሪፖርት አለመድረሱን እና ቁጥሩ ከፍ ሊል እንደሚችል ከቢሮው ብስራት ሰምቷል፡፡

ከመጋቢት 2012 በፊት በክልሉ በድብቅ የተፈጸሙ ጋብቻዎች 161 ብቻ የነበረ ሲሆን ከመጋቢት ወር ወዲህ ቁጥሩ 5,763 መሆኑን አቶ ስማቸው ጨምረው ተናግረዋል፡፡

ወደ ትምህርት ገበታቸው ያልተመለሱትን ተማሪዎች ለመመለስ በየወረዳዎቹ ከወላጆች ጋር ውይይት ተጀምሯል፡፡ እንዲህ አይነት ድርጊቶች ሲፈጸሙ በድብቅ ስለሚከወኑ መረጃዎችን ለማግኘት መምህራን እና ሌሎች የመንግስት ሰራተኞች ጋር በጋራ እየሰሩ መሆኑም ተጠቁማል፡፡

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ለኢፈርት ድርጅቶች ገለልተኛ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር ሾመ!

በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቅራቢነት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በመ/ቁ 263499 በቀን 14/4/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት 7 (ሰባት) አባላት ያሉት ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር ሾሟል፡፡ባለአደራ አስተዳደሩ በፍ/ቤት ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገበት የማስተዳደር ሥራን የሚያከናውን ሲሆን በየጊዜው የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሾመው ፍ/ቤት እንዲሁም ለፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የማቅረብ ኃላፊነት አለበት ይላል ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያገኘነው መረጃ፡፡

የጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደሩ አባላት ገለልተኝነት፣ የትምህርት ዝግጅት፣ የሙያ ሥነ ምግባር እና የነዚህን ዓይነት ትላልቅ የንግድ ድርጅቶችን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት፣ በቦርድ አመራርነት እንዲሁም አባልነት በመምራት ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተመረጡና የተሾሙ መሆናቸውንም መረጃው ጠቅሷል፡፡ለኢፈርት ድርጅቶች ጊዜያዊ ባለ አደራ አስተዳደር በመሾም ሂደት ውስጥ የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ የንግድና ኢንዳስትሪ ሚኒስቴር እና የትግራይ ክልል ጊዜአዊ አስተዳደር ከፍተኛ ሙያዊ ድጋፍና አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን እንዲሁም የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከፍተኛ አመራሮችም ለጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ስራውን ሲመሩ እና ሲከታተሉ መቆየታቸውን በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክተር ጄነራል አቶ አለምአንተ አግደው ገልፀዋል፡፡

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል እስከ ጥር ወር መጨረሻ ድረስ ለ2.3 ሚሊዮን አስቸኳይ ዕርዳታ ፈላጊዎች 116 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው የተመድ አስቸኳይ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ዛሬ በትዊተር ገጹ ባሰራጨው ሪፖርት አስታውቋል፡፡ ከዚህ ውስጥ 64 ሚሊዮን ዶላሩ ዕርዳታ ገና አልተገኘም፡፡ ከዕርዳታ ፈላጊዎቹ መካከል 1.3 ሚሊዮን በግጭቱ ሳቢያ ለተረጅነት የተጋለጡ ናቸው፡፡ ሁለት የተመድ የሰብዓዊ ሁኔታ ገምጋሚ ቡድኖች በመቀሌ እና ሽሬ ከተሞች ግምገማ እያካሄዱ ነው፡፡

በተያያዘ ዜና የተመድ ስደተኞች ድርጅት እስከ መጭው ሰኔ ወር ድረስ ከትግራይ ክልል ግጭት የሚሰደዱ ስደተኞችን ለመርዳት 155 ሚሊዮን ዶላር እንደሚስፈልገው በድረገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል፡፡ ድርጅቱ የዕርዳታ ዕቅዱን ያወጣው፣ እስከ ሰኔ ወር ድረስ የስደተኞች ቁጥር ወደ 115 ሺህ ሻቅባል በሚል ግምት መሆኑን ጠቅሷል፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በማይካድራና አካባቢው በየቦታው ወድቀው የተገኙ 140 አስከሬኖችን ሰሞኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሰብሳባ እንዲቀበሩ ማድረጓን አስታወቀች። ቤተክርስቲያኗ በማይካድራ በጅምላ ለተቀበሩ ወገኖችም የሞቱበትን 40ኛ ቀን ምክንያት በማድረግ የፍትሐት ስርዓተ ጸሎት ፈፅማለች፣ የአደጋው ለተጎዱ ወገኖችም በተለያዩ አካባቢዎች የማፅናኛ ትምህርት መሰጠቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት በመተከል ዞን ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ አመራሮችን በህግ ቁጥጥር ሥር እያዋለ ነው!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት በመተከል ዞን ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ ከፍተኛ እና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችን በህግ ቁጥጥር ሥር ማዋል ጀምሯል፡፡

በዞኑ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር እጃቸው ያለበትን፣ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ አመራሮችን በህግ ቁጥጥር ስር እያዋለ ሲሆን እስካሁንም 5 አመራሮችን በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በዚህም፡- መሠረት

1ኛ. አቶ ቶማስ ኩዊ፡- የኢፌዴሪ ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ

2ኛ. አቶ አድጎ አምሳያ፡- የቀድሞው የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር

3ኛ. አቶ ሽፈራው ጨሊቦ፡-የቀድሞ የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር

4ኛ. አቶ ባንዲንግ ማራ፡- የመተከል ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ

5ኛ. አረጋ ባልቢድ፡- የመተከል ዞን የቀድሞ አመራር የነበሩ

እነዚህ አመራሮች ከመተከል ዞን የጸጥታ ችግር ጋር እጃቸው እንዳለበት በመረጋገጡ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የክልሉ መንግስት በዞኑ የተፈጠረውን ግጭት ለማረጋጋት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ሲሆን፣ ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ተሳትፎ ባደረጉ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ወደ ሠላም ለመመለስ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ እንዲደግፍ የክልሉ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

[የቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት ኮሚኒኬሽን ፅ/ ቤት]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በመተከል ዞን በዛሬው እለት ስለተፈፀመው የንፁሃን ግድያ ያወጣው መግለጫ:

ታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም.

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፡ የሰዎች ደኅንነት ማረጋገጥ ቀዳሚው የመንግሥት ግዴታ ነው

ታኅሣሥ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ከለሊቱ 10፡00 ሰዓት ላይ የታጠቁ ኃይሎች በእንቅልፍ ላይ በነበሩ ነዋሪዎች ላይ በለኮሱት እሳት እና በተኩስ ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው በክልሉ ያለው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዳከመ መሄዱን እንደሚያሳይ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) ገለጸ።

ኢሰመኮ የጥቃቱንሂደት በተመለከተ ታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ከሚመለከታቸው አካላት እና ከተጎጂዎች ጋር በመነጋገር ሲከታተልና ሲያጣራ ቆይቷል። በኩጂ ቀበሌ ከወረዳው መቀመጫ ከሆነችው ቡለን ከተማ 90 ኪ.ሜ. ርቃ የምትገኝ ሲሆን የሺናሻ፣ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ይኖሩባታል። ለቀበሌው የተመደበ የፖሊስ ወይም የፀጥታ ኃይል አለመኖሩን ኮሚሽኑ በክትትሉ መሰረት ተረድቷል።

ኮሚሽኑ ሁኔታውን እስካጣራበት ጊዜ ድረስ በቡለን ሆስፒታል 36 ተጎጂዎች እርዳታእየተደረገላቸው ሲሆን አብዛኞዎቹ በጥይት ሌሎቹ በቀስት የቆሰሉ መሆናቸውን ኢሰመኮ በምልከታ አረጋግጧል። በተጨማሪም ሰዎች ጥቃት የደረሰባቸውን ሁኔታ የሚያሳዩና የሚረብሹ የፎቶግራፍ ማስረጃዎች ለኮሚሽኑ ደርሰውታል። በሰው ሕይወት እና በአካል ላይከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ የደረሱ ሰብሎችና የተሰበሰቡ ማሳዎች በእሳት ጋይተዋል። ቢያንስ18 ያክል ነዶዎች ሲቃጠሉ ማየታቸውን አንድ ተጎጂ አስረድተዋል።

በጨላንቆ እና ዶሼ ቀበሌዎች ቤቶች እየተቃጠሉ እንደሆነ ከአካባቢው ለኮሚሽኑ የተላኩ መረጃዎች ያመለክታሉ። በድባጤ ወረዳዶንበን ቀበሌ ስጋት የገባቸው ነዋሪዎች ከታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ቀዬአቸውን ጥለው እየተሰደዱ እንደሆነም ኮሚሽኑተረድቷል።

አካባቢውን በቅርበት እንዲጠብቅ የተመደበው ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት ታኅሣሥ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ለማረጋጋት ተግባርወደቦታው ተልከው የነበሩ አንድ የፌዴራል እና ሁለት የክልሉ አመራሮችን ለማጀብ በሚል አካባቢውን ለቅቆ መሄዱ ታውቋል። ጥቃቱ የጀመረው ይህንኑ ተከትሎ እንደሆነና ሌሊቱን የጀመረው ጥቃት እስከ ቀኑ አጋማሽ ድረስ መዝለቁንም ለማወቅ ተችሏል። ኮሚሽኑ ያነጋገራቸው ተጎጂዎች እንደሚሉት በጥቃቱ ከሞቱ ሰዎች መካከል አብዛኛው የሺናሻ ተወላጆች ናቸው።

ከዚህ ቀደም በነበሩ ጥቃቶች ፈጻሚዎቹ ከ”ጫካ” የሚመጡ ሰዎች የነበሩ ቢሆንም፣ በዚህኛው ጥቃት “በስምና በመልክ የሚያውቋቸው”የበኩጂ ቀበሌ ነዋሪዎች ጭምር መሳተፋቸውን ከጥቃቱ የተረፉ ተጎጂዎች ገልጸዋል።

ኢሰመኮ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሚከሰቱ ጥቃቶችን ተደጋጋሚነትና የክልሉን ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ሁኔታ አስመልክቶ፣ የፌዴራሉንና የክልሉን መንግሥታት የተጠናከረ ትብብርና ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሻ ሲያሳስብ መቆየቱ ይታወሳል። ይሁንናጥቃቶቹ በመልክ እና በስፋት እየተባባሱ መጥተዋል።

ስለሆነም፣በጥቃቱ ጉዳት ለደረሰባቸው እና ለተፈናቀሉ ሰዎች የህክምና እና ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ፣ እንዲሁም ተገቢው ማጣራትና ጥቃቱን ባለመከላከልም ሆነ በሌላ መልኩ ጥቃቱን የፈጸሙና ያባባሱ ሰዎችን ሕግ ፊት የማቅረቡ ሂደት ከወዲሁ እንዲጀመር ኮሚሽኑ ያሳስባል። በአካባቢው የሚገኘውን የፀጥታ ኃይልና መዋቅር የሰዎችን ደኅንነት ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በከፍተኛደረጃ በአፋጣኝ እንዲጠናከር ኢሰመኮ ጥሪ ያቀርባል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል በወገኖች ላይ በተፈጸመው ኢሰብአዊ ተግባር ማዘናቸውን በማህበራዊ ገፃቸው ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤኒሻንጉል ክልል መተከል ውስጥ በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ ሆኗል ያሉ ሲሆን በወገኖቻችን ላይ በተፈጸመው ኢሰብአዊ ተግባር በእጅጉ አዝኛለሁ ሲሉ ነው የገለፁት።ችግሩን በተለያየ መንገድ ለመፍታት የተደረገው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት እንዳላመጣም በመግለፅ የጠላቶችን ዓላማ በጁንታው ላይ የሠነዘርነውን ብርቱ ኃይል ለመበተን ነው፤ ይህም የሚሳካ አይደለም ብለዋል።መንግሥት ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ አድርጓል፤ የምንፈልገውን ውጤት ለማግኘት ሁላችንም እንደ ከዚህ ቀደሙ በትኩረትና በኅብረት እንድንሠራም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጥሪ አቅርበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞንና በአፋር ክልል ተጎራባች ወረዳዎች በተከሰተ ግጭትበሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።

ግጭቱ ከዚህ በፊት ከነበረው የተለየ ገጽታ አለው ተብሏል፡፡ከአፋር ክልል የሚጎራበተውና ግጭቱ የተከሰተበት የባቲ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ መሐመድ አብዱ ከግጦሽ ሳርና ከውሃ ጋር በተያያዘ ግጭቶች በተለያዩ ጊዜያት ሲከሰቱ መቆየታቸውን አስታውሰው የሰሞኑ ግጭት ግን ከሌላ ጊዜው የተለየ ነው ብለዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አህመድ የግጭቱ መንስኤ አለመታወቁን ያስረዳሉ፡፡ከአፋር ክልል በኩል ያለውን ምላሽ ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ ተደርጎ ባይሳካም በክልሉ የሚንቀሳቀሱት የአፋር ዴሞክራሲዊ ፍትሃዊ ፓርቲ ሊቀመንበር መሐመድ ዳውድ፤ ሁኔታው እነርሱንም ግራ እንዳጋባቸው ተናግረዋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
📷: ደቡባዊ ብሪታንያ ውስጥ በፍጥነት እየተዛመተ ባለው አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ምክንያት ሃገሮች ከብሪታንያ የሚነሱ መንገደኞችን እንዳገቡ በመከልከላቸውና በደቡብ ምስራቅ ብሪታኒያ፣ አሽፎርድ አጠገብ ወደሚገኘው ዶቨር ወደብ የሚወስደው መንገድ በመዘጋቱ፣ የእቃ ጭነት ማመላለሻ መኪናዎች ተሰልፈው የቆሙበትን ኤም 20 የተሰኘ መተላለፊያ ፖሊሶች ጥበቃ እያደረጉ ነው።

በክልከላው ምክንያት መንቀሳቀስ ያልቻሉት ወደ አውሮፓ በመጓዝ ላይ የነበሩት የጭነት መኪናዎች ከብሪታንያ የመውጣት ፈቃቶ ቶሎ እናገኛለን ብለው በተስፋ እየተጠባበቁ ነው።

የደቡብ ምስራቅ ብሪታኒያ ዋና የወደብ መተላለፊያ በሆነው አውራ ጎዳና ላይ እና የተለመደውን አገልግሎት መስጠት ባቆመው ወደብ ላይ የተሰለፉት ከ 1500 የሚበልጡ መኪናዎች በአዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ምክንያት ብሪታኒያ ምን ያክል እንደተገለለች ያመላክታል።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa