YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ላለፋት ሁለት ቀናት ስብሰባውን ሲያካሂድ የነበረው የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን አጠናቀቀ።


ከብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ!

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከታህሳስ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየዉን መደበኛ ስብሰባ አጠናቋል፡፡

ኮሚቴዉ በሰላም፣ በልማት፣ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና መጪዉን አገራዊ ምርጫ በተመለከቱ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት ተወያይቶ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡

በዋናነት ባለፉት ሁለት አመታት ተኩል በአገራችን የታየዉ ለዉጥ በርካታ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፈተናዎችን ተጋፍጦ የአገራችንን ብልጽግና እዉን ለማደረግ ሰፊ እድል የፈጠረና አገራችንን ከብተና አደጋ ያዳነ መሆኑ በዉይይቱ ከስምምነት ተደርሷል፡፡

በተለይም ብልጽግና  ዉሁድ ህብረ ብሄራዊ አገራዊ ፓርቲ ሆኖ መደራጀቱ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ከፍተኛ እድል ከመፍጠሩም በላይ ከአገሪቱ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ተገለዉ የዳር ተመልካች የነበሩ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማቀፍና ለማሳተፍ የቻለ የመጪዉ ትዉልድ ፓርቲ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

በአገራዊ ለዉጡ የተገኙ ድሎችን ጠብቆ በማስቀጠል ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና ማሳደግ እንደሚያስፈልግ የተገለጸ ሲሆን ለዚህም የፓርቲዉን መርሆዎች፣ እሴቶችና አሰራሮችን በጥብቅ ዲሲፕሊን ተግባራዊ ማድረግና ጠንካራ ተቋማዊ ባህል መገንባት አስፈላጊ መሆኑ ከስምምነት ተደርሷል፡፡

ኮሚቴዉ በሁለቱ ቀናት መደበኛ ስብሰባዉ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት ከተወያየ በኋላ የሚከተሉትን አቅጣጫዎች አስቀምጧል፡፡

ዝርዝሩ ከላይ የተቀመጠውን ይመስላል።
@YeneTube @FikerAssefa
ዘመን ኢንሹራንስ ስራ ጀመረ!

ለአመታት በባንክ አገልግሎት ብቻ የሚታወቀው ዘመን የኢንሹራንስ አገልግሎት መጀመሩን ይፋ አድርጓል።ዘመን ኢንሹራንስ በዛሬው እለት ለ3 ወር ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን 13 እጬ ኦፊሰሮች በክሌም ኦፊሰን በአንደር ራይቲን ኦፊሰር በኢንጅነሪን በዛሬው እለት ለመጀመሪያ ጊዜ አስመርቋል።በእለቱ የክብር እንግዳ አትሌት ሀይሌ ገብረሥስላሴ ለተመራቂዎቹ ሰርተፍኬት አበርክተዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የገቢዎች ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ጣና ሐይቅን ለመታደግ 13 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ!

የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን እና የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳድር የሥራ ኀላፊዎችና ሠራተኞች ከወር ደመወዛቸው እና ከተቋማቸው በማዋጣት ለጣና ሐይቅ እና አካባቢው ደኅንነት ፈንድ መሰረት 13 ሚሊዮን ድጋፍ አድርገዋል፡፡

(አብመድ)
@YeneTube @FikerAssefa
በመቐለ 84 በመቶ የሚሆነው የመንግሥት ሠራተኛ ወደ ስራ ገበታው ለመመለስ ሪፖርት አድርጓል ተባለ!

በመቐለ ከሚገኙት 2 ሺህ 26 የመንግሥት ሠራተኞች መካከል እስካሁን 84 በመቶ የሚሆኑት ወደ ሥራ ለመመለስ ሪፖርት ማድረጋቸውን የከተማዋ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ ተናገሩ።ከንቲባው አቶ አታኽልቲ ኃይለሥላሴ የመቐለ ከተማ ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክተው ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ የመቐለ ከተማን ሰላምና መረጋጋት ለማረጋገጥ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከፌዴራል ፖሊስና ከነዋሪዎች ጋር በቅንጅት የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የመደበኛ ፖሊስ አባላትም በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ወደ ሥራ ገበታቸው ለመመለስ ሪፖርት እያደረጉ መሆኑንም ነው የገለጹት።በጎ-ፈቃደኛ እና መልካም ስነ-ምግባር ያላቸው ወጣቶች በከተማዋ ሰላምና መረጋጋት ላይ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።በከተማዋ የሚገኙ የህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትም ተገቢው ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።በከተማዋ ከሚገኙ ሰባት ክፍለ ከተሞች መካከል በአምስቱ ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት የሚሰጡ አመራሮች መመደባቸውን ጠቅሰው፤ በቀሪ ሁለት ክፍለ ከተሞች ላይ ምደባ ለማካሄድ ህዝባዊ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በወረዳ እና በቀበሌ ደረጃ ያሉ ምክር ቤቶች በነበሩበት እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ተቀምጦ ጥሪ ቢደረግም ባለመምጣታቸው ምክር ቤቶቹ በህዝብ ምርጫ እንደ አዲስ እንዲቋቋሙ መደረጉንም ገልጸዋል።ምክር ቤቶችና አመራር የተመደበላቸው ክፍለ ከተሞች ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ መግባታቸውንም ተናግረዋል።በተጨማሪ በከተማዋ ተከስቶ የነበረው የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት በፌዴራል መንግሥት እገዛ ችግሩ መፈታቱን አቶ አታኽልቲ ገልጸዋል።የዋጋ ንረት ችግር እንዲፈታም ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ “የህግ የበላይነት ለሀገራዊ ልማት” የሚል መፅሀፋቸውን ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በተገኙበት እያስመረቁ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ጠ/ሚ ዐቢይ ነገ ለኢጋድ ሀገራት መሪዎች ሪፖርት እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል!

የኢጋድ ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ነገ በጅቡቲ ይካሔዳል፡፡የኢትዮጵያን ውስጣዊ ጉዳይ ጨምሮ የኬንያ እና ሶማሊያ አለመግባባት ዋነኛ የውይይት አጀንዳዎች ይሆናሉ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ 469 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 1294 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 313 የላቦራቶሪ ምርመራ 469 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 119 ሺህ 494 ደርሷል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 1294 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 102 ሺህ 153 ሆኗል።ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 846 ደርሷል።በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 15 ሺህ 493 ሰዎች መካከል 258 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በ2019/20 በጀት ዓመት ከግማሽ ቢሊዮን በላይ ብር ማትረፉን አስታወቀ።

ባንኩ 11ኛ የባለአክስዮኖች ጉባኤውን በአዲስ አበባ በማካሄድ ላይ ይገኛል። የባንኩ ሊቀመንበር ዶክተር ሰውአለ አባተ በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት ባንኩ እየተጠናቀቀ ባለው የፈረንጆቹ 2019/20 በጀት ዓመት 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ገቢ ያገኘ ሲሆን  ከታክስ በፊት 582 ሚሊዮን ብር  ትርፍ አግኝቷል።

ባንኩ በተያዘው ዓመት ያስመዘገበው ትርፍ ባሳለፍነው ተመሳሳይ  ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ43 ሚሊዮን ብር ገደማ ቅናሽ ማሳየቱን ከባንኩ ዓመታዊ ሪፖርት ተረድተናል።ባንኩ ለደንበኞቹ ያበደረው መጠን እስከያዝነው በጀት ዓመት ድረስ 11 ነጥብ 57 ቢሊዬን ብር የደረሰ ሲሆን የወጪ እና ገቢ ንግድ፣ ኮንስትራክሽን ፣ የአገልግሎት ዘርፍ እና የአገር ውስጥ ንግዶች ባንኩ ብድር የሰጠባቸው የስራ ዘርፎች ናቸው።

የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ መጠን አሁን ላይ 14 ቢሊዮን ገደማ ብር የደረሰ ሲሆን በተያዘው ዓመት 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን የባንኩ ዓመታዊ ሪፖርት ያስረዳል።ባንኩ እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት 440 ነጥብ 3 ሚሊዮን የተጣራ ትርፍ ያገኘ ሲሆን 270 ሚሊዮን ብሩን ለባለአክስዮኖች እንደሚያከፋፍል ቀሪውን ብር ደግሞ ወደ መጠባበቂያ ቋቱ እንደሚያስገባ ገልጿል።ከ11 ዓመት በፊት የተመሰረተው ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ 242 ቅርንጫፎች ፣810 ሺህ ገደማ ደንበኞች እንዲሁም 15 ሺህ ባለአክስዮኖች ያሉት የግል ባንክ ነው።

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል መንግሥት በመተከል የሚፈጸመውን ጥቃት ለማስቆም ለፌዴራል መንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን አስታወቀ!

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ዘርን መሠረት ያደረገ ጭፍጨፋ፣ የፌዴራል መንግሥት ሥራ በዝቶበት ከሆነና ማስቆም ካልቻለ፣ የአማራ ክልል መንግሥት ጥቃቱን ለማስቆምና ሕግ ለማስከበር ዝግጁ መሆኑን ገልጾ፣ ይሁንታን ለማግኘት ሐሳብ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡‹‹በመተከል ዞን እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ የቤንሻንጉል ክልል ባለሥልጣናት ቀን ቀን ስብሰባ ላይ ከእኛ ጋር ሲላቀሱ ይውላሉ፡፡ ማታ ማታ ግን ግድያውን ማስቆም አልቻሉም፤›› በማለት የተናገሩት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ናቸው፡፡

በመተከል ዞን በአማራ ተወላጆች ላይ ዘር እየተመረጠ በየትኛውም ዓለም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ዘግናኝና ጭካኔ በተሞላበት ድርጊት ሰዎች ሲገደሉ፣ የፌዴራል መንግሥት ግዴታና ኃላፊነቱን ካልተወጣ የአማራ ክልል የፀጥታ ኃይል ዝግጁ እንደሆነ ኮሚሽነር አበረ ለሪፖርተር ገልጸዋል።ኮሚሽነሩ የችግሩን ቀጣይነት አስመልክተው ሲያብራሩ፣ ከአካባቢው አመራሮች ጋር በተደጋጋሚ ውይይት የተደረገ ቢሆንም፣ ‹‹የችግሩ መንስዔዎች ቀን ቀን አብረውን ስብሰባ ላይ ሲላቀሱ ውለው፣ ማታ ግድያውን ማስቆም የተሳናቸው የሕወሓት ርዝራዦች ናቸው፤›› ብለዋል።‹‹አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች የሚገደሉት አማራ ተብለው ስለሆነ ምናልባት የፌዴራል መንግሥት ሥራ በዝቶበት ከሆነ፣ ለእኛ ይስጠን ብሎ ክልሉ ለፌዴራል መንግሥት ሐሳብ አቅርቧል፤›› ሲሉ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

አንድ ክልል የራሱን የፀጥታ ችግር ማስከበር ካልቻለ የፌዴራል መንግሥት ኃላፊነትና ግዴታ አለበት ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ‹‹አቅጣጫ ያስቀምጥልን፣ ሕዝባችን እንታደግ፤›› ሲሉም የፌዴራሉን መንግሥት ጠይቀዋል።‹‹እንደ ክልል ልናደርግ የምንችለው ወደ ፌዴራል መንግሥት አቤት ማለት ነው፡፡ ነገር ግን አሁንም በአማራ ክልል በኩል የሕዝብን ደኅንነት ለማስጠበቅ ዝግጁ ነን፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡የፌዴራል መንግሥት ከፈቀደ ‹‹የአማራ ክልል የአቅም ውስንነት የለበትም›› ያሉት ኮሚሽነር አበረ፣ በሕወሓት ኃይሎች ላይ እንደተደረገው ዘመቻ ከመከላከያ ጋር በመሆን ሥራውን ለማከናወን ፍላጎት እንዳለ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም በአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማንም ይሁን ማን፣ በየትኛውም ቦታ እኩል የመኖር መብት አለው ብለዋል። ‹‹ነገር ግን በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ ያሉ የወያኔ ተላላኪዎች ሰው ሲገደል ከመከላከል ይልቅ፣ ለምን ተገደለ ብላችሁ ጠየቃችሁን ብለው ያኮርፋሉ፡፡ እንዲህ ዓይነት አካላት የተሰባሰቡበት የአመራር ቡድን በመሆኑ የሰውን ሕይወት ለመታደግ ሲሠሩ አይታዩም፤›› ብለዋል።የአማራና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በጉዳዩ ላይ እየመከሩ እንደሆነ የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ ‹‹ለችግሩ መፍትሔ ያመጣሉ ብለን እናስባለን፡፡ ነገር ግን እንደ ክልል የፀጥታ ኃይል ትዕዛዝ እየተጠባበቅን እንገኛለን፤›› ብለዋል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህንጻ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ!

ስድስት ኪሎ አካባቢ 1.8 ቢሊዮን ብር ለሚገነባው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህንጻ ግንባታ የመረተ ድንጋይ ተቀመጠ።የመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጥ ፕሮግራም ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ፣ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ጌዛሊ አባሲማል እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።አዲስ የሚገነባው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህንጻ 13 ወለሎች የሚኖሩት ሲሆን ለግንባታው 1.8 ቢሊዮን ብር መመደቡን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል በ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር 14 የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ነው፡፡

በመጭዎቹ ሦስት ዓመታት በክልሉ ዝናብ አጠር እና ደረቃማ አካባቢዎች የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች እደሚገነቡ ነው የተገለፀው፡፡ በአማራ ክልል መካከለኛ ከተሞች እና የገጠር ቀበሌዎች ያለውን የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ለማሳደግ ያስችላል የተባለለት ይህ ፕሮጀክት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ በሰሜን ወሎ፣ ማዕካላዊ ጎንደር፣ ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሽዋ ዞኖች እንደሚገነባም ታውቋል፡፡

የዚሁ ፕሮጀክት አካል የሆኑት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አስ ከተማ እና በሰሜን ወሎ ዞን ሰኞ ገበያ የሚገነቡት የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ግንባታ የፊርማ ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል፡፡

የግንባታ ውሉ የፊርማ ሥነ ሥርዓትም በፕሮጀክቱ አስፈፃሚ የአማራ ክልል ውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ እና በሚገነባው የጢስ እሳት ኮንስትራክሽን ድርጅት መካከል ተካሂዷል፡፡14ቱ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች በአየር ንብረት አይበገሬነት የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ፕሮግራም የሚከናወኑ ናቸው ያሉት የአማራ ክልል ውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ ኀላፊ ማማሩ አያሌው (ዶክተር) ግንባታቸው በመጨዎቹ ሦስት ዓመታት ይጠናቀቃል ብለዋል፡፡

[AMMA]
@YeneTube @FikerAssefa
ስልጤ መስጅድ ጀርባ በፈነዳ ቦንብ የ3 ጎዳና ተዳዳሪዎች ህይወት አለፈ!

በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ስልጤ መስኪድ ጀርባ በፈነዳ ቦንብ የሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ቦንቡ ዛሬ ከጠዋቱ 2፡30 ላይ ነው ለልማት ተብሎ በፈረሰ ክፍት ቦታ ላይ የፈነዳው፡፡የእጅ ቦንቡ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ተጥሎ የተገኘ ነው ያለው ኮሚሽኑ በፍንዳታው ምክንያት የሶስት ጎዳና ተዳዳሪዎች ህይወት ማለፉንና አምስት ሰዎች መጎዳታቸውን አስታውቋል።

ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ ያለው የምርመራ ሂደት እየተጣራ ነው ያሉት የኮሚሽኑ የልዩ ልዩና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር አለማየሁ አያልቄ የምርመራ ውጤቱ እንደተጠናቀቀ ለህብረተሰቡ ይፋ ይደረጋል ብለዋል።በተለያዩ ቦታዎች እንደ አልባሌ በሚጣሉ ቦንቦችና ፈንጂዎች ንፁሀን ሰለባ እየሆኑ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ህብረተሰቡ ምንነታቸው ያልታወቁ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ከመነካካት በመቆጠብ ለሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት እንዲጠቁም አሳስበዋል።ከአሁን ቀደም አደዋ ድልድይ አካባቢ መሰል ጉዳቶች ማጋጠማቸው የሚታወስ ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የህወሓት አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ 10 ሚሊዮን ብር ሽልማት ማዘጋጀቱን የመከላከያ ሠራዊት አስታወቀ። ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ እንደተናገሩት የጁንታው አመራሮችን በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ሽልማቱ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።በዚህም የመከላከያ ሠራዊት የህወሓት ጁንታ አመራሮች ያሉበትን ቦታ ለጠቆመ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት እንደሚሰጥ አመልክተዋል፡፡…
ተፈላጊ የህወሓት አባላት የተደበቁበትን ጥቆማ ለሚያደርሱ ዜጎች ስልክ ቁጥሮችን የመከላከያ ሰራዊት ይፋ አድርጓል።

ተፈላጊ የአማፂው አባላት ያሉበትን ለጠቆመ 10 ሚሊየን ብር የማበረታቻ ሽልማት መዘጋጀቱን የመከላከያ ሰራዊት የህብረተሰብ መረጃ ዋና መምሪያ ማስታወቁ የሚታወስ ነው።ጠቋሚዎች ማንነታቸው እንደማይገለፅ የመከላከያ ሰራዊት አስታውቋል።በመሆኑም ዜጎች ጥቆማ የሚያቀርቡባቸው የስልክ ቁጥሮችም 09 43 47 13 36 ወይም 012 5 50 43 48 ናቸው።

@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአፍሪካ ህብረት ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ለወሰደችው የህግ ማስከበር ዘመቻ እውቅና ሰጠ!

የህብረቱ ሊቀመንበር ሙሳፋቂ መሃመድ በኢጋድ ድንገተኛ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የሀገርን አንድነትና ሰላምን ለማስጠበቅ እንዲሁም ህገ መንግስትን ለማስከበር ማንኛውም ሀገር ቢሆን የሚወስደው እርምጃ እንደሆነ ተናግረዋል።ነገር ግን እርምጃውን ተከትሎ የሰብዓዊ ቀውስ መድረሱ እንደማይቀር ያልሸሸጉት ሊቀመንበሩ የኢጋድ አባል ሀገራት ትብብርና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል ለሚገኙ ጤና ተቋማትከ16 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያዎች ተሰራጭተዋል።ጤና ሚኒስቴር ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የተለያዩ መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያዎች በትግራይ ክልል ለሚገኙ ለተለያዩ ጤና ተቋማት በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በኩል ማሰራጨቱን አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ትላንት ጠዋት በመኪና ላይ ተጠመደ ቦንብ ፈንድቶ ዘጠኝ ሰው መሞቱን አሶሴትድ ፕሬስ ዘግቧል።

20 ሰው የቆሰለ ሲሆን ከቁሰሉት ሰዎች መሀል ካሀን መሀመድ ዋርዳክ የተባሉ የሀገሪቱ
የፓርላማ አባል ይገኙበታል።
@Yenetube @Fikerassefa
ጠ/ሚ ዐቢይ የኢጋድ አባል ሀገራት መሪዎች ህግን ለማስከበር እርምጃው ህጋዊነት እውቅና መስጠታቸውን ገለፁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢጋድ አባል ሀገራት መሪዎች በትግራይ ክልል የነበረውን ህግን ማስከበር እርምጃ  ህጋዊነት በመረዳታቸው እና እውቅና መስጠታቸው ምስጋና አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ለመደገፍ ላሳዩት ተነሳሽነትም ጥልቅ ምስጋናየን አቀርባለሁ ብለዋል በትዊተር ገፃቸው ላይ።

@Yenetube @Fikerassefa
የቀድሞ ተጫዋች እና አሰልጣኝ አስናቀ ደምሴ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይፈፀማል።

ለረጅም ዓመታት በኢትዮጵያ እግርኳስ ውስጥ በተጫዋችነት በአሰልጣኝነት ሲያገለግሉ የቆዩትና በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የአሰልጣኞች ማህበር ፕሬዝደንት ሆነው እየሰሩ የነበሩት አሰልጣኝ አስናቀ ደምሴ በድንገተኛ ህመም ቅዳሜ ታህሳስ 10 ቀን 2013 ማረፋቸው ይታወቃል።

የቀብር ሥነ ሥርዓቱም ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 12 ቀን በ09:00 በቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ወዳጅ ዘመድና የስፖርት ቤተሰቡ በተገኘበት ግባዐተ መሬታቸው እንደሚፈፀም ታውቋል።

Via AAFF
Photo: Soccer Ethiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በትግራይ ክልል በግጭት ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ማኅበሩ በትግራይ ክልል ከተካሄደው ህግ የማስከበር ዘመቻ ጋር በተያያዘ ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው 2 ሺህ ዜጎች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ልዩ ልዩ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል፡፡ብርድ ልብስ፣ ምንጣፍ፣ የመመገቢያ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና መሠረታዊ መድኃኒት ማህበሩ ካደረጋቸው ድጋፎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ማህበሩ ከዓለም ዓቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና እርዳታ፣ የአምቡላንስ አገልግሎት፣ የተጠፋፉ ቤተሰቦችን የማገናኘት፣ የተለያዩ የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፎችን አድርጓል፡፡ማኅበሩ በመቐለ ከተማ ተፈጥሮ የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውሀ እጥረት ተከትሎ ለከተማዋ ነዋሪዎች የመጠጥ ውሀ ድጋፍ ማድረጉን ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኤልሻዳይ ድርጅት ታቅፈው የነበሩ ወጣቶች ወደ አዲስ አበባ እየፈለሱ ነው!

በኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዲቨሎፕመንታል አሶሴሽን ከጎዳና ላይ ተነስተው በአፋር ክልል ካምፕ ውስጥ ከ2007 ጀምሮ ሲኖሩ የነበሩ ወጣቶች ከመስከረም ወር ጀምሮ ክፍያ እንዳልተከፈላቸው እና ለችግር እና ለረሀብ በመጋለጣቸው ወደ መሐል ከተማ እየመጡ እንዳሉ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸዉ የአይን እማኞች ተናገሩ።ታህሳስ ሁለት 2013 24 የሚሆኑ ወጣቶች በአዲስ አባባ ሠራተኛና ማኅበራዊ በኩል መቆያ ቦታ እንደተሰጣቸው እና አሁን ደግሞ 22 የሚሆኑ ወጣቶች መጥተው በጎዳና ላይ እንዳሉ ሌሎችም እየመጡ እንደሆነ አዲስ ማለዳ ካየቻቸው ማስረጃዎች ለማወቅ ችላለች።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa