ከትናንት ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘው የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስበስባውን ከትናንት ጀምሮ እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡ዛሬም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከሩን ቀጥሏል፡፡ ኮሚቴው በተለያዩ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል፤ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል ተብሎ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከብልፅግና ፓርቲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa

እናት ባንክ ተቀማጭ ገንዘቤ 8.4 ቢሊዮን ብር ደርሷል አለ፡፡
በ2012 በጀት ዓመት ከባንኩ አስቀማጭ ደንበኞች ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ሴቶች ናቸው ተብሏል፡፡የእናት ባንክ አጠቃላይ ሀብቱ 11.2 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተሰምቷል፡፡
ባንኩ ለወለድ 656 ሚሊዮን ብር ክፍያ ፈፅሟል፡፡የባንኩ ጠቅላላ ወጭ 1.09 ቢሊዮን ብር መሆኑ በ7ተኛው ዓመታዊ ሪፖርት ተመልክቷል፡፡በበጀት ዓመቱ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 1.4 ቢሊዮን ብር ደርሷል መባሉን ተሰምቷል፡፡
[Sheger FM]

ከታገዱት ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የትራንስ ኢትዮጵያ ንብረት የሆኑ ለስራ ወደ ጂቡቲ የተጓዙ እና ወደ ሀገር ቤት ሳይመለሱ የቀሩ 179 የደረቅ ጭነት ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን እና አራት የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ /ቦቴ/ ከጅቡቲ ለመመለስ ውይይት ተካሄደ፡፡
ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እነዚህ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ እና የህዝብን ጥቅም ለማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ ጂቡቲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ከጂቡቲ መንግስት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ዐቃቤ ህግ እና የፖሊስ ተቋማት የበላይ አመራሮች ጋር የተሳከ ውይይት ማድረጉን አስታውቋል፡፡
ተሽከርካሪዎቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ቤት እስከሚመለሱ ድረስ የኢትዮጵያ መንግስት ከጂቡቲ መንግስት ጋር በመተባበር ጠንካራ ጥበቃ እያደረገላቸው መሆኑን በውይይቱ የተሳተፉት የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በወንጀል የተገኙ ሃብቶች ማስመለስ ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ አለም አንተ አግደው ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም ወደ ሀገር ለመመለስ የተደረገው ጥረት ከህዝብ አገልጋይነት ስሜት በተቃረነ ሁኔታ የህወሓት አባል እና የቀድሞ ታጋይ የነበሩት የተሽከርካሪዎቹ ሾፌሮች ተሽከርካሪዎቹን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመሆን ተልዕኮው እንዳይሳካ ጥረት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
ሆኖም ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና ጂቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከጂቡቲ መንግስት ጋር በጋራ በመሆን ተሽከርካሪዎቹን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ተገቢውን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ባለፈው ወር ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በተለያዩ የወንጀል ተግባር ውስጥ ተሳትፈዋል በሚል በተጠረጠሩ ድርጅቶች ላይ የንብረት እገዳ እንዲጣል ማድረጉ ይታወሳል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በውስጡ ለተፈጠረው የድርጅት የባለቤትነት ጥያቄ ላይ ዛሬ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሸገር ዘግቧል፡፡
ይሁንና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) የእነ ዳውድ ኢብሳ ቡድን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በፓርቲው አመራር አባላት አቤቱታ ላይ ለመወሰን ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ውድቅ ማድረጉን ማስታወቁ ይታወሳል።
@YeneTube @FikerAssefa
ይሁንና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) የእነ ዳውድ ኢብሳ ቡድን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በፓርቲው አመራር አባላት አቤቱታ ላይ ለመወሰን ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ውድቅ ማድረጉን ማስታወቁ ይታወሳል።
@YeneTube @FikerAssefa
የቡሩንዲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ፒየር ቡዮያ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን የአጎታቸው ልጅና የዲፕሎማቲክ ምንጮች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።የ71 አመቱ የቀድሞ መሪ በፓሪስም ህይወታቸው እንዳለፈ ተገልጿል።በመፈንቅለ መንግሥት ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዚዳንት ቡሩንዲን ለ13 አመታትም ያህል መርተዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ተቋርጦ የነበረው ከአዲስ አበባ - ባሕር ዳር የአየር በረራ ነገ ይጀምራል፡፡
በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ የአዲስ አበባ - ባሕር ዳር የአየር በረራ ከኅዳር 06/2013 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ ነበር፡፡
በመሆኑም አየር መንገዱ ነገ ታኅሣሥ 10/2013 ዓ.ም ጀምሮ የአየር በረራ አገልግሎት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድና ኤርፖርቶች ድርጅት የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ኀላፊ አዋጁ ባዘዘው አስታውቀዋል፡፡
ደንበኞች የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያን በመጠቀም ወይም ወደ 6787 ደውለው ትኬት በመቁረጥ ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን እንዲቆጥቡም ኀላፊው መክረዋል፡፡

በሱማሌ ክልል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት አለፈ!
በሱማሌ ክልል ሲቲ ዞን በህገ-ወጥ መንገድ ሰዎችን ጭኖ ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲጓዝ በነበረ የሚኒባስ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ23 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደረሰ::አደጋው የደረሰው ትላንት ከለሊት 9 ከ30 ገደማ በሱማሌ ክልል ሲቲ ዞን ከለበዴ ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ጅቡቲ በሚወስደው ፈጣን መንገድ ላይ የሚኒባስ ተሽከርካሪ 32 ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ወደ ጂቡቲ ለማሻገር ጭኖ ሲጓዝ በተጠቀሰው ስፍራ የኋላ ጎማው በመፈንዳቱና ተሽከርካሪው በመገልበጡ ነው፡፡በዚህም ሹፌሩን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በ23 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል::ጉዳት የደረሰባቸው ተጎጂዎች በድሬደዋ ድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ከድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኤርትራ ከተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች ወታደራዊ ዕርዳታ እንዳገኘች ተመድ ለጸጥታው ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት ማሳወቁን ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡13 የኤርትራ አየር ሃይል እና ባሕር ሃይል አባላት ከ5 ዐመታት በፊት በኢምሬትስ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ሥልጠና አግኝተዋል፤ ኢምሬቶች በአሰብ ወደብ ወታደራዊ ጦር ሠፈር እየገነባች እንደሆነም በሳተላይት መረጃዎች ተደርሶበታል- ብሏል ሪፖርቱ፡፡ ኤርትራ ባለፈው የፈረንጆች ዐመት ከሩሲያ፣ ቼክ እና ጣሊያን ወታደራዊ ኩባንያዎች ጭምር ድጋፍ ሳታገኝ እንዳልቀረች ተገልጧል፡፡ ወታደራዊ ድጋፎቹ ጸጥታው ምክር ቤት በሀገሪቱ ላይ የጣለውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንደሚጥሱ ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
በባዕከር፣ በሁመራና በቃፍታ አካባቢዎች የሚሊሻ ዋና አስተባባሪ በነበረበት ወቅት በንጹሃን ላይ ግፍ ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጠረ የሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ግለሰብ በሽሬ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አስታወቀ።
የ5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር የብረት ለበስ አዛዥ ሻምበል አማኑኤል በለጠ ለኢዜአ እንደተናገሩት እንኳአየነው መሰለ የተባለው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር የዋለው ተፈናቃይ በመምሰል በሽሬ ከተማ ሲንቀሳቀስ ነው።ግለሰቡ በባዕከር፣ ሁመራና ቃፍቲያ አካባቢ የሚሊሻ ጽህፈት ቤት ሃላፊና የፀጥታ ዘርፍ አስተባባሪ በመሆን የጁንታው የጥፋት ተልዕኮ ሲያስፈጽም መቆየቱንም ነው የገለጹት።
የህወሃት ጁንታ በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ አራት ቀናት ቀደም ብሎ “ሰራዊቱ በወለጋና በትግራይ ክልል ጭፍጨፋ እያካሄደ ነው” በሚል የሀሰት መረጃ በማሰራጨት የጥፋት ቅስቀሳ ሲያካሂድ እንደነበርም ተናግረዋል።የጁንታውን ሚሊሻዎች በማስተባበር መከላከያ ሠራዊቱ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም በማድረግ ረገድም ጉልህ ሚና እንደነበረውም ጠቁመዋል።በክፍለጦሩ የሁለተኛ ብርጌድ አባል ሃምሳ አለቃ ምህረት ደምሌ በበኩላቸው ተጠርጣሪው ከዚህ ቀደም ስልጣኑን በመጠቀም በተለይ አማራ ተወላጆች ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጭቆና ሲፈፅም መቆየቱን ተናግረዋል።
“የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ መለያን ለብሳችኋል እንዲሁም ‘የእገሌን’ ሙዚቃ አዳምጣችኋል” በሚል ምክንያት በንጹሃን ላይ የሰባዊ መብት ጥሰት በመፈጸም የሚፈለግ ተጠርጣሪ መሆኑንም ነው የተናገሩት።በአካባቢው የተለያዩ የፍተሻ ጣቢያዎችን በማቋቋም የሀገር መከላከያ ሰራዊት መደበኛ እንቅስቃሴን ሲያስተጓጉል መቆየቱንም ጠቅሰዋል።ሻምበል አማኑኤል እና ሃምሳ አለቃ ምህረት ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር በማዋል ረገድ የአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።የአካባቢው ማህበረሰብ በቀጣይ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ በሚደረገው ጥረት ላይ የተለመደ ትብበሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ለ6 ሺህ 284 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 544 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ባወጣው እለታዊ መረጃ 1 ሺህ 108 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውንም አስታውቋል።
እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ ምክንያት 12 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
እስካሁን ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች 96 ሺህ 307 ሲደርሱ 1 ሺህ 843 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
አሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች 16 ሺህ 331 ሲሆኑ 261 ደግሞ በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡

👆👆
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራር አባላት መካከል የተፈጠረ አለመግባባትን አስመልክቶ የተሰጠ ውሳኔ

የባህርዳር ከተማ አውሮፕላን ማርፊያ ስያሜ ተቀየረ!
ባለፉት ዓመታት "የባህርዳር ግንቦት 20 ኤርፖርት" ተብሎ ይጠራ የነበረው የባህርዳር አውሮፕላን ማርፊያ "የባህርዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ኤርፖርት" ተብሎ እንዲጠራ መወሰኑ ተገልጿል።የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ ስያሜው ከ1983 ዓ.ም በፊትም ይጠራበት እንደነበር በማስታወስ እንዲሁም የህዝቡን ፍላጎትና የከተማውን ወካይ ስያሜ በመምረጥ ስሙ እንዲቀየር በሙሉ ድምፅ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል።ተቋርጦ የነበረውም የአውሮፕላን ትራንስፖርት ከነገ ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ አገልግሎት እንደሚጀምር ነው አስተባባሪ ኮሚቴው የገለፀው ሲል የከተማውን ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ጠቅሶ አብመድ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቶ ተሊላ ዴሬሳ የሚመራው የሰራተኛ ማህበር ሰራተኛውን ወክሎ ከየትኛወም አካል ጋር አንዳይደራደር በፍርድ ቤት ታገደ ።
የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርም አቶ ተሊላ ለሚመሩት የሰራተኛ ማህበር የ50+1 እውቅና ሰርተክፌት ያለበቂ መረጃ ሰጥቷል በሚል ክስ ቀረቦበታል።
በካፒቴን የሺዋስ ፈንታሁን የሚመራው የኢትዪጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር ለቂርቆስ ምድብ 2ኛ ፍትሀብሔር ችሎት ባስገባው ክስ ወረቀት መሰረት ፤ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ ተሊላ ዴሬሳ ለሚመሩት ለቀዳማዊ የአየር መንገድ መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር የ50+1 ወይንም የአየር መንገዱ ከግማሽ በላይ ሰራተኛ በአባልነት እንደያዘ በማድረግ የእውቅና ሰርትክፌት ያለ በቂ መረጃ ሰጥቷል በዚህም የአየር መንገድ ግሩፕ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበሩን ጉድቶታል በሚል ክስ ቀርቦበታል።
ፍረድ ቤቱም ቀዳማዊ ሰራተኛ ማህበሩ ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪሰጥ ድረስ ሰራተኛውን ወክሎ ከየትኛውም አካል ጋር አንዳይደራደር አግዷል።
ለታህሳስ 15,2013 በጉዳዩ ላይ የክርክር መልስ ለመስማት ቀጠሮ ይዟል።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ መሰረታዊ እና ቀዳማዊ የሚባሉ ሁለት የሰራተኛ ማህበር ሲኖሩ በዚህ ጉዳይ ከሳሽ ሆኖ የቀረበው መሰረታዊው ማህበር በአግባቡ ተደራጅቼ እንዳልሰራ በአየር መንገዱ አስተዳደር በደል ይደርስብኛል የሚል አቤቱታ በተደጋጋሚ ጊዜ ማንሳቱ ይታወሳል።
Via Fidel Post

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የቀድሞ የደርግ ባለስልጣኖችን የሞት ፍርድ ወደ እድሜ ልክ እስራት እንዲሻሻል ወስነዋል።
ጠቅላይ አቃቤ ህግ በየግማሽ አመቱ የሞት ፍርድ የተወሰነባቸውን ሰዎች ዝርዝር ለርዕሰ ብሔር የሚልክበት አሰራር እንዳለ ይታወቃል። በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ 241 የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ሰዎች አሉም ተብሏል።
ፕሬዚዳንቷ በዚህ ዙር የቅጣት ማሻሻያ ካፀደቁላቸው ሰዎች መካከል የቀድሞ የደርግ ባለስልጣኖች የነበሩት ኮ/ል ብርሃኑ ባየህ እና ሌ/ጄ አዲስ ተድላ ይገኙበታል ።የኢህአዴግ ሰራዊት ሀገሪቱን ሲቆጣጠር በጣሊያን ኤምባሲ መኖር የጀመሩት የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ኮ/ል ብርሃኑ እና የቀድሞ ኢታማዦር ሹም ሌ/ጄ አዲስ በደርግ ጊዜ ለተገደሉ ሰዎች ተጠያቂ ሆነው በሌሉበት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ነበር።
ፕሬዝዳንቷ የቅጣት ማሻሻያ ደብዳቤውን ከአንድ ወር በፊት መፈረማቸውን የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ፕሮቶኮልና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ፍቃዱ ሶቦቃን ጠቅሶ ፎርቹን ዘግቧል።

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐግብሮች ሲያስተምራቸው የነበሩ ተማሪዎቹን አስመረቀ፡፡
ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት ያስመረቃቸው ተማሪዎች ቁጥር 1 ሺህ 300 ተማሪዎች ናቸው፡፡
ከዚህ ውስጥ 1 ሺህ 228 በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን 70 በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም ሁለት ተመራቂዎችን በሶስተኛ ዲግሪ አስመርቋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት ያስመረቃቸው ተማሪዎች ቁጥር 1 ሺህ 300 ተማሪዎች ናቸው፡፡
ከዚህ ውስጥ 1 ሺህ 228 በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን 70 በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም ሁለት ተመራቂዎችን በሶስተኛ ዲግሪ አስመርቋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
በቡራዩ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ግምቱ 10 ሚሊየን ብር የሆነ ንብረት ወደመ!
በቡራዩ ከተማ ትናንት ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ ግምቱ 10 ሚሊየን ብር የሆነ ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።አደጋው የደረሰው በቡራዩ ከተማ ገፈርሳ ኖኖ ቀበሌ ልዩ ስሙ ገብርኤል በሚባል አካባቢ ሲሆን በ16 ሱቆች፣ በ3 መኖሪያ ቤቶችና 3 ባርና ሬስቶራንቶች ላይ ቃጠሎ ደርሷል።
የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በአደጋው 10 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።“እሳቱ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያስከተል በመቆጣጠር 25 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏል” ብለዋል።
በአደጋው በሰው ላይ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰ ጠቁመው፤ እሳቱን ለመቆጣጠር ከአንድ ሰዓት ተኩል በላይ ጊዜ መውሰዱን ተናግረዋል።እሳቱን በማጥፋት የኮሚሽኑ ሰራተኞች፣ የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ አካላትና የአካባቢው ነዋሪዎች መሳተፋቸውንም ገልጸዋል።የአደጋው መንስዔ ገና እየተጣራ ሲሆን ህብረተሰቡ ለእሳት አደጋ መንስዔ ከሆኑ ተቀጣጣይ ነገሮች እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል።
[ENA]

ላለፋት ሁለት ቀናት ስብሰባውን ሲያካሂድ የነበረው የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን አጠናቀቀ።
ከብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ!
የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከታህሳስ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየዉን መደበኛ ስብሰባ አጠናቋል፡፡
ኮሚቴዉ በሰላም፣ በልማት፣ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና መጪዉን አገራዊ ምርጫ በተመለከቱ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት ተወያይቶ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡
በዋናነት ባለፉት ሁለት አመታት ተኩል በአገራችን የታየዉ ለዉጥ በርካታ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፈተናዎችን ተጋፍጦ የአገራችንን ብልጽግና እዉን ለማደረግ ሰፊ እድል የፈጠረና አገራችንን ከብተና አደጋ ያዳነ መሆኑ በዉይይቱ ከስምምነት ተደርሷል፡፡
በተለይም ብልጽግና ዉሁድ ህብረ ብሄራዊ አገራዊ ፓርቲ ሆኖ መደራጀቱ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ከፍተኛ እድል ከመፍጠሩም በላይ ከአገሪቱ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ተገለዉ የዳር ተመልካች የነበሩ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማቀፍና ለማሳተፍ የቻለ የመጪዉ ትዉልድ ፓርቲ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
በአገራዊ ለዉጡ የተገኙ ድሎችን ጠብቆ በማስቀጠል ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና ማሳደግ እንደሚያስፈልግ የተገለጸ ሲሆን ለዚህም የፓርቲዉን መርሆዎች፣ እሴቶችና አሰራሮችን በጥብቅ ዲሲፕሊን ተግባራዊ ማድረግና ጠንካራ ተቋማዊ ባህል መገንባት አስፈላጊ መሆኑ ከስምምነት ተደርሷል፡፡
ኮሚቴዉ በሁለቱ ቀናት መደበኛ ስብሰባዉ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት ከተወያየ በኋላ የሚከተሉትን አቅጣጫዎች አስቀምጧል፡፡
ዝርዝሩ ከላይ የተቀመጠውን ይመስላል።