YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በዘር ጭፍጨፋ ወንጀል ሊጠየቁ ይገባል የሚል አቤቱታ ቀረበባቸው።

ከሁለት አመት በፊት የኖቤል ሰላም ሽልማት እጩ የነበረው አሜሪካዊው ኢኮኖሚስት እና አክቲቪስት ዳቪድ ስቴንማን የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተሩን
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ኢትዮጵያ ውስጥ ዜጎች በማንነታቸው እንዲገደሉና አንዲሰደዱ ይሰሩበት ከነበረው መንግስት ጋር ተባብረዋል ለዚህም ሊጠየቁ ይገባል የሚል አቤቱታ ለአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ማስገባቱን አርቲ ሚዲያ ዘግቧል።

" ዶክተር ቴድሮስ ኢትዮጵያ ውስጥ በስልጣን በነበሩበት ጊዜ የደህነንነት ተግባራት ላይ ሚና የነበራቸው ሲሆን ይሄም የሰዎች መገደል ፣መታሰርና መገረፍን " ያጠቃልል ነበር ይላል ኢኮኖሚስቱ ለፍርድ ቤቱ ያስገባው አቤቱታ ።
" በህውሃት አባልነታቸውና በከፍተኛ የመንግስት ሀላፊነታቸውን ጉልበት አንዲኖራቸው ያገዛቸው ሲሆን በዚህ ሰዎች ያለ ክስ ሲታሰሩና ወደ እስር ቤት ሲታጎሩ የእሳቸው እጅ ነበረበት " ይላል የኢኮኖሚስቱ አቤቱታ።

አቤቱታው ዶ/ር ቴድሮስ በጋራ ሲሰሩበት ከነበረ መንግስት ጋር ፈፅመዋል ይበል እንጂ በተናጥል ይሄን ወንጀል እዚህ ቦታ የሚል አቤቱታ አላቀረበባቸውም።

አቤቱታው ተቃባይነት ካገኘ ዶ/ር ቴድሮስ በስራ ላይ እያሉ በአለም ዓቀፉ የመጀመሪያው ፍርድ ቤት የቀረቡ የመጀሪያው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣን ይሆናሉ።

ይሄ የሚሆነው ግን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ ጠርቶ ያለመከሰስ መብታቸውን ካነሳ ብቻ ነው።

ዶ/ር ቴድሮስ በኢትዮጵያ በሰብአዊ መብት ረገጣ ከዚህ በፊት የቀረበባቸውን አቤቱታ ማጣጣላቸው ይታወሳል።

Fidelpost
@YeneTube @FikerAssefa
በአምስት ወራት ውስጥ 1 ቢሊዮን 356 ሚሊዮን 119 ሺ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዘዋል፡፡

የንግድ ውድድሩን ፍትሀዊ ለማድረግና የፀረ-ኮንትሮባንድ እንቅስቃሴውን ለመጣጠር የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ባደረጉት እንቅስቃሴ ባለፉት አምስት ወራት ከሀምሌ 1 ህዳር 30/2013 ዓ/ም ግምታዊ ዋጋቸው 1 ቢሊዮን 356 ሚሊዮን 118 ሺ ብር የሆነ የወጪና የገቢ ኮንትሮባንዶችን መቆጣጠር መቻሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
Audio
የፀሀይ ሪል እስቴት አልሚ ሚስተር ቼን ከቡና ባንክ የተበደርኩትን ገንዘብ የምከፍልበት የጊዜ ገደብ አላለፈም ሲሉ ለሸገር ነግረዋል፡፡

ቡና ባንክ በፀሀይ ሪል እስቴት አፓርትመንቶች ላይ የሀራጅ ሽያጭ ጨረታ ያወጣው እኔ ከሀገር እንደወጣሁ ስለ ተወራብኝ ነው ብለዋል፡፡

ሸገር በጉዳዩ ላይ ያነጋገረው ቡና ባንክ በበኩሉ ችግሩን ለመፍታት ከፀሀይ ሪል እስቴት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ቡና ባንክ ከፀሀይ ሪል እስቴት አልሚ ግማሽ ቢሊየን ብር እንደሚፈልግ ይታወቃል፡፡

ሸገር ኤፍ ኤም ሁለቱንም ጠይቆ ከላይ የተያያዘውን የድምፅ ዘገባ አሰናድቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
"በመተከል ዞን የሰው ደም በየእርሻ ማሳው እየፈሰሰ ነው" ነዋሪዎችም የድርሱልን ጥሪ እያቀረቡ ነው!

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን አሁንም ሰው እየሞተ ነው፣ መፈናቀሉም ቀጥሏል፣ ነዋሪዎቹም የድርሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው።ቀደም ሲል ቀጣናውን ለማርጋጋት ከፍተኛ የሀገርቱ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ወደ ቦታው አቅንተው ነበር፣ አካባቢው በኮማንድ ፖስት እንዲተዳደርም ተደርጓል።ይሁን እንጂ አሁንም ሞት እና መፈናቀል እየተባበሰ መምጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአብመድ ተናግረዋል።

በቡለን ወረዳ የሚኖሩ ዜጎች "የሰው ደም በየእርሻ ማሳው እፈሰሰ ነው፤ የሚመለከተው አካል ሊድርስልን ይገባል" ብለዋል።በዚህ ሁለት ቀን እንኳን ከጥቃት ለመዳን ሲሉ ከ300 በላይ ነዋሪዎች ቀያቸውን እንደለቀቁ ተናግረዋል።ነዋሪዎቹ ለአካባቢው የወረዳ አስተዳደር የድርሱልን ጥሪ ቢያሰሙም የሚመለከተው የጸጥታ አካል በፍጥነት ደርሶ ሕይወታቸውን መታደግ አለመቻሉንም ገልጸውልናል።ጉዳዩን በሚመለከት ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም እና ህዝብ ደኅንነት ቢሮ ቢደወልም ስልክ አይነሳም፡፡

[አብመድ]
@YeneTube @FikerAssefa
በማዕድንና ምርምር ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 63 ተቋማት ፈቃድ ተሰረዘ!

በማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር  በማዕድን ማምረትና  ተቋማትምርምር ላይ እንዲሰማሩ ፈቃድ ከተሰጣቸው ተቋማት ውስጥ  63  ማዕድን ማምረትና ምርምር ስራዎች ላይ የተሰማሩ ተቋማት ፈቃድ መሰረዙን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ።ሚኒስትሩ ኢ/ር ታከለ ኡማ ዛሬ እንዳስታወቁት፣ ተቋማቱ  ባሳዩት የአፈፃፀም ድክመት፣ እንዲሁም  የህዝብና የመንግስት ሀብትን ማባከናቸው በተደረገ ምርመራና ጥናት በመታወቁ፣ የተሰጣቸው ፈቃድ መሰረዙን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ተናግሯል።

@YeneTube @FikerAssefa
በተሳሳተ መረጃ በትግራይ ክልል ካሉ የስደተኞች ካምፕ የወጡ ኤርትራዊያን ስደተኞች ወደ ካምፕ እየተመለሱ ነው ተባለ!

በኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው በትግራይ ክልል በሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ የተሳሳተ መረጃ ደርሷቸው ወጥተው የነበሩ ስደተኞች ወደ መጠለያቸው መመለሳቸው ታውቋል።በትግራይ የህወሃት ቡድን በፌደራል መንግሥት መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በሽረ የስደተኞች ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤት ስር በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች በተሰራጨ የተሳሳተ መረጃ መነሻነት ቁጥራቸው ውስን የሆነ ስደተኞች ከመጠለያ ጣቢያ በመውጣት ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸው ይታወሳል።በመሆኑም የተሰራጨው መረጃ መሰረተ ቢስ በመሆኑና ስደተኛውን ለአደጋ የሚያጋልጥ ምንም አይነት የፀጥታ ስጋት ባለመኖሩ፣ እንዲሁም የስደተኞች መጠለያ በሚገኝባቸው አካባቢዎች መከላከያ ሰራዊት ተገቢውን ሰላም የማስከበር ሥራ እያከናወነ የሚገኝ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከስደተኞች ጋር በተደረሰ ስምምነት 581 ኤርትራዊያን ስደተኞች ወደ ማይ ዓይኒ እና አዲ ሓሩሽ መጠለያ ጣቢያዎች በሰላም ተመልሰዋል።በተያያዘም አስፈላጊ የሰብዓዊ አገልግሎት ግብአቶችን ለማድረስ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
አዲሱ የብር ኖት ቅየራ ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

መንግስት መስከረም 4 ቀን 2013 ዓ.ም ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 የብር ኖቶች የሚተኩ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶችና አዲሱን የ200 ብር ኖት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ይህን ተከትሎም በአሮጌው ብር የመገበያየት እና የአዲሱ የብር ኖት ቅየራ ጊዜ ገደብ ተቀምጧል፡፡በዚህም መሰረት ዛሬ አዲሱ የብር ኖት ቅየራ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል የተወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞንም እንዲደገም ተጠየቀ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ አባላት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ በአሶሳ ከተማ በተወያዩበት ወቅት ህወሓት የመተከልን የአስተዳደር መዋቅር በማፈራረስ በራሱ ቡድን ለመተካት ጥረት አድርጓል ብለዋል፡፡

በመተከል እየተፈጸመ የሚገኘው ግፍ በትግራይ ክልል በቅርቡ ከሆነው ጥፋት የማይተናነስ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ህወሓት በመተከል ባደረሰው ጥፋት ዋነኛ ተጠቂዎች ሴቶች እና ህጻናት እንደሆኑ በመጥቀስም ችግሩ በፍጥነት መቆም እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡የጥፋት ቡድኑ አመራሮችም በአስቸኳይ ለፍርድ መቅረብ እንዳለባቸው አመልክተው በትግራይ ክልል የተወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ በመተከልም እንዲደገም መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሶማሊያ ከኬንያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን ገለጸች!

ሶማሊያ በአንድ ሳምንት ውስጥ ዲፕሎማቶቿ ከኬንያ እንዲወጡ አዛለች፡፡ሀገሪቱ እርምጃውን የወሰደችው የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ወደ ናይሮቢ ማቅናታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረሥላሴ ወግደረስ የቀብር ስነ ስርዓት ነገ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገልጿል፡፡

ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ከጳጉሜን 5 ቀን 1979 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 29 ቀን 1982 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉ ናቸው።

@YeneTube @FikerAssefa
ፑቲን በመጨረሻ ለባይደን የእንኳን ደስ አሉት መልዕክት አስተላልፉ!

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጆ ባይደንን ዛሬ በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ በመሆናቸው ለጆን ባይደን ከስድስት ሳምንት በኋላ እና የምርጫ ኮሌጁ በይፋ የባይደንን አሸናፊነትን ባረጋገጠ ከአንድ ቀን በኃላ ነው የእንኳን ደስ አሉት መልዕክት ያስተላለፉት፡፡

የምርጫው ውጤት ከታወቀ በጥቂት ቀናት ውስጥ ብዙ የዓለም መሪዎች አዲስ ለተመረጡት ፕሬዚዳንት ባይደን እንኳን ደስ አሉት ሲሉ፣ ፑቲን ግን ለአሸናፊው የእንኳን ደስ አሉ መልእክት ከማስተላለፋቸው በፊት ኦፊሴላዊ ውጤቱን መጠበቁ “ትክክል” ነው ብለው በወቅቱ ተናግረዋል ብሏል ሲኤን ኤ ኤን በዘገባው፡፡ቭላድሚር ፖቲን ለተመራጮ ፕሬዝዳንት ስኬት ተመኝተዋል፡፡በዓለም ላይ በአሁኑ ወቅት እየገጠሟት ያሉትን በርካታ ችግሮች እና ተግዳሮቶች ለመፍታት ልዩነቶች አሉ፡፡

ነገር ግን ለዓለም ደህንነት እና መረጋጋት ሲባል ይህንን ልዩ ሃላፊነት የሚሸከሙት ሩሲያ እና አሜሪካ እንደሚሆኑ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ፑቲን “በእኩልነትና በጋራ መከባበር መርሆዎች ላይ የተመሠረተ የሩሲያ-አሜሪካዊ ትብብር የሁለቱም አገራት ህዝቦች እንዲሁም የመላው ዓለም ማህበረሰብ ፍላጎቶችን የሚያሟላ ነው” ብለዋል ፡፡የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን "እኔ በበኩሌ ከእርሶ ጋር ለመተባበር እና ከእርስዎ ጋር ለመገናኘት ዝግጁ ነኝ" ብለዋል ፡፡

Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ወደ ትግራይ እየተላከ ካለው ድጋፍ 70 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ እንደሆነ የውጭ ጉ/ሚኒስቴር አስታውቋል።

ዛሬ ጠዋት ለተመድ የተለያዩ ኤጄንሲዎች በትግራይ ክልል ሁኔታ ላይ ማብራሪያ መሰጠቱ ተገለጿል፡፡በዚህም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተባበሩት መንግስታትን አመስግኗል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የልደት ካርድ ለሌላቸው ተማሪዎች ሊሰጥ ነው!

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ የልደት ካርድ ለሌላቸው ተማሪዎች ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር የልደት ካርድ ሊሰጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የልደት ካርድ አገልግሎት ዘርፍ ዳይሬክተር ግርማ መኮንን እንደተናገሩት የልደት ካርድ ማለት የአንድን ግለሰብ ትክክለኛ ዕድሜ ከማወቅም በዘለለ ለአንድ አገር የተስተካከለ የሕዝብ ብዛት ለማወቅ ፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሠሩ ፣ ልጁ መብቱ እንዲከበርለት የሚያስችለው ፣ ዜግነት የሚያገኙበት መሆኑን ተናግረዋል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባህር ዳር እና መቀሌ ከተማዎች ለጊዜው ተቋርጦ የነበረውን የበረራ አገልግሎት እንደገና እንደሚጀምር ገለፀ። መንገደኞች በተለመደው መንገድ በመመዝገብ በረራዎቹን መጠቀም የሚችሉ መሆናቸውንም አሳውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👆👆

የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላን አስመልክቶ በወጣ የተዛባ መረጃ ላይ በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ ማብራሪያ

@YeneTube @FikerAssefa
ተሿሚዎች፣ ተመራጮች እና የመንግስት ሰራተኞች እስከ ታህሳስ 20/2013 ዓ.ም ሀብታቸውን ሊያስመዘግቡ እንደሚገባ የአማራ ክልል ሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል እንዲቻል ተሿሚዎች፣ ተመራጮች እና የመንግስት ሰራተኞች የሃብት ማሳወቅ እና ምዝገባ ስራ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰራ ይገኛል፡፡ እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ ከ65 ሺህ በላይ ሀብት አስመዝጋቢዎች የመጀመሪያ ደረጃ ምዝገባ ተከናውኗል፤ ከ15 ሺህ በላይ ደግሞ የዳግም ምዝገባ ተካሂዷል፡፡ሶስተኛው ዙር ምዝገባም መጀመሩን የአማራ ክልል ሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዝግአለ ገበየሁ ገልጸዋል፡፡ተሿሚዎች፣ ተመራጮች እና የመንግስት ሰራተኞች እስከ ታህሳስ 20/2013 ዓ.ም ሀብታቸውን እንዲያስመዝግቡ ኮሚሽነሩ አሳስበዋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በሳዑዲ ጊዜያዊ ስደተኛ ጣቢያዎች የታጎሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አሁንም አያያዛቸው አስከፊ እንደሆነ ሂውማን ራይትስ ዎች አስታውቋል። የስደተኛ ማቆያዎቹ በስደተኞች የተጨናነቁ ሲሆኑ፣ ጥበቃዎችም በስደተኞቹ ላይ ግርፋት፣ ግድያ እና ሌሎች የስቅየት ድርጊቶችን ይፈጽማሉ፤ ባለፉት ሁለት ወራትም 3 ስደተኞች በግርፋት ሕይወታቸው አልፏል- ብሏል ድርጅቱ በሪፖርቱ። ሳዑዲ ዐረቢያ በአስከፊ ሁኔታ የያዘቻቸውን ስደተኞች ባስቸኳይ እንድትለቅ እና እስከዚያው አያያዛቸው ሰብዓዊ ክብራቸውን በጠበቀ አኳኋን እንዲሆን ድርጅቱ በድጋሚ አሳስቧል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ አሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት አቋርጦት የነበረውን በረራ በዛሬው እለት በይፋ ጀመረ።

አየር መንገዱ በትግራይ ክልል በህወሃት ላይ ይወሰድ በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ በረራውን አቋርጦ ነበር።ይሁን እንጂ የህግ ማስከበሩ ከተጠናቀቀ በኋላ በዛሬው እለት ምሽት ከአዲስ አበባ መንገደኞችን ጭኖ የመጀመሪያ
በረራውን በማድረግ መቀሌ አሉላ አባ ነጋ ኤር ፖርት ደርሷል።በኤርፖርት ለደረሱት መንገደኞችም የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አባል ጀነራል ዮሐንስ ገብረ መስቀልና የጊዜያዊ አስተዳደሩ አስተባባሪ አቶ ሃፍታይ ገብረ
እግዚአብሔር አቀባበል አድርገውላቸዋል።መቀሌ የደረሰው አውሮፕላን ሌሎች መንገደኞችን አሳፍሮ
ምሽቱን ወደ አዲስ አበባ መመለሱ ታውቋል።የኤርፖርቱ ሰራተኞችም በሙሉ በስራ ገበታቸው ላይ የተገኙ ሲሆን፣ በቀጣይ አየር መንገዱ በቀን ሁለት ጊዜ የሚያደርገውን በረራ ይቀጥላል በመባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በደቡብ ክልል የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ፌስ ቡክ የተባለው ማህበራዊ መገናኛ ዘዴን በመጠቀም ሐሰተኛ መረጃዎችን አሰራጭተዋል ያላቸውን ሶስት ሰዎች በዘጠኝ ዓመት ፅኑ እስራት ቀጣ።

ፍርድ ቤቱ ዛሬ ባዋለው ችሎት ተከሳሾቹ እያንዳንዳቸው በዘጠኝ ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን በፍርድ ቤት የቴፒ ምድብ ችሎት አስተባባሪ አቶ ሰራዊት ደስኖ ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል ። የፅኑ እስራት ቅጣቱ የተወሰነው ያዕቆብ ተረፈ፣ ዕርቅ ይሁን መንግስቱ እና ሳሙኤል መኳንንት በተባሉ ተከሳሾች ላይ ነው። ግለሰቦቹ የእስር ቅጣቱ ሊወሰንባቸው የቻለው << የቴፒ ልጆች ብቻ >> ፣ << ለቴፒ እታገላለሁ >> እና <<ነፍጠኛው የቴፒ ጀግና በድጋሚ>> የሚል መጠሪያ ያላቸው ሀሰተኛ የፌስ ቡክ አካውንቶችን በመክፈት ያልተረጋገጡና ህዝብን የሚያሸብሩ መረጃዎችን ማሰራጨታቸው በማስረጃ በመረጋገጡ ነው ተብሏል።በመሆኑም ተከሳሾቹ የጥላቻ ንግግርና የሐሰት መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ተላልፈው ተገኝተዋል ሲል የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማስታወቁን ዶይቸ ቬለ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa