የትግራይ ክልል የኢትዮ ቴሌኮምን የመቀሌ ጠባቂ በማባረር አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረጉ በደህንነት ካሜራ በተቀረፀ ምስል ተረጋግጧል ተባለ!
የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ በጥቅምት መጨረሻና ህዳር መጀመሪያ ሳምንታት አካባቢ የስልክ አገልግሎትን በድምጽ ለመስጠት የሚያስችል ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ ተጀምሮ ነበር ብለዋል፡፡
በክልሉ የነበረውን የቴሌኮም አገልግሎት ያቋረጠው ኩባንያው ነው በሚል ሲሰጡ የነበሩ መላ ምቶች ነበሩ፡፡ አገልግሎቱ በምን ምክንያት ሊቋረጥ እንደቻለ ሳይታወቅም ቆይቷል፡፡
ሆኖም በኩባያው የተቋረጠ ነው የሚለውን መላ ምት ያስተባበሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ምክንያቱ መታወቁን ዛሬ በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ አብራርተዋል፡፡
አገልግሎቱ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም መቀሌ ስራ ላይ የነበሩትን የኩባንያውን የጥበቃ ሰራተኛ በክልሉ ልዩ ኃይል እንዲባረሩ በማድረግ ነው መቋረጡንም ነው ወ/ሪት ፍሬሕይወት የገለጹት፡፡
ይህም መቀሌ ካለው የተቋሙ የደህንነት ካሜራ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡ከደህንነት ካሜራው የተገኘው ተንቃሳቃሽ ምስል የትግራይ ልዩ ኃይል አባላትን ደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች የመስሪያ ቤቱን ጥበቃ በሃይል በማስወጣት አገልግሎቱ እንዲቋረጥ ሲያደርጉ ያሳያል፡፡ በዚህም መሰረት የክልሉ የቴሌኮም አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ፡፡
በተመሳሳይ በ14 ቀናት ውስጥ 39 ነጥብ 8 ቢሊዮን የሳይበር ጥቃቶች መፈጸማቸውንም ነው የገለጹት፡፡ ሆኖም ሀገር አቀፉን የቴሌኮም ስርጭት ለማቋረጥ በማሰብ የተፈጸሙትን እነዚህን ጥቃቶች ለማክሸፍ ተችሏል፡፡ሙከራዎቹ በሃገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የፋይናንስ፣ የትምህርት፣ የብሮድካስት እና ሌሎችንም ስርዓቶች ለማናጋት በማሰብ ጭምር የተፈጸሙ ነበሩም ብለዋል።
[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa

YeneTube
የኤርትራ ወታደሮች በትግራዩ ግጭት ተሳትፈዋል ብላ አሜሪካ እንደምታስብ ሮይተርስ ከአንድ የአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣን እና ከ5 የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ዲፕሎማቶች ሰምቻለሁ በማለት ዘግቧል።ኤርትራ ጦሯን ስለማስገባቷ የአሜሪካ መንግሥት ግንዛቤ ያገኘው፣ ከሳተላይት ምስሎች፣ ከተጠለፉ የመልዕክት ልውውጦች እና ከትግራይ ክልል ከሚወጡ ሪፖርቶች እንደሆነ ዘገባው ገልጧል።የአሜሪካ መንግሥት እዚህ ድምዳሜ ላይ ስለመድረሱ…
የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የኤርትራ ወታደሮች በትግራዩ ውጊያ ተሳትፈዋል ለሚለው ውንጀላ ማስረጃ አላገኘንም ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ ጋር በነበረን ቆይታም ስለዚህ ጉዳይ ጠይቄያቸው ነበር ያሉ ሲሆን የኤርትራ ወታደሮች ፈፅሞ ድንበር እንዳልተሻገሩ ነግረውኛል ብለዋል፣ ወታደሮቹ የነበሩት ከዚህ በፊት በሰላም ስምምነት ለኤርትራ ተወስኖ ሳለ በውዝግብ ላይ በነበሩ አካባቢዎች ነው፣ ያንን አልፎ ወደ ኢትዮጵያ መሬት የገባ አንድም የኤርትራ ወታደር እንደሌለ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ እንደነገሯቸው ገልፀዋል።

ዳግም ትኩረት ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ የጤና ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገለፀዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር የዋሉት የአምባሳደር ስዩም መስፍን የትዳር አጋር ወይዘሮ ፈለገህይወት በርሔና ልጃቸው አጋዚ ስዩም ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ከመስከረም 30 በኋላ መንግስት የለም በማለት ከህወሓት ፀረ ሰላም ቡድኖችና ከኦነግ ሸኔ አመራሮች ተልዕኮ በመቀበል በአዲስ አበባ ሁከትና አመፅ ለመቀስቀስ ገንዘብ በማሰራጨትና ወጣቶችን በመመልመል ተጠርጥረው መያዛቸውን መርማሪ ፖሊስ አስታውቋል።ተጠርጣሪዎቹ በስዩም መስፍን ስም በተመዘገበ የመንግስት ቤቶች እና በፀሀይ ሪል እስቴት ውስጥ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ላይ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ምርመራ ተደርጓል ሲል መርማሪ ፖሊስ አስረድቷል።
በተለይም በመንግስት ቤቶች በተደረገው ፍተሻ ሁለት ሽጉጦች ተገኝተዋል።እንዲሁም በፀሀይ ሪል እስቴት በሚገኝ መኖሪያ በተደረገ ብርበራ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ማግኘቱን መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል ሲልም አስረድቷል።
የአቶ ስዩም መስፍን ባለቤት ወይዘሮ ፈለገህይወት አንደኛው ሽጉጥ ባላቤቴ ራሱን የሚጠብቅበት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከውጭ ሀገር በስጦታ የተሰጠው ነው ስትል አብራርታለች።ተጠርጣሪዎቹ ዋስትና እንዲሰጣቸው የጠየቁም ሲሆን፤ ወይዘሮዋ ልጄ አጋዚ የአዕምሮ ህመምተኛ ስለሆነ መድሀኒት እንዲገባልን ስትል ጠይቃለች።ጉዳዩን የተከታተለው ችሎት ለተጨማሪ ምርመራ 8 ተጨማሪ ቀናት በመፍቀድ፣ ለፖሊስ በታሰሩበት ቦታ አስፈላጊው መድሀኒት እንዲገባላቸው አዟል።
Via FBC

አምባሳደር አዲስ ዓለም ባሌማ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ! የቀድሞው የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አዲስ ዓለም ባሌማ (ዶ/ር) በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ፡፡ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባዔ የነበሩት ኬሪያ ኢብራሂምም በቅርቡ እጅ መስጠታቸውን ያስታወሱት አምባሳደር ሬድዋን ሌሎች በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦችን…
ዶክተር አዲሳለም በፀረ-ሰላም ቡድን ተደራጅተው በመስራት ተጠርጥረው ፍረድ ቤት ቀርበዋል።
ተጠርጣሪው አምባሳደር በነበሩበት ዘመንም ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት ለማበላሸት እና ለማስቆም ተፅዕኖ ሲፈጥሩና ሲሰሩ እንደነበር መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።
በተጨማሪም የመንግስት መረጃና ሚስጥሮችን አሳልፈው ሲሰጡ እንደነበር መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አብራርቷል።
ከኦነግ ሸኔ ከፍተኛ አመራሮች ጋርም መረጃ ሲለዋወጡ እና የመንግስትን ምስጢር አሳልፈው በመስጠት ለተፈፀሙ ወንጀሎች በጋራ ሲሰሩ እንደነበር አስረድቷል።የተጠርጣሪው ጉዳይ በችሎት እየታየ ይገኛል።
[Fana]

አምሳ አለቃ ደረጀ አንበሳ በሰሜን ዕዝ የጥገና ክፍል አባል ነው፡፡ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ የአካባቢውን አርሶ አደር ማሽላ ለመቁረጥ መውጣታቸውን የሚናገረው አምሳ አለቃ ደረጀ የተመለሱት ምሽት 11 ስዓት አካባቢ እንደነበርም ነግሮናል፡፡ በስራ የዋለ እና የደከመ አካላቸውን ባሳረፉበት ሌሊትም በህገ ወጡ የትህነግ ቡድን አፈና ተፈፀመባቸው፡፡
ከአንዱ የማጎሪያ ጣቢያ ወደሌላው የማጎሪያ ጣቢያ ሲያንከራትቷቸው መሰንበታቸውን የሚናገረው አምሳ አለቃ ደረጀ በመጨረሻም አስነዋሪ ድርጊት ሊፈፅሙበት ወደአቀዱበት ቦታ 40 ኪሎ ሜትር በእግር እንዲጓዙ እንዳደረጓቸው ይናገራል፡፡
ህፃን ያዘሉ ሴቶች፣ ጓዝ የተሸከሙ ወታደሮች እና ህጻናት ያሉበት የነአምሳ አለቃ ደረጀ ታጋቾች ቡድን ቁጥራቸው 1ሺህ 200 ነው፡፡ አጋቾቹ በግራ እና በቀኝ መሳሪያ አቀባብለው ታጋቾቹን ከአስፓልት እንዳይወጡ ትዕዛዝ እየሰጡ እና እያስፈራሩ ወደፊት እንዲቀጥሉ አደረጉን ይላል፡፡
ቀኑ እየመሸ ሲመጣም መንገዳቸውን ያላቆሙት ታጋቾቹ መብራቱን ያጠፋ ሴኖ ትራክ ከኋላቸው መጥቶ ታሪክ የማይረሳው እና ትውልድ ይቅር የማይለው ድርጊት ፈፀሙባቸው፡፡ አንደበቱ እየተሳሰረ እና ዐይኑ አምባ እያቀረረ ድርጊቱን የሚገልፀው አምሳ አለቃ ደረጀ ሴኖ ትራክ ያገኘውን ተጓዥ እየጨፈለቀ ከአምሳ አለቃ ደረጀ ላይ ሲደርስ እግሩን ሰብሮ ወደገደል ገፈትሮ ጣለው፡፡
የሰሜን እዝ አባል የነበሩና ከታገቱበት የተለቀቁ 2 የመከላከያ ሰራዊት ባልደረቦች ከአብመድ ጋር ባደረጉት ቆይታ ሰዎች በሲኖትራክ ሆን ተብሎ እንዲጨፈለቁ ተደርጓል ይላሉ።
ዝርዝሩ👇👇
https://www.amharaweb.com/የሞትም-ደረጃ-አለው/

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር አባል እና ሰራተኞች የጋና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሂደትን ተከታተሉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር ፍቅሬ ገብረህይወት የተመራው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰራተኞች ቡድን ነው የጋና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሂደትን የተከታተለው።በቆይታቸውም የጋራና ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሂደትን፣ የድምጽ መስጫ ቀን የተደረጉ ተግባራትን፣ የኮቪድ ወረርሽን በመከላከል የተከናወነውን የድምጽ መስጠት ሂደት ተመልክተዋል።
እንዲሁም ምርጫን የኮቪድ ወረርሽኝ ጥንቃቄ በማድረግ ለማከናወን የተደረጉ ተግባራትን፣ የምርጫ አስፈጻሚው ተቋምን አሰራር፣ የምርጫ ክልል ደረጃ ውጤት ቆጠራ፣ ድመራ እና ይፋ የማድረግን ሂደቱንም ተመልክተዋል።
ከጋና ምርጫ ኮሚሽን አመራር አካላትም ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውነም ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ልኡካን ምርጫውን ከመታዘብም በተጨማሪ በተለይ በኮቪድ ወረርሽኝ ስጋት ውስጥ ሆኖ ምርጫ ማከናወን የሚያስፈልጉትን የበጀት እና የሎጄስቲክስ ዝግጅቶችን ከጋና ምርጫ ልምድ መቅሰም መቻላቸውንም ቦርዱ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ 526 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 1 ሺህ 731 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል!
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5 ሺህ 741 የላቦራቶሪ ምርመራ 526 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 115 ሺህ 360 ደርሷል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 1 ሺህ 731 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 88 ሺህ 975 ሆኗል።ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 779 ደርሷል።በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 24 ሺህ 604 ሰዎች መካከል 316 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 689 ሺህ 299 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

በዓለማችን ከኮሮና ተህዋሲ ወረርሽኝ ይልቅ የረሃብ ወረርሽኝ እንደሚያሰጋ የዓለም የምግብ ድርጅት በምህጻሩ WFP አስታወቀ።
ያሸነፈውን የዘንድሮውን የሰላም ኖቤል ሽልማት በቪድዮ በተካሄደ ስነስርዓት የተቀበለው WFP ረሃብ ከኮሮና ሊብስ ይችላል ያለው በዓለማችን የሚካሄዱ ጦርነቶች፣የዓየር ንብረት ለውጥ፣ ረሃብን በፖለቲካ እና በወታደራዊ መሣሪያነት መጠቀምና፣ ዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ተደማምረው ሁኔታውን በማባባስ 270 ሚሊዮን ሰዎች ወደ ረሃብ እየተጓዙ በመሆኑ ነው ብሏል፤እነዚህን ችግሮች መቋቋም አለመቻል ደግሞ የረሃብ ወረርሽኝ እንደሚያስከትል በስነ ስርዓቱ ላይ የተናገሩት የድርጅቱ ዋና ሃላፊ ዴቪድ ቢየስሊ ተናግረዋል።ረሃብን ለመከላከል የተቋቋመው ትልቁ የእርዳታ ድጅት WFP ከተመሰረተበት ከጎርጎሮሳዊው 1961 አንስቶ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን መግቧል። በጎርጎሮሳዊው 2019 ብቻ ድርጅቱ በመላው ዓለም 97 ሚሊዮን ሰዎችን መግቧል።
[DW]

በሰሜን ኢትዮጵያ ከአንድ ወር በላይ በዘለቀው ውጊያ ለተፈጸሙት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂ በሚባሉ የፖለቲካም ሆነ ወታደራዊ ባለሥልጣናት ላይ የአሜሪካን መንግሥት ማዕቀብ መጣልን እንዲያስብበት ሁለት የአሜሪካን ሴኔት አባላት ጥሪ አቀረቡ።
ዴሞክራቱ ሴናተር ቤን ካርዲንና ሪፐብሊካኑ ሴናተር ጂም ሪሽ ጥሪውን ያስተላለፉት ትናንት ባቀረቡት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ነው።በካርዲንና ሪሽ የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥትና ህወሓት፣ ግጭቱን በማቆም ለጦርነቱ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈልጉም ጥሪ አስተላልፏል።የፌደራል መከላከያ ሠራዊትና የህወሓት ኃይሎች ውጊያ ከተጀመረበት ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓም ወዲህ ይህን መሰል ጥሬ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ሲቀርብ የትናንቱ የመጀመሪያው ነው።ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያን ጠቃሚ አጋር አድርጋ ነው የምትወስደው።
ሆኖም በዚህ ጦርነት በሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች ሰላማዊ ሰዎች ተጎድተዋል መባሉ ዩናይትድ ስቴትስ ስለምትከተለው መርህ ግራ የተጋባች መስላለች።የኢትዮጵያ መንግሥት በውጊያው የተፈጸሙ ወንጀሎችን ወይም የጅምላ ግድያዎችን የተመለከቱ ማናቸውንም ዘገባዎችን በራሱ እንደሚያጣራ አስታውቋል።በተመድ ግምት በጦርነቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሳይሞቱ አልቀረም የተፈናቀሉት ደግሞ ከ950 ሺህ በላይ ይሆናሉ።ከመካከላቸው 50 ሺህ ያህሉ ሱዳን እንደሚገኙ ነው ድርጅቱን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል የዘገበው።
[Reuters/DW]

በማይጨው ከተማ በተደረገ የቤት ለቤት ፍተሻ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጦር መሳሪያዎች መገኘታቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ!
በማይጨው ከተማ በተደረገ የቤት ለቤት ፍትሻ ከ426 ሺህ በላይ የክላሽ ጥይት፣ ከ3500 በላይ የብሬን ጥይት፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ክላሽንኮቭና ሽጉጦች፣ ከ1100 በላይ ልዩ ልዩ የእጅ ቦንቦች መያዙን የመከላከያ ሚኒስቴር ለዋልታ በላከው መግለጫ አስታውቀል፡፡በዕዙ የ32ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ብርጌድ ዋና አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል መላኩ ገላነህ እንዳሉት ከሃዲውን ሃይል ለማጥፋት ከተደረገው የህግ ማስከበት ዘመቻ መጠናቀቅ በኋላ በማይጨው ከተማ በተደረገ የቤት ለቤት ፍተሻ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጦር መሳሪያዎች መገኘታቸውን አረጋግጠዋል።ከተማዎችን የጦርነት አውድማ ለማድርግና ዜጎችን ለከፋ ችግር ለመዳረግ በማለም ሰራዊት በህግ የሚከለከልባቸው ቦታዎች ተለይተው በእምነት ተቋማት፣ በመማሪያ ክፍሎች፣ በአገልግሎት መስጫ ተቋማትና በመንግስት መስሪያ ቤቶች በርካታ ቁጥር ያለው የጦር መሳሪያ ተከማችቶ መገኘቱንም ዋና አዛዡ አረጋግጠዋል።
Via Walta

በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ!
በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ደብሪያቆም ቀበሌ ልዩ ቦታው ጥዋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከመካነ ሠላም ወደ አዲስ አበባ 78171 አ.አ ኮድ 2 የሆነ ዶሊፊን መኪና ከሌሊቱ 8 ሠዓት ሠዎችን ጭኖ በመጓዝ ላይ ሣለ በደረሠበት የመገልበጥ አደጋ በ6 ሠዎች የሞት እና በ2 ሠዎች የመቁሠል አደጋ ደርሷል።
ምንጭ፡-ጎንቻ ኮሙኒኬሽን

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከታህሳስ 26 እስከ 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንደማሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ።
በቢሮው የስርዓተ-ትምህርት ፤ የትምህርት ተቋማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀሰበላ አዜን እንደገለጹት፣ ቢሮው በክልሉ በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናውን ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየሰራ ነው።
ፈተናው በ307 የክልሉ የመፈተኛ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ገልጸው፤ የትምህርት አመራሮች፣ የወረዳና የቀበሌ አመራሮችና የወላጅ ተማሪ ህብረት ተወካዮች ተፈታኝ ተማሪዎችን በስነ-ልቦና እንዲዘጋጁ በማድረግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።
አቶ ሀሰበላ አክለውም፣ በዞኑ አንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠረው የፀጥታ ችግር፣ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው ፕሮግራም መሠረት ፈተናውን ለመስጠት አስቸጋሪ እንዳይሆን ወላጆችና ተማሪዎች ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በሻሸመኔ ከተማ ተፈጥሮ በነበረው ችግር የመኖሪያ ቤታቸውን ያጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን መልሶ ማቋቋሙን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ፡፡በወቅቱ በተፈጠረው ግርግር ተቃጥለው የነበሩ ከ800 በላይ ቤቶችን መልሶ መጠገን የተቻለ ሲሆን ሙሉ በሙሉ የወደሙ 17 ቤቶችን ደግሞ እንደአዲስ መገንባት መቻሉ ተገልጿል፡፡
[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከታህሳስ 26 እስከ 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንደማሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ። በቢሮው የስርዓተ-ትምህርት ፤ የትምህርት ተቋማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀሰበላ አዜን እንደገለጹት፣ ቢሮው በክልሉ በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናውን ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየሰራ ነው። ፈተናው በ307 የክልሉ የመፈተኛ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ገልጸው፤ የትምህርት…
የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በሱማሌ ከታህሳስ 7 - 9 እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
የሱማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ መሀመድ ፋታህ እንዳሉት የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከታህሳስ 1 እስከ 30፣2013 ድረስ ተሰጥቶ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ በክልሉ የ8ተኛ ክፍል ፈተና ከታህሳስ 7 እስከ ታህሳስ 9 ለማካሄድ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ኢብኮ ዘግቧል፡፡

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይሆናሉ ተብለው የነበሩት ሱዛን ራይስ ሌላ ሹመት ተሰጣቸው
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር፣ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትርና የአሜሪካ ብሔራዊ የደህንነት አማካሪ የነበሩትን ሱዛን ኤልዛቤት ራይስን የኋይት ሀውስ የሀገር ውስጥ ፖሊሲ ምክር ቤትን እንዲመሩ መረጧቸው፡፡
በጆ ባይደን ዘመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይሆናሉ ተብሎ የተገመተ ቢሆንም ተመራጩ ፕሬዝዳንት ግን አንቶኒ ብሊንከንን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት መርጠዋል፡፡ በመሆኑም ሱዛን ሥራቸው በሀገር ውስጥ ጉዳዮች ብቻ የታጠረ እንደሚሆን ዎል ስትሬት ጆርናል ዘግቧል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ መታዘብ ሥራ መሳተፍ ለሚፈልጉ የአገር ውስጥ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥሪ አቅርቧል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢፌዴሪ ህገመንግስት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና ቦርዱን ባቋቋመው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ ምርጫ ለመታዘብ ለሚፈልጉ የአገር ውስጥ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፈቃድ ለመስጠት እና ለመከታተል የሚያስችለውን መመሪያ አርቅቆ፣ እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ወኪሎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት ያገኘውን ግብዓት በማካተት፣ የአገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች ፈቃድ አሰጣጥ እና የሥነ ምግባር መመሪያ ቁጥር 05/2012ን አፅድቋል፡፡ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ማህበራት በተቀመጠው አድራሻ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

የኢንተርናሽናል ህይወት አድን ኮሚቴ በሸሬ የስደተኞች መጠለያ አንድ ሰራተኞዬ ተገሎብኞል ብሏል።
በትግራይ ሽሬ በሚገኘው በሂትሳት የስደተኞች መጠለያ አንድ ሰራተኞዬ ተገሎብኛል ሲል በሳይኒቲስቱ አልበርት ስታይን የተመሰረተው የኢንተርናሽናል ህይወት አድን ኮሚቴ(International Rescue Committee )
የገለፀ ሲሆን ሰራተኛው በማን እንደተገደለ ያለው ነገር ግን የለም።ዝርዝር ጉዳዮችን በቅርብ ቀን እገልፃለው ሲል ኮሜቴው አስታውቋል።
[IRC/Fidelpost]

በ3 ከባድ ተሽከርካሪዎች መቐለ እየገቡ የሚገኙት የሕክምና ቁሶች ከቅዳሜ ጀምሮ መከፋፈል ይጀምራሉ ተባለ፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አርብ ታኅሣሥ 2 ‹‹በትግራይ ክልል የሰብኣዊ እርዳታ አቅርቦት›› በሚል በእንግሊዘኛ ባወጣው መግለጫ በተመሳሳይ የሕክምና ቁሶችን የጫኑ 7 ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ሽሬ እና አዲግራት ማቅናታቸውንም አሳውቋል፡፡ኅዳር 29፤ 18 ሺሕ 200 ኩንታል የምግብ እርዳታ የጫኑ 44 ከባድ ተሽከርካሪዎች ሽሬ ደርሰው ወደተለያዩ አካባቢዎች የሰብኣዊ አቅርቦት መሰራጨት መጀመሩን መግለጫው አስታውሷል፡፡
ከኅዳር አጋማሽ ጀምሮ ደግሞ የሕክምና ግብኣቶችን ጨምሮ የተለያዩ የምግብ አቅርቦቶች ወደ ዳንሻ፣ ወልቃይት፣ ቃፍታ ሁመራ እና ደባርቅ አካባቢዎች ሲሰራጩ ነበርም ነው ያለው፡፡በሰላም ሚኒስቴር የሚመራው የሰብኣዊ እርዳታ አቅርቦት አስተባባሪ ኮሚቴ የመስክ ምልከታዎችንም ጭምር በማድረግ አስፈላጊ እርዳታዎችን ለማድረስ ጥረት እያደረገ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
መግለጫው ኅዳር 20 የፌደራሉ እና የተባባሩት መንግሥታት የሰብኣዊ እርዳታን በጋራ ለማድረስ መፈራረማቸውን በማስታወስ፤ ይህም የኢትዮጵያ መንግሥት እርዳታዎች በአግባቡ እንዲደርሱ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብሏል፡፡ሆኖም በትግራይ ክልል ከተሞችና የተለያዩ አካባቢዎች ጦርነቱ ባለመብረዱ እርዳታዎች እየታገዱ ነው የሚሉ ስሞታዎች አሉ ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውሸትና ክልሉን ከሕወሓት ጥቃቶች ታድጎ ለማረጋጋት እየሰራ የሚገኘውን የመከላከያ ሰራዊት ጥረት የሚያንኳስስ ነው ሲል ተቃውሞታል፡፡
✍አሐዱ ቴሌቪዥን