በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በየሳምንቱ ለምርመራ ከሚመጡ ዜጎች ውስጥ ከ120 እስከ 150 የሚጠጉ ዜጎች በካንሰር እንደሚያዙ ነው የተገለጸው፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የካንሰር ህክምና ስፔሻሊስቱ ዶ/ር አይናለም አብርሀ ካንሰር እና የጨረር ህክምና በኢትዮጵያ ምን እንደሚመስል ማብራርያ በሰጡበት ሰአት ነው ይህንን የተናገሩት፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ የካንሰር በሽታ በጣም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደሚገኝም ነው ዶ/ር አይናለም የተናገሩት፡፡
ለዚህም እንደምክንያት ያስቀመጡት የህዝቡ የአኗኗር ሁኔታ የህክምና እጥረት እና የአመጋገብ ባህሪያችን ዋነኞቹ ምክንያት እንደሆኑ ነው የተናገሩት፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በአጠቃላይ ከሚፈጠረው የካንሰር መጠን ወደ 33 ከመቶ የሚሆነው የጡት ካንሰር እንደሆነም ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡
በሴቶች ላይ 30 ከመቶ የሚሆነው የጡት ካንሰር አንደኛ ደረጃን ሲይዝ፣ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ከዚያ ቀጥሎ ደግሞ የአንጀት ካንሰር እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡ በወንዶች ላይ ደግሞ በአንደኛ ደረጃ የትልቁ አንጀት ካንሰር፣ በሁለተኛ ደረጃ የፕሮስቴት ካንሰር እና ከተለያዪ እጢዎች የሚነሱ የካንሰር አይነቶችን ይጠቀሳሉ።
በኢትዮጵያካንሰር በርካቶችን በዋናነት ለህልፈት ከሚያበቁ ተላላፊ ያልሆኑ አራት በሽታዎች አንዱ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ይገልፃል። በሀገሪቱ ትክክለኛ ምዝገባ ባለመኖሩ ምን ያህል ሰው በካንሰር እንደተያዘ ለማወቅ አደጋች እንደሆነ ነው የተነገረው
Via EthioFM
@Yenetube @FikerAssefa

በትግራይ ክልል ሰሞኑን በተካሄደው ግጭት አራት የረድኤት ሰራተኞች ተገድለዋል ተባለ!
ሮይተርስ የዜና ወኪል ከናይሮቢ እንደዘገበው በትግራይ ክልል በተካሄደው ዉጊያ በኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ለሁለት የተለያዩ የውጭ ድርጅቶች ይሰሩ ነበር የተባሉ አራት ኢትዮጵያዊያን ተገድለዋል።ዜና አገልግሎቱ አክሎ የዕርዳታ ሰራተኞቹ መገደላቸውን ትናንት ረቡዕ ከባልደረቦቻቸዉ ከረድኤት ሰራተኞችና ከዲፕሎማቲክ ምንጮች አረጋግጫለሁ ብሏል።ሟቾቹ ኤርትራውያን ስደተኞች ከሠፈሩባቸዉ አራት ካምፖች ውስጥ በአንዱ ይሰሩ የነበረ ሲሆን የሞቱበት ሁኔታ ግን ግልፅ አለመሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡የሟቾቹ ቀጣሪዎች የሆኑት የዕርዳታ ድርጅቶች አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውንም ዘገባው አያይዞ ገልጿል።የኢትዮጵያ የፌደራል መንግስትና የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ታጣቂዎች ለ3 ሳምንት ተኩል በገጠሙት ዉጊያ ስለጠፋ ሕይወትና ንብረት በግልፅ የተነገረ ነገር የለም።የርዳታ ድርጅት ሠራተኞች ስለመገደላቸዉም ሁለቱም ወገኖች እስካሁን በይፋ ያስታወቁት ነገር የለም።
[Reuters/DW]
@YeneTube @FikerAssefa

YeneTube
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው! የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ነው እያካሄደ የሚገኘው፡፡በስብሰባው የምክር ቤቱን 6ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ እንደሚያጸድቅ…
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኑክሌርን ለሰላማዊ አገልግሎት የማዋል ስምምነት ረቂቅ አዋጅን አፀጸደቀ!
ረቂቅ አዋጁ የፀደቀው ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት እያካሄደ በሚገኘው 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ኒውክሌርን ለሰላማዊ ዓላማ የማዋል ስምምነት ረቂቅ አዋጅን የሚመለከት ነው። ስምምነቱ የዕውቀት ሽግግርን ለመፍጠር የሚያግዝ፣ ለአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ የሚያደርግ እና ይህን የሚደግፉ አሰራሮች የማበጀት ግዴታ የሚጥል ነው።በተጨማሪም አዋጁ ሀገሪቱ የሀይል አማራጭ እንዲኖራት የባለሙያወችን አቅም ለመገንባት እና ልምድ ለመለዋወጥ እንደሚረዳ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባ ያሳያል።

ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ የሚገነባው የአትክልት ተራ የገበያ ማዕከል በ 2 ሳምንታት ይጠናቀቃል ተባለ!
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ እየተገነባ ያለው የአትክልት ተራ የገበያ ማዕከል የግንባታ ሥራ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ፡፡የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ወደ አንድ ቢሊዮን ብር በሚጠጋ የኮንትራት ዋጋ እየገነባ የሚገኘውን ተለዋጭ የአትክልት ተራ የገበያ ማዕከል በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚያጠናቅቅ አስታውቋል፡፡
የገበያ ማዕከሉን በሁለት ምዕራፍ ከፋፍሎ እየገነባ የሚገኝ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ምዕራፍ 14 የገበያ ሼዶች፣ በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ የፓርኪንግና የአረንጓዴ ቦታዎች፣ መጋዘኖች፣ የአስተዳደር ህንጻዎች እና ሌሎች የግንባታ ስራዎች ይከናወናሉ።የገበያ ማዕከሉ 80 ሺ ካሬ ሜትር ቦታ ሲሸፍን፣ በመጀመሪያው ምዕራፍ የሚገነቡት 14 ሼዶች ውስጥ 588 የመገበያያ ሱቆች እንዳሏቸው የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመለክታል፡፡

ቤተ እስራኤላውያኑ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው!
ትናንት ወደ እስራኤል ያቀኑት 316 ቤተ እስራኤላውያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡ቤተ እስራኤላውያኑ እስራኤል በደረሱ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁን ጨምሮ ምክትል የደህንነት ሚኒስትሩ ጋዲ ይባርከን እና ሌሎችም ከፍተኛ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ተቀብለዋቸዋል፡፡ከአውሮፕላን በወረዱ ጊዜ ባሳዩት የተለየ የደስታ አገላለጽ መገረማቸውን የገለጹት ኔታንያሁን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክትን አስተላልፈዋል፡፡በነገው ዕለት ተጨማሪ 100 ቤተ እስራኤላውያን ይመጣሉም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፡፡ምክትል የደህንነት ሚኒስትሩ ጋዲ በበኩላቸው የረዥም ዓመታት የወሰደው ልፋት ፍሬ ማፍራቱን ገልጸዋል፡፡ከሰሞኑ ኢትዮጵያ ከነበሩት የስደተኛ እና ስደት ተመላሾች ሚኒስትሯ ፕኒና ታመነ ጋር ወደ ያቀኑት ቤተ እስራኤላውያኑ በቀጣዮቹ 2 ወራት ውስጥ ወደ እስራኤል እንደሚያቀኑ ከሚጠበቁት 2 ሺ ቤተ እስራኤላውያን መካከል ናቸው፡፡
[Al-ain]

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ አቅርቦት በነበረው የክስ መዝገብ ላይ ምስክሮችን አሰማ!
በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ዙሪያ ክስ በተመሰረተባቸው 1ኛ ጥላሁን ያሚ፣ 2ኛ ከበደ ገመቹ፣ 3ኛ አብዲ አለማየሁ፣ 4ኛ ላምሮት ከማል ላይ ዓቃቤ ህግ ምስክሮቹን ለፍርድ ቤት አሰምቷል፡፡የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የፀረ ሽብር እና ህገ-መንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ባስቻለው ችሎት ዓቃቤ ህግ ተከሳሾች በክሱ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት መፈጸማቸውን ያስረዱልኛል በሚል ያቀረባቸውን 12 ምስክሮች አሰምቷል፡፡በስተመጨረሻም ምስክሮቹን ያዳመጠዉ ችሎት የምስክሮችን ቃል መርምሮ ብይን ለመስጠት ለየካቲት 10/ 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በተከሳሾቹ ላይ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀፅ 3/2 ስር ክስ መመስረቱ ይታወሳል፡፡
[AG]

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ነገ መደበኛ ስብሰባውን ማካሔድ ይጀምራል!
የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ነገ አርብ ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም መደበኛ ስብሰባውን ማካሔድ ይጀምራል።ኮሚቴው በተለያዩ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
@YeneTube @FikerAssefa
የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ነገ አርብ ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም መደበኛ ስብሰባውን ማካሔድ ይጀምራል።ኮሚቴው በተለያዩ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው ተባለ!
ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዛሬ እንደዘገበው የዕርዳታ ቁሳቁስ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ እየተጓዙ ቢሆንም አሁንም ድረስ በአካባቢው ጦርነት መቀጠሉን ገልጿል።የዜና ምንጩ አንድ የዕርዳታ ሰራተኛን ጠቅሶ እንደዘገበዉ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በሚኖርባት መቀሌ ከተማ ደቡባዊ እና ምዕራባዊ ክፍል ዛሬም ጦርነት እየተካሄደ ነዉ።መንግስት «ሕግ የማስከበር» በሚለው ዘመቻ ከሦስት ሳምንት በላይ በተካሄደዉ ጦርነት 45 ሺህ ሰዎች ወደ ጎረቤት ሱዳን መሰደዳቸውንም ዘገባው አመልክቷል።

🔥1
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላይ ለመሠረተው ክስ፣ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሃ ብሄር ችሎት ታሕሳስ 1 ብይን ለመስጠት ዛሬ ተለዋጭ ቀጠሮ እንደሰጠ ፓርቲው በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል። ኢዜማ በከተማዋ አስተዳደር ላይ የመሠረተው ክስ፣ "የመሰብሰብ ሕገ መንግሥታዊ መብታችን ይከበር፤ ሁከትም ይወገድልን" የሚል ነው። አስተደርሩም በፖሊስ ያሳገደው የፓርቲው የውይይት ስብሰባ ሕጋዊ ፍቃድ እንዳልነበረው ጠቅሶ፤ "ጉዳዩን መመልከት ያለበትም የከተማ አስተዳደሩ ፍርድ ቤት መሆን አለበት" በማለት ባለፈው ኅዳር 22 ለክሱ ምላሽ መስጠቱ ይታወሳል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 595 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤9 ሰዎች በበሽታው ህይወታቸው አልፏል፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 522 የላብራቶሪ ምርመራ 595 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 111 ሺህ 579 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።ከዚህ ባለፈ የ9 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 724 መድረሱንም ሪፖርቱ ያመላክታል።
በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 1 ሺህ 318 ሰዎች ከኮሮና ቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 77 ሺህ 385 መድረሱም ተገልጿል።ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 652 ሺህ 517 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 111 ሺህ 579 ደርሷል።አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 32 ሺህ 468 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 317 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

❗ዛሬ በገንዘብ ሚኒስቴር አካባቢ ምንድነው የተፈጠረው?❗
👉ዛሬ ረፋድ አካባቢ ገንዘብ ሚኒስቴር በሚገኝበት ስፍራ በርከት ያሉ ሰዎች ተሰባስበው፤ እንዲሁም ፌደራል ፖሊስ እነዚህኑ ሰዎች ወደ መሥሪያ ቤቱ እንዳይገቡ ሲከላከሉ ተስተውሏል፡፡
👉ሸገር ጉዳዩ ምን ይሆን? ሲል በአካባቢው ተገኝቶ ለማጣራት ሞክሯል፡፡
👉ከ150 በላይ የሚሆኑ መኪና አስመጪዎች መኪናዎቻችን ያለ አግባብ ጨረታ እንዲወጣባቸው ተደርገዋል የሚል ቅሬታ ያላቸው ወገኖች መሆናቸውን ሰማን፡፡
👉ባለጉዳዮቹ፣ ‹‹መንግሥት ያገለገሉ መኪናዎችን ለማስመጣት በሰጠው የ6 ወር ጊዜ መሠረት መኪናዎቹን ያስመጣን ቢሆንም፤ በኮቪድ 19 መከሰትና በመርከብ ላይ በደረሰ የተፈጥሮ አደጋ የጊዜ ገደቡ ሊጓተትብን ችሏል›› ብለዋል፡፡
👉‹‹ይህን ከግምት ያላስገባው መንግሥት ዘግይተውም ቢሆን የገቡ ንብረቶቻችንን ለጨረታ እንዲቀርቡ አድርጓልና፤ ይህን ቅሬታችንን ለማሰማት ነው እዚህ የተገኘነው›› ሲሉ ለሸገር ተናግረዋል፡፡
👉በመሆኑም እነዚህ መኪኖች በመታገዳቸው ምክንያት መንግሥት እና እናንተ ምን ያህል ኪሳራ ያጋጥማችኋል? ብለን ጠይቀናቸው፣ ከ6 እስከ 20 ቢሊየን ብር ድረስ የሚጠጋ ኪሳራ ሊያጋጥም ይችላል ብለውናል፡፡
👉150 የሚሆኑት እነዚሁ መኪና አስመጪዎች ከ180 በላይ መኪኖች እንደተያዙባቸው ተናግረዋል ሲል ሸገር ኤፍ ኤም ነው።
@YeneTube @Fikerassefa

አዲስ አበባ ለጎብኚዎች ተመራጭ መዳረሻ ዝርዝር ውስጥ ተካተተች!
በአዲሱ የፈረንጆቹ ዓመት፣ለጎብኚዎች ተመራጭ መዳረሻዎች ናቸው ከተባሉ ከተሞች ስም ዝርዝር ውስጥ አዲስ አበባ ተካተተች፡፡
Condé Nast Traveler የተሰኘ መፅሄት በ2021 አዲሱ የፈረንጆች ዓመት፣ለጎብኚች ጥሩ መዳረሻዎች ናቸው ሲል ከዘረዘራቸው 21 ከተሞች ውስጥ የአዲስ አበባ ስም ይገኝበታል፡፡
መፅሄቱ፣በከተማይቱ የሚገኙትን እንደ አንድነት እና እንጦጦ ያሉ ፓርኮችን ቀዳሚ የጎብኚዎች መዳረሻ አድርጎ መርጧቸዋል፡፡
ሙዚየሞችን ጨምሮ፣ቦሌ ዓለም-አቀፍ አየር ማረፊያ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ስፍራዎች ለጎብኚዎች ጥሩ መዳረሻዎች መሆናቸውን መፅሄቱ ጠቁሟል፡፡
ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ፤ ኒውዮርክ ፣ ኦስሎ እና ኪዮቶ-ጃፓን በዚህ በስም ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ከተሞች ናቸው፡፡
ይህን ለጎብኚዎች ጥሩ-መዳረሻዎች የሆኑ ከተሞችን ስም ዝርዝር ያወጣው Condé Nast Traveler የተሰኘዉ መፅሄት ዋና መቀመጫዉን በአሜሪካ ኒውዮርክ ያደረገ ሲሆን ፤ በወር ከ5 ሚልየን የማያንሱ አንባቢዎች አሉት፡፡
ምንጭ:-ብስራት ራዲዮ
@Yenetube @Fikerassefa

ትምህርት ሚኒስቴር የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እስከ ታህሳስ 30 ተሰጥቶ ይጠናቀቃል አለ!
የትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው የግዜ ሰሌዳ መሰረት የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በሁሉም ክልሎች እስከ ታህሳስ 30 ተሰጥቶ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።ይህንንም ተከትሎ የክልል ትምህርት ቢሮዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየትና አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ፈተናውን በተያዘለት የግዜ ገደብ ለመስጠት የራሳቸውን የግዜ ሰሌዳ እያወጡ ይገኛሉ።በዚህም መሰረት የሀረሪ ክልል ከ ታህሳስ 7-9፣ የአማራ ክልል ከታህሳስ 12-14 ፈተናውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።ሌሎች ክልሎችም በቀጣይ ቀናት ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ይፋ የሚያደርጉ ይሆናል።በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከትላንት ጀምሮ መሰጠት መጀመሩ ይታወሳል።
[MoE]

በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ ፓርክ በ70 ሚሊዮን ዩሮ ካፒታል ወደ ስራ የገባው የሶፍሌት ማልት ኢትዮጵያ መጋቢት ወር ላይ ምርት ይጀምራል ተባለ!
በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ ፓርክ በ70 ሚሊዮን ዩሮ ኢንቨስትመንት ካፒታል ወደ ስራ የገባው የሶፍሌት ማልት ኢትዮጵያ ፋብሪካ መጋቢት ወር ላይ ምርት ይጀምራል ተባለ፡፡ፋብሪካው በፈረንሳይ ቀዳሚ የጥራጥሬ ሰብሳቢ ሲሆን በ70 ሚሊዮን ዩሮ ኢንቨስትመንት ካፒታል ወደ ስራ ገብቷል፡፡ተቋሙ በ10 ሄከታር ላይ የሚያርፍ የብቅል ፋብሪካ እየገነባ ያለ ሲሆን ከጅምሩ ከ25ሺ አርሶ አደሮች ጋር የምርት ትስስር ፈጥሮ እየሰራ ይገኛል፡፡
በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር ትስስሩን ወደ 40 ሺ ለማሳደግ አቅዶ እየሰራ እንዳለ ከኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርሬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ሙሉ በሙሉ የሀገር ውስጥ የግብርና ምርትን ተጠቅሞ ከመቶ ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ ብቅል በአመት የማምርት አቅም ያለው ይህ ፋበሪካ በመጋቢት 2013 ዓ.ም ወር ምርት ይጀምራል ተብሏል፡፡
[FBC]

ኦባማ፣ ቡሽና ክሊንተን በቲቪ መስኮት እየታዩ ሊከተቡ ነው!
የቀድሞዎቹ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንቶች ባራክ ኦባማ፣ ጆርጅ ደብልዩ ቡሽ እና ቢል ክሊንተን በቴሌቪዥን መስኮት እየታዩ የኮቪድ-19 ክትባት ለመወጋት ቃል ገብተዋል።ሶስቱ የቀድሞ መራሄ መንግሥታት ክትባቱ በአሜሪካ መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ፈቃድ ካገኘ በኋላ ክንዳችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል ብለዋል።ሁለቱ ዴሞክራቶች ኦባማና ክሊንተን እንደሁም ሪፐብሊካኑ ቡሽ በጤና ሙያ ጥርሳቸውን የነቀሉ ሰዎችን ይሁንታ ካገኙ በኋላ ነው የሚከተቡት።የቀድሞዎቹ መሪዎች ይህን ለማድረግ የቆረጡት ሕዝቡ በክትባት ላይ ያለው እምነት እንዲፀና በማሰብ ነው።
[BBC]

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አዳማ ከተማ አስተዳድር የመሬት ይዞታን ለማዘመን 940 ህገወጥ ቤቶች ትናንት ማፍረስ ተጀምሯል፡፡
የአዳማ ከተማ የመሬት አስተዳደር ሃላፊ አቶ ደስታ መርጋ ስራዉ ከነዋሪዎቹ ጋር በመነጋገር እና በመተባበር መሳካቱን ገልፆ ቤት ለፈረሰባቸው ነዋሪዎችም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ችግሩን በማስተካከል አዲስ ቦታ ከነካርታ እና ፕላን እንደሚያስረክቡ አክሏል።ቤት የፈረሰባቸው ነዋሪዎችም ይህ ተግበራ እስኪጠናቀቅ ድረስ አቅም ያላቸው ሰዎች በኪራይ እንዲቆዩ አቅም የሌላቸው ደግሞ በላስቲክ ቤት ተጠልለው በመቆየት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ካርታ እና ፕላን እንደሚረከቡ ገልፀዋል።
[@addiszeybe]

በሃገሪቱ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ልጆች በነጻ ለማስተማር ቃል እየገቡ ነው፡፡
ከሁለት ዓመታት በፊት በሃገሪቱ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች በቻሉት መጠን ለሃገር ክብር ዘብ የቆሙ የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ልጆች እንዲያሰተምሩ በጋዜጠኛ ባሪያስ በዛብህ የግል ተነሳሽነት በተጠየቁት ጥያቄ መሰረት በመጀመሪያ ጉዞው በሀዋሳና ሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች የቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለው የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ልጆችን በነጻ ለማስተማር ቃል ገብተዋል፡፡በሀዋሳና ሻሸመኔ የሚገኙና ይህንን ዓላማ ለመደገፍ ቃል የገቡ የግል ትምህርት ቤቶችም እንዳላቸው የቅርንጫፍ ብዛት ተማሪዎችን ተቀብለው እንደሚያስተምሩ ነው ለትምህርት ቤቶቹ ጋዜጠኛ ባሪያስ በዛብህ የቀረበው ይህ ጥያቄ ተቀባይነት ሊያገኝ የቻለው፡
ጋዜጠኛ ባሪያስ በዛብህ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገረው በሻሸመኔ የሚገኘው ሉሲ ትምህርት ቤት ባሉት አምስት የማስተማሪያ ቅርንጫፎች አንድ አንድ ተማሪ ለመቀበል ቃል ገብተዋል፡፡የመከላከያ ሰራዊት አባላት ልጆችን ተቀብለው በነጻ ለማስተማር ቃል ከገቡ የክልል ከተሞች ትምህርት ቤቶችም በሃዋሳና ሻሸመኔ የሚገኙት ቢኤንቢ፣ ሉሲ፣ ዩኒየን ማውንት፣ ኦሊቭና ኤስ ኦኤስ ትምህርት ቤቶች ናቸው።ይህንን መልካም ተግባር በአዲስ አበባና በክልል ከተሞችም እንዲቀላቀሉ የማስቀጠል እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ጋዜጠኛ ባሪያስ በዛብህ አስታውቋል፡፡
Via Ethio FM

በአዲስ አበባ ከተማ በአንዳንድ አካባቢዎች ለማሻሻያ ሥራ ሲባል የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል!
ቅዳሜ ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ፣
• በኮተቤ ብረታ ብረት፣ በኮተቤ ኪዳነምህረት ቤተ-ክርስትያን፣ በአንቆርጫ እና አካባቢዎቻቸው፣
በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ፣
• በግብፅ ኤምባሲ፣ በስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ፣ በየካቲት ሆስፒታል፣ በቅድስተ ማርያም ቤተ-ክርስትያን ጀርባ፣ በእሪ በከንቱ፣ በፒያሳ፣ በቀይ ባህር ኮንደሚኒየም፣ በተፈሪ መኮንን ጀርባ፣ በአፍንጮ በር፣ በናይጄሪያ ኤምባሲ፣ በችሎት፣ በጉቶ ሜዳ እና አካባቢዎቻቸው፣
ሰኞ ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ፣
• በላምበረት፣ በመገናኛ፣ በየካ ሚካኤል፣ በሾላ ገበያ፣ በትምህርት ስርጭት፣ በእግዚአብሄር አብ ቤተ-ክርስትያን፣ በሜጋ እና አካባቢዎቻቸው፣
በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡30 ሰዓት ድረስ፣
• በሃና ማርያም፣ በኃይሌ ጋርመንት፣ በቆጣሪ ኮንደሚኒየም፣ በኦሮሚያ ኮንደሚኒየም፣ በማንጎ ሰፈር፣ በወሰን ግሮሰሪ፣ በወንድይራድ ት/ቤት፣ በባድሜ ሰፈር እና አካባቢዎቻቸው፣
በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ፤ ክቡራን ደንበኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ አሳውቋል፡፡
[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት]

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።
አደጋው በድሎ ሬጴ ቀበሌ ውስጥ ትናንት ማምሻውን መድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙዩኒኬሽንናና ሚዲያ ሃላፊ ኮማንደር አስቻለው አለሙ ተናግረዋል፡፡በዚህም አሽከርካሪውን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ህይወት ወደያውኑ ማለፉን አስታውቀዋል።አደጋው የደረሰው ከቡታ ጅራ ወደ ባቱ እየተጓዘ የነበረ ሚኒባስ የህዝብ ማመላለሻ 16 ሰዎች ጭኖ በፍጥነት ሲጓዝ በመገልበጡ መሆኑን ኮማንደር አስቻለው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።በአደጋው ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች በተጨማሪ አምስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶ በአዳማ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል።ከአደጋው አራት ህፃናት ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው መትረፉቸውን ኮማንደር አስቻለው አመልክተዋል።
[ENA]