YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በትግራይ ክልል ወሳኝ የሚባሉ ቦታዎች በመከላከያ ሰራዊት ነፃ መውጣታቸውን የገለፁት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ሕግ የማስከበር ወታደራዊ ዘመቻው በአጭር ጊዜ እንደሚጠናቀቅ ገለፁ፡፡

ከፍራንስ 24 ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉት ሚኒስትሩ ዘመቻው ከአንድ ሳምንት ባጠሩ ቀናት ውስጥ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ተስፋ መደረጉን ነው የጠቀሱት፡፡ንፁሃን እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ እየተደረገ ነው ያሉት አህመድ ሽዴ አሁን ላይ ዘመቻው በመቐለ እና ዙሪያዋ ባለ ጠባብ ቦታ የሚከወን መሆኑን አስተድተዋል፡፡ በሌሎቹና ከሕወሓት ነፃ በሆኑ ቦታዎች የሰብኣዊ አገልግሎቶች እንዲደርሱ ክፍት መደረጉንም አንስተዋል፡፡

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
በራያ ግንባር የተሰለፈው ሰራዊት መቀሌን ለመቆጣጠር 2 ቀናት ብቻ ቀርተውታል።

አበበ ሰማኝ (ከሄዋኔ) ህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም

በራያ ግንባር ተሰልፎ አስቸጋሪ የመሬት ገፆችን በማለፍ የድል ባለቤት የሆነው መከላከያ ሰራዊት ከ2 ቀናት በኋላ መቀሌ ከተማን እንደሚቆጣጠር የግንባሪ መሪ ሌተናል ጄነራል ባጫ ደብሌ ተናገሩ።

በራያ ግንባር ተሰልፎ የጠላትን አከርካሪ በመስበር ግዳጁን እየተወጣ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት በአንድ ብኩል ከጨርጨር እስከ መሆኒ በሌላ በኩል ደግሞ ከቆቦ አለማጣ ኩኩፍቱ እና መሆኒ በማድረግ ግዳጁን በሁለት አበይት አቅጣጫዎች ሲፈፅም ቆይቷል።

ምንም እንኳን የገጠምነው ሃይል የጎበዝ አለቃ ወታደር ቢሆንም አካባቢው ካለው ተራራማ የመሬት ገፅ አንፃር ያሉ ፈታኝ ሁኔታዎችን አልፈን የሚከፈለውን መስዋዕትነት በመክፈል በአሁኑ ሰዓት ከመቀሌ በ30 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ሄዋኔ ከተማን ተቆጣጥረናል ብለዋል።

በቀጣይ ግዳጅ ላይ የምንሰራቸው ማይ ነብሪ እና አዲ ጉዶም የተባሉ ከተማዎችን መቆጣጠር ነው ያሉት ጀነራል ባጫ እነዚህን ተልዕኮዎች በሚገባ በመፈፀም በቀጣይ 2 ቀናት ውስጥ መቀሌ ከተማን እንቆጣጠራልን ሲሉ ተናግረዋል።

ሜጀር ጀነራል አለምእሸት ደግፌ በበኩላቸው ጁንታው ቡድን ለረጅም ጊዜ እዋጋበታለሁ ብሎ የገነባቸው ኮንክሪት ምሽጎች ከ3 ቀናት መራራ ውጊያ በኋላ ሲደመሰሱ ካለአማራጭ ቦታውን ልቆ እንዲሸሽ ተደርጓል ብለዋል።

የመከላከያ ሃይሉ የከባድ መሳሪያ ምድብተኞች በተመረጡና ኢላማቸውን በጠበቁ ተኩሶች የጠላትን የማድረግ አቅም ማዳከም ተችሏል ያሉት ጀነራል አለምሸት በዚህም የጁንታው ቡድን ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ወደ አዲጉዶም ሸሽቷል ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአገር መከላከያ ሠራዊት ሀውዜን፣ አል ነጃሺ፣ አዲ ቀይህ፣ ማይመሳኖንና ውቅሮን ከጁንታው ታጣቂ ኃይል ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ

የአገር መከላከያ ሠራዊት ሠራዊቱ መቀሌን እና የወንጀለኛው ጁንታ ቡድን አባላትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስትራቴጂክ ቦታዎች መያዙን አስታወቀ።

ሠራዊቱ ሀውዜን፣ አል ነጃሺ፣ አዲ ቀይህ፣ ማይመሳኖንና ውቅሮን ከጁንታው ታጣቂ ኃይል ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።

የትግራይ ሕዝብ ከመጀመሪያው ዕለት አንሥቶ ለመከላከያ ሠራዊት ወገንተኝነቱን አሳይቷል።

የሕወሓት ጁንታ በሰላም እጁን እንዲሰጥ መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓታት ጊዜ ሊጠቀም ባለመቻሉ ከትናንት ጀምሮ የሕግ ማስከበር ስራው ቀጥሏል።

በመከላከያ ሠራዊት ኅብረት ሥልጠና ዋና መምሪያ ሓላፊ ሌተናል ጄኔራል ሐሰን ኢብራሂም በሰጡት መግለጫ፣ የሕግ ማስከበር ሂደት በውጤታማነት ቀጥሎ ተጨማሪ የትግራይ ክልል ከተሞችን ከጁንታው ታጣቂ ነፃ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

በዚህም በአድዋ ግንባር የተንቀሳቀሰው ሠራዊት ሃውዜን፣ አብርሃ ወአጽብሃንና ውቅሮን የተቆጣጠረ ሲሆን፣ አጉላን ደግሞ በግማሽ ቀን መቆጣጠሩን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅትም በመቀሌ አቅራቢያ ወደሚገኘው መሰቦ ተራራ እየገሰገሰ ሲሆን፣ ይህም መቀሌን በጥቂት ቀናት ውስጥ ለመቆጣጠር እንደሚያስችል ጠቁመዋል።

በሁለተኛው ግንባርም በአዲግራት በኩል ሳንቀጣ እና አልነጃሺን በመቆጣጠር ውቅሮ ገብቷል።

በሦስተኛው የራያ ግንባር ደግሞ አዲቀይህን የተቆጣጠረ ሲሆን፣ ሄዋናን በመቆጣጠር ሁሉንም ምሽጎች ሰባብሮ ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል።

በመቀሌ ያለውን የወንጀለኛ ቡድን የመቆጣጠር ተግባር በማጠቃላይ ምዕራፍነት የተያዘ ሲሆን፣ ሠራዊቱ ግዳጁን በምን አኳኋን መፈጸም እንዳለበት በቂ ዝግጅት አድርጎ የወንጀለኛውን ቡድን በቁጥጥር ስር ለማዋል መዘጋጀቱን አመልክተዋል።

የትግራይ ሕዝብ ሠራዊቱ የጁንታውን አባላት ለመያዝ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ወገንተኝነት ከማሳየቱም በላይ፣ በሠራዊቱም ላይ ጥይት አለመተኮሱ የትግራይ ሕዝብ እና ጁንታው የተለያዩ መሆናቸውን አረጋግጧል።

የጁንታው ቡድንም በፕሮፓጋንዳ ጭምር እያፈገፈገ መሄዱ ሽንፈቱን እያረጋገጠ መሆኑን አመልክተዋል።

በማጠቃለያው ምእራፍ መቀሌን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስትራቴጂክ ቦታዎች መያዙን አስታወቀ።

በራያ በኩልም አድ ቀይህ፣ አዲመሳኖን እና ሄዋናን ከታጣቂ ኃይሉ መቆጣጠሩን ገልጸዋል።

በጉላን በኩል መንገድ ለመዝጋት ቢሞክርም፣ እንዳልተሳካለት እና ወደኋላ ማፈገፈጉን ተናግረዋል።

አሁን ላይ መቀሌ ብቻ መቅረቱን የገለጹት ሌተናል ጀነራል ሐሰን በጥቂት ቀናት ወስጥ ተጠናቆ ጁንታው ለሕግ እንደሚቀርብ አረጋግጠዋል።

የጁንታው ኃይል በራያ በኩል ያለ የሌለ ኃይሉን በመጠቀም የሠራዊቱን ጥቃት ለመቋቋም ቢሞክርም በመመታቱ ለመልቀቅ ተገዷል ነው ያሉት።

የሕወሓት ጁንታ ሽንፈቱን እያረጋገጠ በመምጣቱ በሐሰት ወሬ ላይ ተጠምዶ ሕዝብን በማደናገር ላይ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
በራያ ግንባር እየተወሰደ ያለው ሕግ የማስከበር እርምጃ ውጤታማ ነው - ሌተና ጄነራል ባጫ ደበሌ

የራያ ግንባር አዛዥ ሌተና ጄነራል ባጫ ደበሌ በራያ ግንባር እየተወሰደ ያለው ሕግ የማስከበር እርምጃ ውጤታማ መሆኑን ገለጹ።

ሌተና ጄነራል ባጫ በሰጡት መግለጫ በግንባሩ የሚገኘው መልክዓ ምድር ፈታኝ እንደነበር ተናግረዋል።

ጄነራሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሠራዊቱ መቀሌ እንደሚገባም አመልክተዋል።

የሠራዊቱ ወቅታዊ ዝግጁነት እና የግዳጅ አፈጻጸም የላቀ መሆኑንም ሌተና ጄነራል ባጫ ጠቅሰዋል።

የራያ ግንባር የከባድ መሣሪያዎች አስተባባሪ ሜጀር ጄነራል ዓለምእሸት ደግፌ በበኩላቸው፣ ሠራዊቱ ታጣቂ ቡድኑን ከሲቪል ነጥሎ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።

ሠራዊቱ ከባድ መሣሪያዎችን በማቀናጀት በአካባቢው በነበረው የትሕነግ ታጣቂ ቡድን ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረሱንም ጠቁመዋል።

Via:- EBC
ፎቶ:- በሻምበል ብርሃኑ ወርቁ
@YeneTube @Fikerassefa
አየር ኃይል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለተለያየ የስራ ጉዳዮች በትግራይ ክልል የሚገኙ ሰራተኞችን ወደ የአካባቢያቸው የማመላለስ ስራ መጀመሩን አሳወቀ።

@Yenetube @Fikerassefa
ዛሬ ማምሻውን ከትግራይ የተወነጨፉ በርከት ያሉ ሮኬቶች አስመራን እንደመቱ ኤርትሪያን ፕሬስ በፌስቡክ ገፁ ፅፏል ።

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)
በርካታ ሮኬቶችን ወደ ተለያዩ የኤርትራ ከተሞች ማስወንጨፉ ተሰማ።

ለ2ኛ ጊዜ የተፈጸመውን ይህን የህወሓት ድርጊት ኤርትራ ፕሬስን ጨምሮ ሌሎች ሚዲያዎች ዘግበውታል።

ህወሓት ጦርነቱን ዓለማቀፋዊ ይዘት ለማላበስ የመጨረሻውን ሙከራ አድርጓል ያለው
ኤርትራ ፕሬስ ወደ አስመራ የተተኮሱት ሮኬቶች በተጨናነቁ የመኖሪያ አካባቢዎች አቅራቢያ ቢያርፉም ያደረሱት አንዳች ጉዳት እንደሌለ አረጋግጫለሁ ብሏል።

ህወሓት ከአሁን ቀደምም ወደ አስመራ ሮኬት ማስወንጨፉ የሚታወስ ነው።

ሆኖም ያደረሰው ጉዳት አልነበረም ብላል።
የኤርትራ መንግስትም ያለው ነገር አልነበረም በወቅቱ።

@Yenetube @FikerAssefa
Forwarded from ABENI★ Fab
videotogif_2020.11.17_05.08.23.gif
1.2 MB
📌አሜሪካ ሰራሹ ተአምረኛው ትሪትመንት አገራችን ገባ በ ቀናት ውስጥ ከ መላጣነት ወደ ማበጠሪያ ተጠቃሚነት ይዞራሉ👉🏼 አላድግም ብሎ ለቀረ
👉🏼 ራሰ በርሃ ለሆነ
👉🏼 ወደራሰ በርሃነት የተጠጋ  ለሳሳ ፀጉር
👉🏼 ወደውስተጥ ለገባ ፀጉር
👉🏼 ፐረም ወይም ጄል ለጨረሰው ፀጉር
👉🏼ላሽ ለበላው #ፂም #ፀጉር
100% በተግባር የታየ ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ 🔽USA🇺🇸 አሁኑኑ ያናግሩን ☞@Brandlife1
በተጨማሪም በተለያዩ አማራጮችየቀረቡ የዉፍረት መቀነሻ ቀበቶዎች, [Human hair ] {Wireless Wifi router}+ለ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ገንቢ የሆኑ ፕሮቲኖች (protein shake), በተለያየ ምክንያት ለመጣ ጠባሳ ማጥፊያ የሚሆኑ ትሪትመንቶችን ከኛ ያገኛሉ፡፡➡️ ☎️+251991203033
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEpoRsmLNv7NNj3K_g
Forwarded from YeneTube
#የጥፋት_አርበኞች
#አዲስ_መጽሐፍ_በገበያ_ላይ

አንዳንድ ሀገሮች የመፈራረስ ዕጣ ፈንታ የገጠማቸው በጥፋት አርበኞች የጀብደኝነት ተግባር እንደሆነ ያውቃሉ? እኛስ እያጋጠመን ያለው ይሄው እጣፈንታ ይሆን?

የጥፋት አርበኞች የሚንቀሳቀሱት ከንቃተ ህሊናቸውን ጋር በተፋቱ ስሜቶቻቸውና በተሳሳቱ እምነቶች እንጂ በምክንያት አይደለም! መመሪያቸው አረመኔያዊነት፣ ተግባራቸውም እንሰሳዊነት ነው ይላል፡፡ #የጥፋት_አርበኞች_ልክ_የበሰበሰ_ሬሳ_ላይ_እንደሚራኮቱ_ምስጦች_የሚተባበበሩት_ለጥፋት_ነው፡፡

#ይሄ_መፅሐፍ_ደግሞ_ብዙ_ የጥፋት_ሚስጥራቸውን_ይገልጥልናል፡፡

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።

ይቀላቀሉን 👉http://tttttt.me/teklutilahun
Forwarded from YeneTube
#መልካም_ሰዎች_ለምን_ይሰቃያሉ?
#ሁለተኛው_ዕትም_በገበያ_ላይ

መልካም ሰዎች ላይ መጥፎ ነገር የሚደርሰው ለምንድን ነው? መከራን የሚቀበሉትስ ለምን ይሆን? ከዚህ ሁሉ ጥያቄ በኋላ እኛ ያላወቅነው ምስጢር ይኖር ይሆን?

ይህ መጽሐፍ ‹‹ፈጣሪ ለምንድነው ይሄን ሁሉ በእኔ ላይ ያመጣብኝ?›› ለምንለው ነገር ሁሉ ምላሽ አለው!!!

“በሃሳቦች የተሞላ፣ በተዋጣላቸው አመክንዮዎች የተተነተነ፣ የመንፈሳዊ ጥንካሬ መመሪያዎችን የያዘ ድንቅ መጽሐፍ!!”
#ዘ_ዋሽንግተን_ፖስት

“ይህ ላዘኑ መጽናናትን፣ ማባሪያ በሌለው ፍርሃት ለተተበተቡት ሰዎች ደግሞ ሰላምን የሚሰጥ የሃሳብ እድገት መጽሐፍ ነው!”
#ስፕሪችዋሊቲ_ኤንድ_ሄልዝ

“ይህ ለሰው ልጆች ሁሉ አስፈላጊ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ በመከራ የተሞሉ የህይወትን ውጣ ውረዶችን ለመረዳትና ፈጠራ በተሞላበት ጥብበ ለመወጣት ይጠቅማል!”
#ኖርማን_ቪንሰንት_ፒል

#ሁለተኛውን_ዕትም_በየመጽሐፍት_መደብሩና_በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል

👉 ይቀላቀሉን http://tttttt.me/teklutilahun
Forwarded from YeneTube
TOP book series 📚ቶፕ የተማሪዎች አጋዥ መፅሀፍት

📌ከ 1-12 ክፍል በ ተለያዩ ቋንቋ የተዘጋጀ
📌በ ኦሮምኛ
📌በ አማርኛ
📌በ እንግሊዘኛ በሁሉም አይነት ትምህርት የተዘጋጀ
- maths chemistry biology physics ...
📌ለ 8 እና 12ኛ ክፍል ፈተና የሚያዘጋጁ
📌ለ ልጆችም 20 አይነት ተረት መጽሀፍት ታትሞዋል

❗️❗️በሁሉም መፅሀፍት ቤት ይጠይቁ
 
ዋና አከፋፋይ : ኤደን መጽሀፍት ቤት  
* * መገናኛ ሀይሌ ህንፅ ፊት ለ ፊት
📞 0911238057
0912732493

@TOPBOOkSERIES
ከ43 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ድንበር አቋርጠው ወደ ሱዳን ገብተዋል።

በትግራይ እየተካሄደ ያለውን ወታደራዊ ግጭት በመሸሽ ወደ ሱዳን በመግባት ላይ ላለው እና ቁጥሩ እየጨመረ ለመጣው ስደተኛ የሚደረገውን ዕርዳታ ኦፕሬሽን ለመመልከት የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የስደተኞች ኮምሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ካርቱም ናቸው።ቁጥሩ ከ43 ሺህ በላይ የሚሆን ተፈናቃይ በያዝነው ድንበር አቋርጦ ምስራቃዊ ሱዳን መግባቱም ተዘግቧል።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን በሙያቸው ለማገዝ ሁለተኛ ዙር የአዲስ አበባ የህክምና ባለሙያዎች ልዑካን ወደ ስፍራው አቀኑ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ ሆስፒታሎች የተውጣጡ ከ60 በላይ የጤና ባለሙያዎችን እና ሁለት ድጋፍ ሰጪ አምቡላንሶች ለመከላከያ ሰራዊት ሙያዊ ድጋፍ ለመሰጠት በዛሬው እለት ወደ ስፍራው አቅንተዋል።የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ለህክምና ባለሙያዎች አሸኛኘት አድርገዋል።

የሀገር ጥሪን በመቀበል ሰራዊቱን በሙያቸው ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹት የጤና ባለሙያዎቹ በዚህም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡በመጀመሪያው ዙር የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላን ጨምሮ ስፔሻሊስት ሀኪሞች እና ነርሶች በጠቅላላው 48 የህክምና ባለሙያዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

[Addis Ababa City PS]
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስም የታተሙ ህገ ወጥ መታወቂያዎች ተገኝተዋል።

በራያ አላማጣ ከተማ ከአንድ የመንግስት ቢሮ ውስጥ በርካታ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስም የታተሙ ህገ ወጥ መታወቂያዎች ተገኝተዋል።በስፍራው አስተያየታቸውን የሰጡት ምክትል ኮማንደር ጥላሁን ታደሰ እንደገለፁት ይህን መታወቂያ የሚጠቀሙት ግለሰቦች በአማራ ህዝብ ስም ወንጀልና የሽብር ጥፋት ለማድረስ ነው ብለዋል።ይህ የትህነግ ድርጊት በተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ህዝብ ስም ወንጀል በመፈፀም የአማራን ህዝብ ከሌሎች ብሄረሰቦች ጋር ለማጋጨት ያሴሩት ሴራ ነው ሲሉ ምክትል ኮማንደሩ ተናግረዋል።ሁሉም የሀገራችን ህዝብ እና የፀጥታ አካላት መታወቂያ በሚያዩበት ጊዜ በደንብ ማስተዋል ይገባል።አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ደግሞ ከሚመለከታቸው አካላት ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ምክትል ኮማንደር ጥላሁን ታደሰ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Via Amhara Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከኅዳር 30 እስከ ታኅሣሥ 2 እንደሚሰጥ ተገለጸ!

በክልል ደረጃ የሚሰጠው የ8ኛ ክፍል ፈተና በኦሮሚያ ከኅዳር 30 እስከ ታኅሣሥ 2 የሚሰጥ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ።በክልሉ ከመዋዕለ ሕፃናት ውጪ ያለው የመማር ማስተማር ሂደት ከመጪው ማክሰኞ አንስቶ እንደሚጀምርም ተገልጿል።የመዋዕለ ሕፃናት ትምህርት መጀመሪያ ጊዜ ለሁለት ሳምንታት መራዘሙ ነው የተገለጸው።

@YeneTube @FikerAssefa
የህወሓት ቡድን ልዩ ሃይል አባላት በአዲ ምስኖ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዛት ያላቸው ጥይቶችን በማከማቸት የአካባቢውን ህብረተሰብ ያስቆጣ ተግባር ፈፅሟል ተባለ።

[አበበ ሰማኝ ( ከግዳጅ ቀጣና )]

አቶ በሀይሉ በርኸ "ቤተ ክርስቶያን ውስጥ የመድፍ ጥይት እና ቢ ኤም መሳሪያ አምጥተው አስቀመጡ፡፡ለምን ስንላቸው ቤተክርስትያኑ አይመታባችሁም ከተመታም የጥይት ሳጥን እንሰጣችሁና እሱን ሸጣችሁ ታስጠግኑታላችሁ አሉን" ብለዋል።

አቶ በሀይሉ፣ ቤተ ክርስትያኑ ፈርሷል ውስጡ ያለው ፅላትም ይኑር አይኑር የምናውቀው ነገር የለም ፥ ወያኔ ለሃይማኖት እኩልነት እቆማለሁ ሲል የነበረ ድርጅት ዛሬ ግን ስጋወደሙ የምንቀበልበትን የእምነት ቦታ አርክሶብናል ሲሉ በሃዘንና በቁጭት ስሜታቸውን አጋርተውናል።

በየትኛውም ፖለቲካዊ እይታ ህዝብን ያልያዘ ሃይል የድል ባለቤት ሊሆን አይችልም፡፡ከሞቱ መቃብር አፋፍ ላይ የሆነው ትህነግ፣ ግን በራሱ ልክ በተሰፋው የሴራ ፖለቲካ ተተብትቦ በሰው ህሊና ሊፈፀሙ አይደለም ሊታሰቡ የማይችሉ ተግባራትን ከመፈፀም አልቦዘነም።

ለሁሉም በመላው ህዝባችን ድጋፍ በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ጀግንነት ዘራፊውና ከሃዲው ቡድን ያለችው የተስፋ ጭላንጭል ተሟጣ የመኖር ጀንበሩ ልትጠልቅ አጭር እድሜ ብቻ ቀርተውታል።

[ፎቶግራፍ ብርሀኑ አባተ]
@YeneTube @FikerAssefa
አዋሽ ባንክ 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር አመታዊ ትርፍ ማግኘቱን ገለጸ ።

አዋሽ ባንክ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 25ኛ  ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።ባንኩ በ2019/ 2020 አጠቃላይ የትርፍ መጠን የስንምት በመቶ ዕድገት በማሳየት 3.6 ቢሊየን አመታዊ ትርፍ ማግኘቱ ባንኩ ገልጿል ።ባንኩ ባለፈው አንድ አመት 57 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ብድር ማበደሩንም አስታውቋል።ባንኩ እንዳስታወቀው በ2019/ 2020  በጀት ዓመት የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 74 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር መድረሱን ገልጿል።ይህም ከዚህ በፊት ከነበረው የ19 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ተገልጿል።በበጀት አመቱ ማጠቃለያ የባንኩ አጠቃላይ የሀብት መጠን 19.7 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ 89.3 ቢሊየን ብር መድረሱንም ተነግሯል ።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢራን የኑክሌር ሳይንቲስቷን ግድያ እንደምትበቀል ዛተች!

የኢራኑ ፕሬዝደንት ሐሰን ሩሃኒ ለአገራቸው ዋነኛ የኑክሌር ሳይንቲስት ግድያ እስራኤልን ተጠያቂ በማድረግ፤ ግድያው የኢራንን የኑክሌር መረሃ ግብር ፍጥነት እንደማይቀንሰው ተናገሩ።ፕሬዝደንቱ ጨምረውም በሳይንቲስቱ ሞህሲን ፋክሪዛዴህ ግድያ የኢራን ጠላቶች ምን ያህል በጠለቀ "በተስፋ መቁረጥና በጥላቻ" ውስጥ እንዳሉ ያሳ ነው ብለዋል።እስራኤል ከኢራን በኩል Iየቀረበባትን ክስ በተመለከተ ምላሽ ባትሰጥም፤ ቀደም ሲል ሞህሲን ፋክሪዛዴህ ኢራን በድብቅ ከምታካሂደው የኑክሌር ጦር መሳሪያ ግንባታ ጀርባ አሉ ስትከስ ነበር።

ኢራን በዋነኛው የኑክሌር ሳይንቲስቷ ሞህሲን ፋክሪዛዴህ ላይ የተፈጸመውን ግድያ እንደምትበቀልም አሳውቃለች።ፋክሪዛዴህ ትናንት አርብ በዋና ከተማዋ ቴህራን አቅራቢያ ባልታወቁ ሰዎች በተፈጸመባቸው ጥቃት ሆስፒታል ተወስደው ነበር ህይወታቸው ያለፈው።የኢራን ሐይማኖታዊ የበላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒ ወታደራዊ አማካሪ ሆሴን ዲጋን እንዳሉት ግድያውን በፈጸሙት ላይ ኢራን "በመብረቃዊ ጥቃት" እንደምትበቀላቸው ተናግረዋል።

የምዕራባዊያን የስለላ ተቋማት እንደሚሉት ሳይንቲስቱ ፋክሪዛዴህ ኢራን በድብቅ እያካሄደች ነው ከሚሉት የኑክሌር ጦር መሳሪያ ግንባታ ፕሮግራም ጀርባ ያሉ ቁል ሰው ናቸው።ነገር ግን ኢራን እያካሄደች ያለው የኑክሌር መረሃ ግብር ለሰላማዊ ዓላማ አገልግሎት የሚውል እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጻለች።ግድያውን ተከትሎ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሐመድ ጃቫድ ዛሪፍ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ "መንግሥታዊ የሽብር ተግባር" ያሉትን እንዲያወግዝ ጠይቀዋል።"ሽብርተኞች ታዋቂውን ኢራናዊ ሳይንቲስት ዛሬ ገደሉት" ሲሉም ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa