YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኢሰመኮ ለንጹሃን ደህንነት መጠበቅ እና ለሰብዓዊ ድጋፎች መድረስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ በድጋሚ አሳሰበ!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሁንም ቢሆን ለንጹሃን ደህንነት መጠበቅ እና ለሰብዓዊ ድጋፎች መድረስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ በድጋሚ አሳሰበ፡፡ኮሚሽኑ በተያዘው ወር መባቻ የሲቪል ሰዎች ደህንነት አጠባበቅን አስመልክቶ ያስተላለፈውን መልዕክት የሚመለከታቸው ወገኖች በሙሉ እንዲያከብሩት በድጋሚ ጠይቋል።ግጭቱ አሁን በደረሰበት ደረጃም ላይ ቢሆን ሰላማዊ መፍትሔዎች ያስፈልጋሉ ያለው ኮሚሽኑ የሰብአዊ እርዳታ እና አገልግሎቶችን በአፋጣኝ ተግባራዊ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ የሰብአዊ ዕርዳታ ጉዳይ ዴስክ እንዲቋቋም ሕዳር 4 ቀን 2013 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቅርቦ ነበር፡፡

ዴስኩ ምናልባትም በሃገር መከላከያ ሰራዊቱ እና/ወይም በፌደራል መንግስት በተለይ የትግራይ ክልልን በተመለከተ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሰረት ለመቋቋም የሚችል ነው እንደኮሚሽኑ ገለጻ፡፡በተጨማሪም ኮሚሽኑ ልክ እንደማይካድራው ሁሉ በጦርነቱ የተከሰቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንደሚያጣራ እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ እንዲሁም ከግጭቱ ጋር በተያያዘ የተከሰቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ስጋቶችን እንደሚከታል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በኮሌራ በሽታ የተጠቃው ሰው ብዛት 104 ደረሰ!

 በደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን በተከሰተው የኮሌራ በሽታ የተጠቃው ሰው ቁጥር 104 ደረሰ፡፡ከቀናት በፊት ባቀረብነው ዘገባ 75 ሰዎች በበሽታው ሲያዙ የ5 ሰዎች ህይወት ደግሞ ማለፉን መግለፃችን ይታወሳል፡፡

ተጨማሪ የ1 ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ አጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት ህክምና ማዕከል አስተባባሪ የሆኑት አቶ ስዩም ከበደ የንፁህ ውሀ አቅርቦት ችግር የበሽታው መንስኤ እንደሆነ ለአዲስ ዘይቤ ገልፀዋል፡፡በዞኑ የመጠጥ ውሃ እጥረት መኖሩን ተከትሎ ነዋሪዎቹ በአከባቢው የሚገኘውን ወራጅ ወንዝ ለመጠጥ እንደሚጠቀሙበትም አክለዋል፡፡

ጉዳዩን  ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ጭምር ሪፓርት መደረጉን የገለፁት አቶ ስዩም በአሁኑ ሰዓት ወደ ማእከሉ መጥተው የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው በበሽታው መያዛቸውከተረጋገጠ ሰዎች ውስጥ 24ቱ በፅኑ ህሙማን ክፍል መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ያገገሙት ደግሞ 5 ብቻ ናቸው፡፡

Via @addiszeybe
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል የመከላከያ ሠራዊቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች የሰብአዊ እርዳታ እየቀረበ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታወቀ።

የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል ለሚገኙ ዜጎች የሚያስፈልገውን የሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ ትኩረቱን ሰጥቶ እንደሚሰራም አስታውቋል።መንግስት በቀጣይም ከአጋር ለጋሽ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያስታወቀው።በክልሉ በተለይ ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ በአፋጣኝ ለማድረስ የሰላም ሚኒስቴር ከሌሎች የፌዴራል ተቋማት ጋር በጋራ እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም የምግብ፣ የመጠጥ ውሃ፣ መድሀኒት እና ሌሎች ምግብ ነክ ያልሆኑ አቅርቦቶችን የፌዴራል መንግስቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ማቅረብ ተጀምሯል።

በስፍራው በአሁኑ ወቅት ስደተኞችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚሆኑ አራት መጠለያ ጣቢያዎች ለማቋቋም እየተሰራ ሲሆን ይህን ለማስተባበር የተቋቋመው ኮሚቴም ዜጎችን በፍቃዳቸው መልሶ ለማቋቋም እንደሚሰራ ተገልጿል።መንግስት የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን መልሶ ለማቋቋም እና የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎችን ጨምሮ ከሁሉም ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ጋር በጥምረት ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመሬትና መሬት ነክ ከሆኑ ጉዳዮች ጋር ተቋርጦ የነበረው የአገልግሎት እገዳ ተነሳ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመሬትና መሬት ነክ ከሆኑ ጉዳዮች ጋር ተቋርጦ የነበረው የአገልግሎት እገዳ ከህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መነሳቱ ተገልጿል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ከተማ አስተዳደር ከነሀሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ መሬትና መሬት ነክ የሆኑ ጉዳዮች አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ ማገዱ ይታወሳል፡፡የከተማ አስተዳደሩ በመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ሲያከናውን የነበረውን የማጥራት ስራዎችን ማጠናቀቅ ተችሏል፡፡ በመሆኑም ከመሬትና መሬት ነክ ከሆኑ ጉዳዮች ጋር ለህብረተሰቡ አገልግሎት ለመስጠት እና የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል እንዲያስችል የተጣለው እገዳ ከህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የተነሳ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በአሁን ሰአት የህወሓት አመራር ያለበት ቦታ በጥልቀት የሚታወቅ ቢሆንም መንግስት ለሰላማዊ ዜጎች ደህንነት ትኩረት በመስጠት እርምጃዎችን በተጠና ሁኔታ ነው የምወስደው ብሏል።

የህወሓት አመራር በአንድ ላይ እንደማይገኝና በከተማይቱ የተለያዩ ስፍራዎች ተሸሽጎ በወታደራዊ ሬዲዮ እንደሚገናኝ መረጃዎች ያመለክታሉ።የህወሓት ዋነኛ የእዝ ቦታዎች እና ዋሻዎች ሞሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ውስጥ ለውሃ ጉድጓድ በሚል በቻይኖች የተቆፈረ እና በኮንክሪት የተሰራ ሁሉም ነገር የተሟላለት ቪላ ቤት፣ አፄ ዮሀንስ ሙዚዬም ውስጥ የሚገኝ ግራውንድ ቤት፣ ኩያ አካባቢ የሚገኝ ኖብል ሆቴል ህንፃ ስር የሚገኝ ቤት፣ ሀውልቲ አካባቢ የሚገኘው የድምፀ ወያኔ ስቲዲዮ ውስጥ ያለ የተሟላ አዳራሽ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ አፅቢ አካባቢ ባለ ጫካ ውስጥ ለመደበቅ ማታ ማታ መንገድ የመጥረግ ስራ እየሰሩ መሆኑንና በአብረሃ ወፅበሃ ገዳም መሸሸጋቸውንም እንዲሁ ይህ ቦታ በኮማንዶ የሚጠበቅ ሲሆን የመሳሪያ ክምችት አለበት ተብሎ የሚጠረጠር መሆኑም ተጠቁሟል።ሆኖም የቡድኑ አጠቃላይ ሁኔታ በዚህ ደረጃ ቢታወቅም መንግስት ለሰለማዊ ዜጎች ሲል የተጠና እርምጃ እንደሚወስድ ነው የገለፀው።

ዘገባው የኢቢሲ ነው
@YeneTube @FikerAssefa
በማይካድራ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል በሚል በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የተገለጸው የሟቾች ቁጥር ስህተት እንዳለበትና ከተጠቀሰውም በላይ እንደሆነ ተገለጸ።

የህወሃት ቡድን በልዩ ሃይሉ አማካኝነት በአገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ በሰሜን ኢትዮጵያ የህግ ማስከበር ዘመቻ ከተጀመረ 18ኛ ቀኑ ላይ ደርሷል።የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በማይካድራ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ ቦታው ላይ በነበረው የመንግስት አስተዳድር ወይም በትግራይ የጸጥታ ሃይል አጋዥነት እና ሳምሪ በተሰኘ የወጣቶች ቡድን መፈጸሙንም በያዝነው ሳምንት ማሳወቁ አይዘነጋም።ኮሚሽኑ በዚህ አሰቃቂ እና ማንነትን መሰረት ባደረገ የግድያ ወንጀል በማይካድራ 600 ንጹሀን ዜጎች መገደላቸውን ገልጿል።የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል የገለጸው ኮሚሽኑ ክስተቱ የጦር ወንጀል የመሆን እድሉ የሰፋ ሊሆን እንደሚችልም በቅድመ ምርመራ ሪፖርቱ ጠቁሟል።

ይሁንና በቦታው ያሉ የህክምና ባለሙያዎች በኮሚሽኑ የተጠቀሰው ቁጥር ስህተት አለበት ሲሉ የህክምና ባለሙያውን ቡድን የመሩት ዶክተር ስምኦን ደሳለኝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።እንደ ዶክተር ስምዖን አስተያየት ከሆነ በአካባቢው በተፈጠረው ጦርነት የተጎዱ ሰዎችን ለማከም ወደ አካባቢው ማምራታቸውን ተናግረው በማይካድራ ሆን ተብሎ ግድያ የተፈጸመባቸው ሰዎች ከ750 በላይ እንደሆነ በአይናቸው ማየታቸውን እና ይሄንን አሃዝም የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ላሰማራቸው መርማሪዎች መናገራቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ በበኩላቸው ጉዳዩን ለመመርመር ወደ ሰፍራው ያቀናው የምርመራ ቡድን መረጃዎችን ሐኪሞችን ጨምሮ በአካባቢው ካሉ የተለያዩ አካላትን ጠይቀው መመለሳቸውን ተናግረዋል።በምርመራው የተገኘውን መረጃ ከተለያዩ ቦታዎች ስለምንቀበል በራሳችን መመዘኛ አጣርተን ነው ይፋ የምናደርገው ሆኖም ግን በዚህ አሰቃቂ ግድያ ህይወታቸው ያለፉ ዜጎች ቁጥር 600 ብቻ ነው ብለን አልገለጽንም በቀጣይ ተጨማሪ እና ዋናው ሪፖርት ሲሰራ ትክክለኛው የሟቾች ቁጥር ይታወቃል ሲሉም ዶክተር ዳንኤል ምላሽ ሰጥተዋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ የትምህርት ሥልጠና ጥራት ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ባለሥልጣን የተቀመጠውን ዝቅተኛ መስፈርት አላሟሉም ያላቸውን 23 ትምህርት ቤቶች የሥራ ፈቃድ መንጠቁን ተናገረ።

የእውቅና ፈቃዳቸው የተወሰደባቸው 15 መዋዕለ ሕፃናት፣ 7 የመጀመሪያ ደረጃ እና 1 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ናቸው።ባለሥልጣኑ የእውቅና ፈቃዳቸውን የሰረዝኩት ከተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ በኋላ ነው ብሏል።ትምህርት ቤቶቹ በዚህ የትምህርት ዘመን ማስተማር እንደማይችሉ የባለሥልጣኑ ሥራ አስኪያጅ ሸዊት ሻንካ ተናግረዋል።ሥራ አስኪያጇ አክለውም፤ ለ60 ትምህርት ቤቶች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል ብለዋል።

በሌላ በኩል ለ574 ትምህርት ቤቶች የእውቅና ፈቃድ የታደሰላቸው ሲሆን 93 አዲስ ትምህርት ቤቶችም ወደሥራ እንደሚገቡ ሥራ አስኪያጇ ተናግረዋል።ወላጆች ልጆቻቸውን ሲያስመዘግቡ በቅድሚያ ትምህርት ቤቶች ፈቃድ ስለማግኘታቸው ማረጋገጥ እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።

ፈቃዳቸው የተሰረዘባቸውን ትምህርት ቤቶች በስም እንዲጠቅሱልን የጠየቅናቸው የባለሥልጣኑ ኃላፊዎች፣ ለየትምህርት ቤቶቹ በደብዳቤ የተነገራቸው መሆኑን እና ይህንኑም ራሳቸው ትምህርት ቤቶቹ ለማኅበረሰቡ እንዲያሳውቁ የተነገራቸው መሆኑን ተናግረዋል።በከተማዋ በአጠቃላይ ከ1,590 በላይ የግል ትምህርት ቤቶች አሉ ተብሏል።

[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
Today is the last day of Virtual Agrofood & Plastprintpack Africa 2020. It has indeed become a truly global event with a clear Africa focus. Considering that the event includes not only the core period from 23 - 26 November, but also a bonus period until 03 December, one can well imagine that the event will become a great success.

Only on the first day:
No fewer than 904 attendees have already become active users, out of the 2,001 meanwhile registered from 81 countries. The attendees networked with each other and of course with the

64 exhibitors from 17 countries participating
4,522 messages were exchanged
444 attendees attended the conference sessions
a total of 2,022 contacts were made
444 participants attended the panel sessions, presentations and product demos
The opening talk on how exhibitors, attendees & speakers can best benefit from the event was followed by 172 participants

You can still be part of this trade fair Today! Register now as an attendee here;, it's free of charge
የሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛ በመጥለፍ በተጠረጠሩ 7 የጄኔራል መኮንኖች ላይ ፖሊስ የጠየቀባቸው ተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ!

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ የልዩ ቀጠሮ ችሎት በሀገር ክህደት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የሚገኙት እነ ሜ/ጄ ገብረመድህን ፈቃዱን ጨምሮ 7 ግለሰቦች ፖሊስ የጠየቀባቸው ተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜን ፈቀደ።በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ ቡድን እነ ሜ/ጄ ገብረመድህን ፈቃዱ፣ ሜ/ጄ ይርዳው ገብረመድህን፣ ብ/ጄ ኢንሱ ኢጳጆ ኢንሱ ኢጳጆ ረሾን ጨምሮ 7 መኮንኖችን በሀገር ክህደት ብሎም ሕገ-መንግሥቱን እና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ በመጣል ወንጀል ነው የጠረጠራቸው።

ተጠርጣሪዎቹ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ ላይ የተደረገውን ጥቃት በመጠንሰስ ትልቅ ሚና እንደነበራቸው የምርመራ ቡድኑ ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ የልዩ ቀጠሮ ችሎት ባቀረበው ማመልከቻ ላይ ጠቅሷል።

የሰሜን ዕዝ የሬዲዮ መገኛ ተቋርጦ የጥቃት ሰለባ እንዲሆን፣ በሠራዊቱ መካከል መከፋፈል እንዲፈጠር የተለያዩ የወንጀል ተግበራትን መፈፀማቸውን የምርመራ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ መጥቀሱ ይታወቃል።ዛሬ ሁሉም ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ የምርመራ ቡድኑ በቀጣይ የምርመራ ሥራ 14 ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው አመልክቷል። ተጠርጣሪዎችም የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው አመልክተዋል።የግራ ቀኙን ክርክር የተከታተለው ችሎቱ 13 ቀን በመፍቀድ ውጤቱን ለመጠባበቅ ለኅዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በልደታ ክፍለ ከተማ ከ55ሺ ብር በላይ ሀሠተኛ ባለ200 የብር ኖቶች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

ከተያዘው የብር ኖት ባለፈ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ አስታውቋል።

ዛሬ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ተግባረድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ ግለሠብ አዲሱን ባለ200 የብር ኖቶ በመቶ ብር ለመቀየር በማፈላለግ እያለ ከህብረተሰቡ ለፖሊስ በደረሠው ጥቆማ መሠረት ግለሰቡ ከ7 ሺህ 400 ሀሠተኛ ባለ2መቶ የብር ኖት ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል።

በፖሊስ ከተያዘው አንድ ተጠርጣሪ መረጃ በመነሳት በተደረገው የክትትልና የኦፕሬሽን ስራ ከተያዘው ተጠርጣሪ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሶስት ተጠርጣሪዎች እና 48ሺህ 200 ሀሠተኛ ባለ2መቶ የብር ኖት በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መርማሪ ዋና ሳጅን በእምነት ግርማ ተናግረዋል።

ከአዲሱ የብር ኖት ቅያሬ ጋር ተያይዞ በርካታ አዲስ ሀሠተኛ የብር ኖቶች ተመሳስለው እየተሰሩ ወደ ህብረተሠሰቡ እየተሠራጩ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ትኩረት ሊሰጥበት እንደሚገባ ዋና ሳጅን በእምነት ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ ግብይት በሚያከናውኑበት ወቅት በአጭበርባሪ ግለሰቦች እንዳይታለልና እንዳይጭበረበር ጥንቃቄ ማድረግና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ መስጠት እንደሚገባም መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት አራት ወራት ከወጪ ንግዱ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ተገኘ!

የንግድና ኢንዱስትሪ በለፉት 4 ወራት ከወጪ ንግዱ 1ነጥብ7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 1ነጥብ1 ቢሊዮን እንዲሁም በጥቅምት ወር 280 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 258 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገልጸዋል፡፡

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
እስር ላይ የሚገኙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ሥነ-ባህሪ ኮሌጅ ዲን፣ እንዲሁም የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባል ዶ/ር ሁሴን ከድር የለገጣፎ ወረዳ ፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸዉን ቢጠብቅም እስካሁን እንዳልተለቀቁ ተነገረ።

ዶ/ር ሁሴን ከድር የተከሰሱት ከአርቲስት ሃጫሉ ግድያ ማግስት በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የተቀሰቀሰውና ለበርካታ ህይወትና ንብረቶች ውድመት በሃሳብና ድርጊት ረድተዋል የሚል ነው። ፍርድ ቤቱ ትናንት በዋለው ችሎት ላለፉት አምስት ወራት በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ዶ/ር ሁሴን ከድር በ10 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ፈቅዶ ነበር፡፡ይሁንና እስከ ዛሬ ማምሻ ድረስ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት ዶ/ር ሁሴን አለመለቀቃቸውን ጠበቃቸው አቶ ከድር ቡሎ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ሁሴን ከዚህ ቀደም በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው ሲታይ በቆየበት ወቅትም ፍርድ ቤት በዋስትና መብት ቢለቃቸውም ፖሊስ በሌላ ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁ በሚል ዳግም በለገጣፎ ክስ እንደመሰረተባቸው አቶ ከድር ተናግረዋል።በኦሮሚያ ክልል የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በተፈጠረው ሁከት የ170 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ከፍተኛ ግምት ያላቸው ንብረቶችም ጉዳት ደርሶባቸው በዚሁ የተጠረጠሩ ከ9000 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው አይዘነጋም፡፡

(DW)
@YeneTube @FikerAssefa
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ ጋር በሰላምና ደህንነት መስኮች የነበራቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ!

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ በሰላምና ደህንነት መስኮች እንዲሁም ሽብርተኝነትን በጋራ ለመከላከል ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ።
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ የሞሳድ ቢሮ ኃላፊ ጋር በዛሬው ዕለት ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከሞሳድ ጋር ትብብሩን በማጠናከር በአፍሪካ ቀንድ ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት፣ በቴክኖሎጂ፣ በአቅም ግንባታ ሥልጠና ዘርፍ ይበልጥ ተባብረው ለመሥራት ማቀዳቸው ተገልጿል።የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከሞሳድ የሚደረግለትን ሁሉን አቀፍ የአቅም ግንባታ እና የቴክኖሎጂ ድጋፎች በመጠቀም ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በመከላከል እና ከሥሩ በመንቀል ረገድ ያላት አቋም ጠንካራ መሆኑን የጠቀሱት የእስራኤል የሞሳድ ዳይሬክተር ጀነራል ሚስተር ዮሴፍ ኮ`ን ልዩ መልዕክተኛ እንዲሁም በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ የሞሳድ ቢሮ ኃላፊ የህዝቦች የጋራ ጠላት የሆነውን ሽብርተኝነትን በተቀናጀ ሁኔታ ለመከላከል ሞሳድ ከኢትዮጵያ አቻ የመረጃና ደህንነት ተቋም ጋር በትብብር እንደሚሰራና ድጋፋኑም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኮንሶ የተፈናቀሉ እርዳታ እየተጠባበቁ ነው!

በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ባለፈው ሳምንት የታጠቁ ሀይሎች አደረሱት በተባለው ጥቃትና ግጭት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን ገለጹ።ከዞኑ ሰስት ወረዳዎች ተፈናቅለው በተለያዩ ቀበሌያትና በአጎራባች ወረዳዎች ተጠልለው የሚገኙ ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ እንዳሉት ከቀያቸው ከወጡ ቀናትን ቢያስቆጥሩም እስከአሁን ግን ያናገራቸውም ሆነ ድጋፍ ያደረገላቸው አካል የለም።የኮንሶ ዞን የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው ከዞኑ ለተፈናቀሉ ከ94 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የቀለብና የአልባሳት ድጋፍ እንዲቀርብ ለደቡብ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በማቅረብ ምላሽ እየጠበቁ እንዳሉ ተናግረዋል።ተፈናቅለዋል በሚል ከዞኑ የቀረበው ቁጥር የተጋነነ ነው የሚሉት የደቡብ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጋንታ ጋሞአ በበኩላቸው የተረጂዎችን ትክክለኛ ቁጥር በባለሙያዎች እየተለየ ይገኛል ብለዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በኤልቲቪ ቴሊቪዥን ጣቢያ ታቀርባቸው በነበሩ አነጋጋሪ ቃለ መጠየቆቿ የምትታወቀው ቤተልሔም ታፈሰ፤ የስራ እና የግል ህይወቷን የተመለከቱ ማስታወሻዎችን ያሰፈረችበት መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።

Via Ethiopia Insider
@Yenetube @Fikerassefa
በቄለምና ምዕራብ ወለጋ የተወሰኑ ስፍራዎች የኢንተርኔትና ስልክ መቋረጥ!

በቄለም ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ ዞን የተወሰኑ ስፍራዎች የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት ከጠፋ ከሁለት ሳምንት በላይ ሆኖታል።

የግምቢ እና ነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ባለመኖሩ ከዘመዶቻቸው ጋር መገናኘት እንዳልቻሉ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

የምዕራብ ወለጋ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኤሊያስ ኡመታ በዞናቸው ስር  ስምንት በሚደርሱ ወረዳዎች የሞባይል ስልክ አገልግሎት መቋረጡን እና ችግሩን ለመቅረፍ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር እየተነጋሩ እንደሆነ አስረድተዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮምዩንኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በበኩላቸው አገልግሎቱ ስለመቋረጡ ምክንያት እንደማያውቁ ገልጸው በጸጥታ ችግርም ሆነ በሌላ ምክንያት የቴሌኮም አገልግሎት እንዲቋረጥ የተላለፈ ውሳኔም በመንግስት በኩል የለም ብለዋል። 

ባለፈው ዓመትም  ከታህሳስ 24 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት ያህል በወለጋ ዞኖችና በተወሰኑ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወረዳዎችም  የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱ የክልሉ መንግስት የአካባቢውን የጸጥታ ችግርን ለመቅረፍ ሲባል መቋርጦ ገልጾ ነበር።

(DW)
@Yenetube @Fikerassefa
ዋልታ ቴሌቪዥን ሰበር ዜና ይኖረናል ካለ አንድ ሰዓት አልፎታል።
የዋልድባው መነኩሴ ነጻ ወጥቷል ወዳሉት ገዳም መመለሳቸውን ተናገሩ!

ከትላልቆቹ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተከርስቲያን ገዳማት የዋልድባ ገዳም ተወካይ የነበሩት አባ ገብረ ኢየሱስ ኪዳነ ማርያምን ዋልድባ ገዳም ነጻ በመውጣቱ ወደ ገዳሙ መመለሳቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡

አባ ገብረየሱስ በቀደመው መንግሥት እስርና እንግልት የደረሰባቸው መሆኑን የገለጹልን ሲሆን፣ አካባቢው ነጻ በመውጣቱ፣ ከተባረሩበትና እንዳይገቡ ተከልክለው ወደ ነበረበት የዋልድባ ገዳም ሰሞኑን የተመለሱ መሆኑንም አጫውተውናል፡፡

የዋልድባ ገዳም፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተከስቲያን ከአሏት ታላላቅ ገዳማት አንዱ መሆኑ ይነገርለታል፡፡

አካባቢውንና የፌዴራል መንግሥቱን ይቆጣጠር ከነበረው፣ የቀደመው መንግሥት ጋር በተፈጠረ ግጭት፣ ከታሰሩና ከገዳሙ እንዲባረሩ ከተደረጉ መነኮሳት መካከል፣ መጋቢ ስርዓት አባ ገብረየሱስ ኪዳነ ማርያም አንዱ ናቸው፡፡ የዋልድባ ገዳም አብረንታንት ቤተ ሚናስ ተወካይ ሆነው ለዓመታት አገልግለዋል። የገዳሙን ቦታዎች ለስኳር ፋብሪካ መታሰቡን በመቃወማቸው እንደ ፖለቲካ እስረኛ በሽብር ወንጀል ተከሰው በማዕከላዊ እስር ቤትና ኋላም በቅሊንጦ ወህኒ ቤት መቆየታቸውንም ገልጸዋል፡፡ መነኩሴው አባ ኪዳነ ማርያም፣"የዋልድባና የህወሓት ፍጥጫ" የሚል መጽሀፍ አውጥተዋል፡፡

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
Audio
በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና በአማራ ልዩ ኃይል ቁጥጥር ሥር ባለቸው አላማጣ ከተማ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ለህግና ማስከበርና ጸጥታ ጉዳዮች ቀዳሚ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚንቀሳቀስ አረጋገጠ፡፡

አዲስ ለተመረጠው ጊዜያዊ አስተዳደር ህዝቡ ሙሉ ድጋፉን እየሰጠ መሆኑን አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የገለጹ አመራሮች ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ቅዳሜ በአላማጣ ከተማና በዙሪያው ባሉ የገጠር ቀበሌዎች በተደረገው ውይይት የራያ አላማጣን 15 የገጠር ቀበሌዎች እንዲሁም የአላማጣ ከተማን አራት ቀበሌዎች በጊዜያዊነት የሚያስተዳድሩ 114 ሰዎች መመረጣቸው ይታወሳል፡፡የዚህ ዜና ዝርዝር የድምፅ ዘገባ ከላይ ተያይዟል።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጆ ባይደን መሸነፋቸውነ ሊቀበሉ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጡ።ትራምፕ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ "ጆ ባይደን በ 'ኤሌክቶራል ኮሌጅ' የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆኑ ከተረጋገጠ መሸነፌን ልቀበል እችላለሁ" ብለዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa