YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአሶሳ ከተማ ጥቃት ለማድረስ ሲሉ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ 152 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ!

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልላዊ መንግስት አሶሳ ከተማ ጥቃት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ 152 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡በአሶሳ ከተማ በቅርቡ የሕወሓትን የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው ጥቃት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር ውለዋል የተባሉት 152 ተጠርጣሪዎች ትናንት በአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አብዱልሙኒየም ኡስማን ግለሰቦቹ ከህወሃት በተቀበሉት ተልዕኮም በሰሜን እዝ ላይ የደረሰውን ጥቃት በአሶሳ ከተማና አካባቢው ለመድገም ሲዘጋጁ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን ተናግረዋል፡፡ከተጠርጣሪዎቹ ጋር የተለያዩ የባንክ ደብተሮች፣ የጦር መሳሪያ፣ ጥሬ ገንዘብና ሌሎች ማስረጃዎች ፖሊስ ማግኘቱን ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል ሲሉም ጠቅሰዋል።

አክለዉም የተጠረጠሩበት ወንጀል ዋስትና የማያሰጥ መሆኑን ተከትሎ በማረሚያ ቤት ሆነው የፍርድ ሂደቱን እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል ሲሉ ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ ያቀረበውን የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤቱ መፍቀዱንም አቶ አብዱልሙኒየም አስታውቀዋል፡፡

Via @addiszeybe
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
Virtual agrofood & plastprintpack 2020 kicked off yesterday with a brilliant start and lived up to its name: A truly global event with a clear Africa focus.

Only on the first day
- no fewer than 904 attendees have already become active users, out of the 2,001 meanwhile registered from 81 countries. The attendees networked with each other and of course with the 63 exhibitors from 17 countries participating
- a total of 2,022 contacts were made
- 4,522 messages were exchanged
- 444 participants attended the panel sessions, presentations and product demos
- The opening talk on how exhibitors, attendees & speakers can best benefit from the event was followed by 172 participants

on today's conference programme we will have 1-panel discussions, 19 presentations, and 3 product demos! Don't miss it!
Not yet registered? register today for free as an attendee right here. https://reg
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር እና ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በአሁኑ ወቅት ቤተሰቦቻቸው በትግራይ ክልል የሚገኙ ወገኖችን ለማገናኘት አስቀድመው ካሳወቋቸው ተጨማሪ ሁለት አዳዲስ ቁጥሮችን ይፋ አደረጉ።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር እና ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በቀድሞዎቹ ቁጥሮች 09 43 12 22 07 እና 0115 52 71 10 መረጃ እየተቀበሉ የቆዩ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ነገር ግን እነዚህ ስልክ ቁጥሮች በርካታ ጥሪዎች እያስተናገዱ በመሆናቸው መረጃ ሰጪ ወገኖች እየተቸገሩ በመሆኑ፤ ችግሩን ለመቅረፍ ተጨማሪ ስልክ ቁጥሮችን ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡

ተጨማሪዎቹ ቁጥሮችም፡- 09 80 19 27 06 እና 09 80 19 27 09 ናቸው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ለታገዱት 38 ድርጅቶች ገንዘብ ገቢ ማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በባንክ በኩል እንዲፈጽም ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አሳሰበ!

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት እና ዘርን መሰረት ያደረገ ኹከት እና ብጥብጥ እንዲነሳ በማድረግ ሂደት ውስጥ እንዲሁም ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ በተፈጸመ ህገ-ወጥ ተግባር ውስጥ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በወንጀል ተግባር ተሳትፈዋል በሚል ተጠርጥረው ምርመራ የተጀመረባቸው ከህወሓት ጋር ግንኙነት ያላቸው 38 ድርጅቶች መታገዳቸው ይታወቃል፡፡

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ላይ እንዳለው ‹‹የድርጅቶቹ የባንክ ሂሳብ መታገዱን ተከትሎ ለድርጅቶቹ ገቢ የሚሆኑ ገንዘቦች በባንክ በኩል መከፈሉ ቀርቶ በእጅ ለእጅ ወይም በካሽ እንዲከፈላቸው የሚጠይቁ እና የሚቀበሉ የታገዱ ድርጅቶችን አመራሮች እና ክፍያውን በዚሁ መልክ የሚፈጽሙ ግለሰቦች እና ተቋማት እንዳሉ ደርሰንበታል፡፡›› ብሏል

‹‹ድርጊቱ የምርመራ ስራውን የሚያደናቅፍ፣ ለግብር ስወራ ወንጀል ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር እና ከብሄራዊ ባንክ መመሪያ ድንጋጌዎች ጋርም የሚጋጭ እና በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር በመሆኑ የድርጅቶቹ አመራሮች እና ሰራተኞች እንዲሁም በዚሁ መልክ ክፍያዎችን እየፈጸማችሁ ያላችሁ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያሳሰብን በድርጊቱ የሚሳተፉ ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን በምርመራ አጣርተን በህግ እንዲጠየቁ የምናደርግ መሆኑን እንገልጻለን›› ሲልም ጨምሮ ገልጿል፡፡

‹‹ማንኛውም ወደ ታገዱት ድርጅቶቹ ገንዘብ ገቢ ማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በባንክ በኩል እንዲፈጽም እያሳሰብን የሚኖሩትን ጥያቄዎች እና ጥቆማዎች ለተቋማችን ማቅረብ የሚችል መሆኑን አክለን እናሳውቃለን ›› ሲል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አውቶብስ የሙከራ ትግበራ ሊደረግ ነው!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የፋይናንስ እና የቴክኒካል ድጋፍ ለማግኘት ከተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ የተጠቆመ ሲሆን በዚህ መሰረት የኤሌክትሪክ አውቶብስ በከተማው ላይ የሙከራ ትግበራ ለማከናወን ተቀማጭነቱ እንግሊዝ አገር ካደረገው C40 Cities ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ ይገኛል።ቢሮው ከC40 Cities ጋር በመተባበርም የኤለክትሪክ አውቶብስ የሙከራ ትግበራ በከተማ ፈጣን አውቶብስ (BRT) ኮሪደር ላይ እንዴት እንደሚተገበር በተመለከተ አለማቀፋዊ የኹለት ቀናት ቨርቹዋል አውደ ጥናት ማካሄዱም ለማወቅ ተችሏል።የከተማ ፈጣን አውቶብስ (BRT) የሚጠቀምባቸውን በናፍጣ የሚሰሩ እና ሌሎቹን አዉቶቡሶች በቀጣይ ወደ ኤሌክትሪክ የመቀየር እቅድ እንደተያዘም ተነግሯል፡፡

Via Addis Ababa City PS
@YeneTube @FikerAssefa
ደቡብ ሱዳን በየትኛውም አጋጣሚ ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን መቆሟን አስታወቀች፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ በጁባ ተወያይተዋል፡፡ሀገራቸው ሉዓላዊ ሆና ቆመችው ኢትዮጵያ በሰራችው ሥራ መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ ጁባ ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን መሆኗን ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው መግለጻቸውን በሀገሪቱ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቋል፡፡

አቶ ገዱ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ሕግ የማስከበርና ሉዓላዊነቷን የማስከበር ሥራዋን እየሰራች መሆኑን ለደቡብ ሱዳን መንግስት አስረድተዋል፡፡

ሕግ የማስከበሩና ሉዓላዊነትን የማስጠበቁ ሥራ የመንግስት ግደታ መሆኑን ያነሱት አቶ ገዱ ይህ በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል ማለታቸውን ኤምባሲው አስታውቋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ የደህንነት አማካሪ በጁባ ቆይታቸው ከደቡብ ሱዳኑ ደህንነት ኃላፊ ጀነራል አኮል ኮር እና በጁባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ጋር መገናኘታቸው ተገልጿል፡፡

አቶ ገዱ ለከሰሞኑ በጅቡቲና በሞቃዲሾ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በጣሊያንና በቤልጀም ከሀገራትና ተቋማት መሪዎች መሪዎች ጋር መወያየታቸው ይታወሳል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የሰብዓዊ ረድዔት ድርጅቶች በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውጊያውን ሸሽተው ወደሱዳን መግባታቸውን የቀጠሉትን ስደተኞች ለመርዳት ጥረታቸውን እያጠናከሩ መሆናቸውን ገለፁ።

በሱዳን የተመድ የስደተኞች ኮሚሽን የአጣዳፊ እርዳታ አስተባባሪ ዬንስ ሄሰማን በየቀኑ በሽዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ድንበር አቋርጠው ሱዳን እየገቡ ነው ብሏል።

የዩኤንኤችሲአር የስደተኛ ተቀባይ ሰራተኞች እስካሁን ከአርባ ሽህ በላይ ኢትዮጵያውያን መመዝገባቸውን ገልጿል።

ስደተኞቹ ድንበር የሚያቋርጡት በሱዳን ከሰላ ክፍለ ግዛት ሃምዲያት፣ በገዳሪፍ ክፍለ ግዛት በሉግዲ የድንበር ኬላዎች በኩል መሆኑን፤ በሌላኛው በደቡቡ አቅጣጫ በአደራፊ በኩል መግባት ጀምረዋል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ሰባት መቶ የሚሆኑ ገብተዋል ብሏል።

ውጊያው ከቀጠለ የሚሰደደው ሰው ቁጥር ፈጥኖ ሁለት መቶ ሽህ ሊደርስ እንደሚችል የተመድ ባለሥልጣን አመልክተዋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
ሰበር ዜና!!

ዲያጎ ማራዶና ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ!

የቀድሞው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና በ 60 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ ከአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ጋር የ 1986 የዓለም ዋንጫን ያሸነፈው ማራዶና በልብ ህመም ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የአርጀንቲና መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ማራዶና ከሁለት ሳምንታት በፊት ነበር ከሆስፒታል መውጣቱ የሚታወስ ሲሆን ቀዶ ጥገና አድርጎ እንደነበርም ተዘግቧል፡የቀድሞው የእግር ኳስ ኮከብ ማራዶና ለአርጀንቲናው ቦካጁኒየርስ፣ለጣሊያኑ ናፖሊና ለስፔኑ ባርሴሎና እና ለሌሎችም ክለቦችም መጫወቱ ይታወሳል፡፡የአርጀንቲናን ብሔራዊ ቡድንን በአምበልነትና በአሰልጣኝነት የመራው ማራዶና በ1986 ዓለም ዋንጫ በእንግሊዝ ብሔራዊ ላይ በእጁ ባስቆጠራት ግብ ብዙዎች ያስታውሱታል፡፡ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና በእግር ኳስ ብቃቱ በርካቶች የሚወዱት እንደሆነ የደይሊ ሜል ዘገባ ያመለከታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰሩ አንዳንድ የትግራይ ተወላጅ ሠራተኞች ዕረፍት እንዲወስዱ ወይም ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ እንደታዘዙ ከምንጮቼ ሰምቻለሁ ሲል ቢቢሲ ዐለማቀፍ ጣቢያ ዘግቧል፡፡ በመንግሥት ጸጥታ ተቋማትም የትግራዋይ ተወላጆች በብሄር ማንነታችን ተለይተን ትጥቅ እንድንፈታ ተደርገናል ማለታቸውን አመልክቷል፡፡ አንዳንዶቹ በሱማሊያ ሰላም ማስከበር የተሠማሩ ወታደሮችና ከፍተኛ መኮንኖች ናቸው- ብሏል ዘገባው፡፡ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከፍተኛ አማካሪ ማሞ ምኅረቱ ግን፣ ርምጃው ከከሕወሃት አክራሪዎች ጋር ግንኙነት ባላቸው አባላት ላይ ብቻ እንዲሆን ለጸጥታ ተቋማት ግልጽ መመሪያ እንደተሰጠ ለጣቢያው ተናግረዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ፌደራዊ መግሥት ጦር ትግራይ ዉስጥ «ሕግ ለማስከበር» ያለዉ የጦር ዘመቻ የመጨረሻ ግብ  በክልሉ ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት ማስፈን እንደሆነ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።በሚንስቴሩ የሕብረት ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ሹማ ኦብሳ  በተለይ ለዶይቼ ቬለ እንደነገሩት ወታደራዊ ዘመቻዉ "መገባደጃና መጨረሻዉ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።የፌደራሉ መንግስት ጦርና የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ታጣቂዎች በገጠሙት ጦርነት ሠላማዊ ሰዎች እንዳይጎዱ ጥንቃቄ ያደርጉ ዘንድ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች እየተማፀኑ ነዉ።ኮሎኔል ሹማ እንደሚሉት ጦራቸዉ ሰላማዊ ዜጎችን ከታጣቂዎች «ለመለየት» አበክሮ ይጥራል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሆሮ ቡሉቅ ወረዳ እና በሰሜን ሸዋ ደራ ወረዳ ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ!

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሆሮ ቡሉቅ ወረዳ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች የኦሮሞ ነፃነት ሸማቂዎችን ከመደገፍ ጋር በተያያዘ ሁለት ወጣቶችንና አንድ መምህር ገደሉ ሲሉ ከቤተሰብ መካከል የቅርብ ዘመድ ነኝ ያሉ ግለሰብ ገለፁ።

የወረዳው ፀጥታና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ግለሰቦቹ ስለመገደላቸው ለፅህፈት ቤታቸው ያሳወቀ ባለመኖሩ ምንም አይነት ምርመራ አለመደረጉን አስታውቋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በሰሜን ሸዋ ደራ ወረዳም አንድ ግለሰብ በፀጥታ ሀይሎች ከተያዘ በኋላ ተገድሎ መገኘቱን አንድ የዐይን እማኝ ገልጿል።

የደራ ወረዳ ፀጥታና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ይህ ተገደለ የተባለው ግለስብ በወረዳችንም አልታሰረም፤ በወረዳችን የተገደለ ሰውም የለም ብለዋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትላንት ማታ ታጋይ ገብረ ገብረፃዲቅ ለትግራይ ቴሌቪዥን የሰጠው መግለጫ።
@Yenetube @Fikerassefa
የህወሃት የእኩይ ተግባር ዕቅድ ይፋ ሆነ! | ፌደራል ፓሊስ

የህወሃት የጥፋት ቡድን በማይካድራ የፈፀመውን አይነት እኩይ ተግባር በመቀሌ ለመድገም እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ፡፡

ኮሚሽኑ የቡድኑ እኩይ ዕቅድ መረጃ እንደደረሰውም አስታውቋል፡፡በትግራይ ክልል የተጀመረው ሕግን የማስከበር እርምጃ ሁለተኛ ምእራፍ ተጠናቆ የመጨረሻውና ሦስተኛው ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱንም ገልጿል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ፅንፈኛው የህወሃት ጁንታ ቡድን መቀሌ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ያልሆኑት ሰዎች ላይ አሰቃቂ ግድያ ለመፈፀም፣ ንብረታቸውን በመዝረፍ ለማቃጠል፣ የመከላከያ ሠራዊት የደንብ ልብስ በመልበስ ሰዎች ላይ በድንገት ተኩስ በመክፈት አስነዋሪ ድርጊት ለመፈፀም ማቀዱን ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡

ቡድኑ ሰሞኑን በማይካድራ የፈፀመውን አስነዋሪና አሰቃቂ ጭፍጨፋ ለመድገም እቅድ አውጥቶ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንና ይህንን እኩይ ተግባር ከፈፀመም በኋላ ድርጊቱ የተፈፀመው በመንግስት ነው ብሎ በሚዲያ ለማሰራጨት የተዘጋጀ መሆኑን ከህዝብ መረጃ ደርሶኛል ነው ያለው ኮሚሽኑ።

በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እና ዓለምአቀፍ ማህበረሰብ ይህንን የጥፋት ሴራ ተከትሎ ጁንታው ቡድን ሊያሰራጭ የተዘጋጀውን የሃሰት ፕሮፖጋንዳና ይህንን እኩይ ተግባር አስቀድሞ እንዲረዳና ተቀባይነት ያጣ ዘንድ የበኩላችሁን ጥረት እንድታደርጉ ማሳሰብ እንወዳለን ሲል አስውቋል።ህዝቡ ማንኛውንም የተለየ እና አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ሲያይ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡

Via:- Federal Police
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ አበባ ለምትገኙ የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች በሙሉ በየአከባቢያችሁ ባለው የአገልግሎት መስጫ ማዕከል መገልገል እንደምትችሉ ገልጿል።

አገልግሎቱን በተለያዩ አማራጮች ለማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ እንደሆነና የዝግጅት ሥራው ተጠናቆ በትላናትናው ዕለት ከግማሽ ቀን በኃላ በሁሉም አገልግሎት መስጫ ማዕከላት መደበኛ አገልግሎት መጀመሩን ማሳወቁ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ በዛሬው ዕለት ባደረግነው ምልከታ በተለይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች በካሳንቺስ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በብዛት ተሰልፈው አገልግሎት ለማግኘት እየተጠባበቁ መሆኑ ተስተውሏል፡፡

ሆኖም አገልግሎቱ በአዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን አውቃችሁ፤ ወቅታዊ የኮሮና ቫይረስ ውረርሽኝን ከመከላከል አኳያ እንዲሁም ጊዜ ለመቆጠብ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል አገልግሎቱን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁሉም የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ካርድ መሙላትም ሆነ ሌሎች የቅድመ ክፍያ የተመለከቱ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት]
@YeneTube @FikerAssefa
የመጨረሻው የዘመቻው ምዕራፍ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ!

ለሕወሓት 'ወንጀለኛ ቡድን' የተሰጠው በሰላም እጅ የመስጫ የ72 ሰአት ጊዜ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል።በዚህም ሕግ የማስከበር ዘመቻው የመጨረሻው ምዕራፍ መጀመሩን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት።በተሰጠው የ72 ሰአታት ጊዜም በሺዎች የሚቆጠሩ የወንጀለኛው ቡድን ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አባላት እጃቸውን ለመከላከያ ሠራዊት መስጠታቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስታውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የተዘረፉ የኢትዮጵያ ቅርሶችን የሚያስመልስ የቅርስ አስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴ ሊቋቋም ነው።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ እንደገና ደሳለኝ በአለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የተዘረፉ ቅርሶችን የሚያስመልስ የቅርስ አስመላሽ ብሄራዊ ኮሚቴ ሊያቋቁም መሆኑን ተናግረዋል።የኢትዮጵያ ቅርስ በተለያዩ ጦርነቶች እንዲሁም በዝርፊያ በተለያዩ አፍሪካን ጨምሮ በአለም ሀገራት ይገኛሉ።

እነዚህን ኢትዮጵያዊ የሆኑ ቅርሶችን ነው ኮሚቴው ለማስመለስ የሚሰራው ነው ያሉት አቶ እንደገና።የብሄራዊ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴው ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ ባለሙያዎች ያሉት መሆኑንም ተሰምቷል።የህግ ባለሙያዎች የታሪክ ምሁራን አርኪዎሎጂስቶች የኪነጥበብ ሰዎች እና ሌሎችንም አካቷል።ኮሚቴው በዛሬው ዕለት ተቋቁሞ የራሱን ሊቀመንበርና የየደረጃ ሀላፊዎችን ይሾማል ተብሏል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በጦርነት ቀጠና ውስጥ ያለው የመተማና ሑመራ አካባቢዎች የሰሊጥ ምርት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መሰብሰቡ ተገለጸ።

ከፍትኛ የውጭ ምንዛሬ ከሚያስገኙ የግብርና ምርቶች ውስጥ ሰሊጥ አንዱ ሲሆን በተለይም በእስያ እና አውሮፓ አገራት ፋብሪካዎች ተፈላጊ ነው።በሰሜን ኢትዮጵያ በተጀመረው የህግ ማስከበር ዘመቻ ምክንያት ሰብሉ ሳይሰበሰብ ለብክነት ይዳረጋል የሚል ሰፊ ስጋትም ነበር።ይሁንና በመተማና ሁመራ አካባቢ ያለው የሰሊጥ ምርት ከ92 በመቶ በላይ መሰብሰቡን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።በሚኒስቴሩ የሰብል ልማት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኢሳያስ ለማ እንዳሉት በዓመቱ የሰሊጥ ምርት ተሰብስቧል፡፡

በመላ አገሪቱም ከ13 ሚለየን ሄክታር በላይ መሬት በሰሊጥ የተሸፈነ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው የሰሊጥ ምርት የሚገኘው በሁመራ እና መተማ አካባቢዎች ነው።በኦሮሚያ፣ደቡብ እና ጋምቤላ ክልል ያለው የሰሊጥ ምርትም ከ70 በመቶ በላይ መሰብሰቡ ተገልጿል፡፡በተያያዘ ዜናም ቀድመው የሚደርሱት የአብዛኛው የቆላማ አካባቢዎችም ስንዴን ጨምሮ በቆሎና ጤፍ እየተሰበሰበ ይገኛል ያሉን ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ማሽላ እየደረሰ ይገኛል ብለዋል።በቀጣይ በአብዛኛው ሰብል የሚሰበሰበው ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ መሆኑን ያነሱልን አቶ ኢሳያስ በዚህ ጊዜ ውስጥ በደጋማው የሃገሪቱ ክፍል ላይ የሰብል መሰብሰቡ ሂደቱ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ሕግና ስርዓትን በማስከበሩ ሂደት የሚስተጓጎል የልማት ስራ አይኖርም አሉ፡፡

በበረሃ አንበጣ ምክንያት የታጣውን የመኸር ምርት ለማካካስ ለመስኖ ልማት ትኩረት እንደተሰጠም ተናግረዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት የፌደራል መንግሥት ሕግን ለማስከበር በጀመረው ስራ የአማራ ክልል ልዩ ሃይል እና ሚሊሻ ለመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረጉ ነው፡፡ከዚህ ሕግ የማስከበር ስራ ጎን ለጎን የልማት ስራዎች ሳይስተጓጎሉ እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡በበረሃ አንበጣ፣ በጎርፍ እና በልዩ ልዩ ምክንያቶች የታጣን የመኸር ምርት ለማካካስ ለመስኖ እርሻ ትኩረት እንደተሰጠም ጠቅሰዋል፡፡ባለሃብቶች ለመስኖ ልማቱ የሚውሉ የውሃ ፓምፖችን ለአርሶ አደሮች እንዲያቀርቡ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ መናገራቸውን የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት መረጃ ጠቅሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ህዳሴ ግድብ በያዝነው አመት ሰኔ ወር ላይ የመጀመሪያውን ዙር ሃይል ማመንጨት እንደሚጀምር የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሩ ዩሲኤል ከተሰኘ የዩናይት ኪንግደም ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎችና ተማሪዎች ጋር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ተወካይ በተገኙበት ኢትዮጵያ በታዳሽ ሃይል ልማት ዘርፍ የምታከናውናቸውን ተግባራት በተመለከት ያላቸውን ልምድ ባካፈሉበት መድረክ ነው ይህንን የተናገሩት።

[ኤፍ ቢ ሲ]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢሰመኮ ለንጹሃን ደህንነት መጠበቅ እና ለሰብዓዊ ድጋፎች መድረስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ በድጋሚ አሳሰበ!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሁንም ቢሆን ለንጹሃን ደህንነት መጠበቅ እና ለሰብዓዊ ድጋፎች መድረስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ በድጋሚ አሳሰበ፡፡ኮሚሽኑ በተያዘው ወር መባቻ የሲቪል ሰዎች ደህንነት አጠባበቅን አስመልክቶ ያስተላለፈውን መልዕክት የሚመለከታቸው ወገኖች በሙሉ እንዲያከብሩት በድጋሚ ጠይቋል።ግጭቱ አሁን በደረሰበት ደረጃም ላይ ቢሆን ሰላማዊ መፍትሔዎች ያስፈልጋሉ ያለው ኮሚሽኑ የሰብአዊ እርዳታ እና አገልግሎቶችን በአፋጣኝ ተግባራዊ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ የሰብአዊ ዕርዳታ ጉዳይ ዴስክ እንዲቋቋም ሕዳር 4 ቀን 2013 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቅርቦ ነበር፡፡

ዴስኩ ምናልባትም በሃገር መከላከያ ሰራዊቱ እና/ወይም በፌደራል መንግስት በተለይ የትግራይ ክልልን በተመለከተ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሰረት ለመቋቋም የሚችል ነው እንደኮሚሽኑ ገለጻ፡፡በተጨማሪም ኮሚሽኑ ልክ እንደማይካድራው ሁሉ በጦርነቱ የተከሰቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንደሚያጣራ እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ እንዲሁም ከግጭቱ ጋር በተያያዘ የተከሰቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ስጋቶችን እንደሚከታል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa