YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ከወቅቱ የህግ ባስከበር ዘመቻ ጋር ተያይዞ ተፈላጊ ግለሰቦችን የውጭ መንግስታት አሳልፈው እንዲሰጡ መንግስት እንደሚጠይቅ አስታወቀ።በጉዳዩ ላይ ተጠይቀው ማብራሪያ የሰጡት ዋና አቃቤ ህግ ጌዲዎን ጢሞቲዎስ እንደገለፁት ከህግ ማስከበር ሂደቱ ጋር ተያይዞ የሚፈለጉ ግለሰቦችን አሳልፈው እንዲሰጡን አገራትን እንጠይቃለን ብለው። እስካሁን ይፋዊ ጥያቄ አላቀረብንም ብለዋል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል በኦነግ ሸኔ ላይ በተወሰደ እርምጃ 160 የሚሆኑት ሲደመሰሱ፣ 68 በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም 1 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ለቡድኑ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ እና 104 የሚሆኑት ከህወሓት ቡድን ጋር በቀጥታ ግንኙነት የነበራቸው መሆኑ ተረጋግጦ በቁጥጥር ስር ውለዋል እንዳሉ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

'ሽፍታው' በሚንቀሳቀስባቸውን ዞኖች የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ጠንካራ ስራ እየተሰራ እንዳለም ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡በቦረናና ጉጂ ዞን ቡድኑን ለመያዝ ከአባ ገዳዎችና ነዋሪዎች ጋር እየተሰራ እንዳለም ገልፀዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን በኮሌራ በሽታ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በደቡብ ብሄር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን በተከሰተ  የኮሌራ በሽታ 75 ሰዎች መጠቃታቸውን የዞኑ ተቅማጥና ትውከት ህክምና ምዕከል አስተባባሪ አቶ ስዩም ከበደ ለአዲስ ዘይቤ ገልፀዋል፡፡

 በሶስት ቀናት ውስጥ በተደረገው ምርመራ በሽታው የ5 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል፡፡ግለሰቦቹ ህክምና ቦታ ከመድረሳቸው በፊት ህይወታቸው ማለፉን አቶ ስዩም አክለዋል፡፡በአሁን ሰዓት 29 የሚሆኑ ህሙማን በዞኑ ሆስፒታል ውስጥ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑንም ገልፀዋል።

የክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይረክተር አቶ እንዳሻው ሽብሩ በበኩላቸው በሽታው የተነሳው በዳውሮ ዞን ዋና ከተማ ተርጫ አካባቢ መሆኑን በመግለፅ በሽታውን በፍጥነት መቆጣጠር ካልተቻለ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንደሚሰራጭ አሳስበዋል።

Via @addiszeybe
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮሳትን ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ለማስገባት 20 ሺህ ወጣቶች በቴክኒክና ሙያ ተቋማት እንደሚሰለጥኑ ተገለጸ።

የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እና ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጁትና ኢትዮሳትን ወደ ስራ ለማስገባት ለወጣቶች የሚሰጥ ስልጠና ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ እንደገለጹት፣ ሀገራችን የራሷ የሆነ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት የሌላት በመሆኑ ከብሮድካስት ስራዎች አኳያ በሌሎች ሀገራት ላይ ጥገኛ እንድንሆን ከማስገደዱ ባለፈ ከተለያዩ አካባቢ ለሚሰራጩ አፍራሽ ይዘት ላላቸው ሚዲያዎች ተጋላጭ እንድንሆን አድርጎናል ብለዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ባለስልጣኑ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ ይገኛል ሲሉ በመድረኩ ላይ ተናግረዋል።በዚህም SES ከተባለ የሳተላይት አገልገሎት አቅራቢ ጋር በተደረሰ ስምምነት NSS-12 ላይ ኢትዮሳት ፕላትፎርምን ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።ፕላትፎርሙን በመላ ሀገሪቱ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ለማስገባት 20 ሺህ የሚሆኑ ወጣቶችን በዲሽ ማዞር ስራ ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማሰልጠንና ወደ ስራ ማስገባት ያስፈልጋል ሲሉ አክለዋል።የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት በበኩላቸው፣ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቶ በሁሉም ክልሎች ሰልጣኞችን የማሰልጠን ስራ እንደሚሰራ መግለፃቸውን የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ መረጃ ያመለክታል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ራሳቸውን ከመድፍ ጥቃት እንዲጠብቁ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ብቻውን በቂ እንዳልሆነ የሂውማን ራይተስ ዎች ዋና ዳይሬክተር ኬኔት ሮዝ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡ሠራዊቱ በከተማዋ የሚቆዩትን ሰላማዊ ነዋሪዎች ጭምር ከአደጋ የመጠበቅ ሃላፊነት አለበት እንጅ፣ ዛቻ መሰንዘር ትክክል አይደለም በማለትም አክለዋል ዳይረክተሩ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የአላማጣ ከተማና ዙሪያ የገጠር ቀበሌዎች ጊዜያዊ አስተዳደር መቋቋም

በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ሥር በሚገኙት የአላማጣ ከተማና ዙሪያ የገጠር ቀበሌዎች ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋቁሟል፡፡ጊዜያዊ አስተዳደሩ የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ ከማስከበር ባለፈ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች እንዲቀጥሉ ያደርጋል ብለዋል፡፡ከራያ አላማጣ ተፈናቅለው በቆቦ መጠለያ ሰፍረው የነበሩ የአካባቢው ተወላጆች ቃል አቀባይ ሰሎሞን ቀለሙ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ እንደገለጹት ባለፈው ቅዳሜ በአላማጣ ከተማና በዙሪያው ባሉ የገጠር ቀበሌዎች በተደረገው ውይይት የራያ አላማጣን 15 የገጠር ቀበሌዎች እንዲሁም የአላማጣ ከተማን አራት ቀበሌዎች በጊዜያዊነት የሚያስተዳድሩ 114 ሰዎች ተመርጠዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኤርትራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎቹ በቤት ውስጥ እንዲቆዩ አሳሰበ።

አሜሪካውያን አሁንም ጥንቃቄ እንዳይለያቸው እና የግድ አስፈላጊ ካልሆነ ጉዞ እንዳያደርጉም መክሯል። ኤምባሲው ማሳሰቢያውን የሰጠው በአስመራ ለሚገኙ ዜጎቹ ዛሬ ሰኞ ህዳር 14 ምሽት ባሰራጨው የማስጠንቀቂያ መልዕክት ነው። ለማሳሰቢያው መነሻ ምክንያት የሆነው በኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት ትዕዛዝ ለአስመራ ነዋሪዎች የተነገረ መልዕክት ነው።የአሜሪካ ኤምባሲ ያገኛቸውን ሪፖርቶች ጠቅሶ እንዳስታወቀው በተወሰኑ የአስመራ ክፍል የሚገኙ የአካባቢ ጥበቃዎች፤ የከተማይቱ ነዋሪዎች ምሽቱን በቤታቸው እንዲያሳልፉ ነግረዋቸዋል። የአስመራ ከተማ ነዋሪዎች ከቤት ውጭ እንዳያንቀሳቀሱ የተነገራቸው በምን ምክንያት እንደሆነ ኤምባሲው የሰጠው ማብራሪያ የለም።የኤርትራዋ መዲና ባለፈው ህዳር 5 ምሽት ከትግራይ ክልል በተወነጨፉ ሚሳኤሎች መመታቷ ይታወሳል። የሚሳኤል ጥቃቱን ያደረሰው የትግራይ ክልል ኃይል እንደሆነ የህወሓት አመራሮች በወቅቱ ገልጸው ነበር። የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚሳኤል ጥቃቱን አጥብቀው መኮነናቸው አይዘነጋም።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube @FikerAssefa
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ዛሬ ማክሰኞ ስብሰባ ሊያደርግ ነው።

በቪዲዮ ኮንፍረንስ ይደረጋል የተባለው ይሄው ስብሰባ ለህዝብ ክፍት እንዳልሆነ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት የዲፕሎማቲክ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።በተመድ የአልጀዚራ ዘጋቢ የሆነችው አማንዳ ፕራይስ፤ የምክር ቤቱ ስብሰባ "ኢ-መደበኛ ምክክር" እንደሆነ ከዲፕሎማቶች መስማቷን በትዊተር ገጿ ጽፋለች።የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ ለመነጋገር ስብሰባ ሲጠራ የአሁኑ የመጀመሪያው ነው።በትግራይ ክልል የተከፈተው ወታደራዊ ዘመቻ ዛሬ ሶስተኛ ሳምንቱን ይደፍናል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሹም ሽር እያካሄደ ነው!

በቅርብ ቀናት ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነታቸው ተነስተው ወደ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት የተዛወሩት አቶ ተመስገን ጥሩነህ በተቋሙ ውስጥ የሚታዩ የተጋላጭነት ቀዳዳዎችን ለመድፈን ይረዳል የተባለ ሰፊ የሹምሽር እያደረጉ መሆኑን ዋዜማ ራዲዮ ከተቋሙ ሁነኛ ምንጮች ስምቻለው ብላለች።አዲሱ ሹም ሽር የተደረገው አሁን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ሆነው የተሾሙት ደመላሽ ገብረ ሚካኤል መስሪያ ቤቱን ከመልቀቃቸው በፊትና ከለቀቁ በሁዋላ የተደረገ የስጋት ግምገማን መነሻ በማድረግ እንደሆነም መረዳት ተችሏል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ የደህንነት መስሪያ ቤትን አሰራር ለማሻሻልና በኢህአዴግ አስተዳደር ዘመን የነበረውን ቅጥ ያጣ ስልጣን በህግ ለመገደብ የሚያስችሉ ስራዎች ቢከናወኑም በተመሳሳይ ግን ተቋሙ መሰረታዊ በሆኑ የሀገሪቱ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ በነበረው አፈጻጸም ደካማ ነበር የሚል ትችት ቀርቦበታል።በኦሮሚያና ሌሎች ክልሎች የበርካቶችን ህይወት የቀጠፉ የጸጥታ ችግሮች ሲፈጠሩ ፣ በትግራይ ክልል መጠነ ሰፊ የጦርነት ዝግጅቶች ሲደረግ ፣ በኦነግ ሸኔም ሰፊ ጥፋቶች ሲደርሱ አስቀድሞ ለመከላከል የሚረዱ የደህንነት ስራዎችን በተገቢው ፍጥነትና ጥራት ማከናወን ላይ ጉድለቶች ታይተውበታል ተብሏል።

መስሪያ ቤቱ ” የጸረ ለውጥ ” ቡድን አባላት ተባባሪ የሆኑ ጥቂት ሰራተኞች እንደነበሩበት በማመንም እርምጃዎችን ወስዷል።በተቋሙ በቁልፍ ሀላፊነት ላይ ያሉ አመራሮች ሹምሽር የተደረገው ጉድለት ተብለው ከቀረቡት የግምገማ ግኝቶች በመነሳት ነው።በዚህም መሰረት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አሰፋ አብዩ ከሀላፊነታቸው መነሳታቸውን ተሰምቷል። አሰፋ አብዩ ወደ ደህንነት መስሪያ ቤት ከመምጣታቸው በፊት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ነበሩ።በቅርቡ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራልነታቸው የተነሱት እንደሻው ጣሰው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

እንዲሁም የፀረ ስለላና የፀረ ሽብር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች እና የሲቪል ማህበራት ክትትል መምሪያ ኃላፊ ፣ የሀገር ውስጥ ደህንነት ፀረ ስለላና የአየር መንገድ እና ኢምግሬሽን ደህንነት ኃላፊ፣ የአስተዳደርና ኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊን ጨምሮ ሌሎች ስድስት አንጋፋ ባለሙያዎችና የዘርፍ አመራሮች ከሀላፊነት እንዲነሱ ተደረጓል።ዋዜማ የሀላፊዎቹን ስም ዝርዝር ከስራቸው የስሱነት ጠባይ ጋር በተያያዘ ይፋ ከማድረግ እቆጠባለው ብላለች።የሹም ሽሩ በዚህ እንደማያበቃና ተቋሙ አዳዲስ ለውጦችን በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ድርጅት 858 የሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን እንዳልተቀበለ አስታወቀ።

የትግራይ ቴሌቪዥን በትናንት ምሽት ዘገባው ባሰራጨው መረጃ በትግራይ መንግስት ስር ያሉ 858 የሰሜን ዕዝ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ለዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል አስረክበናል ብሎ ነበር።በርክክቡ ወቅትም የቀይ መስቀል አባላት በአካል ተገኝተው ነበርም ሲል ነው ቴሌቪዥን ጣቢያው የገለፀው።

ይሁንና ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ተቋም ግን 858 የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን እንዳልተቀበለ በድረገፁ አሳውቋል።

ቀይ መስቀል በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት የተጎዱ ዜጎችን ህክምና እንዲያገኙ በማድረግ ላይ መሆኑን አስታውቋል።ድርጅቱ ከሁለቱም ወገኖች የተጎዱ ዜጎችን በ11 አንቡላንሶችን በማሰማራት ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑንም ገልጿል።

በጦርነቱ የተጠፋፉ ቤተሰቦችንም የማገናኘት ስራ በመስራት ላይ ሲሆን አሁንም ቤተሰብ የጠፋባችሁ ዜጎች በስልክ ቁጥር 0943122207 ወይም በ0115527110 ደውላችሁ ብታስመዘገቡ ልንረዳችሁ እንችላለን ብሏል።

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያን ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚያስተሳስረው የዲማ - ራድ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ።

60 ነጥብ 2 ኪሜ እርዝመት ያለው ይህው የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፍጻሜውን ማግኘቱ አማራጭ የገቢ ወጪ ንግድን ለማሳለጥ ከፍተኛ ተቀሜታን ያበረክታል።የዲማ - ራድ ድልድይ የመንገድ ግንበታ ፕሮጀክት ለሀገራችን ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝላትን ቡናን ጨምሮ የፍራፍሬ ፣ማር እና ቅመማ ቅመም ምርት ውጤቶችን ከምዕራቡ የአገሪቷ ክፍል ወደ ውጪ በመላክ ሀገራዊ ሚናው የጎላ ሲሆን በአካባቢው ያሉትን አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

መንገዱ ከዚህ ቀደም ለትራንስፖርት አመቺ ያልሆነ የተጎዳ ጠጠር መንገድ የነበረ ሲሆን መስመሩ ሊያበረክተው ከሚችለው ፋይዳ አኳያ ወደ አስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እንዲያድግ ተደርጓል፡፡
ፕሮጀክቱን በኢትዮጵያ መንግስት በተመደበ 856 ሚሊዮን ብር ገንብቶ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ኮንስተራክሽን ስራዎች ኮርፖራሽን ነው።

የማማከር እና የቁጥጥር ስራውን ያከናወነው ደግሞ የኢትዮጵያ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ኮርፖራሽን ነው፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘም የደቡብና ጋምቤላ ክልልን የሚያገናኘው የዚሁ የመንገድ ትስስር አካል የሆነው የሚዛን ዲማ የመንገድ ፕሮጀክትም በመጠናቀቅ ላይ ነው።ይህው ፕሮጀክት 91 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመትን ይሸፍናል።ለፕሮጀክቱ የሚውለውን 1.2 ቢሊየን ብር የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው።የመንገድ ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው MCC17 የተባለ የቻይና አለማቀፍ የስራ ተቋራጭ ድርጅት ነው።የማማከሩን ተግባር ደግሞ የህንዱ አርቪ አሶሲዬት ኮንሰልታንሲ ከኢትዮጽያው አማካሪ ድርጅት ኔት ጋር በጋራ እየሰሩ ነው።

Via ERA
@YeneTube @FikerAssefa
አምነስቲና የተባበሩት መንግሥታት ለመቀለ ሰላማዊ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲደረግ ጠየቁ!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንም ትናንት በነበራቸው መግለጫ መቀሌ በመከላከያ ሠራዊት ከ50-60 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ተከባ እንደምትገኝ ተናግረዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለህወሓት መሪዎች በሰጡት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በንሑሃን እና በንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከዚህ በኋላ ብቸኛው አማራጭ እጅ መስጠት መሆኑን አስገንዝበው ነበር።የጠቅላይ ሚንስትሩ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚገመቱ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች አስፈላጊው ከለላና ጥበቃ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

በተመሳሳይ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናልም ሁለቱ ኃይሎች ለሰላማዊ ዜጎች ደኅንነት ቅድሚያ እንዲሰጡ ጠይቋል።በክልሉ የሰብዓዊ እርዳታ የሚደርስበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹም አስገንዝቧል።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተር ዴፕሮስ ሙቼና፤ "በሁለቱም ወገን ያሉ የጦር አዛዦች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕጎችና መርሆችን እንዲያከብሩ እጠይቃለሁ። በሰላማዊ ሰዎችና ወታደራዊ ባልሆኑ መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የሚቻለውን ጥንቃቄ ሁሉ እንዲያደርጉ፤ ሰላማዊ ሕዝብ በሚበዛባቸው ሰፈሮች የወታደራዊ ቁሳቁሶች ክምችትን እንዲያስወግዱ፣ የወታደሮች እንቅስቃሴም በሰላማዊ ነዋሪዎች መኖርያ አካባቢ እንዳይሆን ጥሪ አቀርባለሁ" ብለዋል።
በተጨማሪም ተዋጊዎች ሰላማዊ ዜጎችን ጋሻ ከማድረግ እንዲቆጠቡ አምነስቲ ጠይቋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ኢሎን መስክ የአለማችን ሁለተኛው ባለፀጋ ሰው ሆነ!

የቴስላ መኪና አምራችና ስፔስ ኤክስን ጨምሮ የበርካታ ኩባንያዎች ባለቤት የሆነው፣ የደቡብ አፍሪካ ተወላጅ ኢሎን መስክ የማይክሮሶፍት ኩባንያ ባለቤት የሆነውን ቢል ጌትስን በመብለጥ ነው የአለም ሁለተኛው ሃብታም ሰው ሊሆን የቻለው።የ49 አመቱ ኢሎን መስክ እየተገባደደ ባለው የፈረንጆች አመት ብቻ ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱም ጥቅል ሃብቱ እንዲመነደግ እንዳገዘው ተገልጿል።የዚህም ዋነኛው ምንጭ የቴስላ የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ኩባንያ የአክሲዮን መጠን ከፍ ማለቱ እንደሆነ ብሉምበርግ ጠቅሷል።በአሁኑ ሰአት የኢሎን መስክ አጠቃላይ ሃብት 127.9 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቢል ጌትስ ደግሞ 127.7 ቢሊዮን ነው።አንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የአለማችን ባለፀጋው ሰው የአማዞን ኩባንያ ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ሲሆን ጥቅል ሃብቱ 182 ቢሊዮን ዶላር ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
ጎንደር አዲስ ከንቲባ ሾመች፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በ4ተኛ ዙር 8ኛ ዓመት 2ኛ አስቸኳይ ጉባዔው አቶ ሞላ መልካሙ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ እና ቻይና የዲፕሎማሲ ግንኙነት የጀመሩበት ግማሽ ምዕት አመት እየተከበረ ነው። ለዘመናት የቆየው እና በጊዜያትም እየጠነከረ የመጣው የኹለቱ አገራት ግንኙነት በጠንካራ መሰረት ላይ እንዲገነባ ላደረጉም ምስጋና ማቅረቡን አዲስ አበባ የሚገኘው የቻይና ኢምባሲ በትዊተር ገፁ አስነብቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ጃዋር መሃመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሃምዛ አዳነ ወይም ሃምዛ ቦረናን ጨምሮ ሌሎች ተከሳሾች ዐቃቤ ህግ ያገደባቸውን የንብረት እግድ ይነሳልን ሲሉ ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ሆነ፡፡ 

የንብረቱን እግድ በተለመለከተ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳያቸውን ተመልክቷል፡፡አቶ ጁዋር መሃመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሃምዛ አዳነ ወይም ሃምዛ ቦረና በችሎቱ ያልተገኙ ሲሆን ቀሪዎቹ ተከሳሾች ግን ተገኝተዋል፡፡

ለምን እንዳልተገኙ ለችሎቱ ያስረዱት የተከሳሽ ጠበቃ ለሃገሪቱ ደህንነት ሲባል አንቀርብም ማለታቸውን አብራርተዋል፡፡

ይሁንና ፍርድ ቤቱ የተከሳሾች የታገደው ንብረታችን ይነሳልን አቤቱታን እና ዐቃቤ ህግ የንብረታቸው የወንጀል ፍሬ ነው መነሳት የለበትም ሲል ያቀረበውን ምላሽ መርምሮ ችሎቱ የታገደውን ንብረት ሊነሳ አይገባም ሲል ብይን ሰጥቷል፡፡

ነገር ግን የተከሳሾችን ቤተሰብ ቀለብ በተለመለከተ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ለህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ ጃዋር መሃመድን ጨምሮ አጠቃላይ ተከሳሾች ላይ ዐቃቤ ህግ ያቀረበባቸው ክስ ላይ የሚያቀርቡት የክስ መቃወሚያ በመመልከት አንደኛ የህገ መንግስት እና የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት ለህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

 Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከታህሳስ 1 እስከ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ደግሞ መንግስት የህግ ማስከበር ስራውን እንዳጠናቀቀ ይሰጣል ተብሏል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት እጅ እየሰጡ ነው ተባለ!

መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅግ በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በየግንባሩ እጅ እየሰጡ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።

በአፋር ክልል በኩል ብዙዎች ገብተው እጅ የሰጡ ሲሆን በማይጸብሪ ተቆርጦ የቀረው ኃይል እጁን በሰላም በመስጠት ላይ መሆኑንም ጠቅሷል።

ጥሪውን ሰምተው እጅ በመስጠት ላይ ለሚገኙ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት ለሕዝባቸው በማሰባቸው መንግሥት ምስጋናውን ያቀርባልም ብሏል።

“በጁንታው ኃይል ተጽዕኖ ውስጥ ሆናችሁ እጅ ለመስጠት ያልቻላችሁ ሁሉ በያላችሁበት ትጥቃችሁን ፈትታችሁና የጁንታው መጠቀሚያ ከመሆን ተቆጥባችሁ፣ መከላከያ እስከሚደርስላችሁ እንድትጠብቁ በአጽንዖት እናሳስባለን” ብሏል የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ ባወጣው መረጃ።

@YeneTube @FikerAssefa
በሶማሌ ክልል ዘመናዊ የግመል እርባታ ጣቢያ ስራ ጀመረ!

በሶማሌ ክልላዊ መንግስት ፋፈን ዞን ሸበለይ ወረዳ በ26,550,000 ብር ዘመናዊ የግመል እርባታ ጣቢያ ስራ ጀመረ።በግል ባለሃብት የተቋቋመው ጣቢያው ከ18 በላይ ለሆኑ ሰዎች የስራ ዕድል ፈጥሯል፡፡በአሁኑ ሰዓትም በዘመናዊ መልክ ከ234 በላይ ግመሎች እየረቡ መሆናቸውን የግመል እርባታ ላይ የተሰማሩት ወ/ሮ ፈራህ አብዱ ወሊ ለአዲስ ዘይቤ ገልፀዋል፡፡

በ 52 ካሬ ሜትር ላይ በተዘጋጀ ስፍራ አልፋ አልፋ እና የሱዳን ግራስ የተሰኙ ቶሎ ተዘርተው ቶሎ የሚደርሱ ተክሎች ተዘርተው ለግመሎቹ መኖ ግብአትነት እየዋለ መሆኑንም አክለዋል፡፡
ግመሎቹ በቀን 450 ሊትር በላይ ወተት ለጅግጅጋ ከተማ ያቀርባሉ፡፡

ሆኖም በከተማዉ ካለው የወተት ፍላጎት አንፃር በቂ አለመሆኑን ወ/ሮ ፈራህ ተናግረዋል፡፡አክለውም የተጠቃሚውን ፍላጎት ያገናዘበ አቅርቦት ከማሻሻል ባሻገር በቀጣይ የግመል ወተትን በዘመናዊ ማሽን በማቀናበር በወተት እርጎ እና አይብ መልክ አሽጎ ከማቅረብ ጀምሮ ለእርድ አገልግሎት የሚውሉ ግመሎችንም ለተጠቃሚ የማድረስ እቅድ ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
ከባሕር ላይ የተነሳ ከባድ አውሎ ነፋስ ሶማሊያን ሲመታ ዛሬ ጂቡቲ ላይ ጉዳት ያደርሳል ተብሎ ተሰግቷል።

ጋቲ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ከባሕር ላይ የሚነሳው ከባድ አውሎ ነፋስ ሶማሊያን የመታው እሁድ ዕለት ነበር። ጋቲ በሶማሊያ እና ሶማሊላንድ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱም ተገልጿል።ከባዱ አውሎ ነፋስ የሁለት ዓመት ዝናብ መጠን ያለውን ዝናብ በአንድ ጊዜ ይዞ ተከስቶ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። የሰዎች ሕይወትም አልፏል።የአየር ትንበያ ባለሙያዎች ከባዱ አውሎ ነፋስ ዛሬ ጂቡቲን እንደሚመታ ተንበየዋል።ከባድ ነፋስ እና ጎርፍ እንደሚያስከትልም ባለሙያዎቹ አስጠንቅቀዋል።ይህ አይነት ከባድ አውሎ ነፋስ ሲከሰት በአፍሪካ ቀንድ የመጀመሪያው መሆኑም ተነግሯል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa