YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የልዩ ዕድል ሎተሪ በወቅታዊ የአገሪቱ ሁኔታ ምክንያት የመውጫ ቀኑ ህዳር 30/2013 ድረስ ተራዘመ፡፡

በርካቶች በጉጉት የሚጠብቁትና በ1ኛ ዕጣ 20 ሚሊዮን ብር፣ በ2ኛ ዕጣ 10 ሚሊዮን ብር፣ በ3ኛ ዕጣ 5 ሚሊዮን ብር፣ በ4ኛ ዕጣ 3 ሚሊዮን ብር እና ሌሎችም በርካታ አጓጊ ሽልማቶችን ይዞ ገበያ ላይ የቆየው ልዩ ዕድል ሎተሪ የመውጫ ቀኑ ህዳር 10/2013 ዓ.ም ቢሆንም አገሪቱ በአጋጣማት ወቅታዊ ችግር የመውጫ ቀኑ ህዳር 30/2013 ዓ.ም ድረስ ተራዝሟል፡፡

[የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን የመከላከያ ሰራዊት በማንኛውም አካል ጥቃት ሊደርስበት አይገባም አለ!

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ፅህፈት ቤት በኢትዮጵያ በወቅቱ በተከሰተው ግጭትና በንፁሀን ዜጎች ላይ እየተከሰተ ባለው ዘርን ያማከለ ጥቃት ዙርያ ጋዜጣዊ መግለጫ ያወጣ ሲሆን ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ በጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የተከፈተውን ጥቃት እንዲሁም በማይካድራና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ህይወታቸውን ዘርን ባማከለ ጥቃት ምክንያት ባጡ ኢትዮጵያውያን የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

Via @AddisZeybe
@YeneTube @FikerAssefa
የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን በመጀመሪያ ሩብ አመት የ4 ወር አፈፃፀም 107 ቢሊየን ብር ከሀገር ውስጥ ታክስ፣ ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ እና ከሎተሪ ሽያጭ ሰበሰበ።በአጠቃላይ አፈፃፀሙ ከእቅዱ 103 በመቶ ሲሆን ከባለፈው እመት ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 19 በመቶ ወይም 17 ቢሊየን ብር ብልጫ አሳይቷል።

[ካፒታል]
@YeneTube @FikerAssefa
የጦር ሀይሎች ጠ/አዛዥ ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ፣ ከደቂቃዎች በሁዋላ በውቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ይሰጣሉ።

@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል ሰገን ህዝቦች ዞን በአሌ እና በኮንሶ በተነሳው ግጭት ብዙዎች መሞታቸውንና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ተገለጸ።

ካለፈው አርብ እለት ጀምሮ በደቡብ ክልል በአሊ አካባቢ የተቀሰቀሰው ግጭት ለቀናት መዝለቁ ነው የተሰማው፡፡ኢትዮ ኤፍ ኤም ከአካባቢው ነዋረዎች ሰማው እንዳለው አብዛኛው ነዋሪዎችና የመንግስት ሰራተኛ በሳውላ በኩል መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው መሰደዳቸውን ተሰምቷል፡፡ከዚህ ጥቃት በተአምር ነው የተረፍኩት ያለችን አንድ የአካባቢው ነዋሪ “እንዲህ አይነት ችግሮች በአካባቢው ላይ ከወረዳና ከዞን ጥያቄ ጋር በተገናኘ የተለመደ እየሆነ ቢመጣም አሁን ግን ጥቃትና ግድያውን ፈጸመዋል የሚባሉት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው” ስትል ግምቷን ተናግራለች፡፡

በአርባ ምንጭ ባለው የነጭ ሳር ፖርክ አቅራቢያ ባለው የአባያ ሀይቅ አካባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ምሽግ እንዳላቸው እና ከዚህ ፓርክ እየወጡ እያጠቋቸው እንደሆኑ ተፈናቃዮቹ ተናግረዋል፡፡ከቅርብ ቀናት በፊትም መንግስት ባደረገው መጠነ ሰፊ ዘመቻ የጦር መሳሪዎች መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡እኛም ቢሆን በአካባቢያችን ላይ የምናያቸውን ፀጉረ ልውጥ ሰዎችን ለአካባቢው ፖሊስ ጠቁመናል ነው ያሉት፡፡ይሁን አንጂ አሁን ላይ ጥቃቱን በሚያደርሱት ታጣቂዎች ላይ የጸጥታ ሀይሉ እርምጃ እየወሰደ አለመሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ምላሽ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው አንድ የደቡብ ክልል መንግስት ስማቸውና ድምጻቸው እንዳይገለጽ ጠይቀው በተጠቀሱት አካባቢዎች ጥቃት መፈጸሙን ተናግረዋል።በዚህ ጥቃት ምክንያትም ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ዜጎች በዚህ ጥቃት ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን እና ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ተናግረዋል።ከትላንት ጅምሮም የደቡብ ክልል መንግስት የጸጥታ ተቋማት አመራሮች ወደ ቦታው አምርተው በቀጣይ ስለሚወሰዱ እርምጃዎች በመምከር ላይ መሆናቸውንም ሃላፊው ገልጸዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የጦር ሀይሎች ጠ/አዛዥ ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ፣ ከደቂቃዎች በሁዋላ በውቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ይሰጣሉ። @YeneTube @FikerAssefa
የጦር ሀይሎች ጠ/ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ፣ ሠራዊቱ በሁሉም ግንባሮች ድልን እየተጎናፀፈ እንደሚገኝ ተናገሩ።

'ጁንታው' እያንዳንዳቸው 2ሺ 500 የሰው ሀይል የያዙ 11 ብርጌድ ልዩ ሀይል፣ 14 ብርጌድ የዞን ታጣቂ እና አንድ ብርጌድ ሚሊሻ ቢገነባም ፣ አሁን ነፍስ አውጭኝ ላይ ይገኛል ብለዋል ።ጀግናው ሠራዊታችን በምዕራብ ትግራይ ከዳንሻ - ባዕከር ፣ አዲጎሹ ፣ አዲ ሀገራይ ፣ አዲጉዞምን ሰብሮ ትናንት ሽሬን መቆጣጠሩን አረጋግጠዋል።በደቡቡ ግንባርም ከዋጃ ጀምሮ አላማጣ ፣ ኮረምን ይዞ ወደፊት ቀጥሏል።በምስራቁ ግንባር ፣ ጨርጨር ፣ መሆኔ ፣ ራያ ቆቦና ሌሎች ቦታዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል። 'ጁንታውን' ለህግ ለማቅረብም ግስጋሴውን ቀጥሏል ።

ነጻ በወጣው አካባቢ የሚገኘው ህብረተሰብ ለሠራዊታችን ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጀነራል ብርሀኑ አስታውሰው ፣ ህዝቡ ሠራዊታችንን ከሁዋላው እንዲመታ ቢያስታጥቁትም ፣ ምንም ሳይተኩሱ 200 መትረየስና ክላሽ አዲኮኮብ እና ሽሬ ላይ ለሠራዊታችን እስረክቧል ብለዋል።'ጁንታው' ኮማንድ ፖስቱን እና ትኳሾቹን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቢያደርግም ሠራዊታችን ነጥሎ ለመምታት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል ።በአሁኑ ሰዓት 'ጁንታው' ኢትዮጵያን ወደ ጦርነት ለማስገባትና ለመበታተን ያቀደው እንደከሸፈበትና በመከበቡ ነፍስ አውጭኝ ላይ ይገኛልም ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ ወለጋ ዞን በ142 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡

በምዕራብ ወለጋ ዞን በቅርቡ በተደረገው ኦፕሬሽን በ142 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ እንደተወሰዳባቸው፣48 ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉና፣ 64 ደግሞ በህብረተሰቡ ውስጥ ከተበታተኑ በኋላ መያዛቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ አስታውቀዋል፡፡

ለኦነግ ሸኔ አባላት የሎጂስቲክስና ስልጠና ሲሰጡ የነበሩ 1 ሽህ 341 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 104 የጽንፈኛው የህወሃት ቡድን አባላት መሆናቸው ተገልጿል፡፡በምዕራብና በደቡብ ኦሮሚያ አካባቢዎች አንፃራዊ ሰላም እንደሰፈነ ኮሚሽነሩ መግለፃቸውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ደመቀ መኮንን ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ!

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሺሰኬዲ ጋር ተወያዩ።ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ: ኢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ የኤርትራ ከፍተኛ ሹማምንት ግብፅ እንደነበሩ ተሰምቷል፡፡

የኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ እና የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አማካሪ የማነ ገብረአብ ናቸው ዛሬ ካይሮ የታዩት፡፡በሁለቱ ሹማምንት የተመራው ልዑክ ከግብፅ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ ጋር መወያየቱን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው ላይ ፅፏል፡፡የኤርትራዊያን ባለስልጣናት የካይሮ ጉዞ ሁለቱ አገራት በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የሚያደርጉት መደበኛ ምክክር አካል ነው ያሉት አቶ የማነ ገብረመስቀል፣ ባለሥልጣናቱ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር እና በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይም ሐሳብ መለዋወጣቸውን ጽፈዋል፡፡

[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የአገር ክህደት ወንጀል በፈጸሙ 76 ጄነራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች እና የበታች ሹማምንቶች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ወጣ፡፡

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ከጣና ሐይቅ ላይ እምቦጭን ለማስወገድ ለአንድ ወር ሲካሄድ የነበረው ዘመቻ እስከ ሕዳር 30 እንዲቀጥል ተወሰነ።

እስካሁን በነበረው ዘመቻ ከፍተኛ ውጤት እንደተመዘገበ የዘመቻው አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡የዘመቻውን መራዘም አስመልክቶ የዘመቻው አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ ዛሬ ማምሻውን በውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ከጥቅምት 9 እስከ ሕዳር 9 ቀን 2013 ሲካሄድ በቆየው ዘመቻ በተለያዩ ምክንያቶች ሁሉንም ቀናት መጠቀም ባለመቻሉ የዘመቻውን ጊዜ እስከ ኅዳር 30 ማራዘም አስፈላጊ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

እስካሁን በነበረው የዘመቻ ጊዜ አረሙን በማስወገድ ረገድ ተጨባጭ ለውጥ መታየቱም ተገልጿል፡፡በመግለጫውም በእስካሁኑ ዘመቻ የእምቦጭ አረም ተከስቶባቸው ከነበሩት 30 ቀበሌዎችን ከሚያዋስነው የሐይቁ አካል በ17 ቀበሌዎች ውስጥ የተከሰተውን አረም ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡በዘመቻውም ከ200 ሺህ በላይ የሰው ኃይል መሳተፉ በመግለጫው ተመልክቷል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በሱማሊያ ከሠፈሩት የኢትዮጵያ ወታደሮች ውስጥ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወታደሮች ትጥቃቸውን እንዲፈቱ እንደተደረጉ ከዲፕሎማቲክ እና ደኅንነት ምንጮች ሰምቻለሁ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ትጥቅ እንዲፈቱ የተደረጉት አንድ ወታደራዊ ምክትል አዛዥን ጨምሮ፣ በአሚሶም ስር የሚገኙ እና በተናጥል የሠፈሩ ወታደሮች ናቸው፡፡ ትጥቅ የፈቱት ወታደሮች ከ200 እስከ 300 የሚገመቱ እንደሆኑ እና ከጦር ሠፈራቸው እንዳይወጡ መታዘዛቸውን ዘገባው ጠቅሷል፡፡ ርምጃው የተወሰደው በወታደሮቹ ታማኝነት ላይ ስጋት በመፈጠሩ ነው ተብሏል፡፡ መንግሥትም ሆነ አሚሶም እስካሁን ለዘገባው ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ አልሰጡም፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa