YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ ከረፋዱ 5:30 ላይ ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለው በሚል ፕሮግራም ተካሄዷ።

📸ተክለሃይማኖት አከባቢ አዲስ አበባ
@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
34 የህወሃት የፋይናንስ ተቋማትን ማሳገዱን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል። ሜጋ ማተሚያ፣ ሱር ኮንስትራክሽን ፣ ጉና የንግድ ስራዎች ፣ ኢፈርት ኤሌክትሪካል ቢዝነስ ፣ ትራንስ ኢትዮጵያ ፣ መስፍን ኢንደስትሪያል ኢንጂነሪንግ ፣ ሠላም የህዝብ ማመላለሻ ማህበር፣ ኢፈርት ኃ/የተ/የግ ማህበር እገዳው ከተላለፈባቸው መካከል ናቸው። @YeneTube @FikerAssefa
የባንክ ሂሳብ የታገደባቸው 34 የኤፈርት ድርጅቶች የወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ነው!

የፈደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የባንክ ሂሳባቸው እንዲታገድ ያደረገባቸው 34 የትግራይ የመልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኤፈርት) ድርጅቶች ላይ የወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። ጠቅላይ አቃቤ ህግ የድርጅቶቹን የባንክ ሂሳብ ያሳገደው ሰኞ ህዳር 7፤ 2013 ለባንኮች በጻፈው ደብዳቤ ነው።

ሰላሳ አራቱ ድርጅቶቹ የባንክ ሂሳባቸው እንዲታገድ የተደረገው ከተጠረጠሩባቸው ሶስት ወንጀሎች ምርመራ ጋር በተያያዘ መሆኑን መስሪያ ቤቱ በደብዳቤው አስታውቋል።ድርጅቶች ከተጠረጠሩባቸው ወንጀሎች መካከል “በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች የሚፈጸሙ የዘር ተኮር ጥቃቶችን፣ የሽብር ተግባራትን እና ሕገ መንግስታዊ ስርዓትን በኃይል ለመናድ ከሚሰሩ አካላት ጋር በመመሳጠርና ግንኙነት በመፍጠር በገንዘብ መደገፍ” የሚል ይገኝበታል።

ድርጅቶቹ በሙስና እና በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀሎችም ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የጠቅላይ አቃቤ ህግ ደብዳቤ ያስረዳል። የፈደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለምርመራው ይረዳው ዘንድ የድርጅቶቹን የባንክ ሂሳብ እንቅስቃሴ የሚያመለክቱ ማስረጃዎች በአስቸኳይ እንዲላክለትም ጠይቋል።

* የ34ቱን ድርጅቶች ሙሉ ዝርዝር ከላይ ከተያያዘው ምስላዊ መረጃ ይመልከቱ

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የባንክ ሂሳብ የታገደባቸው 34 የኤፈርት ድርጅቶች የወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ነው! የፈደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የባንክ ሂሳባቸው እንዲታገድ ያደረገባቸው 34 የትግራይ የመልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኤፈርት) ድርጅቶች ላይ የወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። ጠቅላይ አቃቤ ህግ የድርጅቶቹን የባንክ ሂሳብ ያሳገደው ሰኞ ህዳር 7፤ 2013 ለባንኮች በጻፈው ደብዳቤ ነው። ሰላሳ አራቱ ድርጅቶቹ…
ከ34ቱ ተቋማት ትምዕት እና መሶቦ ሲሚንቶ ከድምጸ ወያኔ መገናኛ ብዙሃን ጋር ሼር እንዳላቸው መረጋገጡን ከጠቅላይ አቃቤ ህግ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በዚህ መሰረት ድምጸ ወያኔ ከትምዕት 8 ሚሊዮን ብር ብሎም ከመሶበ ሲሚንቶ 61 ሚሊዮን ብር በላይ የአክሲዮን ድርሻ እንዳለው ተቋሙ ገልጿል።በዚህም ድምጸ ወያኔ አሁን ላይ በኢትዮጵያ እያካሄደ ባለው ግጭት የገንዘብ ድጋፍ ከእነዚህ ተቋማት እንደሚያገኝ በሰነድ መረጋገጡን ኃላፊው ተናግረዋል።ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከአምስት በላይ የሚሆኑ የተቋሙን አዋጅ መነሻ በማድረግ በሁሉም ባንኮች የ34ቱንም የፋይናንስ ተቋማት የሂሳብ አካውንት ማሳገዱን ለማወቅ ተችሏል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ለህወሀት ቡድን የዲፕሎማሲ ስራ ሲሰሩ እንደነበር አንድ የኢትዮጵያ ባለስልጣን ተናገሩ፡፡

የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ለህወሀት ቡድን የዲፕሎማሲ ስራ ሲሰሩ እንደነበር ተገለፀ፡፡ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ለህወሀት ቡድን ዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ ድጋፍ እንዲደረግ የአለም መንግስታትን በመጠየቅ ረገድ ሙሉ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ገልፀዋል፡፡ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ለአናዶሉ ኤጀንሲ እንደተናገሩት የሀገር መከላከያ ሰራዊት በህወሀት ቡድን ላይ ህግ የማስከበር ዘመቻ ከጀመረበት ዕለት አንስቶ ዶ/ር ቴውድሮስ ሲያደርጉት የነበረውን እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ መንግስት ጠንቅቆ ያውቃል ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በህወሃት ላይ የሚወስደውን ወታደራዊ እርምጃ እንዲያስቆሙ እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲያሳድሩ ሲጠይቁ ነበር ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል፡፡እንደ አውሮፓውያኑ ከ 2017 ጀምሮ በአለም ጤና ድርጅት (WHO) ውስጥ እያገለገሉ የሚገኙት ዶ/ር ቴድሮስ የህወሀት ቡድን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ሲያገለግሉ እንደነበር ይታወቃል፡፡እንደ አውሮፓውያኑ ከ 2005 እስከ 2012 የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር እንዲሁም ከ 2012 እስከ 2016 ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡

የአናዶሉ ዜና👇👇

https://www.aa.com.tr/en/africa/ethiopia-who-director-general-works-as-tplf-diplomat/2046193

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ነጻ በሆኑ አካባቢዎች መዋቅሩን እንደሚያደራጅ ገለጸ!

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከህወሃት ጁንታ ቡድን ነጻ በሆኑ አካባቢዎች መዋቅሩን እንደሚያደራጅ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ገለጹ።ዋና ስራ አስፈጻሚው በሰጡት መግለጫ፤ ዋና ስራ አስፈጻሚው የፕሬዚዳንቱን ስራ ስለሚሰራ ክልሉ ሙሉ ለሙሉ ነጻ ሲወጣ መንግስታዊ ስራውን ተክቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል።በዚህም መሰረት የክልሉን ካቢኔ እንደሚያደራጅና የዞን አስተዳዳሪዎችን እንደሚሾም ገልጸው፤ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤቶች ባሉበት እንዲቀጥሉ የሚደረግ መሆኑን አመልክተዋል።ስራ አስፈጻሚውን አካል እንደሚመራ፣ እንደሚያስተባብር እንዲሁም የክልሉን ዕቅድና በጀት እንደሚያጸድቅ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሰሜን በሚደረገው የህግ ማስከበር ዘመቻ የተሰደዱ ወገኖችን የመመለስና መልሶ የማቋቋም ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሰላም ሚንስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል አሳሰቡ፡፡

በሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሚመራው ከአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተውጣጡ የስራ ሃላፊዎችን የያዘው የሰብዓዊ ድጋፍ ቡድን በሰሜን እየተደረገ ካለው የህግ ማስከበር እንቅስቃሴ ጎን ለጎን የተፈናቀሉና ከአገር ውጭ የተሰደዱ ወገኖችን ወደ ቤታቸው የመመለስና መልሶ የማቋቋም ስራውን አጠናክሮና በተቀናጀ መልኩ መቀጠል እንደሚገባው ተገልጿል።

ከሰብዓዊ ድጋፍ ቡድኑ ጋር በተዘጋጀ የምክክር መድረክ የሰላም ሚንስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ድጋፉ ከመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት በመተባበር እንደ ሁኔታው አስቸኳይነት በፍጥነት መተግበሩን እንዲቀጥል አሳስበዋል። ሚኒስትሯ ጉዳዩ ፋታ የሚሰጥ ስላልሆነ የቡድኑን ከፍተኛ ርብርብ እንደሚሻም ተናግረዋል።የሰብዓዊ ድጋፍ ቡድኑ የተሰደዱና የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ የማቋቋሙ ስራ ላይ ፈጣንና የተደራጀ እንቅስቃሴ የሚደረግበትን አቅጣጫ አስቀምጠዋል ብለዋል።

ምንጭ፦ ሰላም ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኒጀር አቻውን በአዲስ አበባ ስቴዲዮም ያስተናገደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 3 ለ0 አሸነፈ!

ዋልያዎቹ በ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ፣ መስኡድ መሀመድ እና ጌታነህ ከበደ ጎሎች ኒጀርን ከከመልካም የጨዋታ እንቅስቃሴ ጋር በማሸነፍ በስድስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚያስቀምጣቸውን ትልቅ ውጤት አስመዝግበዋል።

[Hatrick Sport]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የአውሎ ሚዲያ ጋዜጠኛ የሆነው በቃሉ አላምረው ዛሬ ከጠዋቱ 2 ሰዓት አካባቢ በሶስት ፖሊሶችና አንድ የፀጥታ ባለሙያ ተወስዶ እንደታሰረ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። @YeneTube @FikerAssefa
የአውሎ ሜዲያ አዘጋጅ ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ዛሬ ዋስትና አስይዞ ከእስር እንዲፈታ ፍርድ ቤት ቢወሰንለትም፣ ፖሊስ ይግበኝ እንደጠየቀበት ሜዲያው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ዘግቧል፡፡ በይግባኙ የተነሳ ጋዜጠኛው ሳይፈታ ቀርቷል፡፡ ጋዜጠኛው 10 ሺህ ብር ዋስ አስይዞ እንዲፈታ ነበር ፍርድ ቤት ዛሬ ጧት የወሰነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የመከላከያ ሠራዊት በዛሬው ዕለት በትግራይ በምሥራቅና በምዕራብ ግንባሮች ወሳኝ ድሎችን ተቀዳጅቷል ተባለ።

በምሥራቁ ግንባር ራያ ሙሉ በሙሉ ነጻ ወጥቷል። ጨርጨር፣ ጉጉፍቶ መሖኒን ሠራዊቱ ነጻ አውጥቷል። በየቦታው የነበሩ ወሳኝ የኮንክሪት ምሽጐችንም አፍርሷል። ሠራዊቱ በአሁኑ ጊዜ ወደ መቀሌ በመገሥገሥ ላይ ነው። በምዕራብ ግንባር ደግሞ በአዲ ነብሪድና በአዲ ዳእሮ የሚገኙ ከባድ ምሽጎችን በማፍረስ ሽሬን ተቆጣጥሮ ወደ አክሱም በመገሥገሥ ላይ ይገኛል።

በውጊያው እጅግ ብዙ መሣሪያዎች ከመማረካቸውም በላይ ህወሓት ለክፉ ዓላማው ያሰለፋቸው የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት በቁጥጥር ሥር ውለዋል።የመከላከያ ሠራዊቱ የህወሓት ጁንታን በሕግ ቁጥጥር ሥር ለማዋል እየገሠገሠ ሲሆን የጁንታው ኃይል የመከላከያ ሠራዊቱን ክንድ መቋቋም አቅቶት ወደኋላ እየሸሸ ነው።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
<<"የኢትዮጵያ መንግሥት ከደቡብ ሱዳን የጦር ድጋፍ እንዲደረግለት በደብዳቤ ጠይቋል" ተብሎ የሀሰት ዜና ተሰራጭቷል። እንዲህ ያሉ የፈጠራ ዜናዎች፣ የሀገር ውስጥ ጉዳያችንን ቀጣናዊ ገጽታ ያለው አስመስሎ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለማቅረብ በአጥፊዎቹ አካላት የሚደረግ ጥረት ነው። ሁሉም ሰው ይህን የመሰሉ የሀሰት ዜናዎችን ባለማጋራት፣ የተሳሳተ መረጃን ከማሰራጨት እንዲቆጠብ ጥሪ እናደርጋለን።>>

[የአስቸኳይ አዋጅ መረጃ አጣሪ]
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ህወሓት በኤርትራ ላይ የፈጸመውን ጥቃት አወገዙ።

ውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ "ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ በኤርትራ ላይ የፈጸመውን ጥቃት እና ግጭቱን ዓለም አቀፋዊ ለማድረግ ያደረገውን ሙከራ አጥብቀን እናወግዛለን።ህወሓት እና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ግጭቱን ለማብረድ፣ ሰላምን ለማስፈን እና የሰላማዊ ሰዎችን ደሕንነት ለመጠበቅ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ እናቀርባለን" ብለዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 339 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 3,778 የላብራቶሪ ምርመራ 339 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,588 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 163 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 64,293 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 103,395 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሕወሐት ወደ መቀሌ የሚያስኬዱ አራት ድልድዮችን እያፈረሰ ነው ተባለ።

የመከላከያ ሠራዊት ወደፊት መገሥገሡ ያስጨነቀው 'ጁንታ'፣ በሁሉም አቅጣጫ ወደ መቀሌ በሚወስዱት መንገዶች ላይ የሚገኙ አራት ድልድዮችን ማፍረሱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል።የተማመነባቸው ከባድ ምሽጎቹ ፈራርሰው፣ በሽሬ መንገድ የደረሰበት ሽንፈት ያንገበገበው ጁንታ፣ በሽሬና በአክሱም መካከል የሚገኘውን አስፓልት በግሬደር ቆፍሮ ወደ ጉድጓድነት ቀይሮታል።የሕወሐት ጁንታው እስከዛሬ ከፈጸማቸው ወንጀሎች በተጨማሪ ባወደማቸው መሠረተ ልማቶች በቅርቡ ይጠይቅባቸዋልም ብሏል መረጃው።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
"ከ 27,000 በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከትግራይ ወደ ሱዳን ገብተዋል" የተመድ ስደተኞች ኮሚሽን

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን በፌዴራልና በትግራይ ክልል መንግሥታት መካከል ተቀስቅሶ ለሁለት ሳምንታት ያህል እየተካሄደ ባለው ወጊያ ሳቢያ በቀን በአማካይ ከ4000 በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከኖቬምበር 10 ወዲህ የሱዳንን ድንበር እየተሻገሩ መሆኑ የሰብዓዊ ዕርዳታ ቀውስ ያሳሰበው መሆኑን ገልጧል።

የተመድ ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን ቃል አቀባይ የሆኑት ባባር ባሎች ሁነቱ የሰብዓዊ ቀውሱን ወደ ላቀ ደረጃ እያመራው መሆኑን ጠቁመው በኮሚሽኑ በኩል "የእርዳታው አስፈላጊነት በጨመረ ቁጥር ሰብዓዊ ዕገዛውን ከፍ እያደረገ" ያለ መሆኑን አስታውቀዋል።በጦርነቱም ሳቢያ የረድኤት ሠራተኞች ክልሉን ለቅቀው እየወጡ ይገኛሉ።

አንድ ዲፕሎማት አክለውም ከጦርነቱ በፊት በርካታ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የእርዳታ ምግብ እየተደጎሙ ያሉ እንደነበር፣ በዚህ ሳምንት ውስጥ 600 ያህል አብዛኛውን የውጭ አገር ዜጎች በሁለት ኮንቮይ አዲስ አበባ የገቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው ህግን የማስከበር ሂደት ወንጀለኞችን ለህግ ከማቅረብ ያለፈ አላማ እንደሌለው መንግሥት አስታወቀ።

የጠቅላይ ሚንስቴር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ሕወሓትን ከትግራይ ሕዝብ መለየት የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እና ሕገ ወጥ ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሜ ያረጋግጣል:: ነገር ግን ይህ ሕግ የማስከበር እንቅስቃሴ በብሔር ወይም በሌላ ወገንተኝነት ላይ የተቃኘ ነው የሚለውን የተሳሳተ እሳቤ አጥብቆ ያወግዛል፡፡

በአሁኑ ወቅት በትግራይ የሚካሄደው ሕግ የማስከበር ሥራ በዋነኝነት ኢትዮጵያን በማተራመስ ላይ በተሠማሩ ሥርዓት አልበኞች፣ በተንኮልና በሤራ በተሞሉ የሕወሐት ቡድን አባላት ላይ ያነጣጠረ ስለመሆኑ ማንም ሰው ጥርጣሬ ሊገባው አይገባም፡፡

በትግራይ ክልል ሕዝብ ላይ ሳይቀር የከፋ በደል የሚፈጽመውን ይህን የሕወሐት ጁንታየወንጀል ሰንሰለት ለማስቆም የፌዴራሉ መንግሥት ቆርጦ ተነሥቷል፡፡በዚህ ሕግ የማስከበር ዘመቻ የትግራይ ሕዝብ የመጀመሪያው ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ለኢትዮጵያ ያለን ራእይ በብዝኃነት የሚኮሩ ብሔር ብሔረሰቦች በአንድነት የሚኖሩባት የበለጸገች ኢትዮጵያን ማየት ነው፡፡ የትግራይ ሕዝብ ሕዝባችን ነው። በዚህ ሕዝባችን ላይ ምንም ዓይነት ክፉ ነገር እንዲደርስ አንፈልግም። ይሄንን የሚያደርጉትንም አንታገሥም ሲል ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ቀደም ሲል የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በግል ለመውሰድ በሚቀርባችሁ ትምህርት ቤቶች ተመዝግባችሁ የነበራችሁ ተፈታኞች ቀደም ሲል ተመዝግባችሁበት የነበረዉ ትምህርት ቤት የሚገኝበት ክፍለ ከተማ በመሄድ በአስቸካይ እንድትመዘገቡ እያሳሰበ ለምዝገባ በምትሄዱበት ጊዜ ከዚህ በፊት ስትመዘገቡ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ በመያዝ እና አዲስ መመዝገብ የምትፈልጉ ተፈታኞች ደግሞ 260 ብር በመክፈል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡

[የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የሚገኙ የአልኮል ፋብሪካዎች ባጋጠማቸው የሞላሰስ እጥረት ምክንያት ሥራቸውን ለመቀጠል እንቅፋት ስለሆነባቸው ምርት ለማቆም መገደዳቸውን አስታወቁ።ልዩ አዲስ የአልኮል መጠጦች ኢንዱስትሪ እና መስከረም አልኮል እና ለስላሳ መጠጥ ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ እንዲሁም ብሔራዊ የአልኮል እና የአረቄ ፋብሪካ ደግሞ በግማሽ በአልኮል እና በሞላሰስ እጥረት ምክንያት ምርት ለማቆም እየተገደዱ እንደሆነ አስታውቀዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የልዩ ዕድል ሎተሪ በወቅታዊ የአገሪቱ ሁኔታ ምክንያት የመውጫ ቀኑ ህዳር 30/2013 ድረስ ተራዘመ፡፡

በርካቶች በጉጉት የሚጠብቁትና በ1ኛ ዕጣ 20 ሚሊዮን ብር፣ በ2ኛ ዕጣ 10 ሚሊዮን ብር፣ በ3ኛ ዕጣ 5 ሚሊዮን ብር፣ በ4ኛ ዕጣ 3 ሚሊዮን ብር እና ሌሎችም በርካታ አጓጊ ሽልማቶችን ይዞ ገበያ ላይ የቆየው ልዩ ዕድል ሎተሪ የመውጫ ቀኑ ህዳር 10/2013 ዓ.ም ቢሆንም አገሪቱ በአጋጣማት ወቅታዊ ችግር የመውጫ ቀኑ ህዳር 30/2013 ዓ.ም ድረስ ተራዝሟል፡፡

[የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን የመከላከያ ሰራዊት በማንኛውም አካል ጥቃት ሊደርስበት አይገባም አለ!

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ፅህፈት ቤት በኢትዮጵያ በወቅቱ በተከሰተው ግጭትና በንፁሀን ዜጎች ላይ እየተከሰተ ባለው ዘርን ያማከለ ጥቃት ዙርያ ጋዜጣዊ መግለጫ ያወጣ ሲሆን ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ በጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የተከፈተውን ጥቃት እንዲሁም በማይካድራና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ህይወታቸውን ዘርን ባማከለ ጥቃት ምክንያት ባጡ ኢትዮጵያውያን የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

Via @AddisZeybe
@YeneTube @FikerAssefa
የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን በመጀመሪያ ሩብ አመት የ4 ወር አፈፃፀም 107 ቢሊየን ብር ከሀገር ውስጥ ታክስ፣ ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ እና ከሎተሪ ሽያጭ ሰበሰበ።በአጠቃላይ አፈፃፀሙ ከእቅዱ 103 በመቶ ሲሆን ከባለፈው እመት ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 19 በመቶ ወይም 17 ቢሊየን ብር ብልጫ አሳይቷል።

[ካፒታል]
@YeneTube @FikerAssefa