YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 336 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 4,213 የላብራቶሪ ምርመራ 336 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ12 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,581 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 264 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 64,130 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 103,056 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ በትናንትናው የአየር ጥቃት ዙሪያ ያለው:

"በሁለት ዓለም ዐቀፍ መገናኛ ብዙኃን አማካኝነት፣ በመቐለ የአየር ጥቃት መደረጉን የሚገልጹ አርዕስት እና አጭር ቪዲዮዎች ወጥቷል። እነዚህ መረጃዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ኃይሉ ሳያረጋግጡ በሕወሐት መረጃ ላይ ብቻ የተመሠረቱ ሐሰተኞች ናቸው፡፡በተመሳሳይ ሁኔታ በሂደቱ ውስጥ ሰላማዊ ሰዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል የሚለው መረጃም እንዲሁ ሐሰት ነው፡፡

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመሥርቶ በወሳኝ የሕወሕት ዒላማዎች ላይ ከመቀሌ ከተማ ውጭ የታለመ የአየር ጥቃት አካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሕግ የበላይነትን የማስከበር እንቅስቃሴ ዒላማን በጥንቃቄ መምታትን መሠረት ያደረገ ነው።ሕወሐት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃቱን ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ፣ የመከላከያ ሠራዊቱ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማስቀረት ሲል ከከተሞች የራቀ ጥቃት ላይ አተኩሯል::"

@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሽያ እጁን ለመከላከያ ሠራዊት በመስጠት ራሱንና ሕዝቡን እንዲያድን የተሰጠው የ3 ቀን የጊዜ ገደብ ስለተጠናቀቀ በቀጣይ ቀናት የመጨረሻው ሕግ የማሰከበር ወሳኝ ተግባር ይከናወናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦፊሴላዊ የፌስቡክ ሰሌዳቸው፣ በዚህ ጥሪ የተጠቀሙ የትግራይ ልዩ ኃይልና የሚሊሽያ አባላት ለወሰዱት ኃላፊነት የተሞላው ሕዝባቸውን የማዳን ውሳኔ ይመሰገናሉ ብለዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት ቀናት በተደረጉ ፍተሻዎች ከአንድ ሺህ በላይ ሽጉጥን ጨምሮ ቦምብ፣ ፈንጂ፣ የጦር ሜዳ መነጽር እና የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች መያዛቸው ተገለጸ።

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ኮሚሽነሩ በመላ አገሪቱ በሚገኙ ከተሞች ጸጥታ የማደፍረስ ሙከራዎች ሊደረጉ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ችግሩን ለመከላከልም ጠበቅ ያለ የፍተሻ ስራ እንደሚሰራ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በሌላ በኩል በቅርቡ የታገዱ 14 የግል የጥበቃ ድርጅቶች ስር ተቀጥረው የሚሰሩ የጥበቃ ሰራተኞች ስራቸውን በጥንቃቄ እንዲያከናውኑ ኮሚሽኑ አሳስቧል።በታገዱት ድርጅቶች ስር ተቀጥረው የሚሰሩ የጥበቃ ሰራተኞች ውስጥ ሰላማዊ የሆኑትን ሰላማዊ ካልሆኑት የመለየት ስራ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመው፤ ውጤቱ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ አመልክተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጥቆማ‼️

በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ዘመዶቻቹ የጠፉባችሁ(የት እንዳሉ የማታውቋቸውን) ሰዎች ደህንነት ለማወቅ ከላይ በተቀመጠው የቀይ መስቀል ስልክ ደውላችሁ መረጃ ማግኘት እንደምትችሉ አለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታውቋል።የስልክ መስመሮቹ ከሚደውለው ሰው ብዛት አንፃር ሊጨናነቁ ስለሚችሉ ደጋግመው ይሞክሩ።

ስልክ ቁጥሮቹ:

+251943122207
+251115527110 ናቸው።

Forward በማድረግ ለወዳጅዎ ያጋሩ!
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ከረፋዱ 5:30 ጀምሮ "ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ" በሚል የ2 ደቂቃ ፕሮግራም ይካሄዳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎችን ጥሪ የተቀበሉ ኢትዮጵያውያን በያሉበት ሆነው ለ1 ደቂቃ ቀኝ እጃቸውን በግራ ደረታቸው ላይ አድርገው በመቆም ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ክብር ይገልጻሉ።

ይህ ሲጠናቀቅ በቀጣዩ አንድ ደቂቃ ባሉበት ሆነው ባለማቋረጥ ለ አንድ ደቂቃ ያጨበጭባሉ።

5:33 ደቂቃ ሲሆን መገናኛ ብዙኃን የጥላሁን ገሠሠን ኢትዮጲያ የሚለውን ሙዚቃ ያጫውታሉ።

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ስሙ ኢንፎኔት ኮሌጅ አካባቢ አንድ በርሜል ገንዘብ ወድቆ ተገኘ።

በዚህ ስፍራ በአንድ በርሜል ተጠቅጥቆ መገኘቱን የኢትዮ ኤፍ ኤም ሪፖርተር በአካል ተገኝቶ አረጋግጧል።የተገኘው ገንዘብ የኢትዮጵያ ብር እና ዶላር ሲሆን ገንዘቡን ማን እንደጣለው ያልተተረጋገጠ ሲሆን የአካባቢው ፖሊስ በመኪና ጭኖ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰደውም ሪፖርተሩ አረጋግጧል።በተያያዘ ዜና በዚሁ ወረዳ ጣልያን ሰፈር ልዩ ስሙ ጉሊት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ አዛውንት ቤት ቁጥሩ እስካሁን ያልተረጋገጠ ገንዘብ በማዳበሪያ እና በመዘፍዘፊያ አስቀምጠው ተይዘዋል።አዛውንቷ በልመና ስራ የሚተዳደሩ ናቸው የተባለ ሲሆን የገንዘቡን መጠን ለማወቅ ቆጠራ እየተካሄደ መሆኑን ተሰምቷል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ጅቡቲ ለኢትዮጵያ የግዛት አንድነት መጠበቅ የዐቢይ አህመድ አስተዳደርን “ብቸኛው ዋስትና” አድርጋ አቀረበች!

ህወሓት በትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከፈጸመበት ከዛሬ 15 ቀናት በፊት ጀምሮ የተቀሰቀሰውን ግጭት በአንክሮ እየተከታተልኩ ነው ያለችው ጅቡቲ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት መጠበቅ እንደምትደግፍ አስታወቀች፡፡የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ሁኔታውን የተመለከተ መግለጫን አውጥቷል፡፡

በመግለጫው የጅቡቲ መንግስት ለኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት መጠበቅ “ብቸኛው ዋስትና” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ናቸው የሚል የተረጋገጠ አቋም እንዳለው አስታውቋል፡፡በተጨማሪም ጅቡቲ ይህ ውስጣዊ ያለችው ችግር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አመራር በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጥሪ አቅርባለች፡፡ለችግሩ ሰላማዊ መፍትሄ ለመስጠት የሚደረገውን ጥረት በተፈለገችበት ጊዜ ለመደገፍ የሚያስችል ዝግጁነት እንዳላትም ሪፐብሊካዊቷ ጂቡቲ አስታውቃለች፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
34 የህወሃት የፋይናንስ ተቋማትን ማሳገዱን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል።

ሜጋ ማተሚያ፣ ሱር ኮንስትራክሽን ፣ ጉና የንግድ ስራዎች ፣ ኢፈርት ኤሌክትሪካል ቢዝነስ ፣ ትራንስ ኢትዮጵያ ፣ መስፍን ኢንደስትሪያል ኢንጂነሪንግ ፣ ሠላም የህዝብ ማመላለሻ ማህበር፣ ኢፈርት ኃ/የተ/የግ ማህበር እገዳው ከተላለፈባቸው መካከል ናቸው።

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ከረፋዱ 5:30 ላይ ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለው በሚል ፕሮግራም ተካሄዷ።

ከተላኩል ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች በጥቂቱ

ፎቶ 📸 ከወሎ ዩንቨርስቲ !
@Yenetube @Fikerassefa
ዛሬ ከረፋዱ 5:30 ላይ ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለው በሚል ፕሮግራም ተካሄዷ።

📸አዲስ አበባ ሚሊኑክ አደባባይ
@Yenetube @Fikerassefa
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ ከረፋዱ 5:30 ላይ ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለው በሚል ፕሮግራም ተካሄዷ።

📸ተክለሃይማኖት አከባቢ አዲስ አበባ
@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
34 የህወሃት የፋይናንስ ተቋማትን ማሳገዱን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል። ሜጋ ማተሚያ፣ ሱር ኮንስትራክሽን ፣ ጉና የንግድ ስራዎች ፣ ኢፈርት ኤሌክትሪካል ቢዝነስ ፣ ትራንስ ኢትዮጵያ ፣ መስፍን ኢንደስትሪያል ኢንጂነሪንግ ፣ ሠላም የህዝብ ማመላለሻ ማህበር፣ ኢፈርት ኃ/የተ/የግ ማህበር እገዳው ከተላለፈባቸው መካከል ናቸው። @YeneTube @FikerAssefa
የባንክ ሂሳብ የታገደባቸው 34 የኤፈርት ድርጅቶች የወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ነው!

የፈደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የባንክ ሂሳባቸው እንዲታገድ ያደረገባቸው 34 የትግራይ የመልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኤፈርት) ድርጅቶች ላይ የወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። ጠቅላይ አቃቤ ህግ የድርጅቶቹን የባንክ ሂሳብ ያሳገደው ሰኞ ህዳር 7፤ 2013 ለባንኮች በጻፈው ደብዳቤ ነው።

ሰላሳ አራቱ ድርጅቶቹ የባንክ ሂሳባቸው እንዲታገድ የተደረገው ከተጠረጠሩባቸው ሶስት ወንጀሎች ምርመራ ጋር በተያያዘ መሆኑን መስሪያ ቤቱ በደብዳቤው አስታውቋል።ድርጅቶች ከተጠረጠሩባቸው ወንጀሎች መካከል “በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች የሚፈጸሙ የዘር ተኮር ጥቃቶችን፣ የሽብር ተግባራትን እና ሕገ መንግስታዊ ስርዓትን በኃይል ለመናድ ከሚሰሩ አካላት ጋር በመመሳጠርና ግንኙነት በመፍጠር በገንዘብ መደገፍ” የሚል ይገኝበታል።

ድርጅቶቹ በሙስና እና በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀሎችም ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የጠቅላይ አቃቤ ህግ ደብዳቤ ያስረዳል። የፈደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለምርመራው ይረዳው ዘንድ የድርጅቶቹን የባንክ ሂሳብ እንቅስቃሴ የሚያመለክቱ ማስረጃዎች በአስቸኳይ እንዲላክለትም ጠይቋል።

* የ34ቱን ድርጅቶች ሙሉ ዝርዝር ከላይ ከተያያዘው ምስላዊ መረጃ ይመልከቱ

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የባንክ ሂሳብ የታገደባቸው 34 የኤፈርት ድርጅቶች የወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ነው! የፈደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የባንክ ሂሳባቸው እንዲታገድ ያደረገባቸው 34 የትግራይ የመልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኤፈርት) ድርጅቶች ላይ የወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። ጠቅላይ አቃቤ ህግ የድርጅቶቹን የባንክ ሂሳብ ያሳገደው ሰኞ ህዳር 7፤ 2013 ለባንኮች በጻፈው ደብዳቤ ነው። ሰላሳ አራቱ ድርጅቶቹ…
ከ34ቱ ተቋማት ትምዕት እና መሶቦ ሲሚንቶ ከድምጸ ወያኔ መገናኛ ብዙሃን ጋር ሼር እንዳላቸው መረጋገጡን ከጠቅላይ አቃቤ ህግ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በዚህ መሰረት ድምጸ ወያኔ ከትምዕት 8 ሚሊዮን ብር ብሎም ከመሶበ ሲሚንቶ 61 ሚሊዮን ብር በላይ የአክሲዮን ድርሻ እንዳለው ተቋሙ ገልጿል።በዚህም ድምጸ ወያኔ አሁን ላይ በኢትዮጵያ እያካሄደ ባለው ግጭት የገንዘብ ድጋፍ ከእነዚህ ተቋማት እንደሚያገኝ በሰነድ መረጋገጡን ኃላፊው ተናግረዋል።ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከአምስት በላይ የሚሆኑ የተቋሙን አዋጅ መነሻ በማድረግ በሁሉም ባንኮች የ34ቱንም የፋይናንስ ተቋማት የሂሳብ አካውንት ማሳገዱን ለማወቅ ተችሏል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ለህወሀት ቡድን የዲፕሎማሲ ስራ ሲሰሩ እንደነበር አንድ የኢትዮጵያ ባለስልጣን ተናገሩ፡፡

የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ለህወሀት ቡድን የዲፕሎማሲ ስራ ሲሰሩ እንደነበር ተገለፀ፡፡ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም ለህወሀት ቡድን ዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ ድጋፍ እንዲደረግ የአለም መንግስታትን በመጠየቅ ረገድ ሙሉ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ገልፀዋል፡፡ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ለአናዶሉ ኤጀንሲ እንደተናገሩት የሀገር መከላከያ ሰራዊት በህወሀት ቡድን ላይ ህግ የማስከበር ዘመቻ ከጀመረበት ዕለት አንስቶ ዶ/ር ቴውድሮስ ሲያደርጉት የነበረውን እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ መንግስት ጠንቅቆ ያውቃል ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በህወሃት ላይ የሚወስደውን ወታደራዊ እርምጃ እንዲያስቆሙ እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲያሳድሩ ሲጠይቁ ነበር ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል፡፡እንደ አውሮፓውያኑ ከ 2017 ጀምሮ በአለም ጤና ድርጅት (WHO) ውስጥ እያገለገሉ የሚገኙት ዶ/ር ቴድሮስ የህወሀት ቡድን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ሲያገለግሉ እንደነበር ይታወቃል፡፡እንደ አውሮፓውያኑ ከ 2005 እስከ 2012 የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር እንዲሁም ከ 2012 እስከ 2016 ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡

የአናዶሉ ዜና👇👇

https://www.aa.com.tr/en/africa/ethiopia-who-director-general-works-as-tplf-diplomat/2046193

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ነጻ በሆኑ አካባቢዎች መዋቅሩን እንደሚያደራጅ ገለጸ!

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከህወሃት ጁንታ ቡድን ነጻ በሆኑ አካባቢዎች መዋቅሩን እንደሚያደራጅ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ገለጹ።ዋና ስራ አስፈጻሚው በሰጡት መግለጫ፤ ዋና ስራ አስፈጻሚው የፕሬዚዳንቱን ስራ ስለሚሰራ ክልሉ ሙሉ ለሙሉ ነጻ ሲወጣ መንግስታዊ ስራውን ተክቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል።በዚህም መሰረት የክልሉን ካቢኔ እንደሚያደራጅና የዞን አስተዳዳሪዎችን እንደሚሾም ገልጸው፤ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤቶች ባሉበት እንዲቀጥሉ የሚደረግ መሆኑን አመልክተዋል።ስራ አስፈጻሚውን አካል እንደሚመራ፣ እንደሚያስተባብር እንዲሁም የክልሉን ዕቅድና በጀት እንደሚያጸድቅ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሰሜን በሚደረገው የህግ ማስከበር ዘመቻ የተሰደዱ ወገኖችን የመመለስና መልሶ የማቋቋም ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሰላም ሚንስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል አሳሰቡ፡፡

በሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሚመራው ከአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተውጣጡ የስራ ሃላፊዎችን የያዘው የሰብዓዊ ድጋፍ ቡድን በሰሜን እየተደረገ ካለው የህግ ማስከበር እንቅስቃሴ ጎን ለጎን የተፈናቀሉና ከአገር ውጭ የተሰደዱ ወገኖችን ወደ ቤታቸው የመመለስና መልሶ የማቋቋም ስራውን አጠናክሮና በተቀናጀ መልኩ መቀጠል እንደሚገባው ተገልጿል።

ከሰብዓዊ ድጋፍ ቡድኑ ጋር በተዘጋጀ የምክክር መድረክ የሰላም ሚንስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ድጋፉ ከመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት በመተባበር እንደ ሁኔታው አስቸኳይነት በፍጥነት መተግበሩን እንዲቀጥል አሳስበዋል። ሚኒስትሯ ጉዳዩ ፋታ የሚሰጥ ስላልሆነ የቡድኑን ከፍተኛ ርብርብ እንደሚሻም ተናግረዋል።የሰብዓዊ ድጋፍ ቡድኑ የተሰደዱና የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ የማቋቋሙ ስራ ላይ ፈጣንና የተደራጀ እንቅስቃሴ የሚደረግበትን አቅጣጫ አስቀምጠዋል ብለዋል።

ምንጭ፦ ሰላም ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኒጀር አቻውን በአዲስ አበባ ስቴዲዮም ያስተናገደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 3 ለ0 አሸነፈ!

ዋልያዎቹ በ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ፣ መስኡድ መሀመድ እና ጌታነህ ከበደ ጎሎች ኒጀርን ከከመልካም የጨዋታ እንቅስቃሴ ጋር በማሸነፍ በስድስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚያስቀምጣቸውን ትልቅ ውጤት አስመዝግበዋል።

[Hatrick Sport]
@YeneTube @FikerAssefa