YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
YeneTube
መቐለ ከተማ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ መጀመሩን የBBC ትግርኛ ዘጋቢ ከሆነው ግርማይ ገብሩ ፌስቡክ ገፅ ተመልክተናል። @Yenetube @Fikerassefa
የትግራይ ክልልና የፌደራል መንግሥት ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ከገቡ ሶስተኛ ቀናቸውን አስቆጥረዋል። ግጭቱን ተከትሎ በመቀሌ ከተማና በክልሉ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክና #የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀምሯል።

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ትናንት ጥቅምት 26/2013 ዓ.ም የተመለሰ ሲሆን የትራንስፖርት አገልግሎት ደግሞ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 27/2013 ዓ.ም መጀመሩን የመቀሌ የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል።

ምንም እንኳን ትራንስፖርት ቢጀመርም ከመቀሌ ከተማ ወደተለያዩ ክፍሎች የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች በሙሉ ከከተማው ፖሊስ ልዩ ፍቃድ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።

ግጭቱን ተከትሎ የተቋረጠው የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት እንደተቋረጠ ነው።
ከቀናት በፊት ተኩስ የተሰማባት መቀሌ ከተማ በአንፃራዊ ሁኔታ የተረጋጋ ሁኔታ ላይ ብትገኝም ማህበረሰቡ ግን ጦርነቱ በፈጠረው ውጅንብር ስጋት ላይ መሆኑንም የቢቢሲ ዘጋቢ ይናገራል።
በትናንትናው እለት በመቀሌ ከተማ የጦር አውሮፕላን ሲያንዣብብ የነበረ መሆኑን የታዘበው የቢቢሲ ዘጋቢ በድምፁም በርካቶች #መደናገጥና ፍራቻ ውስጥ እንደገቡ አክሎ ገልጿል።

[BBC]
@Yenetube @Fikerassefa