በመተከል ዞን ወንበራና ቡለን ወረዳዎች የተከሰተውን የፀጥታ ችግር የማረጋጋት ስራ እየተሰራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር አምሳሉ ኢረና እንዳሉት ከሰሞኑም በመተከል ዞን ቡለንና ወንበራ ወረዳ በሚገኙ አንዳንድ ቀበሌዎች ላይ "የጥፋት ተልእኮ በተሰጣቸው ኃይሎች" የተከሰተው የፀጥታ ችግር የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች፣ የፌደራል ፖሊስና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በቦታው ተገኝቶ የህግ የበላይነትን የማስፈንና የማረጋጋት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡የፀጥታ ኃይሎች እየሰሩት ባለው ስራ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ምክትል ኮሚሽነሩ በወንበራ ወረዳ መልካን ቀበሌ በጥፋት ኃይሎች 26 ንጹሃን ዜጎች መታገታቸውን አስታውቀዋል፡፡
በተመሳሳይ በቡለን ወረዳ ኤፓር ቀበሌ ላይ የጥፋት ቡድኑ በንፁኃን ዜጎች ላይ ጥቃት ማድረሱን ያስታወቁት ምክትል ኮሚሽነሩ በፀጥታ ችግሩ የደረሰው የጉዳት መጠን ምን ያክል መሆኑን በአካባቢው የኔት ወርክ ችግር ያለ በመሆኑ ትክክለኛ አሁናዊ መረጃ ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ እንደሌላቸው ጠቁመዋል፡፡የደረሰውን ጉዳት ትክክለኛ መረጃ በማጣራት ኮሚሽኑ በቀጣይ ለህብረተሰቡ የሚያሳውቅ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡የአካባቢውን ሰላምና የህዝቡን ደህንነት ለማስከበር የጸጥታ አካሉ ከሚያደርገው ጥረት ጎን ህብረተሰቡም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር አምሳሉ ኢረና ጥሪ አቅርበዋል፡፡
[የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት]
@YeneTube @FikerAssefa

አዲስ አበባ ራሷን የቻለች የፌደሬሽኑ ክልል እንድትሆን ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ጥሪ አድርጓል። የክልልነት መብትን በሕጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እና የከተማው ነዋሪዎች በሚሳተፉበት ሕዝበ ውሳኔ ለማረጋገጥ እንዲቻል መንግሥት ላይ ግፊት ለማድረግ ጥሪ አድርጓል። የከተማዋ ነዋሪ ፓርቲው ትናንት በጀመረው የፊርማ ማሰባሰብ እንቅስቃሴ በነቂስ እንዲሳተፍም ፓርቲው አሳስቧል።
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
animation.gif
338 KB
የቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ ከተናገሩት👇👇
<<የቤቶች ግንባታ የተጀመረው ከ15 ዓመታት በፊት ሲሆን፣ እስካሁን ተገንብተው ከተላለፉት፣ እየተገነቡ ካሉትና ዕጣ ሊወጣባቸው ከታቀዱት ከ300 ሺሕ በላይ ቤቶች ውስጥ በከተማው ካቢኔ የተወሰነው ለ20 ሺሕ አርሶ አደሮች ነው።እንዲህ ዓይነት ውሳኔዎች አሁን የተጀመሩ አይደሉም።ከዚህ በፊትም (በቀድሞዎቹ አስተዳደሮች) ለመምህራንና ለጤና ባለሙያዎች፣ ለፓርላማ አባላት፣ እንዲሁም ለአገር መከላከያ ሠራዊት የጦር ጉዳተኞች በተመሳሳይ ውሳኔ ሲሰጥ ነበር።የአርሶ አደር ሲሆን የፖለቲካ ፓርቲ አጀንዳ የሚሆንበት ምንም ምክንያት የለም።
አርሶ አደር በመሆናቸው በደሉን ተሽክመው ይኑሩ የሚል ጭፍን ፍርድ ከሌለ በስተቀር። አርሶ አደሩ እኮ ለብዙ ዓመታት ከራሱ መሬት፣ ከራሱ የእርሻ ማሳ ‹‹በልማት›› ምክንያት (በሪል ስቴት፣ በኢንዱስትሪ ፓርክ፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ) ምክንያት ከመሬቱ ተነቅሏል። እኛ ያደረግነው ምንድን ነው? በአጠቃላይ ከ6 ክፍላተ ከተሞች ከኑሮአቸው ስለተፈናቀሉ እንዲቋቋሙ ስለተፈለገ በካቢኔ አስወሰንን።ይህም ማለት ከአጠቃላይ የቤቶች ግንባታ ስድስት በመቶ ለተፈናቀሉ አርሶ አደሮች እንዲሰጥ ነው የወሰንነው።
ከ20 ሺሕ ውስጥ አርሶ አደር ያልሆኑ ሰዎች አሉ፣ በጥናታችን ለይተናል ካሉ ደግሞ ይህ ሥራቸው ያስመሠግናቸዋል።ነገር ግን ይህንን ጥናት ያሉትን ነገር ይፋ ለማድረግ ለምን የአመራር ሽግሽግ ወቅት ጠበቁ? ለምን አሁን? እኔ ወደ ሌላ ኃላፊነት እየሄድኩ ባለበት ወቅትና የቀረበውን ትችት መልስ ለመስጠት በማልችልበት ወቅት ለምን ለማቅረብ መረጡ የሚለውን ጥያቄ አንስቼ መልሱን ለራሳቸው መተው እፈልጋለሁ።>>
ሙሉውን ለማንበብ👇👇👇
https://telegra.ph/-09-09-1117

ሸገር ፓርክ ነገ ይመረቃል።
በጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስተባባሪነት እየተገነባ ያለው የሸገር ፓርክ ነገ ይመረቃል ተብሏል።ፓርኩን ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት እንደሚመረቅ ከጠቅላይ ሚንስቴር ጽህፈት ቤት ሰምተናል።የፓርኩ ምረቅ ስነ ስርዓነገ ጠዋት ጀምሮ እስከ ምሽት የሚቆይ ፕሮግራም መዘጋጀቱንም ኢትዮ ኤፍ ኤም ከጽህፈት ቤቱ ያገኘው የዝግጅት ሰነድ ይጠቁማል።የሸገር ፓርክ ግንባታ ከአንድ ኣመት በፊት "ገበታ ለሸገር" በሚል በተሰናዳ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ በተሰበሰበ ገንዘብ መገንባቱ ይታወሳል።የፓርኩ ዋና ዋና ግንባታ በመገባደዱ ምክንያት ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።
[Ethio FM]

ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በወልቃይት ጠገዴ በተለይም በአማራ እና ትግራይ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት እንደነበር የአካባቢው የፀጥታ አካላት ለቢቢሲ ተናገሩ።
ቢቢሲ የሁለቱንም ክልል የፀጥታ ኃላፊዎች ያነጋገረ ሲሆን አንዳቸው በሌላኛቸው ክልል ወገን ግጭት መቀስቀሱን ገልፀዋል።ቢቢሲ በአማራ ክልል ሥር የሚገኘው የጠገዴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ሙሉጌታ ስለ ጉዳዩ ጠይቆ፣ እርሳቸው በሚያስተዳድሩት ወረዳ ምንም ግጭት አለመኖሩን ገልጸው በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኘው የጸገዴ ወረዳ ግን ከምርጫው ጋር ተያይዙ ግጭት መኖሩን እንደሰሙ ለቢቢሲ ገልጸዋል።ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ የትግራይ ክልል ፀጥታ ከፍተኛ ኃላፊም በምዕራብ ትግራይ ጸገዴ አካባቢ በትግራይ መሬት ገብቶ የተኮሰ አካል እንደሌለ በመግለጽ "በአማራ ክልል ውስጥ ግን ተኩስ እንደነበረ ሰምተናል" ሲሉ ተናግረዋል።
[BBC]

YeneTube
ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በወልቃይት ጠገዴ በተለይም በአማራ እና ትግራይ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት እንደነበር የአካባቢው የፀጥታ አካላት ለቢቢሲ ተናገሩ። ቢቢሲ የሁለቱንም ክልል የፀጥታ ኃላፊዎች ያነጋገረ ሲሆን አንዳቸው በሌላኛቸው ክልል ወገን ግጭት መቀስቀሱን ገልፀዋል።ቢቢሲ በአማራ ክልል ሥር የሚገኘው የጠገዴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ሙሉጌታ ስለ ጉዳዩ ጠይቆ፣ እርሳቸው በሚያስተዳድሩት ወረዳ…
የአማራ ክልል የፀጥታ ኃይል ፣ የትግራይ ክልል በሚያስተዳድረው «ፀገዴ» ወረዳ ጨጓርጉዶና ማይወዲሳህላይ በተባሉ ቀበሌዎች ጥቃት ለማድረስ ተንቀሳቅሷል የሚለውን ስሞታ በአማራ ክልል የጠገዴ ወረዳ አስተባበለ።
በአማራ ክልል የ «ጠገዴ» ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ሙሉጌታ ለዶይቼ ቬለ በስልክ እንደተናገሩት «የአማራ ክልል የፀጥታ ኃይል ትግራይ በሚያስተዳድረው «ፀገዴ» ወረዳ ጨጓርጉዶና ማይወዲሳህላይ በተባሉ ቀበሌዎች ጥቃት ለማድረስ ሲንቀሳቀስ በትግራይ የፀጥታ ኃይል ተመትቶ ተመለሰ» እየተባለ ከወደትግራይ የሚነዛው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው» ብለዋል።
ችግሩ አልመርጥም ምረጥ በሚል እሰጣ ገባ፣ እዛው የራሳቸው የፀጥታ ኃይል በነዋሪው ኅብረተሰብ ላይ የፈጠረው ችግር እንደሆነ ነው አቶ ጌታቸው ያስረዱት።«የወሰደው ምንም ዓይነት እርምጃ የለም፤ ምንም ዓይነት ጥቃት የለም ከእውነት የራቀ ነው ይሄ። የራሳቸው ኃይል የፈጠረው ችግር እንጂ ወደእነርሱ የሄደ ኃይል የለም። እዛው ላይ ምርጫውን መሠረት አድርጎ ምርጫ አንመርጥም የሚል አካል አለ፤ እዚያው እርስ በርሳቸው የተፈጠረ ችግር ነው። በፍጹም ስህተት ነው። ከእውነት የራቀ ነው።»ስለጉዳዩ ከትግራይ ክልል የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም።
[DW]

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 916 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ የ17 ሰዎች ህይወት አለፈ!
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 15,561 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 916 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
319 ሰዎች ሲያገግሙ 17 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
እስካሁን በአጠቃላይ 61,700 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 23,054 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ966 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

የሻምበል አበበ ቢቂላ የሮም ኦሎምፒክ ድል ዛሬ ስልሳ አመት ሞላው!
ሁሌም አዲስ አመትን ስናከብር ከምንጊዜውም ጀግናችን የአፍሪካ ኩራት ሻምበል አበበ ቢቂላ የሮም ኦሊምፒክ ድል ጋር ነው።ይሄ ታላቅ ድል ዘንድሮ 60 ዓመት ሞላው።
ወቅቱ በኢትዮጵያ ቀን አቆጣጠር የአዲስ አመት ዋዜማ ምሽት ጳጉሜ 5/1952 ዓ,ም በዛሬዋ ቀን ነበር አዲሱን ዓመት 1953ን በታላቅ ደስታ ኢትዮጵያዊያን መስከረምን የተቀበሉበት።ይህ ታላቅ ድል ለአፍሪካ ከተመዘገበ 60ዓመት ሞላው።
★ክብር ለጀግኖቻችን
★መልካም አዲስ አመት
Via EOC

ለፀጥታ ሲባል በአዲስ አበባ ማንኛውም ግለሰብ ሪችት መተኮስ እንደማይችል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት የሚዲያ ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሰጡት መግለጫ÷ ሪችትን ምክንያት በማድረግ የሽብር ጥቃት ለማድረስ እየተዘጋጁ ያሉ ግለሰቦች መኖራቸውን ፖሊስ በጥናት ደርሶበታል ብለዋል።ስለሆነም ወንጀልን ለመከላከል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ማንኛውም ግለሰብ ሪችት መተኮስ አይችልም ብለዋል። ይህንን ተላልፎ ሪችት የሚተኩስ ማንኛውም ሰው በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚውል ተናግረዋል።
በተያያዘ ዜናም በአዲስ አበባ በአስሩም ክፍለ ከተማ በጥናት በተደረገ ፍተሻ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።በፍተሻው አንድ ቦምብ እና አራት ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው የተናገሩት።ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም የተጠረጠሩ 180 ግለሰቦች ተይዘው ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑንም አመላክተዋል።ዋና ኢንስፔክትር ማርቆስ አያይዘውም ህብረተሰቡ የራሱን ሰላም በመጠበቅ፣ ሰላምን ሊያውኩ የሚችሉ ወንጀለኞችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት እንዲተባበርም ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ እና ተመድ 7 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር የዘላቂ ልማት ትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈራረሙ!
ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ7 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር የዘላቂ ልማት ትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈራረሙ።ማዕቀፉ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን ከአውሮፓውያን 2020 እስከ 2025 የሚተገበር መሆኑ ተነግሯል፡፡የስምምነት ሰነዱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴና በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ተጠሪ ዶክተር ካትሪን ሶዚ ተፈራርመዋል።አቶ አህመድ በስምምነቱ ወቅት ማዕቀፉ በአገሪቱ ለሚተገበረው የ10 ዓመት ዕቅድ በአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ ግብር ለተካተቱና አገሪቱ ቅድሚያ ለሰጠቻቸው የልማት ጉዳዮችን ይውላል ሲሉ ነው የገለጹት።
[FBC]

በትግራይ ምርጫ ለሊቱ ድምፅ ሲቆጠር አድሯል፡፡ በሁሉም የምርጫ ጣብያዎች ውጤት ይፋ እየተደረገ ነው፡፡ህወሓት ከፍተኛ ድምፅ ማግኘቱ በአንዳንድ ጣብያዎች የተለጠፈ ውጤት ያመለክታል፡፡
Via Million HaileSelasie
@YeneTube @FikerAssefa
Via Million HaileSelasie
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በሬድዮ በቀጥታ ለማስተላለፍ ለሚፈልጉ ድርጅቶች ሊሸጥ ነው!
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒ በ2013 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በሬድዮ የቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ ለሚፈልጉ የሚዲያ ተቋማት ሊሸጥ መሆኑን አስታውቋል።የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒ የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን ለመምራት የተቋቋመ ህጋዊ ተቋም ነው፡በመሆኑም ካምፓኒው በቀጣይ የሚካሄደውን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በቀጥታ የሬድዮ ስርጭት ለማስተላለፍ የሚያስችለውን መብት፣ ህጋዊ ፍቃድ ላላቸው የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት ለመሸጥ በሚቀጥለው ሳምንት ጨረታ እንደሚያወጣ ተነግሯል፡፡ሊግ ካምፓኒው ቀደም ሲል የሊግ ውድድሩን የቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት እና የውድድር ስያሜ ሽያጭ ጨረታ አውጥቶ አሸናፊውን ለመለየት በሂደት ላይ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡የሚያገኘው ገቢ የካምፓኒውን እና የተወዳደዳሪ ክለቦችን ፋይናንሻል አቅም ያሳድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በ7 ተከሳሾች ላይ አቃቤ ህግ ክስ መሰረተ።
ክሱ በሁለት የተከፈለ ሲሆን፥ ከአቶ እስክንድር ነጋ እስከ 3ኛ ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ በሽብር ወንጀል ነው ክስ የተመሰረተው።ቀሪዎቹ ማለትም ከ4ኛ እስከ 7ኛ ተከሳሾች ላይ ደግሞ የእርስ በእርስ ግጭት በመፍጠር ወንጀል ነው ክስ የተመሰረተው።ክሱ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው የተመሰረተው።ተከሳሾቹ በሰኔ 23 እና 24 2012 ዓ.ም የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ፣ ማደራጀትና ማስተባበር ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ ሲከናወንባቸው መቆየቱ የሚታወስ ነው።በአሁኑ ወቅት ችሎቱ ጉዳያቸውን እየተመለከተ እንደሆነ ፋና ዘግቧል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ 508 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሱን አስታወቀ።
የውሳኔ ሀሳቡ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደድር ቀርቦ ተቀባይነት ያገኙ በመሆኑ ከነገ መስከረም 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚለቀቁ በክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፤ የሕግ አገልግት ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ንጋቱ ዓለሙ ዛሬ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።አቶ ንጋቱ እንደተናገሩት ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች በማረሚያ ቤት የስነ ምግባር ለውጥ ያሳዩ ናቸው።
የሚፈቱት በፈጸሙት ወንጀል የተጸጸቱ ይኸንንም ማረሚያ ቤቱ ያረጋገጠላቸው ታራሚዎች ሲሆኑ ከአንድ ዓመት ከአራት ወር እስከ አስራ ሰባት ዓመት በእስር ቤት የቆዩ ናቸው።በዚሁ መሰረት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ከሚገኙት ሶስት ዞኖች ከካማሺ ማረሚያ ቤት 69 ታራሚ፣ ከመተከል ዞን 312 እና ከአሶሳ ዞን ደግሞ 127 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን ነጋሳ ደሳለኝ ከአሶሳ ዘግቧል። ከሚፈቱት መካከል ሰባቱ ሴቶች ናቸው።