YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአሜሪካ ኮንግረስ 6 አባላት አገራቸው ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ዕርዳታ ከመከልከል እንድትታቀብ ጠየቁ።

ለውጭ ጉዳይ ምኒስትር ፖምፔዎና የግምዣ ቤት ኃላፊው ስቴፈን ምኑችን በጻፉት ደብዳቤ ውጥረቱን ለማርገብ አሜሪካ ገለልተኛ ልትሆን ይገባል ብለዋል።ዕርዳታ ክልከላው "እምነት ከሚጣልባት ወዳጃችን ያለንን ግንኙነት ከማሻከር በተጨማሪ ስሱ በሆነው የኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ የድርድር ሒደት ያለንን ሐቀኛ የአደራዳሪነት አቋም ያሳጣል" ሲሉ የፖምፔዎ መሥሪያ ቤት የደረሰበትን አቋም ነቅፈዋል።የትራምፕ አስተዳደር ውሳኔ "የአሜሪካን ገለልተኛ ታዛቢነት በመካድ ለአንድ ወገን ያደላ፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሸረሸረ እና የአፍሪካ ኅብረትን ጥረት የቀለበሰ" ሲሉ ያጣጣሉት የኮንግረስ አባላት በቀጠናው ካላት ጥቅም እንደሚቃረንም ጠቁመዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ፤ ነሐሴ 30 በጠራው ስብሰባ ላይ በራያ፣ ወልቃይትና ወጂራት አካባቢዎች ይደርሳል የሚሉትን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንዲወያይና የመፍትሔ አቅጣጫ እንዲያስቀምጥ ትናንት ምክር ቤቱ አጠገብ ሰልፍ የወጡ ጠይቀዋል። የወጣው ሰው በኮቪድ-19 ምክንያት የተወሰነ እንደነበረም ተገልጿል።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የተጠየቁት የትግራይ ክልል የኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊያ ካሳ የወልቃይትና የራያ ህዝብ የራሳቸውን እድል በራሳቸው እንዲወስኑ በትግላቸው ያረጋገጡት የትግራይ ምርጫ ለመረበሽ በጣም ጥቂት በብር የተገዙ ሰዎች ያካሄዱት በማለት አጣጥለውታል።ወይዘሮ ሊያ "በክልሉ የሰብአዊ መብት ጥሰት አለ የተባለው ከሓቅ የራቀና ለህዝብ ንቀት ያላቸው እኛ እናውቅላሃለን በማለት ረብሻ ለመፍጠር በማሴር ነው እንዲህ የሚሉት" ብለዋል።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
ሱዳን በጎርፍ ምክንያት የሶስት ወር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አዋጀች!

የሰዱን የጸጥታና የመከላከያ ምክርቤት እስካሁን ለ99 ሰዎች ሞት ምክንያት በሆነው ጎርፍ ምክንያት ለሶስት ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጇን አስታወቀች፡፡የሱዳን ሰራተኛና ማህበራዊ ልማት ሚኒስትር እንዳሉት ከሞት በተጨማሪ ጎርፉ በ46 ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱንና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎችን መጉዳቱናከ100ሺ በላይ ቤቶችን ማውደሙን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡በሱዳን በዚህ አመት የተመዘገበው የዝናብ መጠን በፈረንጆቹ 1946ና 1988 ተመዝግቦ የነበረውን ክበረ ወሰን መስበሩን ሚኒስትር ሌና ኢል ሸክ ተናግረዋል፡፡ምክር ቤቱ በፈረንጆቹ 2020 ጎርፉ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ ኮሚቴ አቋቁሟል፡፡

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ ባስከተለው ጎርፍ በፈንታሌ ወረዳ 25 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ!

የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ ባስከተለው ጎርፍ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በፈንታሌ ወረዳና መተሀራ ከተማ ከ25 ሺህ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቀሉ።የኢዜአ ሪፖርተር ተዘዋውሮ እንደተመለከተው በመተሀራ ከተማ ብቻ ተፈናቃዮች በሰባት መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ይገኛሉ።በአካባቢው የሀሮ አዲ ቁጥር አንድ ትምህርት ቤትም በርከት ያሉ ተፈናቃዮች መኖራቸውንም ተመልክቷል።ተፈናቃዬዮች ጎርፉ ያደረሰው የሃብትና ንብረት ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ መንግስት አስቸኳይ ድጋፍ ያድርግልን ብለዋል።

ከተፈናቃዮቹ መካከል የሰባት ልጆች እናት ወይዘሮ ጽጌ ቱፋ አንዷ ናቸው።ጎርፉ ቤት ንብረታቸውን በማውደሙ የሚቀመስ ነገር በሌለበት፣ መብራትና ውሃም ጠፍቶ ችግር ላይ እንገኛለን ብለዋል።እስከ ትናንት ጥዋት ድረስ ከመንግስትም ሆነ ከለጋሾች ምንም አይነት ድጋፍ አለማግኘታቸውን ገልጸው አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።በትምህርት ቤቱ ውስጥ ተጠልለው የነበሩ አርሶ አደር መልካሙ አበራና ወጣት ዝናሽ መገርሳም በህይወት ዘመናቸው አይተውት የማያውቁት የጎርፍ አደጋ መድረሱን ይናገራሉ።

በመጋዘኖች የተከማቸ እህል በጎርፍ መወሰዱን ገልፀው አደጋው አቅም ደካሞችን ለከፋ ችግር ዳርጓል ይላሉ።የመተሀራ ከተማ ከንቲባ አቶ ታደለ ደሪርሳ ከተማዋ ሁለት ቀበሌና 14 ቀጠና ያላት ሲሆን አንዱ ቀበሌ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ወድሟል ብለዋል።በከተማዋ እስካሁን ከ13 ሺህ በላይ ቤተሰቦች ተፈናቅለው ከፌዴራል፣ ከክልልና ከህዝቡ የተሰበሰበ ድጋፍ ዛሬ መድረስ ጀምሯል ብለዋል።ለመጠለያ የሚሆን ሸራ፣ ለአስቸኳይ ምግብ የሚሆን ሩዝ ቴምር እንዲሁም መደሃኒት በማቅረብ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

እስካሁን የከተማዋ ነዋሪዎች በርካታ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀው በቀጣይ ሌሎች አካላትም እንዲረባረቡ ጠይቀዋል።

የምስራቅ ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ኢብሳ ሳዲቅ በዞኑ ስድስት ወረዳዎች እስካሁን ከ30 ሺህ በላይ ሰዎች በጎረፉ ሳቢያ መፈናቀላቸውን ገልጸዋል።በዞኑ በሉሜ፣ በዱግዳ ፣በቦሰት፣ በሊበን፣ በአዳማና ፈንታሌ ወረዳዎች ጎርፉ ከባድ ጉዳት አድርሷል ብለዋል።የወንዙ ሙላት የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ብዙ ጥረት ቢደረግም ባለመሳካቱ ተፈናቃዮች በትምህርት ቤቶችና ሌሎች ቦታዎች ተጠልለው ይገኛሉም ነው ያሉት።

የዞኑ ምክትል ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አበበ ማሞ በበኩላችው ተፈናቃዮች ለጤና ችግር እንዳይጋለጡ እየተሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።አሁን ላይ መድሃኒት መቅረብ መጀመሩንና በሶስት የተለያዩ አካባቢዎች የህክምና አገልገሎት ሲሆን 10 ሺህ አጎበር እና 80 ሺህ ማስክም ዝግጁ ሆኗል ነው ያሉት።በቀጣይ የመንግስት ድጋፍ እንዳለ ሆኖ ሌሎች አካላትም ለድጋፍ እጃቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ ቀርቧል።

[ኢዜአ]
@YeneTube @FikerAssefa
👎1
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን የምርጫ እንቅስቃሴ በተመለከተ የምክር ቤቱ የህገ መንግስት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ በዝግ እየመከረ ነው።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የፖለቲካ ፓርቲዎች በብሄራዊ መግባባት ዙሪያ እየተወያዩ ነው፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መሪነት፤ ከኢትዮጵያ የምስረታ ዘመን እስከ ስርአቶች ዝርጋታ ታሪካዊ - ጥናታዊ የመነሻ ሃሳብ ቀርቦ ወይይት መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡ዛሬም ለሁለተኛ ጊዜ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን /ኢ.ሲ.ኤ/ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

Via Prosperity Party
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን የምርጫ እንቅስቃሴ በተመለከተ የምክር ቤቱ የህገ መንግስት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ በዝግ እየመከረ ነው። [FBC] @YeneTube @FikerAssefa
በምክር ቤቱ የሕገ መንግሥትና የማንነት ጉዳዮች ቃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ወርቁ አዳሙ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ምክር ቤቱ ሕገ መንግሥቱን የመተርጎም ስልጣኑን በመጠቀም በሰጠው ውሳኔ መሠረት እንዲካሄድ ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃረን ምርጫ ለማድረግ የጀመረውን ጉዞ በተመለከተ ሦስት የውሳኔ ሐሳቦች ለምክር ቤቱ አቅርበው ውይይት እየተደረገበት ነው።

የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ወደ ጎን በመተው የትግራይ ክልል መንግሥት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 እና አዋጁን መሠረት አድርጎ ያተቋቋመውን የምርጫ ኮሚሽን ያሳለፋቸው ውሳኔዎችና የፈጸማቸው ተግባራት የሕገ መንግሥት ትርጉም ውሳኔ እንዲሰጥበት በሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

[አብመድ]
@YeneTube @FikerAssefa
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መረሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 1043 ተማሪዎች አስመረቀ::

በዛሬውም ቀን በመደበኛና በተከታተይ መረሃ ግብሮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ድግሪ ያሰለጠናቸውን 283 እንዲሁም በሰርተፊኬት 760 በጥቅሉ 1043 ተማሪዎችን አስመርቋል::

[Bule Hora University]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በምክር ቤቱ የሕገ መንግሥትና የማንነት ጉዳዮች ቃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ወርቁ አዳሙ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ምክር ቤቱ ሕገ መንግሥቱን የመተርጎም ስልጣኑን በመጠቀም በሰጠው ውሳኔ መሠረት እንዲካሄድ ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃረን ምርጫ ለማድረግ የጀመረውን ጉዞ በተመለከተ ሦስት የውሳኔ ሐሳቦች ለምክር ቤቱ አቅርበው ውይይት እየተደረገበት ነው። የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ወደ…
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም እንደ ራያ ዴሞክራሲያው ፓርቲና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ምርጫውን በሙሉ ዝግጅት ለመሳተፍ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታ ሳይኖር በዚህ ወቅት ምርጫ መደረጉ አግባብነት የለውም ብለው ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት ያለው መሆኑን ጉባኤው በውሳኔ ሀሳብነት አካቶታል፡፡

እንደ ወልቃይትና ራያ ባሉ አካባቢዎች ከማንነት ጉዳይ ጋር የተነሱ ቅሬታዎች ከምርጫው ጋር ተያይዞ በአካባቢዎቹ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመ ነው በሚል የቀረቡ አቤቱታዎችም ህገ መንግስታዊ መሰረት ያላቸው በመሆኑ ሊጤኑ እንደሚገባ ጉባኤው አመልክቷል፡፡የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ያቀረባቸውን የውሳኔ ሀሳቦችን ተከትሎ የፌደሬሽን ምክር ቤት ይበጃል ያለውን ውሳኔ እንዲያሳልፍ ጠይቋል፡፡

የፌደሬሽን ምክር ቤትም ዛሬ በጠራው አስቸኳይ ስብሰባው የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ባቀረበለት የውሳኔ ሀሳቦች ዙሪያ በዝግ እየመከረ ይገኛል፤ ይህን ተከትሎም የምክር ውይይት ካደረገበት በኋላ ውሳኔም ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን ከ900 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።

የሶስተኛ ትውልድ ዩኒቨርስቲ የሆነው የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ መርሃግብሮች ያስተማራቸውን 929 ተማሪዎች ዛሬ ለ7ኛ ጊዜ ባካሄደው የምረቃ ፕሮግራም አስመርቋል።

[MoSHE]
@YeneTube @FikerAssefa
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 326 ተማሪዎችን ዛሬ አስመረቀ።

ከተመራቂዎቹ መካከል 1 ሺህ 621 በመጀመሪያ፣705 ደግሞ በሁለተኛ ድግሪ ሲሆን ከመካከላቸውም 503 ሴቶች ናቸው።ተመራቂዎቹ በምህንድስና፣ ጤና፣ ተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ ዘርፎች በመደበኛ፣ ክረምት፣ ኤክስቴንሽንና ርቀት መረሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳምጠው ዳርዛ ገልጸዋል።ተማሪዎቹ ለዓለም ስጋት በሆነው የኮሮና ወረርሽኝ ፈተና ውስጥ ሆነው ቴክኖሎጂን በመጠቀም ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ለምረቃ መብቃታቸውን አስታውቀዋል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም እንደ ራያ ዴሞክራሲያው ፓርቲና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ምርጫውን በሙሉ ዝግጅት ለመሳተፍ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታ ሳይኖር በዚህ ወቅት ምርጫ መደረጉ አግባብነት የለውም ብለው ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት ያለው መሆኑን ጉባኤው በውሳኔ ሀሳብነት አካቶታል፡፡ እንደ ወልቃይትና ራያ ባሉ አካባቢዎች ከማንነት ጉዳይ ጋር የተነሱ ቅሬታዎች…
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ያካሄደውን አስቸኳይ ስብሰባን ተከትሎ ያወጣው መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል!

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ ዙር የፓርላማ ዘመን 5ኛ አመት 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ወደ ጎን በመተው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 እና አዋጁን መሰረት አድርጎ ያቋቋመው የምርጫ ኮሚሽን፣ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች እና የፈፃማቸው ተግባራት የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔ እንዲሰጥበት በሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ተጣርቶ ለመጨረሻ ውሳኔ ለምክር ቤቱ በሕገ መንግስት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች በኩል በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ውይይት አድርጓል፡፡

በውይይቱም ላይ በእስከ አሁኑ ሂደት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለትግራይ ሕዝብ ትልቅ ክብር ያለው መሆኑንና ህገወጥ አካላት በሚፈፅሙት ድርጊት ምክንያት በሕዝቡ ላይ ጉዳት ሊደርስበት አይገባም ብሎ የሚያምን መሆኑ እና በቀጣይም ችግሮችን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመፍታት እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡በሌላ በኩል የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የራያ ራዩማ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ እና የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ ያቀረቧቸውን ቅሬታዎች በመጥቀስ የትግራይ ክልል እያካሄደ ካለው ህገወጥ ምርጫ ጋር ተያይዞ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በሕገ መንግስቱ የተረጋገጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መብት አለማክበር ተቀባይነት የሌለውና ሊታረም የሚገባው መሆኑ ከማስቀመጡም ባሻገር የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛውን አገራዊ ምርጫ በተመለከተ ያስተላለፈውን ውሳኔ እና የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ በደብዳቤ ሕገ መንግስቱና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ እንዲከበር የሰጡትን ማሳሰቢያ አለመቀበሉ ኢ-ሕገ መንግስታዊ ነው ብሏል ምክር ቤቱ፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የሚከተሉትን የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔዎች በሙሉ አፅድቋል፡፡

1) የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 ከሕገ መንግስቱ አንቀጽ 55(15) እና አንቀጽ 55(2)(መ) ጋር ይቃረናል፤

2) የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012ን መሰረት አድርጎ የምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሙ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 102 ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠውን ስልጣን ይጥሳል፤

3) የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት፣ አስፈፃሚ አካላት እና የምርጫ ኮሚሽን ምርጫን በሚመለከት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 ያሳለፏቸው ውሳኔዎች እና የፈፀሟቸው ተግባራት ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 9(1) መሰረት እንዳልተደረጉ የሚቆጠሩ፣ የማይፀኑ እና ተፈፃሚነት የሌላቸው ናቸው በማለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ የመጨረሻ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢራን ኮሮና እየተስፋፋ ባለበት ወቅት ለ15 ሚሊዮን ተማሪዎቿ ት/ቤቶችን ከፈተች!

በኢራን ምንም እንኳን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እተባባሰ ቢሄድም ሀገሪቱ ለ15 ሚሊዮን ተማሪዎቿ ትምህርት ቤቶችን ከተዘጉ ከ7 ወራት በኋላ ልትከፍት ነው፡፡በመንግስት የተሾሙት የኢራን ሜዲካል ካውንስል ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ሬዛ ዛፋርጋንዲ ለትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ በጻፉት መልእክት የትምህርት ቤቶች በድንገት መከፈት በጤና ባለሙያዎች ላይ ጫና እንደሚያሳድር ጥርጥር እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክልል ደቡባዊ ዞን የአዋሽ ወንዝ ባደረሰዉ የጎርፍ አደጋ ከ130ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸዉ ተገለጸ!

በአፋር ክልል ደቡባዊ ዞን በአምስት ወረዳዎች የአዋሽ ወንዝ ባደረሰዉ የጎርፍ አደጋ ከ130ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸዉን ክልሉ አስታውቋል፡፡የአዋሽ ወንዝ ሊያስከትለዉ የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል የክልሉ መንግስት ከፌደራል መንግስት እና አዋሽ ተፋሰስ ባለስልጣን ጋር ሰፊ ስራዎች ቢሰሩም የዘንድሮዉ ክረምት ዝናብ ከፍተኛ በመሆኑ ከክልሉ አቅም በላይ ሆኗል ተብሏል፡፡አሁን ላይ በውሃ የተከበቡ ወገኖችን ህይወት ለመታደግ በሁለት ሄሊኮፕተሮች በመታገዝ ተጎጂዎችን የማውጣት ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡በአፋር ክልል ደቡባዊ ዞን በደረሰ የጎርፍ አደጋ የተለያዩ የአገልግሎት ተቋማት እና መሰረተ ልማቶች መውደማቸውን እና በሺዎች ሄክታር የሚቆጠር ማሳ ከጥቅም ውጪ ሆኗል ተብሏል፡፡ተፈናቃዮችም መንግስት አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 950 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፣ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል፣ 164 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል። በኢትዮጵያ እስከዛሬዋ ቀን ድረስ የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ ከ1 ሚሊዮን አልፏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኦሳማ ቢን ላድን የእህት ልጅ የሆነችው ኑር ቢን ላዲን የመስከረም 11 አይነት ጥቃት ዳግም እንዳይከሰት መከላከል የሚችለው ትራምፕ ብቻ ነው ማለቷ እያነጋገረ ይገኛል።የ33 አመቷ ኑር ራሷ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ እንደሆነች የተናገረች ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ካልተመረጠ ከሳምንት በኋላ ከተከሰተ 19 አመት የሚሞላውና በአጎቷ ጠንሳሽነት የተፈፀመው የመስከረም 11 ጥቃት አይነት ሊደገም እንደሚችል ለኒውዮርክ ፖስት ግምቷን ተናግራለች።ኑር አሁን ላይ ስዊዘርላንድ ውስጥ ነው የምትኖረው።

@YeneTube @FikerAssefa