YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
መሠረታዊ የምግብ ሸቀጣሸቀጦች ከቀረጥ ነጻ ሆነው ወደ አገር ውስጥ እዲገቡ ተፈቀደ!

በኪቪድ 19 ወረርሽን ምክንያት ህብረተሰቡን ተጽእኖ እንዳይፈጥርበት ሲባል ምግብ፣ ስኳር፣ ዳቦ ፣ሩዝ እና የሕጻናት ወተት ከቀረጥ ነጻ ሆነው እንዲገቡ መፈቀዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ።በሚንስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆኑት ወንድሙ ፍላቴ እንደገለጹት፤ 480 ብር ይሸጥ የነበረው ባለ አምስት ሊትር የሰሊጥ ዘይት በአሁን ወቅት ከ280 እስከ 320 ብር እየተሸጡ እንደሆነም ከሚንስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
ፕሮፌሰር ደበላ ሁንዴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ፕሮፌሰር ደበላ ሁንዴ በጅማ በብዝኃ ሕይወት ጥበቃ እና አስተዳደር መስክ በርካታ የጥናት እና የምርምር ስራዎችን በመስራት ይታወቁ ነበር። ፕሮፌሰር ሁንዴ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት፣ በተመራማሪነት እንዲሁም በኮሌጅ አመራርነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ፕሮፌሰሩ ሰባት የከፍተኛ ትምህርት የመማርያ እና በዓለም አቀፍ መድረኮች የቀረቡ የምርምር ስራዎችን ሰርተዋል። በተጨማሪም ከ50 በላይ ጥናታዊ ጽሁፎችን በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ መድረኮች አቅርበው ዕውቅና እንደ,ተሰጣቸው እና ለህትመትም ለህትመት መብቃቱን የቀረበው የሕይወት ማህደራቸው ያስረዳል።ፕሮፌሰሩ ህይወታቸው እስካለፈበት ድረስ በነበረ ያለፈውን አንድ አመት በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ማዕከል ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ፕሮፌሰር ደበላ ሁንዴ ፈይሳ ባደረባቸው ህመም ሆስፒታል ገብተው ህክምናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ቢሆንም ማገገም ባለመቻላቸው ትናንት ምሽት በተወለዱ በ59 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ፕሮፌሰር ደበላ ሁንዴ ባለትዳር ነበሩ።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ የሚታየውን የመሬት ወረራ ለማስቆም እየተሰራ ስላለው ስራ ከETV ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ ወደ ስልጣን እንደመጡ ቀድሞ ያደረጉት ለመሬት አስተዳደር አሁን ያለው የመሬት ምዝበራን በአግባቡ መቆጣጠር እስኪቻል ድረስ የይዞታ ማረጋገጫ እንዳይሰጥና የስም ማዘዋወር እንዳይከናወን የሚያግድ ደብዳቤ መፃፋቸውንም ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ከነሐሴ 21 እስከ 28/2012 ዓ.ም ባሉት ቀናት በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።የተያዙት ዕቃዎች የህዝብ ጤንነት እና ሰላም አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ ህጋዊ የንግድ ውድድርን የሚያዛቡ የጦር መሳሪያዎች፣ መድኃኒቶች፣ አደንዛዥ እፆች፣ ኤሌክትሮኒክሶች፣ የተሽከርካሪ ጎማ እና ልዩ ልዩ ምርቶች ናቸው።የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በፍተሻ፣ ጫካ እና ቤት ውስጥ ተከማችተው በጥቆማ ተደርሶባቸው፣ በከባድ ጭነት ተሽከርካሪ ባለ 40 ጫማ ባዶ ኮንቴነር ውስጥ ተደራቢ ላሜራ በውስጥ በኩል በማዘጋጀት ባዶ ኮንቴይነር በማስመሰል ለማለፍ ሲሞከር ነው።

ከተጠቀሰው ጠቅላላ ግምታዊ ዋጋ ውስጥ 12 ሚሊዮን ብር የሚገመተው በህገ-ወጥ መንገድ የጉምሩክ ክልልን በመግባታቸው በጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት የተያዙ የተለያየ ሞዴል ያላቸው አምስት ተሽከርካሪዎች ናቸው።ከብር 5 ሚሊዮን በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ሲጋራ እና ሺሻ የነዳኝ መኪና ታንከር ውስጥ በመደበቅ ለማሳለፍ ሲሞከር በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በቁጥጥር ስር መዋሉ የሚታወስ ነው።የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት በዝውውሩ እጃቸው ሊኖርበት ይችላል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
በራሽያ የተዘጋጀው ክትባት ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን አስገኝቷል ተባለ!

በራሽያ የተዘጋጀው ‘ስፑትኒክ-ቪ’ የኮሮና ክትባት ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እንደተገኙበት ‘ላንሴት’ በተሰኘው ዓለም አቀፍ የህክምና መጽሄት ላይ የወጣ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡የክትባቱን የመጀመሪያና የሁለተኛ ዙር የክሊኒካል ፍተሻ ውጤቶች የገመገመው ጥናቱ ክትባቱን ከወሰዱ 76 በጎ ፈቃደኞች መካከል የአብዛኞቹ ሰውነት ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችል ጸረ እንግዳ አካል (አንቲቦዲ) ለማዘጋጀት መቻሉን ጠቅሷል፡፡ጸረ እንግዳ አካሉ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ሰውነት ውስጥ የሚገኘው ጸረ እንግዳ አካል የሚሰጠውን ምላሽ ያህል ለቫይረሱ ምላሽ መስጠት እንደሚችልም ጥናቱ አመልክቷል፡፡ሆኖም የክትባቱ ውጤታማነት በ3ኛ ዙር ክሊኒካል የፍተሻ ሂደቶች የሚረጋገጥ ነው የሚሆነው፡፡የዓለም ጤና ድርጅት ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ ክትባቶች እስከቀጣዩ የፈረንጆች አመት አጋማሽ ድረስ በስፋት ይገኛሉ ተብሎ እንደማይታሰብ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

[CNN & Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የአቶ ልደቱ አያሌው የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ!

በምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የአቶ ልደቱ አያሌውን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።ፍርድ ቤቱ ለአቃቤ ህግ ክስ የመመስረቻ የ15 ቀን ጊዜ የፈቀደ ሲሆን ክስ እስከሚመሰረት ድረስም በፖሊስ ጣቢያ በእስር እንዲቆዩ ማዘዙን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በእነ አቶ ጃዋር መሃመድ ላይ ክስ ለመመስረት 15 ቀን ይሰጠኝ ሲል ጠየቀ፡፡

ጠቅላይ አቃቤ ህግ ያቀረባቸውን የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን አጠናቆ ይበቃኛል በማለቱ አቶ ጃዋርን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ እስክመሰርትባቸው የክስ መመስረቻ 15 ቀናት ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ባለፈው 24 ሰዓት ለ4639 ሰዎች በተደረገ ምርመራ 289 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል በተጨማሪ 114 ሰዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ተገኘ።

ባለፉት 24 ሰዓታት ለ6 ሺህ 224 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ በ114 ሰዎች ላይ የኮሮናቫይረስ መገኘቱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል። አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ቁጥርም 2 ሺህ 707 መድረሱ ተገልጿል።

በዕለታዊ ሪፖርቱ 38 ሰዎች ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ወደ 1 ሺህ 500 ከፍ ብሏል። በዕለቱ 14 ታካሚዎች በፅኑ ሕሙማን እንደሚገኙና ሕይወቱ ያለፈ ሰው እንደሌለም ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ለተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ሹመቶችን ሰጠ።

በዚህም መሰረት፦
1. አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ- በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊና የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ

2. አቶ ማሄ ቦዳ- የትምህርት ቢሮ ሃላፊ
3. አቶ ተሾመ ታከለ- የኢንዱስትሪና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሃላፊ

4. አቶ አክሊሉ አዱኛ- የውሃና መስኖ ልማት ቢሮ ሃላፊ

5. አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል- የዴሞክራሲ ስርዐት ግንባታ ማሰተባበሪያ ማእከል ምክትል አስተባባሪ

6. አቶ ይሁን አሰፋ- በዴሞክራሲ ስርዐት ግንባታ ማሰተባበሪያ ማእከል የህዝብ ግንኙነትና ማህበራዊ ሚዳያ ዘርፍ ሃላፊ

7. አቶ ንጉሴ አስረስ- የደቡብ አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

[የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1303 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 23,712 የላብራቶሪ ምርመራ 1303 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ24 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 880 አድርሶታል። በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 329 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው የገገሙ ሰዎችን ቁጥር 20,612 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 56,516 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ ኮንግረስ 6 አባላት አገራቸው ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ዕርዳታ ከመከልከል እንድትታቀብ ጠየቁ።

ለውጭ ጉዳይ ምኒስትር ፖምፔዎና የግምዣ ቤት ኃላፊው ስቴፈን ምኑችን በጻፉት ደብዳቤ ውጥረቱን ለማርገብ አሜሪካ ገለልተኛ ልትሆን ይገባል ብለዋል።ዕርዳታ ክልከላው "እምነት ከሚጣልባት ወዳጃችን ያለንን ግንኙነት ከማሻከር በተጨማሪ ስሱ በሆነው የኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ የድርድር ሒደት ያለንን ሐቀኛ የአደራዳሪነት አቋም ያሳጣል" ሲሉ የፖምፔዎ መሥሪያ ቤት የደረሰበትን አቋም ነቅፈዋል።የትራምፕ አስተዳደር ውሳኔ "የአሜሪካን ገለልተኛ ታዛቢነት በመካድ ለአንድ ወገን ያደላ፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሸረሸረ እና የአፍሪካ ኅብረትን ጥረት የቀለበሰ" ሲሉ ያጣጣሉት የኮንግረስ አባላት በቀጠናው ካላት ጥቅም እንደሚቃረንም ጠቁመዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ፤ ነሐሴ 30 በጠራው ስብሰባ ላይ በራያ፣ ወልቃይትና ወጂራት አካባቢዎች ይደርሳል የሚሉትን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንዲወያይና የመፍትሔ አቅጣጫ እንዲያስቀምጥ ትናንት ምክር ቤቱ አጠገብ ሰልፍ የወጡ ጠይቀዋል። የወጣው ሰው በኮቪድ-19 ምክንያት የተወሰነ እንደነበረም ተገልጿል።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የተጠየቁት የትግራይ ክልል የኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊያ ካሳ የወልቃይትና የራያ ህዝብ የራሳቸውን እድል በራሳቸው እንዲወስኑ በትግላቸው ያረጋገጡት የትግራይ ምርጫ ለመረበሽ በጣም ጥቂት በብር የተገዙ ሰዎች ያካሄዱት በማለት አጣጥለውታል።ወይዘሮ ሊያ "በክልሉ የሰብአዊ መብት ጥሰት አለ የተባለው ከሓቅ የራቀና ለህዝብ ንቀት ያላቸው እኛ እናውቅላሃለን በማለት ረብሻ ለመፍጠር በማሴር ነው እንዲህ የሚሉት" ብለዋል።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
ሱዳን በጎርፍ ምክንያት የሶስት ወር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አዋጀች!

የሰዱን የጸጥታና የመከላከያ ምክርቤት እስካሁን ለ99 ሰዎች ሞት ምክንያት በሆነው ጎርፍ ምክንያት ለሶስት ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጇን አስታወቀች፡፡የሱዳን ሰራተኛና ማህበራዊ ልማት ሚኒስትር እንዳሉት ከሞት በተጨማሪ ጎርፉ በ46 ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱንና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎችን መጉዳቱናከ100ሺ በላይ ቤቶችን ማውደሙን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡በሱዳን በዚህ አመት የተመዘገበው የዝናብ መጠን በፈረንጆቹ 1946ና 1988 ተመዝግቦ የነበረውን ክበረ ወሰን መስበሩን ሚኒስትር ሌና ኢል ሸክ ተናግረዋል፡፡ምክር ቤቱ በፈረንጆቹ 2020 ጎርፉ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ ኮሚቴ አቋቁሟል፡፡

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ ባስከተለው ጎርፍ በፈንታሌ ወረዳ 25 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ!

የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ ባስከተለው ጎርፍ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በፈንታሌ ወረዳና መተሀራ ከተማ ከ25 ሺህ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቀሉ።የኢዜአ ሪፖርተር ተዘዋውሮ እንደተመለከተው በመተሀራ ከተማ ብቻ ተፈናቃዮች በሰባት መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ይገኛሉ።በአካባቢው የሀሮ አዲ ቁጥር አንድ ትምህርት ቤትም በርከት ያሉ ተፈናቃዮች መኖራቸውንም ተመልክቷል።ተፈናቃዬዮች ጎርፉ ያደረሰው የሃብትና ንብረት ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ መንግስት አስቸኳይ ድጋፍ ያድርግልን ብለዋል።

ከተፈናቃዮቹ መካከል የሰባት ልጆች እናት ወይዘሮ ጽጌ ቱፋ አንዷ ናቸው።ጎርፉ ቤት ንብረታቸውን በማውደሙ የሚቀመስ ነገር በሌለበት፣ መብራትና ውሃም ጠፍቶ ችግር ላይ እንገኛለን ብለዋል።እስከ ትናንት ጥዋት ድረስ ከመንግስትም ሆነ ከለጋሾች ምንም አይነት ድጋፍ አለማግኘታቸውን ገልጸው አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።በትምህርት ቤቱ ውስጥ ተጠልለው የነበሩ አርሶ አደር መልካሙ አበራና ወጣት ዝናሽ መገርሳም በህይወት ዘመናቸው አይተውት የማያውቁት የጎርፍ አደጋ መድረሱን ይናገራሉ።

በመጋዘኖች የተከማቸ እህል በጎርፍ መወሰዱን ገልፀው አደጋው አቅም ደካሞችን ለከፋ ችግር ዳርጓል ይላሉ።የመተሀራ ከተማ ከንቲባ አቶ ታደለ ደሪርሳ ከተማዋ ሁለት ቀበሌና 14 ቀጠና ያላት ሲሆን አንዱ ቀበሌ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ወድሟል ብለዋል።በከተማዋ እስካሁን ከ13 ሺህ በላይ ቤተሰቦች ተፈናቅለው ከፌዴራል፣ ከክልልና ከህዝቡ የተሰበሰበ ድጋፍ ዛሬ መድረስ ጀምሯል ብለዋል።ለመጠለያ የሚሆን ሸራ፣ ለአስቸኳይ ምግብ የሚሆን ሩዝ ቴምር እንዲሁም መደሃኒት በማቅረብ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

እስካሁን የከተማዋ ነዋሪዎች በርካታ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀው በቀጣይ ሌሎች አካላትም እንዲረባረቡ ጠይቀዋል።

የምስራቅ ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ኢብሳ ሳዲቅ በዞኑ ስድስት ወረዳዎች እስካሁን ከ30 ሺህ በላይ ሰዎች በጎረፉ ሳቢያ መፈናቀላቸውን ገልጸዋል።በዞኑ በሉሜ፣ በዱግዳ ፣በቦሰት፣ በሊበን፣ በአዳማና ፈንታሌ ወረዳዎች ጎርፉ ከባድ ጉዳት አድርሷል ብለዋል።የወንዙ ሙላት የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ብዙ ጥረት ቢደረግም ባለመሳካቱ ተፈናቃዮች በትምህርት ቤቶችና ሌሎች ቦታዎች ተጠልለው ይገኛሉም ነው ያሉት።

የዞኑ ምክትል ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አበበ ማሞ በበኩላችው ተፈናቃዮች ለጤና ችግር እንዳይጋለጡ እየተሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።አሁን ላይ መድሃኒት መቅረብ መጀመሩንና በሶስት የተለያዩ አካባቢዎች የህክምና አገልገሎት ሲሆን 10 ሺህ አጎበር እና 80 ሺህ ማስክም ዝግጁ ሆኗል ነው ያሉት።በቀጣይ የመንግስት ድጋፍ እንዳለ ሆኖ ሌሎች አካላትም ለድጋፍ እጃቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ ቀርቧል።

[ኢዜአ]
@YeneTube @FikerAssefa
👎1
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን የምርጫ እንቅስቃሴ በተመለከተ የምክር ቤቱ የህገ መንግስት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ በዝግ እየመከረ ነው።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የፖለቲካ ፓርቲዎች በብሄራዊ መግባባት ዙሪያ እየተወያዩ ነው፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መሪነት፤ ከኢትዮጵያ የምስረታ ዘመን እስከ ስርአቶች ዝርጋታ ታሪካዊ - ጥናታዊ የመነሻ ሃሳብ ቀርቦ ወይይት መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡ዛሬም ለሁለተኛ ጊዜ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን /ኢ.ሲ.ኤ/ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

Via Prosperity Party
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን የምርጫ እንቅስቃሴ በተመለከተ የምክር ቤቱ የህገ መንግስት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ በዝግ እየመከረ ነው። [FBC] @YeneTube @FikerAssefa
በምክር ቤቱ የሕገ መንግሥትና የማንነት ጉዳዮች ቃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ወርቁ አዳሙ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ምክር ቤቱ ሕገ መንግሥቱን የመተርጎም ስልጣኑን በመጠቀም በሰጠው ውሳኔ መሠረት እንዲካሄድ ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃረን ምርጫ ለማድረግ የጀመረውን ጉዞ በተመለከተ ሦስት የውሳኔ ሐሳቦች ለምክር ቤቱ አቅርበው ውይይት እየተደረገበት ነው።

የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ወደ ጎን በመተው የትግራይ ክልል መንግሥት ያወጣው የምርጫ አዋጅ ቁጥር 351/2012 እና አዋጁን መሠረት አድርጎ ያተቋቋመውን የምርጫ ኮሚሽን ያሳለፋቸው ውሳኔዎችና የፈጸማቸው ተግባራት የሕገ መንግሥት ትርጉም ውሳኔ እንዲሰጥበት በሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

[አብመድ]
@YeneTube @FikerAssefa
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መረሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 1043 ተማሪዎች አስመረቀ::

በዛሬውም ቀን በመደበኛና በተከታተይ መረሃ ግብሮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ድግሪ ያሰለጠናቸውን 283 እንዲሁም በሰርተፊኬት 760 በጥቅሉ 1043 ተማሪዎችን አስመርቋል::

[Bule Hora University]
@YeneTube @FikerAssefa