የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡
በዚሁ መሰረት፦
1. ወይዘሮ አልፍያ ዩሱፍ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ
2. አቶ ኤፍሬም ግዛው በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ ጽህፈት ቤት ኃላፊ
3. አቶ መለሰ አለሙ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
[Addis Ababa City PS]
@YeneTube @FikerAssefa

ለ20/80 እና 40/60 ተመዝጋቢ ሆነው ቤት ያልደረሳቸው ፍላጎት እና አቅም ያላቸው ነዋሪዎች በማህበር ተደራጅተው የጋራ ቤት ለመገንባት እንዲችሉ የአማራጭ የውሳኔ ሀሳብ ተላለፈ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ ለ20/80 እና 40/60 ተመዝጋቢ ሆነው ቤት ላልደረሳቸው ፍላጎት እና አቅም ያላቸው ነዋሪዎች በማህበር ተደራጅተው የጋራ ቤት ለመገንባት እንዲችሉ አማራጭ የመፍትሄ ሀሳብ አስተላልፏል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው ዕለት 30ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል።ጉባኤው በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ የተወያየ ሲሆን÷ በከተማዋ የሚታየውን የመኖሪያ ቤትና የትራንስፖርት ችግር ከመፍታት አንፃር አፅንኦት ሠጥቶ ተወያይቷል።ችግሮቹን ለመፍታትም ካቢኔው በተለያዩ አማራጮች ሃሳቦች ዙሪያ ሠፊ ውይይት አድርጎ ውሳኔውን አስተላልፏል።
በዚሁ መሰረት የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ ለ20/80 እና 40/60 ተመዝጋቢ ሆነው ቤት ያልደረሳቸው ፍላጎት እና አቅም ያላቸው ነዋሪዎች በማህበር ተደራጅተው የጋራ ቤት ለመገንባት እንዲችሉ ከተማ አስተዳደሩ የመሬት አቅርቦት በማድረግ እራሳቸው እንዲገነቡ ለማድረግ አማራጭ የመፍትሄ ውሳኔ አስተላልፏል።ከዚያም ባለፈ በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ 400 አውቶቢሶች ግዢ በልዩ ሁኔታ እንዲከናወን እና በብልሽት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ 125 አውቶቡሶች በአስቸኳይ አስፋላጊው ጥገና ተደርጎላቸው ከአዲስ አመት የመጀመሪያ ቀናት ጀምሮ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ውሳኔ ተላልፏል።የማህበር ቤት ልማት መመሪያ እና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ቢሮ በቀጣይ ዝርዝር መረጃ የሚሰጥ መሆኑን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
[FBC]

በኮንሶና ጉራጌ ዞኖች ጸጥታ መደፍረስ የተጠረጠሩ 34 አመራሮችና ባለሙያዎች ተያዙ!
በደቡብ ክልል በኮንሶና በጉራጌ ዞኖች በተፈጠረ የጸጥታ መደፍረስ ባስከተለው የዜጎች መፈናቀል፤ሞትና በንብረት ውድመት የተጠረጠሩ 34 አመራሮችና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።የፓርቲው ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ የለውጥ ሂደቱን ተከትሎ በከልሉ በርካታ አከባቢዎች በተፈጠረ የጸጥታ መደፍረስ ምክንያት አስቸጋሪ ጊዜያት መታለፋቸውን ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ የጸጥታ ሃይሎች ከህዝቡ ጋር በመሆን ባደረጉት ርብርብ ከጊዜ ወደ ጊዜ በክልሉ አንጻራዊ ሠላም መስፈኑንና አሁን ላይ በልማት ተግባር ላይ እንደሚገኝ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
“ህዝቦች ሁሌም በወሰን አከባቢ በጋራ ይኖራሉ” ያሉት አቶ ጥላሁን “በተለይ በኮንሶና በአሌ ማህበረሰብ ለረጅም ዘመናት በጋራ የሚጠቀሙት ከሰላ የሚባል ደን ምክንያት ተደርጎ የተፈጠረው ችግር ሰዉ እርስ በርስ እንዲያልቅ ታቅዶ የተሠራ ነው” ብለዋል።
የችግሩ መንስኤ የሆኑና የመሩ 11 አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለው በህግ እንዲጠየቁ ምርመራ መጀመሩን አቶ ጥላሁን ተናግረዋል።
ችግሩ የከፋ እንዲሆን ያገዙ አካላትን አጣርቶ በቁጥጥር ስር ለማዋልም እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
“ህዝቦችን በማጣላት የፖለቲካ ትርፍ የሚያገኙ የብሄር ነጋዴዎችን ለማሳፈርና ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት ሁለቱ ህዝቦች ችግሮችን መፍታት የሚችሉባቸው ጠንካራ ባህላዊ ዕሴቶችን በመጠቀም በድርድርና በዕርቅ ለመጨረስ ስራዎች እየተከናወኑ ነው”ብለዋል።
በደቡብ ኦሞ፤ቤንች ሼኮና ምዕራብ ኦሞ አካባቢዎች መጠነኛ የሆኑ የጸጥታ ችግሮች እንዳሉ ገልጸው የጸጥታ ሃይሉ በከፍተኛ ንቃት የእርምት ርምጃ እየወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።
በተመሳሳይም በጉራጌ ዞን መስቃንና ማረቆ ማህበረሰብ መካከል ለተፈጠረው ችግር ድርጅቱ ባካሄደው ግምገማ እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 23 አመራሮችና ባለሙያዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
[ኢዜአ]

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መመሪያ የኮሮና ቫይረስ እለታዊ ሪፓርት
ዛሬ በላብራቶሪ የተመረመሩ ብዛት :- 246
ዛሬ የተያዙ :- 17
ዛሬ ህይወታቸው ያለፈ :- 0
ዛሬ ከበሽታው ያገገሙ :- 72
________,
በአጠቃላይ የተመረመሩ :- 9558
በበሽታው የተያዙ :- 1004
በአሁን ሰዕት ህክምና ላይ ያሉ :- 555
ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ ያገገሙ :- 439
@Yenetube @Fikerassefa
ዛሬ በላብራቶሪ የተመረመሩ ብዛት :- 246
ዛሬ የተያዙ :- 17
ዛሬ ህይወታቸው ያለፈ :- 0
ዛሬ ከበሽታው ያገገሙ :- 72
________,
በአጠቃላይ የተመረመሩ :- 9558
በበሽታው የተያዙ :- 1004
በአሁን ሰዕት ህክምና ላይ ያሉ :- 555
ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ ያገገሙ :- 439
@Yenetube @Fikerassefa
የብልጽግና ፓርቲ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ በጀመረው የብልጽግና ፓርቲ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ላይ በፌዴራል መንግስት መዋቅር ውስጥ ከሚኒስትር እስከ ምክትል ዳይሬክተር ያሉ ከ420 በላይ አመራሮች ተሳታፊ ናቸው።
ለተከታታይ አምስት ቀናት በሚቆየው ስልጠናው በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት ጉዳዮች ዘርፍ ሃላፊ በዶ/ር አለሙ ስሜ የመክፈቻ ንግግር ተከፍቷል።
በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ዶ/ር አለሙ ስሜ ስልጠናው ለውጡን በማስቀጠል አገራዊ ብልፅግናን እውን ማድረግ የሚያስችል አቅም መፍጠር ያለመ ነው ብለዋል።
የኢቢሲ ዘገባ እንዳመለከተው ስልጠናው አመራሩ የጠራ አስተሳሰብ ይዞ ለጋራ አላማ በጋራ እንዲሰራ ለማድረግ ያለመ መሆኑንም ፓርቲው በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል።
Via:- FBC

ከጤና ሚኒስቴር የተሰጠ ማብራሪያ
በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ አገልግሎት ሰራተኞች እና በአንዲት ወጣት ሴት መሀል፣ ወደ አንቡላንስ ለማስገባት ጥረት ሲያደርጉ የተከሰተውን መጓተት፣ የሚያሳየውን ቪዲዮ፣ በሀዘኔታ ተመልክተነዋል፡፡ አጋጣሚ ሆኖ፣ ቪዲዮው የሚያሳየው፣ የታሪኩን፣ ትንሽ ክፍል ብቻ ነው፡፡ ሙሉ ታሪኩን ለህብረተሰባችን ለማሳወቅ እና፣ አገልግሎት በሚሰጥበት ሰአት፣ ሀይል መጠቀምን የማንቀበል መሆናችንን ለማስገንዘብ፣ የሚከተለውን ማብራሪያ መስጠት፣ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
አጋጣሚው የተከሰተው፣ ሰኔ 11/2012 ሲሆን፣ ወጣቷ ኢትዮጵያዊ፣ ከምትሰራበት የመካከለኛው ምስራቅ አገር፣ ወደ አገሯ በተመለሰች፣ በ2ኛ ቀኗ ነበር፡፡ በተለመደው የአቀባበል ደንብ መሰረት፣ ወጣቷም ሆነች፣ ከእርሷ ጋር የነበሩ ሌሎች ተመላሾች፣ ወደ አንድ ለይቶ ማቆያ ሆቴል እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ ወጣቷ ሴት፣ በጉዞ ወቅትም ሆነ ሆቴል በነበሩበት ጊዜ፣ ከሌሎች ጋር ለመግባባት የማትሞክር፣ አልፎ አልፎም ትረብሽ እንደነበረ፣ አብረዋት የነበሩ ተናግረዋል፡፡ እኛም፣ ለይቶ ማቆያው ውስጥ እያለች ባደረግነው ክትትል፣ ከፍተኛ የአእምሮ ህመም ሳይኖርባት እንደማይቀር እና በተለየ ሀኪም ቤት ውስጥ ህክምና ማግኘት እንደሚያስፈልጋት ተገንዝበናል፡፡
በቪዲዮው ላይ የሚታየው መጓተት የተፈጠረውም፣ ወጣቷን፣ ከለይቶ ማቆያው ሆቴል፣ የአእምሮ ህክምና ወደሚሰጥበት ተቋም በምትወሰድበት ወቅት ነው፡፡ በዚያ ሰአት፣ የወጣቷ፣ የኮቪድ ምርመራ ውጤት አይታወቅም ነበር፡፡ ወጣቷ፣ ወደ ሰፈረ ሰላም የህክምና ተቋም ተወስዳ፣ በአእምሮ ሀኪሞቻችን አማካይነት፣ለአምስት ቀናት ያህል ተገቢውን ህክምና ከማግኘቷም ባሻገር፣ ጥሩ የሚባል የጤና መሻሻልም አሳይታ ነበር፡፡ የኮሮና ቫይረስ እንደሌለባት በምርመራ ከተረጋገጠ በኋላም፣ በሰላም ወደ ቤቷ ተሸኝታ፣ ከቤተሰቦቿ ጋር ተቀላቅላለች፡፡ የጤና ሁኔታዋንም፣ በመከታተል ላይ ትገኛለች፡፡
በዚህ አጋጣሚ፣ የጤና ሚኒስቴር፣ ልባዊ እና ትህትና የተሞላበት አገልግሎት ለሁሉም የህብረተሰባችን አባላት፣ ለመስጠት ምንጌዜም እንደሚተጋና የሚፈጠሩ ክፍተቶችን በየደረጃው ለማሻሻል እንደምንሰራ ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡ የአእምሮ ህመም፣ በየትኛውም ሰው እና ጊዜ ሊደርስ የሚችል አጋጣሚ ሲሆን፣ መፍትሄውም፣ የጤና ባለሙያዎችን፣ የግለሰቦችን፣ የቤተሰቦችን፣ እና የማህበረሰቡን፣ ተባብሮ እና ተቀናጅቶ መስራት፣ እንዲሁም፣ ተገቢውን እንክብካቤ እና ህክምና በሰአቱ መስጠትን ግድ ይላል፡፡
Via:- Minister of Health

የኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ጠበቃ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ደንበኛዬ እየተጉላላብኝ ነው አለ፡፡
ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ ከቤታቸው የተያዙት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ያለ ፍርድ እስር ቤት እንደሚገኙ ነው ጠበቃቸው የተናገሩት፡፡የኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ጠበቃ የሆኑት አቶ አዲሱ ጌታነህ ደንበኛዬ ከተያዘ ሁለት ወር እንደሞላው ተናግረው በነዚህ ሁሉ ጊዜያቶች ውስጥ ፖሊስ ለምርመራ ጊዜ እየወሰደ ፍርድ ቤትም ተገቢ ያለውን ጊዜ እየሰጠ እስካሁን ድረስ ቆይተናል፡፡ነገር ግን ፖሊስ ምርመራዬን ጨርሻለሁ ብሎ ለፍርድ ቤት ካስረከበ እና መዝገቡም ለአቃቢ ህግ የሰጠው ነሀሴ 13 ነው ስለዚህ የምርመራ መዝገቡ ከተዘጋ ኢንጂነር ይልቃል በዋስ መውጣት ይገባቸው ነበር ያ ግን ሊሆን አልቻለም ብለዋል፡፡
አቃቢ ህግ በእለቱ ቀርቦ ክስ ለመመስረት የ15 ቀን ቀነ ገደብ እንዲሰጠው ለፍርድ ቤት በደብዳቤ ጠይቆ ፍርድ ቤትም 10 ቀን በቂ ስለሆነ አቃቢ ህግ በዚህ ቀን ክስ እንዲመሰረት ሲል ትዛዝ ሰቶ ነበር፡፡ነገር ግን ፍርድ ቤት የሰጠው ቀን ነሀሴ 22 ነበር ለሶስት ቀናት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይኖር ደንበኛዬ እስር ቤት ተቀምጠዋል ብለዋል ጠበቃ አዲሱ ጌታነህ፡፡የፍትህ ስርአት ማሻሻያ እየተደረገ ነው እየተባለ ባለበት ወቅት እንደዚህ ያሉ የመብት ጥሰቶች የሚደረጉ ከሆነ የህግ ስርአቱን ይጎጋዋል ሲሉም ተናግዋል አቶ አዲሱ፡፡ደንበኛዬ አሁንም ቢሆን መጠርጠር የሚያስችል በቂ የሆነ ማስረጃ ያስፈልጋል ያሉት አቶ አዲሱ ከልክ በላይ ምርመራም ማድረግ አያስፈልግም ነበር ብለዋል፡፡
[Ethio FM]

የቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት የአቶ ልደቱ አያሌውን ፋይል ዝግቶ በነፃ አሰናበታቸው፡፡
የቢፍሾቱ ከተማ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት የኢዴፓ መስራችና የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት ጉዳይ ምንም የሚያስጠይቃቸው ነገር እንዳላገኘ በመግለፅ በነፃ እንዳሰናበታቸው ተሰማ፡፡
ሸገር የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር የሆኑትን አቶ አዳነ ታደሰን በስልክ አነጋግሮ አቶ ልደቱ ተጠርጥረው ለእስር የተዳረጉበት የፍርድ ቤት መዝገብ መዘጋቱን አረጋግጧል፡፡
ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ ከፖሊስ ጋር ያላቸውን ጉዳይ ጨርሰው እንዲለቀቁ ማዘዙን ሸገር ከአቶ አዳነ ሰምቷል፡፡
አቶ ልደቱ አያሌው የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በቢሾፍቱ በተፈጠረው ረብሻ አመፅ በማነሳሳትና በገንዘብ በመርዳት በሚል ጠርጥሬአቸዋለሁ ባለው የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለው በፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ሲከታተሉ መክረማቸው ይታወቃል ።
Via:- Shager FM

Audio
በአዲስ አበባ ከተማ የገዳ ሥርዓት እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ሊሰጥ ነው የሚለው ወሬ ከተሰማ በኋላ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች እየተሰሙ ነው፡፡
የከተማዋ ትምህርት ቢሮ የገዳን ሥርዓት እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ለማስተማር የመረጠበት መስፈርት ምንድነው?
ኢትዮጵያ የተለያዩ ባህላዊ ሥርዓቶች ያሉባት አገር፣ አዲስ አበባም የሁሉም ብሔሮች መናኸሪያ ሆና ሳለ የገዳ ሥርዓት ብቻ ተለይቶ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት በከተማው እንዲሰጥ እንዴት ተመረጠ?
ለምንስ ለኦሮሚያ ቋንቋ ተናጋሪ ተማሪዎች ብቻ ለመስጠት ታሰበ? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች እየተሰሙ ነው፡፡
ሸገር እየቀረቡ ያሉ ጥያቄዎችን ለከተማዋ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ አቅርቦላቸዋል፡፡
ሀላፊው እንደተናገሩት የገዳ ሥርዓት ስርዓተ ትምህርቱ ተጠናቆ የመፅሐፍ ዝግጅት ላይ ተደርሷል፡፡
የመፅሐፍ ዝግጀቱም በ2 እና 3 ሳምንታት ያልቃል በአዲሱ የትምህርት ዘመን የገዳ ሥርዓት እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት መሰጠት ይጀምራል ብለዋል፡፡
ትምህርቱን የሚሰጠው በአዲስ አበባ የኦሮምኛ ቋንቋ ትምህርት በሚሰጥባቸው 7 ትምህርት ቤቶች ናቸው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ሙሉ ወሬውን ከላይ የተያያዘውን የድምፅ ዘገባ ያዳምጡ!
[ሸገር ኤፍ ኤም]

ከሊባኖስ 165 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ!
በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 165 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡ኢትዮጵያውያኑ ወደ አገራቸው የተመለሱት በግለሰቦች፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና ቡድኖች በተደረገላቸው የትራንስፖርት ወጪ ነው፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተመላሾቹ የአውሮፕላን ቲኬት ቅናሽ በማድረጉም ተገልጿል፡፡በቀጣይም በራሳቸው ሙሉ ወጪ 243 ኢትዮጵውያን ወደ አገራቸው ይመለሳሉ ተብሏል፡፡ወደ አገራቸው ለመመለስ ከ650 በላይ ዜጎች መመዝገባቸውም ተመልክቷል ፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮስኮ) ለበርካታ ወራት በጅቢቲ አስቀምጦት የነበረውን አርማታ ብረት ማጓጓዝ መጀመሩን አስታወቀ!
ኮርፖሬሽኑ ለ6 ወራት ግድም ወደ አገር ውስጥ ማጓጓዝ ያልቻለውን የብረት ክምችት ማጓጓዝ የጀመረው ለቀረጥ እና ሌሎች ክፍያዎች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ500 ሚሊየን ብር ብድር ስለተለቀቀለት መሆኑን አስታውቋል፡፡መንግስታዊ የግንባታ ተቋም የሆነው ኢኮስኮ የዛሬ አመት ግድም ባወጣው ጨረታ የ 15ሺ 400 ሜትሪክ ቶን የተለያዩ መጠን ያላቸውን ብረቶች ከውጭ አቅራቢ መግዛቱ ይታወቃል፡፡ሆኖም ምርቱን ወደ አገር ውስጥ ከማስገባቱ በፊት ሊከፈሉ የሚገባቸውን እንደ ቀረጥ እና የማጓጓዣ ወጪዎች በግዜው መፈፀም ባለመቻሉ ምርቱ ለወራት በወደብ አካባቢ እንዲቆይ ግድ መሆኑ ታውቋል፡፡በዚህም ለማይገባ የቆይታ ክፍያ መዳረጉን ጉዳዩን የሚያውቁት ተናግረዋል፡፡ብረቱ በ8.5 ሚሊየን ዶላር መገዛቱን የተናገሩት የኢኮስኮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጠንፉ ሙጬ ምርቱን ለማጓጓዝ በቅድሚያ ለሚከፈሉ ወጪዎች የሚሆን ገንዘብ ከንግድ ባንክ በመለቀቁ ምርቱ በአንድ ወር ግዜ ውስጥ ተጓጉዞ ወደ አገር ውስጥ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
[Capital]

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ በአዲስ አበባ እየተደረገ ነው ያለውን የመሬት ወረራና ህገ-ወጥ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላ በተመለከተ ሊሰጠው የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ለሁለተኛ ጊዜ ተከለከለ፡፡
የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ እንዳሉት ጋዜጣዊ መግለጫው የተከለከለው መግለጫ የሚሰጥበት ቦታ የሆነው ራስ ሆቴል ከሰላም ሚኒስቴር የተፃፈ ደብዳቤ ስጡኝ በማለቱ ፤ የሰላም ሚኒስትር ደግሞ ደብዳቤ ለመፃፍ ባለመፍቀዱ ነው ሲሉ ነግረውናል፡፡
ፓርቲው ለሁለተኛ ጊዜ መግለጫ እንዳይሰጥ ስለተከለከለ፣መግለጫውን በፅ/ቤቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደሚሰጥ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ነግረውናል፡፡
ሸገር ይህንኑ ጉዳይ ለማጣራት ወደ ሰላም ሚኒስትር ቢሮ ደውዬ ተነገረኝ እንዳለው፣ የሚኒስትሯ ፅህፈት ቤት ፈቃዱን የሚሰጠው አካል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚኒስትሮች ኮሚቴ መሆኑን ጠቅሶ፣ ለኢዜማ ደብዳቤው ያልተፃፈለት ፣ሚኒስትሯ ስለሌሉ ነው ብሏል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ አክሎም በደብዳቤው ላይ የሚፈርሙት ሚኒስትሯ ስለሌሉ ነው እንጂ፣ኢዜማ ፈቃድ አልተከለከለም ብለዋል፡፡
[Sheger FM]

የሱዳን መንግስትና አማጺው ቡድን የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ!
የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት በዳርፉርና በሌሎች የሀገሪቱ ግዛቶች ከሚንቀሳቀሰው የሱዳን አብዮታዊ ግንባር ጋር በጁባ የሰላም ስምምነት መፈረሙን አስታወቋል፡፡
[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት በዳርፉርና በሌሎች የሀገሪቱ ግዛቶች ከሚንቀሳቀሰው የሱዳን አብዮታዊ ግንባር ጋር በጁባ የሰላም ስምምነት መፈረሙን አስታወቋል፡፡
[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በጀርመን የሊባኖስ አምባሳደር ሙስጠፋ አዲብ የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆኑ ነው!
ለሊባኖስ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሾም እየተደረገ ባለው ጥቆማ ሙስጠፋ አዲብ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን ለመሆን ከጫፍ መድረሳቸው ተገለጿል፡፡
[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ለሊባኖስ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሾም እየተደረገ ባለው ጥቆማ ሙስጠፋ አዲብ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን ለመሆን ከጫፍ መድረሳቸው ተገለጿል፡፡
[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ችሎቱ አቶ ልደቱን የሚያስከስስ ማስረጃ አለማገኘቱን ገልጾ ጉዳዩን ቢቋጨውም፣ አቶ ልደቱ እስካሁን [እስከ ዛሬ ቀትር ድረስ] እንዳልተለቀቁ ተናግረው፤ ስለዚህም አባላቸው ከእስር እንዲወጡ ነገ ሁለት ማመልከቻዎችን ሊያስገቡ እንዳሰቡ የኢዴፓ ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ተናግረዋል። "አንደኛው የዋስ መብት የሚጠየቅበት ማመልከቻ ነው። ሌላኛው ደግሞ አካልን ነጻ የማውጣት ክስም እንመሰርታለን” ብለዋል።
[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ_አበባ_ከተማ_የመሬት_ወረራ_እና_የጋራ_መኖሪያ_ቤቶች_ኢፍትሃዊ_ዕደላን_አስመልክቶ_የተደረገ_ጥናት.pdf
278.1 KB
👆👆👆
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ "መሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላ" ላይ ያደረገው ጥናት ውጤት።

YeneTube
በአዲስ_አበባ_ከተማ_የመሬት_ወረራ_እና_የጋራ_መኖሪያ_ቤቶች_ኢፍትሃዊ_ዕደላን_አስመልክቶ_የተደረገ_ጥናት.pdf
የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በተመለከተ በከተማዋ ያለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ ታስቦ የተጀመረው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ከታሰበለት ጊዜ በጣም ዘግይቶ ችግሩን መቀነስ አለመቻሉ ሳያንስ ቤቶቹን ለመረከብ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው ከ15 ዓመታት በላይ የቆጠቡ የከተማዋ ነዋሪዎች ቤት ሳያገኙ ግንባታቸው ያለቁ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላልተመዘገቡ እና ቁጠባ ላልፈፀሙ ሰዎች ተላልፈው እየተሰጡ መሆኑን በጥናት ደርሼበታለሁ ብሏል ኢዜማ።
በሥልጣን ላይ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለማስተላለፍ የወጣውን መመሪያ በመቀየር በግለሰብ ትዕዛዝ ቤቶች በሕገ-ወጥ መንገድ ከታለመላቸው ዓላማ ውጪ እንዲሰጡ ምቹ ሁኔታን መፍጠሩ በጥናቱ ተረጋግጧልም ብሏል።
እነዚህ ሕገ-ወጥ ተግባሮች ያላቸው ተፅዕኖ ዛሬን የሚሻገር፣ ለነገም የሚተርፍ እና የህብረተሰቡን ቀጣይ ሕግን የማክበር ባሕሪ በከፍተኛ ደረጃ የሚጎዳ በመሆኑ ጥፋቱ የከፋ ነው ብሏል የጥናቱ ሪፖርት፡፡በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በጥናቱ የተገኙ ውጤቶችና ድምዳሜዎችን ተመልክቶ የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብር የጠየቀው ኢዜማ፣ የመሬት ወረራውና ከሕግ አግባብ ውጪ የተካሄደው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕደላ የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ባሉ ባለስልጣናት እጅግ ሲከፋ ቀጥተኛ በሆነ የጥቅም ተጋሪነት ሲያንስ ደግሞ ኃላፊነታቸውን በትክክል ካለመወጣት በተሰጠ ሽፋን የተፈፀመ በመሆኑ፣ በዚህ ተግባር ውስጥ እጃቸው ያለበት ኃላፊዎች ላደረሱት ጉዳትና ለፈፀሙት ወንጀል በሕግ የሚጠየቁበት ሥርዓት ሊበጅ ይገባል ብሏል፡፡