YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አፋን ኦሮሞ የፌደራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን በጨፌ ኦሮሚያ የማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ወ/ሮ አለምነሽ አስፋው አስታወቁ፡፡

መንግስት አፋን ኦሮሞ አንዲስፋፋ ካከናወናቸው ስራዎች መካከል አንዱ በዚህ አመት የኦሮሚያ ት/ት ቢሮ መፅሀፍቶችን በማሳተም ለዘጠኝ ክልሎች በማበርከት ሁሉም ክልሎች ቋንቋውን እንዲያስተምሩ መደረጉን ወ/ሮ አለምነሽ ለኦቢኤን ገልፀዋል፡፡ጨፌ ኦሮሚያ አፋን ኦሮሞ ይበልጥ እንዲስፋፋ ከ1ኛ ክፍል አስከ PHD ድረስ በቋንቋው ትምህርት እንዲሰጥ ሲሰራ ቆይቷል ነው ያሉት ሊቀመንበሯ፡፡በዚህ አመት በአምቦ ዩንቨርስቲ በተደረገ ፎረም ላይ ሌሎች ክልሎች የተሳተፉ ሲሆን ቋንቋውን የፌደራል የሥራ ቋንቋ ማድረግ በሚቻልበት ሂደት ጥናታዊ ፅሁፍ ቀረቧል፡፡ጨፌው ጥናቶቹን እንደግብአት በመጠቀም እየተሰራ መሆኑን ወ/ሮ አለምነሽ ተናግረዋል፡፡በህግ መንግስቱ ላይ የተቀመጠውን የፌደራል የሥራ ቋንቋ አማርኛ ብቻ የሚለውን ለማሻሻል የሁሉም ክልሎች ተወካዮች ቢያንስ 2/3ኛው ጉዳዩን አምኖበት ሊወስን ይገባል ብለዋል፡፡

#OBN
@YeneTube @FikerAssefa1