YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአማራ ብልፅግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች መድረክ ቀጥሎ እየተካሄደ ነው!

የአማራ ብልፅግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች መድረክ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳይች ላይ በባህርዳር ከተማ እያካሄደው ያለው መድረክ እንደቀጠለ መሆኑን ፓርቲው አስታወቀ።መድረኩን በተመለከተ እንደተጠናቀቀ አጠቃላይ መረጃ የሚሰጥ መሆኑንም የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያመለክታል።ሆኖም ግን በአንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ከመድረኩ ባህሪና ነባራዊ ሁኔታ ባፈነገጠ መንገድ የተዛቡ መረጃዎች እየተዘዋወሩ መሆኑንም አስገዝንቧል።ለአብነት ያህል “በመድረኩ አመራሩ ለሁለት ተከፍሏል” የሚሉና አመራሮቹን በስም በመጥራት እገሌ ይህንን ብለዋል በሚል የተለቀቁ የሀሰት መረጃዎች ይገኙበታል ብሏል ጽህፈት ቤቱ።በመሆኑም መረጃወቹ ከእውነት የራቁ መሆኑን ያስታወቀው ጽህፈት ቤተ፥ በመድረኩ የሚደረሱ ድምዳሜወችንና የፓርቲውን አቋም የግምገማ መድረኩ እንደተጠናቀቀ እንደሚያደርስም አስታውቋል።

#APP
@YeneTube @FikerAssefa