YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ዋልድባ! በዋልድባ ገዳም መነኮሳት አባቶች ላይ ቀርቦ የነበረው ክስ አለመቋረጡ ተሰምቷል። በተለያዩ የማህባረሰብ ሚዲዎች የመነኮሳቱ ክስ ዛሬ ተቋርጧል በሚል መረጃዎች ሲሰራጩ ቢውልም ጠበቃቸው ለቪኦኤ በሰጡት ቃል የመነኮሳቱ ክስ አለመቋረጡን ገልፀዋል። እንደ ጠበቃቸው ገለፃ የክስ ሂደቱ እንደሚቋረጥ ከፍርድ ቤት አካባቢ መረጃ ደርሷቸው የነበር ቢሆንም በዛሬው እለት ከዋለው ችሎት ክሱ አለመቋረጡን ሊረዱ ችለዋል።

በተጨማሪ፦ በዛሬው እለት መነኮሳቱ ለችሎት ቀርበው በእስር ቤት ውስጥ ሃይማኖት ልብሳቸውን እንዲያወልቁ መገደዳቸውን እንዲሁም መደብደባቸውን ተናግረዋል።

#VOAamharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጠ/ሚ ፅ/ቤት እስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳይ...

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ እስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደሃገራቸው መመለስን ጉዳይ አስመልክቶ ከቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር ያደረጉት ውይይት የለም ሲሉ የጠ/ሚ ፅህፈት ቤት ምንጮች ገልፁልኝ ሲል የአሜሪካ ድምፅ ዘግቧል።

የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር በዋቢነት የጠቀሰው 'The Times Of Israel' /ዘ ታይምስ ኦፍ ኢስራኤል/ “የኢትዮጵያው መሪ ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደሃገራቸው በመመለሱ ሂደት ዕገዛ ለማድረግ ተስማምተዋል” ሲል ነው ሰሞኑን የዘገበው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ፅህፈት ቤት ምንጮች እንዳሉት ግን የስደተኞችን ወደሃገራቸው የመመለስ ጉዳይ እንዲያውም በሁለቱ መሪዎች ውይይት አልተነሳም ።

#VOAAmharic
@YeneTube @Fikerassefa
" የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ላይ እጁ የለበትም " ሲል የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ( 'ኦነግ ሸኔ ' ) መሪ ጃል መሮ ( ኩምሳ ድሪባ ) የመንግስትን ክስ አስተባበለ ።

#VOAamharic

@YeneTube @FikerAssefa1