YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሀዋሳ ኖት ? አዲሱን ጎለት ለንደን ባስ በርገርን ቢያዙን በ25 ደቂቃ ውስጥ ቤቶ ድረስ እናመጣለን።

30% የዴሊቨሪ ክፍያ ላይ ቅናሽ ተደርጓል እንዲሁም ለጤና ባለሙያዎች በነፃ እናደርሳለን።

Join @Deliveryhawassa
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሦስቱ አገራት መካከል ሲካሄድ በሰነበተው ድርድር በበርካታ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት መደረሱ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ስለድርድሩ ሂደት ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳለው አብዛኞቹ ቴክኒካዊ ጉዳዮች በድርድሩ መፍትሄ እንዳገኙ የገለጸ ሲሆን ነገር ግን ለድርድሩ መቋጫ ለማበጀት ሕጋዊ ጉዳዮች ላይ ገና መስማማት እንደሚያስፈልግ አመልክቷል።

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
ከስጋና ወተት ምርት 68 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ!

በ2012 በጀት ዓመት 11 ወራት ውስጥ ወደ ውጪ ከተላከ የስጋና ወተት ምርት 68.13 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒቴር ገለፀ፡፡ሚኒስቴር መ/ቤቱ የስጋና ወተት ኢንስቲትዩት የ2012 በጀት ዓመት የ11 ወራት የኤክስፖርት አፈፃፀምን በዘርፉ ከተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል፡፡በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ከስጋና ወተት 113.81 ሚሊያን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 68.13 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን ከበግና ፍየል ስጋ 61.31 ሚሊዮን ዶላር፣ ከዳልጋ ከብት 1.3 ሚሊዮን ዶላር፣ ከእንስሳት ተረፈ ምርት 2.93 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ከማር፣ ከሰም፣ ከዓሳ ምርት እና ከወተት 2.60 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡

ምንጭ: የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
በህንድ በአንድ ቀን ብቻ 12 ሺህ 881 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ!

በህንድ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 12 ሺህ 881 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።ይህም በአገሪቱ በአንድ ቀን ውስጥ እስካዛሬ ድረስ ከተመዘገበው ከፍተኛው ቁጥር መሆኑን አናዶሉ ኤጀንሲ ዘገቧል።በአለም አቀፍ ደረጃ በአንድ ቀን ውስጥ ከተመዘገበው ቁጥርም በሶስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በመረጃው ሰፍሯል።ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የ334 ሰዎች ህይወት በማለፉ የሟቾች ቁጥር 12 ሺህ 237 መድረሱም ተገልጿል።በአገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 366 ሺህ 946 የደረሰ ሲሆን 194 ሺህ 324 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን መረጃው አስታውሷል። እስካሁን በዓለም ከ 8 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን 451 ሺህ 463 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

#ENA
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ በሀዋሳ ሚሊንየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው!

የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።የምክር ቤቱ አባላት በ4 አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ምክክር ያደርጋሉ።የደቡብ ክልል ምክር ቤትየኮሮና ወረርሽኝን መከላከል እና ቁጥጥር ስራዎች አስመልክቶ በቀረበው ሪፖርት ላይ መወያየት የ2012 በጀት አመት ተጨማሪ ረቂቅ በጀት ላይ መወያየት ሁለተኛው አጀንዳ ነው።ምክር ቤቱ በ3ኛ አጀንዳው በአዲስ መዋቅር መደራጀት የቀረበ ጥያቄ ምላሽ እና የውሳኔ ሀሳብ ሪፖርት ይቀርባል፡፡ በመጨረሻም የስልጣን ርክክብ ማድረግ ተጠቃሽ ናቸው፡፡በአሁኑ ሰዓት የደቡብ ክልል ምክር ቤት የኮሮና ወረርሽኝ መከላከል እና ቁጥጥር ስራዎች አስመልክቶ በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ በአቶ አቅናው ካውዛ አማካኝነት ሪፖርት እየቀረበ ነው።

ምንጭ:የክልሉ መንግስት ኮሙኒዩኔሽን
@YeneTube @FikerAssefa
ቻይና ለአፍሪካ አገራት የሰጠችውን ወለድ አልባ ብድር ሰረዘች!

ቻይና ለአፍሪካ አገራት የተሰጡ እና እ.አ.አ 2020 ላይ እንዲመለሱ ዕቅድ የተያዘላቸው ወለድ አልባ ብድርን እንደምትሰርዝ ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ አስታወቁ።ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያስታወቁት በትላንትናው ዕለት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን መዋጋት ዓላማው ባደረገው እና በቪዲዮ አማካኝነት በተካሔደ የቻይና-አፍሪካ ልዩ ጉባኤ መሆኑ ተገልጿል።ከዚህ ባለፈ ለአፍሪካ አገራት ሆስፒታሎች ለመገንባት እና የሕክምና ባለሞያዎች ለመላክ ቃል ገብተዋል። የቻይና ኤግዚም ባንክ እና የቻይና ልማት ባንክ የመሳሰሉ የፋይናንስ ተቋማት “ከአፍሪካ አገራት ጋር በንግድ ጉዳይ በተሰጡ የብድር ስምምነቶች ላይ ውይይቶች እንዲያደርጉም” አሳስበዋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ እየተካሄደ ባለው የሶስትዮሽ ድርድር አብዛኛዎቹ ቴክኒካዊ ጉዳዮች እልባት ማግኘታቸው ተሰማ፡፡

በአብዛኛዎቹ የቴክኒክ ጉዳዮች እልባት ቢገኝም አጠቃላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ ገና መፈታት ያለባቸው የህግ ጉዳዮች እንደሚቀሩ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ ይናገራል፡፡የሶስትዮሹ ድርድር ባለፉት 7 ቀናት በግድቡ የመጀመሪያ ደረጃ ውሃ ሙሌትና ዓመታዊ አስተዳደር ላይ መከናወኑን ከመግለጫው ተመልክተናል፡፡የሶስቱ አገራት የቴክኒክና የህግ ቡድን ከሚኒስትሮቹ ድርድር አስቀድሞ በተጓዳኝ መወያየታቸውና የደረሱበትን ለሚኒስትሮቹ ማቅረባቸውንም ሰምተናል፡፡

እስካሁን በተካሄደው ድርድርም አብዛኛዎቹ የቴክኒክ ጉዳዮች መፈታታቸውን እና ከህግ አኳያ የሚቀሩ ጉዳዮች መኖራቸውን ሚኒስቴሩ ተናግሯል፡፡የሱዳን ተደራዳሪ ቡድን እስካሁን የተደረሰበትን ሁኔታ በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን ማነጋገር እንደሚፈልጉ በመጥቀስ ይኸው እንዲፈቀድላቸው መጠየቃቸውንም መግለጫው ያስረዳል፡፡የሱዳን ተደራዳሪ ቡድን ከጠቅላይ ሚኒስትራቸው ጋር ከተነጋገረ በኋላ ውይይቱን ለመቀጠል ከስምምነት ተደርሷል ተብሏል፡፡ኢትዮጵያ መርሆዎችን መሰረት አድርጋ ግድቡን የመሙላትም ሆነ የመጠቀም ሙሉ መብት እንዳላት ለግብፅ እና ለሱዳን አስረግጣ እንደነገረቻቸው መግለጫው ይናገራል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
ዴክሳሜታሶን ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቅም ላይ ስለሚውልበት ሁኔታ ባለሙያዎች ሐሳብ አቀረቡ!

ዴክሳሜታሶን ስለተባለውና ብዙ ስለተነገረለት መድኃኒት ዝርዝር ሁኔታና በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቅም ላይ ስለሚውልበት መንገድ ምርመራ በማድረግ ሃሳብ እንዲያቀርቡ የተጠየቁት ባለሙያዎች፤ የደረሱበትን ውጤት ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ማቅረባቸው ተሰማ።በጤና ሚኒስቴር የህክምና ግልጋሎት ዋና ኃላፊ የሆኑት አቶ ያዕቆብ ሰማን ለቢቢሲ እንደገለጹት በመድኃኒቱ ላይ ምርመራውን እንዲያደርግ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውስጥ ከኮሮናቫይረስ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ለተቋቋመው የባለሙያዎች አማካሪ ቡድን በሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ነው መመርያው ምርመራውን እንዲያደርጉ የተጠየቁት።በዚህ መሰረትም ቡድኑ ይፋ የተደረገውን ሙሉውን ጥናት ከመረመረም በኋላ የደረሰበትን እንዲሁም ይሆናል ያለውን ምክረ ሐሳብ አቅርቧል ሲሉ አቶ ያቆብ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ባለሙያዎቹ በዴክሳሜታሶን ዙርያ የተደረገው ጥናትና ሙከራን በተመለከተ የተዘጋጀው ጭምቅ ሐሳብ ታትሞ ለሕዝብ ይፋ ከሆነ በኋላ ስለመድኃኒቱ ጠቅላላ ይዘት እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቅም ላይ ሊውል ስለሚችልበት ሁኔታ ጥናት በመድረግ ሐሳብ እንዳዘጋጁ ታውቋል። ስለመድኃኒቱ አጠቃቅም ይጥናት ቡድኑ ያቀረበው ምክረ ሃሳብ ዝርዝር ይዘት ገና ይፋ አልተደረገም።አቶ ያዕቆብ እንዳሉት ዴክሳሜታሶን ከዚህም ቀደም ለተለያዩ በህመሞች ማከሚያነት ሲውል የነበረ መሆኑን አስታውሰው መድኃኒቱ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።

በዚህም መሰረት በበርካታ መገናኛ ብዙሃን ተጋንኖ እንደተዘገበው ሳይሆን የመድኃኒቱ ፋይዳ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ በፅኑ ሕክምና ላይ የሚገኙ ህሙማንን የሞት መጠን መቀነስ እንደሆነ፣ ይህ አዎንታዊ ጠቀሜታውም በቁጥር ደረጃ ሲሰላ አነስተኛ ነው ብለዋል።"በማኅበረሰቡ ዘንድ መዘናጋትን እንዳይፈጠር እና አሁንም ዋነኛው መተኮር ያለበት መንገድ ባለሞያዎች የሚሰጧቸውን የመከላከያ እርምጃዎች መተግበር ነው ሲሉ" ገልጸዋል።በርካሽ ዋጋና በስፋት የሚገኘው ዴክሳሜታሶን በኮቪድ-19 በጽኑ የታመሙ ሰዎች ሕይወትን ሊታደግ እንደሚችል የዩናይትድ ኪንግደም ባለሙያዎች ባደረጉት ምርምር እንደደረሱበት መግለጻቸው ይታወሳል።

በሙከራው ይህ መድኃኒት በኮሮናቫይረስ በጽኑ ከታመሙ ሦስት ሰዎች ውስጥ የአንዱን ሕይወት መታደግ እንደሚችል እና በወረርሽኙ ሰበብ ኦክስጂን በሚያስፈልጋቸው አምስት ሰዎች ላይ ሊያጋጥም የሚችልን አንድ ሞት ሊያስቀር እንደሚችል ተገልጿል።ተመራማሪዎች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንደተከሰተ በዩናይትድ ኪንግደም መድኃኒቱ በስፋት ጥቅም ላይ ቢውል ኖሮ እስካሁን ድረስ የ5000 ሰዎችን ሕይወት ማትረፍ ይቻል ነበር ብለዋል።የዓለም የጤና ድርጅትም መድኃኒቱ በወረርሽኙ በተያዙ ጽኑ ህሙማን ላይ የሚኖረውን አውንታዊ ውጤት እንደተቀበለው ገልጿል። ዴክሳሜታሶን ከ1960ዎቹ (እአአ) ጀምሮ በተለያዩ ህመሞች ምክንያት የሚያጋጥሙ እብጠቶችን ለመቀነስና የተወሰኑ አይነት የካንስር ህመሞችን ለማከም ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዳሴ ግድብ ከሕዝብ ፕሮጀክትነት ወርዶ የአንድ ግለሰብ ፕሮጀክት ሆኖ ነበር-አምባሳደር ዓለማየሁ ተገኑ!

የቀድሞው የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር እና በሩሲያ የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ዓለማየሁ ተገኑ፣ የሕዳሴው ግድብ ከሕዝብ ፕሮጀክትነት ወርዶ የአንድ ግለሰብ ፕሮጀክት ሆኖ ነበር፤ ይህም የግድቡን ግንባታ ለውድቀት ከመዳረጉ ባለፈ “በአገራችን ታሪክ የሚያሳዝን ድርጊት ሆኖ አልፏል” አሉ።አምባሳደሩ አቶ መለስ በሕይወት እስከነበሩበት ጊዜ ድረስ በየወሩ ይገመገም እንደነበር እና ከእርሳቸው ሕልፈት በኋላ ግምገማው መቅረቱን አስታውቀዋል።በዚህም የተነሣ የሕዳሴ ግድቡን ፕሮጀክት የመብራት ኃይል ቦርድ አካል የመገምገም ዕድል እንዳልነበረው ተናግረዋል። ፕሮጀክቱን በሚመለከት በየጊዜው ለቦርዱ ጥያቄ ያቀርቡ የነበረ ቢሆንም፣ ቦርዱ የግምገማውን ውጤት ወደ ውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አይልክም፤ የዘርፉ ባለቤት ብንሆንም ተገልለን ነበር ብለዋል።

የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከመብራት ኃይል የሚያገኘውን መረጃ ይዞ እንደ ዘርፍ መግለጫ ሲሰጥ “ምን አግብቷችሁ ነው መግለጫ የምትሰጡት” በማለት የቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በኩል ቁጣ ይመጣ እንደነበር ገልጸዋል። በወቅቱ የሕዳሴ ግድቡ ሥራ እና ውሳኔዎች በሰብሳቢው ውሳኔ ስር የነበሩ በመሆናቸው እና የቦርድ አባላትም ፕሮጀክቱን በአካል ስለማይገመግሙ ትልቅ ውድቀት አጋጥሞ እንደነበር ጠቁመዋል።በወቅቱ የነበረውን ቦርድ ችግሮች በሚገባ ለማየት አሁን የተቀየረው ቦርድ በአጭር ጊዜ ያመጣውን ለውጥ ማየት አሳማኝ እና በቂ ነው ብለዋል።“ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት ከግለሰብ እጅ ወጥቶ ወደ ሕዝባዊነቱ ተመልሷል። አገግሞ እና የኮንትራት አስተዳደሩም ተለውጦ አስደናቂ ለውጥ በማምጣት ዳግም አገራዊ ተስፋ ፈጥሯል” ሲሉ ተናግረዋል።

“አቶ ኃይለማርያም በወቅቱ በጠሩት እና በገመገሙት ስብሰባ ላይ ፕሮጀክቱ መዘግየቱ መግባባት ላይ ተደርሷል። ሳሊኒም ሜቴክ ባልሠራቸው ሥራዎች ምክንያት የራሱን ሥራ መሥራት እንዳልቻለ በግምገማው ላይ ተነሥቷል። በዚህ ወቅትም ቢሆን ለሥራው መጓተት ዋናው ምክንያት ሜቴክ እንደሆነ ተረጋግጧል። ቦርዱም እርምጃ እንዲወሰድ አቅጣጫ ቢቀመጥም ማስተካከል ሳይቻል ቀርቷል” በማለት ገልጸዋል።በግድቡ ግንባታ ሂደት ሜቴክ ሥራውን በጊዜ ባለመጨረሱ ሲቪል ሥራው ቆሞ ነበር ያሉት አምባሳደሩ፣ ለዚህ ችግር ተጠያቂው ሜቴክ ሆኖ ሳለ ቦርድ ሰብሳቢው እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ለሜቴክ ሽፋን በመሆን አልፈውታል። አሁን ያለው ለውጥ ባይመጣ ሜቴክን ይዞ የመቀጠል አቋማቸው የጸና ነበር ማለታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በዓለማችን በይፋ ከተነገረዉ ዉጭ በትንሹ ከ130 ሽህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉን አጥተዋል ተባለ፡፡

በ27 ሀገራት ላይ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት፣በጥናቱ በተካተቱ በሁሉም ሀገራት የሞት መጠን በአስደንጋጭ ሁኔታ ጨምሮ ተገኝቷል፡፡በቢቢሲ የተሰራዉ ይህ ጥናት፣ በኮሮና ቫይረስ ሞቱ የተባሉትን ሰዎች ሳያካትት የተሰራ ሲሆን፣በዚህም በመንግስታት ሪፖርት ያልተደረጉና ለሞታቸዉ ምክንያት ግን የኮሮና ቫይረስ ሊሆን እንደሚችል ምልክት ያሳዩ ከ130 ሽህ በላይ ሰዎች መሞታቸዉን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡በጤናዉ ዘርፍ ላይ የኮሮና ቫይረስ ባደረሰዉ ተጽዕኖ በሌሎች በሽታዎች የተጠቁና ህክምና ሳያገኙ የሞቱ በርካታ ሰዎች መኖራቸዉንም ተገንዝቤያለሁ ብሏል ጥናቱ፡፡ለሞት የተዳረጉት ከ130 ሽህ በላይ ሰዎች ምርመራ ያልተደረገላቸዉና ከሆስፒታል ዉጭ የሞቱ ሲሆን ብራዚል፣ጣሊያን፣ እንግሊዝና ደቡብ አፍሪካ በብዛት ይህ አሳዛኝ ድርጊት የተስተዋለባቸዉ ሀገራት ናቸዉ ተብሏል፡፡

ለማሳያነትም በዩናይትድ ኪንግደም በጠቅላላዉ 64 ሽህ 500 ሰዎች ለሞት የተዳረጉ ሲሆን ሪፖርት የተደረገዉ ግን 42 ሽህ 153 ብቻ ነዉ፤ይህም ከ22 ሽህ በላይ ሰዎችን ያላጠቃለለ ሪፖርት ነዉ ተብሏል፡፡በጣሊያንም 42 ሽህ 900 ሰዎች መሞታቸዉ ሲረጋገጥ የተነገረዉ ግን 34 ሽህ 448 ሰዎች መሞታቸዉ መሆኑን ይገልጣል፡፡ጥናቱ እንደሚለዉ አሁንም ቢሆን በተለያዩ ሀገራት ምርመራ ሳያደርጉና የሆስፒታል በር ሳያዩ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ለቀጣይ በርከት ላሉ ወራት የሚቀጥል መሆኑን የሚጠቁም ነዉ፡፡እናም ሀገራት የምርመራ አቅማቸዉን ማሳደግና ለብዙሃኑ ተደራሽ ማድረግ ካልቻሉ፣በቫይረሱ ምክንያት በየቤታቸዉ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ ሊያሻቅብ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የወባ መድኃኒት ለኮሮናቫይረስ ህክምና ለማዋል ሲደረግ የነበረው ጥናት ተቋረጠ!

የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ ታማሚዎችን ለማከም ይረዳል በተባለለት ሃይድሮክሎሮኪን ላይ ያደርግ የነበረውን ጥናት ማቋረጡን አስታወቀ።ጸረ-ወባ የሆነው መድኃኒት በሽታውን ቀድሞ ለመከላከልም ሆነ የታመሙትን ለማከም ሊውል ይችላል የሚል ሰፊ ቅድመ ግምት ነበር። ይሁን እንጂ ይህ በጥናት ሳይረጋገጥ ቆይቷል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት ተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ብቻ ግምታዊ ዋጋቸው ከ16 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ንግድ ማጭበርበር በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል የተለያዩ ዓይነት አዳዲስና አሮጌ አልባሳት፣ የአዋቂና የህፃናት ጫማዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ተሽከርካሪዎች፣ የተሸከርካሪ ጎማና መለዋወጫ (ስፔር ፓርት)፣ የምግብ ዘይት፣ ጫት፣ ሃሺሽ እና ልዩ ልዩ ዓይነት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እንዲሁም በቦሌ፣ በሞጆ እና በአንዳንድ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ በተደረገው ከፍተኛ 120,000 ሀሰተኛ ዶላርም በሞያሌ ቅርንጫፍ መያዙ ተገልጿል።ህብረተሰቡ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ የሃገሪቱን እድገት የሚያቀጭጭ መሆኑን በመገንዘብ ጥቆማ በመስጠት ከጎኑ እንዲሆኑ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።

#AMN
@YeneTube @FikerAssefa
በሶማሌ ክልል ርዕስ መስተዳደር በአቶ ሙስጠፌ መሃመድ ዑመር የሚመራው የብልፅግና ፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደዉ ሰብሰባ ሁለት አዳዲስ ሹመቶችን አፅድቋል።በቀጣይም ለሶማሊ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ሹመታቸው እንደሚፀድቅ ይጠበቃል።
ለሹመት የቀረቡት
1.ኢብራሂም ኡሰማን / ለክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳደርነት
2.አቶ መሎዉ ኢብራሂም አብዲ/ ለክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤነት
እንደሆነ ከክልሉ የመንግስት/ኮ/ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት በ5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤው የ2012 በጀት አመት ተጨማሪ ረቂቅ በጀት 2 ቢሊየን 641 ሚሊየን 964ሺ 422 ብር በጀት አጽድቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል ምክር ቤት የሲዳማ ዞን የአገሪቱ አስረኛ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ የሥልጣን ርክክብ ለማድረግ የቀረበውን አጀንዳ ተቀብሎ አጸደቀ።

ምክር ቤቱ አጀንዳውን ያጸደቀው ከደቂቃዎች በፊት በሀዋሳ ከተማ በጀመረው የምክር ቤቱ አምስተኛ ዙር አምስተኛ ዓመት ሁለተኛ አስቸኳይ ጉባኤው ነው ። በጉባኤው መክፈቻ ላይ የምክር ቤቱን የመወያያ አጀንዳዎች ያቀረቡት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሄለን ደበበ ምክር ቤቱ በዚህ ጉባኤ ከሚመለከታቸው አጀንዳዎቹ መካከል አንዱ የሲዳማ ዞን የሥልጣን ርክክብ መሆኑን ለጉባኤው አባላት ገልጸዋል። አሁን ለጉባኤው የቀረበው አጀንዳ የሲዳማ ህዝብ በራስ ገዝ አስተዳደር ( ክልል ) ለመደራጀት ባለፈው የኅዳር ወር ያካሄደውን ሕዝበ ውሳኔ ተከትሎ የክልል ምስረታው ሂደት ተጓቷል በሚል ከተለያዩ አካላት እየቀረበ ለሚገኘው ወቀሳ የመጨረሻ አልባት ይሰጣል ተብሎ ታምኖበታል።ምክር ቤቱ ሕዝባችን በክልል ለመደራጀት ላቀረበው ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ አልሰጠም በሚል ራሳቸውን ከአባልነት ማግለላቸውን ከቀናት በፊት ያስታወቁት 38 የወላይታ ሕዝብ ተወካዮች በዚህ ጉባኤው አልተገኙም።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa
የአምባሳደር ፓርክ የእድሳት ስራ ተጠናቀቀ!

በአራዳ ክፍለ ከተማ ራስ ዳምጠው ጎዳና ላይ የሚገኘው የአምባሳደር ፓርክ እድሳት መጠናቀቁን መልከዐ ምድር ንድፉን እና እድሳቱን የሰራው ዛና ላንድስኬፒንግ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር አስታወቀ። ወደ አስር ሺ ካሬ ሜትር የሚጠጋ መሬት ላይ ያረፈው አምባሳደር ፓርክ የሚገኝበት አካባቢ ለብዙኃኑ ተስማሚ ከመሆኑ በተጨማሪ ፤ በወቅቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወንዝ ዳርቻና የአረንጓዴ አካባቢዎች ኤጀንሲ ስር እየተሰራ ከሚገኘው የከተማ ማስዋብ ስራ አካል ስለመሆኑ በፕሮጀክቱ ጅማሬ ወቅት ተገልጾ እንደነበር ይታወሳል።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
የሽንኩርት ዋጋ መናር ምክንያት ላይ ጥናት በማድረግ ምክንያት ሆነው በተገኙ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስትር ዴኤታው አቶ እሸቴ አስፋው በሚኒስቴሩ የሚመራው የገበያ ማረጋጋት ብሔራዊ ግብረ ኃይል የሽንኩርት ዋጋ ጭማሪውን አስመልክቶ ጥናት መካሄዱን ተናግረዋል።በጥናቱ መሰረት ለሽንኩርት ዋጋ ጭማሪው የምርት እጥረት መኖሩ አንድ ምክንያት ቢሆንም ችግሩ በዋናነት የተፈጠረው ግን የሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ጣልቃ ገብነት መሆኑ ተረጋግጧል።በመሆኑም ሽንኩርትና ቲማቲም የመሳሰሉ አትክልቶች የሃገር ውስጥ ፍላጎትን ሳያሟሉ ወደ ውጭ እንዳይወጡ ለሁሉም የጉምሩክ ጣቢያዎች ደብዳቤ በመፃፍ ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል። እስካሁን በተደረገው ክትትልም ምርቶቹ በሱማሌ ክልልና በድሬዳዋ በማቆራረጥ ወደ ጂቡቲ፣ ሱማሊያና ኬንያ እየተላኩ መሆኑ ተደርሶበታል።ሕገወጥ ነጋዴዎች 11 መኪና ሽንኩርት ወደ ጅቡቲ ሲያስወጡ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አቶ እሸቴ ተናግረዋል።

በተጨማሪም አዳማ ላይ ቲማቲም፣ ሽንኩርትና መሰል ምርቶችን በሕገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የተያዙ ስለመኖራቸውም ጠቅሰዋል።ከአሁን ቀደም በሱዳን በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው የሽንኩርት ምርት ከኮሮና መከሰት ጋር ተያይዞ መቅረቱ የራሱ ተፅዕኖ እንደነበረውም አክለዋል።ሚኒስትር ዴኤታው በሱዳን በኩል የነበረው የሽንኩርት አቅርቦት የሚቀጥልበት ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑንም ተናግረዋል።ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት አቅርቦትና ምርት ላይ የሚሰራው እንዳለ ሆኖ የኅብረተሰቡም ትብብር በመኖሩ ሕገወጥ ደላሎችና ነጋዴዎችን ወደ ሕግ የማቅረቡን ስራ እናጠናክራለን ብለዋል።

ምንጭ: ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 195 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ 2 ሰዎችም ሕይወት አልፏል

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4853 የላብራቶሪ ምርመራ 195 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውና የ 2 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3ሺህ 954 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ የ2 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ፣ ባጠቃላይ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 65 ደርሷል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ያለፈ 2 ሰዎች ሁኔታ

1.በህክምና ላይ የነበሩ የ80 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ (ወንድ)

2.በህክምና ላይ የነበሩ የ60 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ (ሴት)

@YeneTube @FikerAssefa