YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዛሬ በሀረሪ ክልል በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙ በሀገር አቀፍ ሪፖርት የተገለጹት ሶስቱም ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው እንዲሁም የውጪ ጉዞ ታሪክም የሌላቸው መሆኑ ተረጋግጧል።በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ድምር 8 ደርሷል። ዝርዝር ሪፖርቱን ከላይ ይመልከቱ ።

@YeneTube @FikerAssefa
በጋሞ ዞን በመሬት ናዳ እና ጎርፍ ጉዳት የደረሰባቸውን አርሶ አደርች በሰፈራና ስግሰጋ ለማስፈር ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት መዘጋጀቱን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ ገለጿል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ በኦሮሚያ ክልል በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙ በሀገር አቀፍ ሪፖርት ከተገለጹት 22 ሰዎች 20ዎቹ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ 2ቱ ደግሞ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው እንዲሁም የውጪ ጉዞ ታሪክም የሌላቸው መሆኑ ተረጋግጧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽ ስርጭትን ለመግታት የሚያግዙ የሞባይል መተግበሪያዎች ተዘጋጁ!

የኢትዮጵያ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር እና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ሁለት የኮሮናቫይረስ ወረርሽ ስርጭትን ለመግታት የሚያግዙ የሞባይል መተግበሪያዎችን አዘጋጀ። ከመተግበሪያዎቹ መካከል አንደኛው በኮረናቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር ያለውን ንክኪ የሚለይ ነው።ይህ መተግበሪያ በብሉቱዝ ብቻ ግንኙነት የሚያደርግና በሁለት ሜትር ርቀት ላይ መረጃውን የሚያሳይ መሆኑም ነው ዛሬ ኢንስቲትዩቱ በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሲሰጥ ያመለከተው።ሌላኛው መተግበሪያ ደግሞ በኮረናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን የሚከታተሉ የጤና ባለሙያዎች ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያግዝ ነው።መተግበሪያዎቹን ከኢንስትቲዩቱ ድረገጽ እና ከጎግል ፕሌይ ላይ ደቦ እና ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ በሚል አውርዶ መጠቀም እንደሚቻል ተገልጿል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
በሲዳማ የመጀመርያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መገኘቱ ታወቀ!

ኑሮውን በአዲስ አበባ አድርጎ በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርቶ የነበረ ሹዴ ፍቅሬ የተባለ የ20 ዓመት ወጣት በቅዱስ ፓውሎስ ሆስፒታል በተደረገለት ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጦ በለይቶ ማቆያ የነበረ ቢሆንም ከማቆያ በማምለጥ በሲዳማ አከባቢ ልዩ ስሙ በንሳ ወደ ተባለ ስፍራ ቤተሰቦቹ ጋር በሄደበት ተይዞ ወደ ይርጋለም የኮቪድ-19 ማከምያ ማዕከል መወሰዱን የሲዳማ ጤና ቢሮ(መምሪያ) ሀላፊ የሆኑት አቶ በላይነህ በቀለ ተናግረዋል። ከግለሰቡ ጋር አብረው ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ በንሳ ያመሩ 11 ሰዎች በንሳ ዳዬ ካምፓስ የለይቶ ማቆያ እንዲገቡ መደረጉን አክለው ለSMN ገልጸዋል።

Via ማለዳ ሚድያ
@YeneTube @FikerAssefa
በቴሌግራም @Orangebusinessnetwork ን በመጎብኘት ለእርሶ እና ለድርጅቶ እድገት የሚረዱ መረጃዎች ፤ሀብቶችን እና ማበረታቻዎችን ያገኙ!

የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ
T.me/Orangebusinessnetwork
የአዲስ አበባ ኮቪድ-19 ሪፖርት
ግንቦት 22/2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የCovid-19 አስመልክቶ የወጣ ዝርዝር ሪፖርት

@YeneTube @FikerAssefa
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በመተላለፍ ሰላማዊ ሰልፍ የሚጠሩ ሰዎች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ሲል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ መንግሥት የሕግ የባላይነትን ለማስከበር ከምንጊዜውም በላይ እንደሚሰራም ገልጿል።የቢሮው ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ መንግሥት ዜጎችን ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጥቶ ጥረት እያደረገ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሕዝቡን ለሰላማዊ ሰልፍ የሚጠሩ ሰዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ የገለጹት አቶ ጌታቸው የክልሉ መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ከምንጊዜውም በላይ እንደሚሰራም አመልክተዋል።

“አንዳንድ አካላት ክልሉን የሁከትና የብጥብጥ ማዕከል ለማድርግ እየሰሩ በመሆኑ ሕዝቡ ነቅቶ ሊጠብቅ ይገባል” ብለዋል።ከአራት ሰዎች በላይ መሰብሰብ በማይቻልበት በአሁኑ ወቅት ኅብረተሰቡን ለችግር ለማጋለጥ የሚደረገውን ጥረት ሕዝቡ ተረድቶ ሊጠነቀቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።ጥሪውን የሚያቀርቡ ሰዎች የሽግግር መንግሥት ይመስረት የሚሉ አካላትና በአቋርጭ ሥልጣን ለመያዝ የሚፈልጉ ኃይሎች መሆናቸውንና እነዚህም ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ አቶ ጌታቸው ተናግረዋል።የክልሉ መንግሥት በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀስ ማንኛውንም ኃይል የሚያበረታታና የሚደግፍ መሆኑን ጠቅሰው፣ በሕገወጥ መንገድ በሚንቀሳቀሱት ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል።

ምንጭ: ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 323 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በ2ኛው ዙር ዛሬ ከሊባኖስ ወደ አገራቸው  ተመለሱ ።

ኢትየጵያውያኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ፣ የሰላም ሚኒስትር ዴአታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው፣ የሴቶቸ፣ ህጸናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ስመኝ ውቤ፣ የዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ጉዳይ የኢትዮጵያ ተወካይ ማውሪን አቼንግ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አካላት ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳይ አስፈጻሚን ጠርቶ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ይደገፋሉ ያላቸው ሚሊሻዎች በሱዳን ግዛት ውስጥ በሱዳን ዜጎችና ወታደሮች ላይ እየፈጸሙት ያለውን ጥቃት ማውገዙን ሱና ዘግቧል።

Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
ጅቡቲ ባለፉት 24 ሰዓታት 1109 ሰዎችን መርምራ 280 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን አግኝታለች። ይህንን ተከትሎ በቫይረሱ የተያዙባት ሰዎች ድምር 3,194 ደርሷል። ተጨማሪ 2 ሰዎች የሞቱባትም ሲሆን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 22 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 22 ሰዎች 18ቱ የዳንጎቴ ሲሚንቶ ሰራተኞች እንደሆኑ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። እነሱን ጨምሮ 19 ሰዎች ከምዕራብ ሸዋ ዞን ሲሆኑ፣ 18ቱ ከዳንጎቴ ሲሚንቶ አዳ በርጋ ዲስትሪክት ነው የተገኙት።በክልሉ እስካሁን 67 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 11ዱ አገግመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ 9ኛው ሞት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተመዝግቧል!

በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ 45 ሰዎች መካከል የአንዲት የ29 አመት ሴት ህይወት ማለፉ ታውቋል።እስካሁን በሃገራችን በቫይረሱ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ብዛት 9 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል የኢትዮጵያ አስረኛ ክልል ሆኖ ለሚቋቋመው ሲዳማ ዞን ሥልጣን ለማስረከብ "ሽግግር" መጀመሩን አቶ ርስቱ ይርዳው ተናገሩ።

የደቡብ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ይኸን ያሉት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የተደነገገው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃጸም መርማሪ ቦርድ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።በውይይቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጴጥሮስ ወልደሰንበት "የሲዳማ ዞን ሽግግር ላይ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ አመራሮቹ ከደቡብ ክልል ጋር ያለን ግንኙት እንደድሮው አይደለም፣ ተገቢውንም ድጋፍ አላገኘንም አያሉ ይገኛሉ" በማለት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።የደቡብ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው "ሲዳማ ሽግግር ላይ ነው ያለው። የዞኑ አመራር አጠቃላይ በዞኑ እና በከተማ ያሉ ሥራዎችን ወስዶ እንዲሰራ አድርገናል" ብለዋል። በደቡብ ክልል ቴሌቭዥን ጣቢያ በተላለፈ ንግግራቸው አቶ ርስቱ በክልሉ እና በዞኑ አመራሮች መካከል ያለው ግንኙነትም "መልካም ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። የሲዳማ ዞን ክልል ለመሆን ያቀረበውን ጥያቄ ለመወሰን ሕዝበ-ውሳኔ ከተካሔደ ስድስት ወራት ተቆጠሩ። ባለፈው ኅዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም. በተካሔደው ሕዝበ-ውሳኔ ድምፅ ከሰጡ የዞኑ ነዋሪዎች 98.51 በመቶው ሲዳማ 10ኛው ክልል እንዲሆን ደግፈዋል። ከደቡብ ክልል ወደ ሲዳማ ዞን መደረግ የነበረበት የሥልጣን ሽግግር መዘግየት በፖለቲካ ፓርቲዎች እና የለውጥ አራማጆች ከፍተኛ ተቃውሞ ሲቀርብበት ቆይቷል። አቶ ርስቱ ይርዳው የሽግግር ሥራ ተጀምሯል ቢሉም በትክክል መቼ እንደሚጠናቀቅ ያሉት ነገር የለም።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
አብን "አምነስቲ ኢንተርናሽናል" ኢትዮጵያን አስመልክቶ ያወጣው ሪፖርት ወገንተኛ መሆኑን አስታወቀ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እንዳስታወቀው አምንስቲ ኢንተርናሽናል የተሰኘው የሰብአዊ መበት ጥበቃ ተቋም ሰሞኑን በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት አስመልክቶ ያወጣው ሪፖርት ገለልተኝነትን ያልተከተለ ነው ብሏል። ንቅናቄው በመግለጫው ቀደም ሲል የሰብአዊ መብቶች አያያዝን አስመልክቶ "አምነስቲ ኢንተርናሽናል" ሲያወጣቸው ከነበሩ በአንፃራዊነት የተሻለ ገለልተኝነት ከነበራቸው ሪፖርቶች በተለየ መልኩ የተጠናቀረዉ ይህ ሪፖርት በደል የደረሰበትን ወገን በበዳይነት ፈርጆ ቀርቧል ብሏል።

ይህ ሪፖርት በተለይ ለሰብአዊ መብቶች ጥበቃ እሰራለሁ ከሚል ተቋም ፍፁም የማይጠበቅ መሆኑንም ገልጿል።የታገቱ ሴት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉዳይ ፤በአማራ ፣ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተፈጥረው በነበሩ ግጭቶች የተሳተፉ አካላት ለህግ አለመቅረብ፣ የሰኔ 16 የአማራ ክልል የአመራሮች ግድያ እና ሌሎች ጉዳዮች በሪፖርቱ መካተት ነበረባቸው ሲል ጠቁሟል።

በአጠቃላይ በ"አምነስቲ ኢንተርናሽናል" በኩል ተጠናቅሮ የቀረበዉ ሪፖርት የጥሰቶችን ትክክለኛ ማኅበራዊ፣ ሕጋዊ እና ፖለቲካዊ አንድምታዎች ባለመግለፅ ሆነ ብሎ ለመደበቅ የተሰራ መሆኑን ንቅናቄው አስታውቋል።እንዲሁም ሪፖርቱ ዓለማቀፍ ገለልተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ተቋም መከተል ያለበትን የመረጃ አሰባሰብ መርኆዎች ያልተከተለ መሆኑን፤ ገለልተኝነት በሌላቸው ወኪሎች የተጠናቀረ መሆኑንም ገልጿል።በዚህ ረገድ "አምነስቲ ኢንተርናሽናል" ጉዳዩን በጥልቀት በመመረመር ተገቢውን የእርምት እርምጃ እንዲወስድ እና በምትኩ ትክክለኛ እና ገለልተኛ ሪፖርቱን እንዲያወጣ ንቅናቄው ጠይቋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር የተፈጠረው ክስተት በውይይት የሚፈታ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ከአንድ ሳምነት በፊት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በሞቱ የሁለቱም አገራት ዜጎች ማዘኑን ገልጿል።በሁለቱ ድንበሮች የተፈጠረው ክስተትም አገራቱ ከዚህ በፊት ባስቀመጡት የድንበረር ማካለል መርህ እና ባደረጓቸው ወታደራዊ ስምምነቶች በውይይት እንደሚፈቱም አስታውቋል።በሁለቱ አገራት ድንበሮች አካባቢ የተፈጠረው ክስተትም የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ወዳጅነት እንደማይወክል ሚኒስቴሩ በድረገጹ አስታውቋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በሜኖሶታ ሚኒያፖሊስ ከተማ በተከሰተው የጆርጅ ፍሎይድ አሳዛኝ ግድያ፣ ይህንን ተከትሎም በተከሰተው የተቃውሞ ሰልፍ፣ ብሎም ረብሻና ቃጠሎ እስካሁን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ንብረት የሆነ ቦሌ ሬስቶራንት የተባለ ምግብ ቤት እና አንድ የፈርኒቸር ኩባንያ በቃጠሎ መውደማቸውን አምባሳደር ፍፁም አረጋ ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣው መግለጫ የተዛባና ሚዛናዊነት የጎደለው ነው ብሏል የአማራ ክልል መንግስት።

የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙልነህ ጉዳዩን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫውም አምነስቲ ኢንተርናሽናል በአማራ ክልል በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች በነበረው ችግር ላይ ያቀረበው ሪፖርት ከግጭቱ መነሻ ምክንያት ጀምሮ በርካታ ክፍተቶች ያሉት፣ የተዛባና በአንድ ወገን መረጃዎች ላይ የተመሠረተ ሚዛናዊነት የጎደለው መሆኑን ነው ዳይሬክተሩ የገለፁት።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ግጭት ተፈፀመባቸው በተባሉ ቦታዎች የአማራ ተፈናቃዮች፣ መሠረታዊ የሆኑ የክልሉ መንግስት አመራሮች እና ተቋመት ተጠይቀው ተገቢ መረጃ ተሰብስቦ ሳይካተት ሚዛናዊነት በጎደለው ሁኔታ መግለጫ መስጠቱ መታረም እንዳለበት ተናግረዋል።

ሪፖርቱ በቅማንት ላይ የብሄር ጥቃት እንደተፈፀመ እና ቅማንት ብቻ የጠፈናቀለ አድርጎ ማቅረቡ ሁለቱን ህዝቦች እንደገና ወደቁርሾ የሚመራ፣ ለአንድ ወገን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደተፈፀመ የሚገልፅ ትክክለኛነት የጎደለው ነው ብለዋል።አምነስቲ ኢንተርናሽናል የክልሉ መንግስት እና የፌደራል መንግት የሠሩትን ስራ እውቅና በመንፈግ አንድ ወገንን ማዕከል አድርጎ ሪፖርቱን ማዘጋጀቱ ለሪፖርቱ ሚዛናዊ አለመሆን ማሳይ አድርገው አቅርበዋል አቶ ግዛቸው።በመሆኑም ድርጅቱ ያወጣውን መግለጫ እንደገና እንዲመለከተው ጠይቋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የኮቪድ-19 ሕሙማንን ለሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች ጊዜያዊ መኖሪያ ቤቶች ተዘጋጁ!

በአዲስ አበባ የኮቪድ-19 ሕሙማንን እያገለገሉ ለሚገኙ 1 ሺህ 750 የጤና ባለሙያዎች ጊዜያዊ መኖሪያ ቤቶች መዘጋጀታቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።ኮቪድ-19ን ለመከላከል ለሚሠሩ የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች ሠራተኞች የሚውሉ የኢንፌክሽን መከላከያ ቁሳቁስ ለማሟላት እየተሰራ መሆኑንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa