YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ትንቢተ_ፍጻሜ

እያንዳንዷን ቀን በጥንቃቄ እና በብልሀት መኖርን መዘንጋት የለብንም፡፡ እኛ የመጨረሻዎቹ የሰው ልጅ ፍጥረቶች መሆናችንን ተገንዝበን ይህችን ዓለም ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እንደምንሰናበታት ባወቅን ጊዜ በእያንዳንዷ ቀናችን ጠንቃቃና ዝግጁ መሆን እንዳለብን መካሪ አያሻንም፡፡ ለሞት ከሚያበቁ በሽታዎች በርን ዘግቶ ማምለጥ፣ ከድንገተኛ መቅሰፍት እና ከወቅታዊ ወረርሽኝ ራስን በመሰወር የመጨረሻዋን ምድራዊ ሕይወት ኑሮ ጨርሶ ወደ ዘላለማዊ ቤታችን ጠቅልሎ ለመሄድ መጠንቀቅ የብልሆች ስራ ነው፡፡ ይህን እያሰባችሁ መኖር እንዳለባችሁ ለማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡
#ሲልቪያ_ብራውን
#END_of_DAYS መጽሐፍ
#ትንቢተ_ፍጻሜ በሚል በአማርኛ ተተርጉሞ በገበያ ላይ ውሏል፡፡

*************
በክርስትና፣ በእስልምና፣ በጆሆቫ፣ በራስ ተፈሪያኖች… በሁሉም ኃይማኖቶች ስለዓለም ፍጻሜ የተነበየ መጽሐፍ፡፡
#ኢትዮጵያ_እና_የንጉሶች_ንጉስ_የሆኑት_አጼ_ኃይለስላሴም_በዚህ_መጽሐፍ_ውስጥ_ተጠቅሰዋል፡፡ ከትንቢተ ፍጻሜው ጋር ምን ያገናኛቸው ይሆን?
#እውን_እንደሚባለው_ዓለም_ፍጻሜዋ_አሁን_ይሆን? #ወይስ_ስንት_ዘመን_ትቆይ_ይሆን?

ተርጓሚ ራሴላስ ጋሻነህ
የመጽሐፈ ሔኖክ ኢትዮጵያዊና የስኬት ፍልስፍና መጽሐፍት ተርጓሚ
#በዓለማችን በኮሮና ከተጠቁ ሰዎች ውስጥ ከ723 ሺህ በላይ ዜጎች ድነዋል፡፡

በአለም ዙርያ ይሄንን ዜና እስካጠናቀርንበት ሰአት ድረስ 2 ሚሊዮን 646 ሺህ 428 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ 723 ሺህ 713 ያህሉ ሲያገግሙ 184 ሺህ 353 ያህሉ ደግሞ ህይወታቸው አልፏል፡፡

በህመሙ ከተጠቁት ውስጥ 1 ሚሊዮን 600 ሺህ 140 ያህሉ በደህና ሁኔታ ውስጥ ሲሆኑ 58 ሺህ 222 ሰዎች ህመሙ ፀንቶባቸው በፅኑ ህሙማን ማቆያ ውስጥ ናቸው፡፡

- በኮሮና ተጠቂ ብዛት #አሜሪካ አንደኛ ስትሆን ከሁለተኛ እስከ ሰባተኛ ያሉት የአውሮፓ ሀገራት ናቸው፡፡

- #አሜሪካ በኮሮና ከተጠቁባት 849 ሺህ 92 ሰዎች መካከል 84 ሺህ 50 ያህሉ ሲድኑ 47 ሺህ 681 ደግሞ ሞቶባታል፡፡

- #ስፔን_ጣልያንና_ኢራን በቅደም ተከተል ብዙ ዜጎቻቸውን በሞት ያጡ አገራት ናቸው።
የወረርሽኙ መነሻ የሆነችው ቻይና 82 ሺህ 798 ተጠቂ አስመዝግባ 77 ሺህ 207 ሰዎች ሲድኑ ከ4 ሺህ በላይ ያህሉ ደግሞ ሞተዋል፡፡

- ወደ ደበቡ አሜሪካ ስናቀና በኮሮና ተጠቂ ብዛት #ብራዚል ትቀድማለች፤ 46 ሺህ 182 ተጠቅተው 25 ሺህ 318 አገግመው 2 ሺህ 924 ሞተውባታል፡፡

- የመካከለኛው ምስራቅ ሀያል ሀገር እስራኤል 14 ሺህ 592 ተጠቂ አስመዝግባ 5 ሺህ 334 አገግመው 2 ሰው ብቻ ሞተውባታል።

- #ሳውዲ_አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ከ20 ሺህ በላይ ዜጎች በቫይረሱ ሲጠቁ ከ150 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

- #በአውስትራሊያ 6 ሺህ 660 ሰው በኮሮና ተይዞ 75 ሰዎች ሞተዋል፡፡

- #ከአፍሪቃ በተጠቂዎች ብዛት ቀዳሚ የሆነችው አገር ደግሞ #ግብፅ ነች፤3 ሺህ 659 ተጠቂ አስመዝግባ 935 ያህሉ ሲያገግሙ 276 ያህል ሰዎች ሞተውባታል፡፡

- #ደቡብ_አፍሪካም ከግብፅ ጋር ተቀራራቢ ያህል ሰው ነው በኮሮና የተጠቃባት፤ 3 ሺህ 635 ሰው ተጠቅቷል፡፡ 1 ሺህ 55 ሰው ሲያገግም 65 ሰው ደግሞ ሞቷል፡፡

- ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት #ጅቡቲ ብዙ ሰው በኮሮና የተያዘባት ሀገር ነች፡፡ 974 ሰው ተይዞ 183 አገግሞ 2 ደግሞ ሞቷል፡፡

- #ኬንያ 303 ተጠቂ አስመዝግባ 83 አገግመውላታል 14 ሰዎች ደግሞ ሞተውባታል፡፡ #ሶማሊያ 286 ሰዎች ተጠቅተው 4 አገግመው 8 ደግሞ ሞተዋል፡፡

- #ኤርትራ 39 ሰው ተጠቅቶ 6ቱ ሲያገግሙ እስካሁን የሞተ ሰው የለም፡፡

- ሀገራችን #ኢትዮጵያ 116 የኮሮና ተጠቂ ስታስመዘግብ 21 ሰዎች አገግመው 3 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡


Via:- Ethio FM // ጆንሆፕኪንስ ዩንቨርሲቲ ድረገጽ
@Yenetube @Fikerassef