YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለተለያዩ አካባቢ ወጣቶች የበዓል ስጦታ አበረከቱ።

ለተለያዩ አካባቢዎች 40 በሬዎች የተከፋፈሉ ሲሆን ስጦታዎቹ ከባለሀብቶች የተሰባሰቡ ናቸው። ወጣቶቹም ስጦታውን በመቀበል ለየአካባቢው አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የሚያከፋፍሉ ይሆናል።ኢንጂነር ታከለ በከተማዋ በተለያየ አካባቢ ለሚገኙ ወጣቶች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ወጣቶቹ ለከተማ አስተዳደሩ ጥሪ የሰጡትን ፈጣን ምላሽም አድንቀዋል።በየአካባቢዎቹ የሚገኙ አቅመ ደካማዎችን በመደገፍ ወጣቶቹ እያሳዩ ያሉት ተነሳሽነት አርአያ የሚሆን ነው ብለዋል።

Via Mayor office
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች የስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ማስተካከያ ተደረገበት!

በኮሮና ቫይረስ መከላከል ብሔራዊ ግብረ-ሃይል ውሳኔ መሰረት የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች የስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት መሻሻሉን የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በዛብህ ገብረየስ ለኢዜአ እንዳሉት በኮሮና ቫይረስ መከላከል ብሔራዊ ግብረ-ሃይል ውሳኔ መሰረት የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች የስራ መግቢያ ሰዓት ጠዋት 1 ሰዓት ከ30 የስራ መውጫ ሰዓት ደግሞ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 እንዲሆን ተወስኗል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ለፋሲካ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 10፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለፋሲካ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልካም ምኞት መልዕክታቸው “ትንሳኤን ስናስብ ምን ጊዜም በህሊናችን የሚመጣ አንድ ነገር አለ፤ ከህማማት በኋላ ደስታ ከሞት በኋላ ትንሳኤ፤ ከጨለማ በኋላ ብርሃን እንደሚመጣ እናውቃለን” ብለዋል።

ይህ ያለንበት ወቅት የተለየ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ፥ ኮሮና ቫይረስ ዓለምን ያለጦር መሳሪያ እንደወረረ እና ሀያላንን ለማንቀጥቀጥ ጊዜ እንዳልፈጀበት ነው ያነሱት።

ይህ ቫይረስ በሀገሪቱ ብዙዎችን መያዙን፣ የሰው ህይወት መቅጠፉን እና በኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ሃይማኖታዊ ህይወታችን ላይ ተፅእኖ ማሳደሩን፤ የወረርሽኙ ወደፊት ምን ዓይነት ፈተና እና ችግር ይከተለን በሚል ስጋት የምናስታግደው የስነ ልቦና ተፅእኖም ቀላል አለመሆኑን ተናግረዋል።

“ከገጠመን የበለጠ ፈተና እንዳይገጥመን እንደ መንግስትና እንደ ህዝብ እስከምን ድረስ ራሳችንን ማዘጋጀት እንዳለብን ሁላችንም እንደ አንድ ልብ መክረን እና እጅ ለእጅ ተያይዘን ለተግባራዊነቱ መትጋት ይገባናል” ብለዋል።

ቫይረሱ ለሚያስከትለው ሀገራዊ ፈተናና ችግር በሚገባ ከተዘጋጀን ያለከባድ ችግር ልንወጣው እንችላለንም ነው ያሉት፥ ፈተናውን የምናልፈው በዝግጅታችን መጠንና ለተግባራዊነቱ ባለን ፅናት ልክ መሆኑን በመጠቆም።

ያለጥርጥር ይህ የወረርሽኝ ጊዜ ያልፋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ማድረግ የሚገባውን ነገር ሁሉ ካደረግን የፈተናውን ጊዜ እናሳጥራለን ብለዋል።

“ከላይ እስከታች በተሰማራንበት መስክ፣ በተሰጠን ሀላፊነት እና ባገኘነው እውቀት የሚገባንን ከሰራን የችግሩ ጊዜ የከፋ ጉዳት ሳያመጣ በአጭሩ ያልፋል፤ የኢትዮጵያ የትንሳኤ ዘመንም ይረዝማል” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ለህክምና ባለሙያዎች ጥበብን፣ ግንባር ቀደም ሆነው ለተሰለፉ ጀግኖች ሀይልና ብርታትን፣ ትግሉን እያገዙ ላሉ ደጋግ ልቦች በረከትን፣ በቫይረሱ ለተያዙት መዳንን፣ በወረርሽኝ ምክንያት ለተጎዱ ፅናትን እና ለህዝቡ ደግሞ መታዘዝን ተመኝተዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
ሲ.አር.ሲ የተባለ የቻይና አለም አቀፍ የሥራ ተቋራጭ 15ሺ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ለትራንስፖርት ዘርፍ ድጋፍ አደረገ፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ሰለ ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች ተጨማሪ ማብራሪያ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም በወጣው የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃጸም መመሪያ መሰረት የቤት ተሽከርካሪዎች (ኮድ-2) ፈረቃ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ መተግበር ይጀምራል።

በዚህም መሰረት የሰሌዳ ቁጥራቸው መጨረሻ ጎዶሎ የሆነ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ የሚችሉት ሰኞ፣ ረቡዕ እና አርብ ሲሆን ፥ የሰሌዳቸው የመጨረሻ ቁጥር ሙሉ ወይም ዜሮ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ደግሞ መንቀሳቀስ የሚችሉት ማክሰኞ፣ ሀሙስ እና ቅዳሜ ብቻ ነው።

እሁድ እለት ደግሞ ሁሉም ተሸከርካሪዎች መንቀሳቀስ ተፈቅዶላቸዋል።

አንዳንድ ግለሰቦች ከስራቸዉ ፀባይ አንፃር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ፣ በደንቡ ወይም በአፈፃፀም መመሪያዉ የተገለፁት ጉዳዮች ላይ በቀጥታ የሚሳተፋ ሰዎች ከባለስልጣኑ በሚሰጣቸዉ ልዩ የይለፍ ፈቃድ ብቻ እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል።

Via:- ትራንስፖርት ሚኒስቴር
@Yenetube @Fikerassefa
በዩናይትድ ስቴትስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 710,331 ደርሷል። ትናንት ብቻ 30,579 ሰዎች የተያዙ ሲሆን 2,618 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። እስከዛሬ የሞቱትም ቁጥር 37,150 ሲሆን 42,154ቱ አገግመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት ድጋፍ ለሚሹ ለ949 የኅብረተሰብ ክፍሎች የትንሳኤ በዓል መዋያ ድጋፍ አበረከተ።

ሚያዝያ 10/2012 ዓ.ም በዛሬው ቀን የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከኒቲባ አቶ ሰብስቤ ቡናቤና የከተማው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሻምበል ሸዋ በከተማው በሚገኙ በቀድሞው 11ዱም ቄበሌያት በመዘዋወር ድጋፍ ለሚሹ ለ949 የኅብረተሰብ ክፍሎች የትንሳኤ በዓል መዋያ የፉርኖ ዱቄት፣የሳሙናና ፓስታ ድጋፍ አበረከቱ።የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እና መቆጣጠር በተቋቋመው የሃብት አሰባሰብ ግብረ ኃይል ከተሰበሰበው የተወሰደ 237 ኩንታል ፉርኖ ዱቄት ፣ 95 ካርቶን ፓስታና 950 ሳሙና ድጋፍ ለሚሹ ለ949 የማኅበረሰብ ክፍሎች ለትንሳኤ በዓል መዋያ የሚሆን ለእያንዳንዳቸው 25 ኪሎ ፉርኖ ዱቄት፤2 ፓስታና፣ ሳሙና ድጋፍ አድርገዋል።

Via Arbaminch city Admin
@YeneTube @FikerAssefa
የማላዊ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሀገሪቱ መንግስት ያወጀውን የ21 ቀን የእንቅስቃሴ ገደብ ውድቅ አርጓል።

Via CGTN
@YeneTube @FikerAssefa
#105
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 105 ደረሰ!

ባለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ ከተደረገላቸው 659 ሰዎች መካከል 9 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ገለጸ። በዚህም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 105 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የታማሚዎቹ ሁኔታ:

8 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 1 የኢኳቶሪያል ጊኒ ዜግነት ያለው ነው።

➡️ የጅማ ነዋሪ፣ የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ በፊት ከሊባኖስ የመጣች፣ ዕድሜ 20

➡️ሁለት ሴትና(ዕድሜ 40ና 42) አንድ ወንድ(ዕድሜ 13) የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ በበሽታው ከትተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው።

➡️ከአሜሪካ የመጡና በለይቶ ማቆያ የቆዩ፣ ዕድሜ 73፣ ፆታ ወንድ

➡️ከጅቡቲ የመጡና በለይቶ ማቆያ ያሉ 3 የድሬዳዋ ነዋሪዎች፣ እድሜ 19፣ 20ና 19፣ ሶስቱም ወንዶች ናቸው ።

➡️የ38 አመት ኢኳቶሪያል ጊኒያዊ ከእንግሊዝ የመጣና በለይቶ ማቆያ ያለ

@YeneTube @FikerAssefa
ሚሊኒዬም አዳራሽ ለኮሮና ቫይረስ ህክምና ስፍራ ለማድረግ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ይገኛሉ።የማዘጋጀቱ ስራ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እየተከናወነ ሲሆን፣ 1000 አልጋዎችን እንዲይዝ ተደርጎ እየተዘጋጀ ይገኛል፣ ስራው በያዝነው የፈረኝጆች ወር መጨረሻ ተጠናቆ አገልግሎት ይጀምራል።

@YeneTube @FikerAssefa
አንድ ተጨማሪ ሰው አገግሟል እንዲሁም የኢትዮጵያ ኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ

- ዛሬ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች :- 9

- በለይቶ ማቆያ ህክምና ያሉ ታማሚዎች :- 85

- ፅኑ ህሙማን :- 1

- ከበሽታው ያገገሙ :- 16

- በሽታው ህይወታቸውን ያለፈ ድምር :- 3


@Yenetube @Fikerassefa
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የለይቶ ማቆያን ካምፓስ ጎበኙ!

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከተለየዩ አገሮች ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ሰዎች የለይቶ ማቆያ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ካምፓስን ጎበኙ።ካምፓሱ በዋናነት ከውጭ አገሮች መጥተው ለአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ በተዘጋጁ ሆቴሎች ለመቆየት አቅም ለሌላቸው ኢትዮጵያውያን አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ይታወሳል።

የሚኒስትሯ ጉብኝት በዋናነት በካምፓሱ ውስጥ የሚከናወኑ አገልግሎት አሰጣጦች ምን እንደሚመስሉ ለመገምገም መሆኑ ነው የተገለጸው። በጉብኝታቸውም ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና በጉዳዩ ከሚሰሩ ሌሎች አካላት ጋር ተወያይተዋል።አሁን ላይ በካምፓሱ ከተለያዩ አገሮች የመጡ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 321 ሰዎች ያሉ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 49ኙ ሴቶች ናቸው።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
ደብረብርሃን የቀንድ ከብት ገበያ !

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ እየተደረገ አለመሆኑ እንዲሁም ስለ ኮሮናም ግድ የለቸው በከፍተኛ ጥግግት ግብይት እየተደረገ ይገኛል።

@Yenetube @FikerAssefa
አዲስ አበባ አያት አከባቢ ገበያው ደርቷል 😢 አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በትክክል ተግባራዊ እየተደረገ አለመሆኑ ተመልክተናል።
ሀዋሳ በተለምዶ አላሙራ ተብሎ የሚጠራ ቦታ የዶሮ ገበያ ⬆️

- መ ራ ራ ቅ ለራስ ጤንነት ነው።
@Yenetube @Fikerassefa
ራይድ 50,000 የሰርጂካል ጭንብሎችን ለኢትዮጵያ ህክምና ማህበር አስረክቧል 

የኮሮናቫረይስ ህክምና ለማገዝ በማሰብ የራይድ ትራንስፖርት ቴክኖሎጂ ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት ሳምራዊት ፍቅሩ ለኢትዮጵያ ሀኪሞች ማህበር 50,000 የሰርጂካል ጨንብሎችን ዛሬ አስረክባለች።
የሰርጂካል ጭንብሎቹ ዋጋ 1.4 ሚልየን ብር ይገመታል ።

የማህበሩ የቦርድ አባል የሆነችው ዶ/ር መስከረም አለቃ በርክክቡ ወቅት አንዳለችው ” የዚህ አይነቱ ድጋፍ የህክምና ባለሙያዎች የህክምና ስራቸውን በጥንቀቄ አንዲሰሩ እና ለበሽታው አንዳይጋለጡ ያግዛል።የጤና ባለሙያዎች ከሚቸገሩበት አንዱ የሰርጂካል ጭንብሎ ማግኘት ነው ይሄን ተረድተው ሌሎችም ድርጅቶችም ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅበቸዋል “ብላለች ።

ወይዘሮት ሳምራዊት ፍቅሩ በበኩሏ “ህይወታቸውንና ጊዜያቸውን አየሰው የእኛን ህይወት ለማትረፍ ቀድመው ለሚረዱን ሀኪሞች የዚህ አይነት ድጋፍ ማድረግ ሞራላዊ ግዴታ አለብን ራይድም የዚህ አይነቱን ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል” ብላለች።

Via:- fidelpost.com
@Yenetube @Fikerassefa