YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በሩስያ በ24 ሰዓት ውስጥ 2,186 ኮቪድ19 ኬዝ እና 24 ሞት ተመዝግቧል።

በሩስያ በአጠቃላይ 15,770 ኮቪዲ19 ኬዝ እስከዛሬ 130 ሰዎች ሞተውባታል።

@Yenetube @Fikerassefa
የትንሣኤን በዓል በጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠር ዛሬ ለሚያከብሩ ሰዎች ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በመላው ዓለም እንዲሁም በኢትዮጵያ ለምትገኙና የትንሣኤን በዓል በጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠር ዛሬ የምታከብሩ ክርስቲያኖች ሁሉ መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ ብለዋል።

"በኮቪድ19 ወረርሽኝ የተነሣ በአካል መራራቅ ቢያጋጥምም፣ በመንፈስ አንድ ሆናችሁ ይህን በዓል ስታከብሩ፣ ብርታት እና መጽናናት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ" ሲሉ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልእክታቸውን ያስተላለፉት።

Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ የአፍሪካ መረጃ!

➡️52 የእፍሪካ ህብረት አባላገራት ቫይረሱን ሪፖርት አድርገዋል።

➡️13,686 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

➡️744 ሰዎች ተይዘው ሞተዋል።

➡️2283 ሰዎች አገግመዋል።

ምንጭ:CDC Africa
@YeneTube @FikerAssefa
የቀብሪ ደሃር የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተመረቀ!

በቀብሪ ደሃር የተገነባው የባለ 132/33 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በይፋ ተመርቆ ስራ ጀመረ።የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያውን የመረቁት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ናቸው።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋገጠ!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 286 ግለሰቦች መካከል ሁለቱ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 71 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
የታማሚዎቹ ሁኔታ:-

- የመጀመሪያዋ የ24 ዓመት እድሜ ያላትና ከአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውሳኔ በፊት ከዱባይ የተመለሰች መሆኗን መግለጫው አመላክቷል።

- ሁለተኛዋም ግለሰብ የ35 ዓመት እድሜ ያላትና ከቱርክ ወደ ኢትዮጵያ መጥታ በተመሳሳይ ሁኔታ በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ክትትል ስታደርግ የነበረች ናት።

@Yenetube @Fikerassefa
ዶ/ር ሊያ ታደሰ :-

- በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የተመረመሩ ሰዎች 3863 ሰዎች መሆናቸው መግለጫው ያመለክታል።

- በ24 ሰዐት ውስጥ 286 ሰዎች ተመርምረዋል ከዛም ውስጥ 2 ሰው በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጠዋል።

- በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው 56 ሰዎች ህክምና እየተደረገላቸው።

- በኮቪድ-19 ሶስት ሰዎች ሞተዋል

- ሁለት ሰዎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል

- አስር ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል

@Yenetube @Fikerassefa
ኬንያ ውስጥ ዛሬ ስድስት አዲስ ተጠቂና አንድ ሞት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተመዝግቧል። ይህንንም ተከትሎ የሟቾች ቁጥር ስምንት ሲድርስ የተጠቂዎች ቁጥር ደግሞ መቶ ዘጠና ሰባት ነው፣ ያገገሙት ደግሞ ሃያ አምስት ናቸው።

ምንጭ:MoHK
@YeneTube @FikerAssefa
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ዙሪያ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እየሰጡት ያለውን ማብራሪያ በቀጥታ ዶ/ር ሊያ ታደሰ Facebook አካውንት በመግባት ያገኛሉ።

Link ⬇️
https://www.facebook.com/liatadsmoh/

@YeneTube @Fikerassefa
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ከኮሮና አገግመው ከሆስፒታል ወጡ

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከኮሮና ቫይረስ ህመም አገግመው ከሆስፒታል ወጡ።

የ55 ዓመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በወረርሽኙ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ ለንደን በሚገኝ ሆስፒታል ለ10 ቀናት ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተዋል።

በሆስፒታሉ ለ3 ቀናት በፅኑ ህሙማን ክፍል የቆዩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሆስፒታል ቢወጡም ከከተማ ወጣ ብለው እንደሚያገግሙ የዘገበው ቢቢሲ ነው።

Via:- BBC /EBC
@Yenetube @Fikerassefa
ለሕክምና ባለሙያዎች የሕይወት መድህን ዋስትና ሊገባላቸው እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ!

በኢትዮጵያ የኮሮና ህሙማንን በቅርብ ለሚከታተሉ የሕክምና ባለሙያዎች የሕይወት መድህን ዋስትና ሊገባላቸው እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ዛሬ በፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት ባደረጉት ውይይት በተለይ የኮሮና ህሙማንን በቅርበት ለሚከታተሉ የሕክምና ባለሙያዎች የሕይወት መድህን ዋስትና ለመግባት እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልፀዋል።የሕክምና ባለሙያዎች ደህንነታቸው ተጠብቆ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል የመኖሪያ ቤት፣ ስልጠና እና የመከላከያ አልባሳትን በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑንም ነው ሚንስትሯ የገለፁት።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ:-⬆️⬆️

"ህግና ሰላም በማሰከበር ሂደት አጉል ህዘበኝነትን ለማትረፍ በሚንቀሳቀሱና መሃል ሰፋሪ በሆኑ አንዳንድ የፖለቲካ እና የጸጥታ ሀይል አመራሮች ላይ መንግሰት እርምጃ እንደሚወስድ እንገልጻለን፡፡"

Via ELU
@YeneTube @FikerAssefa
የአለም የጤና ድርጅት በደቡብ ሱዳን ደቡባዊ ክፍል የብጫ ወባ መከሰቱን ይፋ አድርጓል።

ምንጭ: CGTN
@YeneTube @FikerAssefa
ለምስራቁ አገሪቱ ክፍል ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በሁለት ሰዓት ልዩነት 384 ናሙና መመርመር የሚችል ላብራቶሪ ማዕከል ተመረቀ።

በሀረማያ ዩኒቨርስቲ ሀረር ካምፓስ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሣሪያው በተለይ በሀረሪ ክልል እና በአካባቢው በቫይረሱ የተጠረጠሩ ሰዎችን በመመርመር በውጤቱበመመስረት አፋጣኝ ላይም በአፋጣኝ የመከላከል እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል እንደሆነ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናግረዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ጀማል ዩስፍ ላብራቶሪው አገልግሎት መስጠት በጀመረበት ወቅት እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ቫይሱን ለመከላከል በአካባቢው ለሚገኙ ማህበረሰብና ተቋማት በግንዛቤ የማስጨበጥ፣ የድጋፍ እና የቴክኖሎጂ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

Via Harari Communication
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል የትራንስፖርት እገዳው ማሻሻያ ተደረገበት!

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በደቡብ ክልል በህዝብ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው ክልከላ ማሻሻያ እንደተደረገበት የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አስታወቀ።በዚህም መሰረት ከየትኛውም አካባቢ ወደ ክልል የሚንቀሳቀስ ሀገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከመጫን አቅሙ ግማሹን በመቀነስ መንቀሳቀስ እንደሚችል ገልጸዋል። እንዲሁም የከተማ አውቶብስ፣ የግል ተሸከርካሪዎች፣ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተሸከርካሪዎችም እንዲሁ ከዚህ በፊት ከሚይዙት ተሳፋሪ በግማሽ ቀንሰው እንዲጭኑ ተወስኗል ነው ያሉት።

“የባለ 2 እግር ሞተር ሳይክል፣ ባለሶስት እግር ባጃጆችና የከተማ ታክሲ አገልግሎት ቀደም ሲል በክልሉ በግብረ-ሀይሉ የተላለፈው ውስኔ እንደተጠበቀ ሆኖ የሚሰሩ ይሆናል” ብለዋል።መናኸሪያዎችም ተከፍተው ስራ የሚጀምሩት ለተሳፋሪው የእጅ መታጠቢያ ስፍራና አስፈላጊ ቁሳቁስ መሟላታቸው ሲረጋገጥ እንደሆነ ተናግረዋል።በተጨማሪም መንገደኞች ወደ መናኸሪያ ሲገቡና ሲወጡ የሙቀት ልኬት ማከናወን የሚያስችል ልኬታቸው አጠራጣሪ ሲሆን ለይቶ ለማቆያ ስፍራዎች መዘጋጀት እንዳለባቸው ተገልጿል።

ምንጭ: ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
በሶማልያ ሁለተኛ ሞት ተመዝግቧል።

ሟቹም የhirshabella ስቴት የፍትህ ሚንስትር መሆናቸውን ከቪኦኤ ተመልክተናል።

@Yenetube @Fikerassefa