YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
YeneTube
የኢትዮጵያ አየር መንገድ መደበኛ ሰራተኞቼን እየቀነስኩ እንዳለው በየሚዲያው የሚወራው ሀሰት ነው ብሏል ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ። መግለጫው ግን በዋነኝነት ቅሬታውን ስላቀረቡት በኮንትራት ይሰሩ ስለነበሩ ሰራተኞች የሚለው ነገር የለም። @YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየርመንገድ መሰረታዊ ሰራተኞች ማህበር ለአየር መንገድ ላወጣው የሰጠው ምላሽ ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰአታት በፊት ባወጣው መግለጫ መደበኛ ሰራተኞቹን እንደቀነሰ በየሚዲያው የሚወራው ሀሰት ነው ብሏል። መግለጫው ግን በዋነኝነት ቅሬታውን ስላቀረቡት በኮንትራት ስለሚሰሩ ሰራተኞች እና በህገወጥ መንገድ የስራ ውሉ ስለተቋረጠው ስለ ማህበራችን ሊቀመንበር ካፒቴን የሺዋስ ፈንታሁን የሚለው ነገር የለም።

ይሕ መግለጫ ፤ በተደጋጋሚ ማህበራችን እያሰማ ካለው የ ኮንትራት ሰራተኞች (የበረራ አስተናጋጆች፣ የትኬቲንግ ሰራተኞች፣ ቴክኒሽያኖች እንዲሁም ሌሎች) ያለ ደሞዝ እረፍት እንዲወጡ መደረግ ጉዳይ ጋር ግንኙነት የሌለው ፣ ቋሚ ሰራተኞችን ብቻ ማእከል ያደረገ ህዝብ እና መንግስት ላይ ብዥታ የሚፈጥር ሆኖ አግኝተነዋል!

ስለዚህ የማህበራችን አባላት ፣ ሰራተኞች፣ የኢትዮጲያ ሕዝብ እና መንግስት ማህበራችን በአሁኑ ወቅት በዋናነት እያነሳ ያለው ጉዳይ የኮንትራት ሰራተኞች ያለ ክፍያ እረፍት እንዲወጡ መደረጉ ጋር የተያያዘ ምንም አይነት ነገር አለመጠቀሱን ልብ እንድትሉልን እንወዳለን!

#ፍትህ_ለሰራተኞች!!
#ፍትህ_ለማህበራችን_ሊቀመንበር_ካፒቴን_የሺዋስ!

Via:- Tsefay Getent
@Yenetube @Fikerassefa