YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ዱከም

ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በምትገኘው የዱከም ከተማ በኮሮና የተያዙ ኢትዮጵያዊት ተገኙ።

የ65 አመቷ የዱከም ነዋሪ ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ ወጥተው እንደማያውቁ የጤና ምኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ይፋ ያደረጉት መረጃ ይጠቁማል።

በመግለጫው መሠረት በኢትዮጵያ በኮሮና የተያዙ 44ኛ ሰው የሆኑት የዱከም ነዋሪ ተሕዋሲው ካለበት ሰው መገናኘታቸው አልተረጋገጠም።

የዶክተር ሊያ መግለጫ «ታማሚዋ በሌላ ተጓዳኝ በሽታ ምክንያት ሆስፒታል ገብተው የነበረ ሲሆን በተጨማሪም የኮሮና ቫይረስ በሽታ በማሳየታቸው በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል» ብሏል።

በኢትዮጵያ በኮሮና ከተያዙ ሰዎች ሁለቱ በትናንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ሌሎች ሁለት ሰዎች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። አራት ደግሞ አገግመዋል። በአሁን ወቅት 36 ሕሙማን በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ይጠቁማል።
እስካሁን የጤና ሚኒስቴር ባረጋገጠው መረጃ መሠረት የኮሮና ወረርሽኝ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ተገኝቷል። አዳማ፣ ድሬዳዋ፣ ባሕር ዳር እና አዲስ ቅዳም የተባሉ ከተሞች በኮሮና የተያዙ ሰዎች የተኙባቸው ከተሞች ናቸው።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa