YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በኢራን በኮሮና ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል

የኢራን መንግስት ዜጎች የሚሰጣቸውን የጤና ምክር ካልሰሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ዜጎች ሊሞቱ ይችላሉ አለ፡፡

ኢራን ከቻይናና ጣልያን ቀጥሎ በቫይረሱ ክፉኛ የተጠቃች ሀገር ስትሆን ቫይረሱ አሁን 147 ሰዎች ህይወትን የቀጠፈ ሲሆን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 1135 ደርሷል፡፡

በኢራን በቫይረሱ የተያዙ ቁጥር ደግሞ 17 ሺ መድረሱን ነው የህክምና ባለስልጣናት የሚናገሩት፡፡

የጤና ባለሙያዎች እንደሚሉት በእድሜ የገፋና የቆየ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች በሽታውን የመቋቋም አቅማቸውም ደካማ መሆኑ ይገለፃሉ፡፡

ይህንን ተከትሎ በቫይረሱ ሳቢያ አንድ የእምነት ስፍራ በመንግስት እንዲዘጋ ተደርጓል።

ምንጭ:- ኢቢኤስ አዲስ ነገር
@Yenetube @Fikerassefa