YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጂንካ ከተማ ገቡ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት ለስራ ጉብኝት ደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ገብተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጂንካ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የደቡብ ክልል እና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የአገር ሽማግሌዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጂንካ ከተማ ስታዲየም ለህዝቡ ንግግር እንደሚያደርጉ እና ከደቡብ ኦሞ ዞን ብሔረሰቦች ተወካዮች ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በጂንካ ተገኝተዋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የሸገር ዳቦ ፋብሪካ የግንባታ ስራው ተጠናቆ የማሽን ተከላ እየተከናወነ ነው።

ኢ/ር ታከለ ኡማ ፋብሪካው ያለበት ደረጃን ተመልክተዋል።ከወራት በፊት ግንባታው የተጀመረው የሸገር ዳቦ ፋብሪካ የሲቪል ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም የማሽን ተከላው እየተከናወነ ይገኛል።ኢ/ር ታከለ ኡማ የፋብሪካው ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል።የማምረቻ ማሽን ተከላው በውጪ ባለሙያዎች እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን ማሽኑ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ያማሏ ዘመናዊ ማሽን ነው።

ፋብሪካው የሚያስፈልገውን ሀይል ማቅረብ የሚችል ትራንስፎርመር በግዢ ሂደት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከቀናት በኋላ ይጠናቀቃል።ከዳቦ ፋብሪካው ግንባታ ጎን ለጎንም የዱቄት ፋብሪካ ግንባታ ተጠናቆ የማሽን ተከላ ላይ ይገኛል።
ዳቦ ፋብሪካው ከቅርብ ጊዜ በኋላ ስራውን የሚጀምር ሲሆን ምርቱን በየክፍለ—ከተማዎች የሚያሰራጩ ተሽከርካሪዎችም ተዘጋጅተዋል።የዳቦ ምርቱን ለተጠቃሚዎች ለማድረስ ወጣቶች የተደራጁ ሲሆን ለመሸጫ የሚሆኑ አራት መቶ ከአገልግሎት ውጪ የነበሩ አንበሳ የከተማ አውቶብሶች ዝግጁ ተደርገዋል።

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
እንኳን ለማርች 8 የሴቶች ቀን በዓል አደረሳችሁ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የምክክር መድረክ የህዳሴ ግድብ በተመለከተ ወቅታዊ የአቋም መግለጫ

እኛ የመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕሬዜዳንቶች እና ምክትል ፕሬዜዳንቶች በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ኢፍትሃዊ የሆነ ውሳኔ ለመወሰንና ለማስወሰን እንዳንድ ሀገራት የተዛባ ውሳኔ እንዲሰጥ ጫና ለመፍጠር እየጣሩ ይገኛሉ፡
በአንድ ወቅት ተመሳሳይ የተዛባ ውሳኔ በ League of Nations ሲተላለፍ በ1949 የወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር የነበሩት የሚከተለውን ብለው ነበር፡፡

‹‹ሀገሬ ኢትዮጵያ በአለም ሸንጎ ላይ ፍርድ ተነፍጓት ስታዝን የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም፡፡ ለነፃነቷና ለመብቷ ከኮሎኒያልስት ጣሊያን ጋር በየጊዜው ስትዋጋ ያሸነፈችውም ብቻዋን ነው፡፡ የተጠቃችውም ብቻዋን ስለሆነ ሀገሬ መቼውንም በሚደርስባት አደጋ ከማንም እርዳታ አገኛለሁ ብላ አትጠብቅም፡፡››
ዛሬም ሆነ ነገ ነፃነቷን ለመጠበቅ ታሪኳን ለማስከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ አለባት፡፡

እሷ እራሷ ብቻ ናት! እንዳሉት ሁሉ አሁንም ያለን ትውልዶች የተዛባውን ሚዛን ማስተካከል ያለብን እኛው ነን እና የአድዋውን ድል በተባበረው በአያቶቻችን ክንድ እዳሸነፍነው ሁሉ የህዳሴውንም ግድብ በተባበረው አንድነታችን፣ ክንዳችን እና ሀብታችን ሰርተን የምንጨርሰው መሆናችን እያረጋገጥን አቋማችንን በጋራ ስንገልፅ መነሻ ያደረግነው

1. የግድቡ መገንባት በአገሪቱ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ላይ ልዩነት እንደሌለው፣

2. ኮሎኒያሊስቶች አፍረካን እና ሀብቷን ለመቀራመት አውጥተውት የነበረና አሁን የሚያፍሩበት የ1029 እና የ1929 ዓ/ም ኢትዮጵያ ባልተወከለችበት የሕግ ተገዥ የምትሆንበት ሕጋዊም ሆነ አመክኒያዊ ነገር የሌለ መሆኑን፣

3. የሀገራችን ምሁራን በሰሯቸው ጥናቶች ግድቡ የሚገነባው ለመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭ ባልሆነ ቦታ ከመሆኑ በተጨማሪ ውኃው ግብፅ ወይም ሱዳን ላይ ቢከማች ኖሮ በትንነት የሚባክነውን ውኃ ስለሚያስቀር ተመራጭ የሚያደርገው መሆኑን ነው፡፡
ከዚህ በላይ በቀረበው መነሻነትም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ባለ ስድስት ነጠብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡

1ኛ/ የጀመርነው እውን ለማድረግ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደምናደርግ እናረጋግጣለን፡፡

2ኛ/ የህዳሴው ግድብ የአንድነታችን ተምሣሌት በመሆኑ በዘር፣ በኃይማኖትና በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳይኖር የመንግስትን አቋም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲደግፍ እንጠይቃለን፡፡

3ኛ/ እኛ ጠግበን በብርሃን እየኖርን እናንተ በረሃብና በጨለማ ኑሮ ከሚል እና እራስ ወዳድ አስተሳሰብን በፅኑ እናወግዛለን፡፡

4ኛ/ እኛ የኢትዮጵያ የመንግስ ዩኒቨርስቲ አመራሮች በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን የየድርሻቸውን እንዲወጡና ዲፕሎማሲያዊ ጫና እንደያሳድሩ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

5ኛ/ የአረብ ሊግ በኢትዮጵያ ህዳሴ ላይ ሰሞኑን የወሰደውን ኢ-ፍትሐዊ ውሣኔ እየተቃወምን የአፍሪካ ህብረት እንዲህ ዓይነት ጣልቃ ገብነትን እንዲቃወምና መርህን እና ሕግን መሠረት በማድረግ ከኢትዮጵያ ጐን እንዲቆም እንጠይቃለን፡፡

6ኛ/ የአሜሪካ መንግስት በታዛቢነት ገብቶ ሀብት እና የዲፕሎማሲያዊ ኃይሉን በመጠቀም ወደ አደራዳሪነት እራሱን ከማሸጋገር በላይ የወሣኝነት ሚና ያለው የሚመስል መግለጫ ማውጣቱን አጥብቀን እንቃወማለን፡፡

የካቲት 28 /2012 ዓ/ም
ካፒታል ሆቴል
አዲስ አበባ

ምንጭ: አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ
@YeneTube @FikerAssefa
እነ አቶ በረከት ስምዖን የተፋጠነ ፍትሕ ጠየቁ!

ለገጠማቸው የጤና ችግር በአካባቢው ሕክምና ማግኘት እንደማይችሉ ተናግረዋል።ከጥረት ኮርፖሬት ድርጅቶች ጋር በተያያዘ በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙ እነ አቶ በረከት ስምዖን፣ ‹‹በሕመም እየተሰቃየን ስለሆነ የተፋጠነ ፍትሕ ይሰጠን፤›› ሲሉ ለፍርድ ቤት አመለከቱ፡፡አቶ በረከት ስምዖን፣ አቶ ታደሰ ካሳና አቶ ዳንኤል ግዛው ሐሙስ የካቲት 26 ቀን 2012 ዓ.ም. በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርበው፣  የተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ተመርምሮ አፋጣኝ ፍትሕ ማግኘት ሲገባቸው መዘግየቱን ተናግረዋል፡፡

አቶ በረከት ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዱት፣ ቀደም ብሎ የጀመራቸው የጤና መታወክ እየተባባሰባቸው ነው፡፡ ባህር ዳር ውስጥ ያሉ የሕክምና ማዕከላት የተወሰዱ ቢሆንም፣ ተገቢ የሆነ ሕክምና ማግኘት ባለመቻላቸው ሕመማቸው እየተባባሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ተከሳሾቹ የመከላከያ ምስክሮቻችን አሰምተው እንደ ጨረሱ የክርክር ማቆሚያ ንግግር ማድረግ ሲገባቸው፣ ራሳቸው በጠየቁት ተጨማሪ የማብራሪያ ሰነድ ላይ አስተያየት እሰጣለሁ በሚል ዓቃቤ ሕግ ለሚያቀርበው ጥያቄ ሊፈቀድለት እንደማይገባ አስረድተዋል፡፡

አቶ ታደሰ ካሳም ለፍርድ ቤቱ የክስ ሒደቱ ሆን ተብሎ እንዲዘገይ እየተደረገ መሆኑን በመግለጽ፣ በአጭር ቀጠሮ ውሳኔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ ያላግባብ የሆነ ተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ እየተሰጠ እየተጉላሉ እንደሆነም አክለዋል፡፡ተከሳሾቹ ለፍርድ ቤት አቤቱታቸውን ያቀረቡት የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰምተው ከጨረሱ በኋላ፣ አስፈላጊ የሆኑና በዳሸን ቢራ አክሲዮን ማኅበር ውስጥ የሚገኙ የሰነድ ማስረጃዎች በትዕዛዝ እንዲቀርቡላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ፍርድ ቤቱ የተቀበለው ቢሆንም፣ ዓቃቤ ሕግ ግን በሰነዶቹ ላይ አስተያየት ለመስጠት ጊዜ እየወሰደ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የግራ ቀኙን አቤቱታ የሰማው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰጠው ምላሽ፣ እንኳን የጤና ችግር ያለባቸውን ተከሳሾች ቀርቶ ለሌሎች ተከሳሾችም ቢሆን ሕገ መንግሥቱን መሠረት ያደረገ የተፋጠነ ፍትሕ የማግኘት መብት እንዳላቸው ገልጿል፡፡ከጉዳዩ ውስብስብነት አንፃር አጫጭር ቀጠሮዎችን በመስጠት ማስረጃዎችን በማሰባሰብና በመመርመር አፋጣኝ መፍትሔ ለመስጠት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አክሏል፡፡ ምንም እንኳን ፍርድ ቤቱ ብዙ መዝገቦች ቢኖሩትም ጎን ለጎን በማየት በተፋጠነ ጊዜ ውሳኔ ለመስጠት እንደሚሠራ ገልጿል፡፡ ተከሳሾች ከምርመራ መዝገቡ ጋር ባያያዙት ማስረጃ ላይ ዓቃቤ ሕግ መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. መልስ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡    

ምንጭ: ሪፖርተር
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በቡልቡላ ማሰልጠኛ ማዕከል ለ30ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ልዩ የፖሊስ ኃይል አባላትን ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ "በዚህ ሀገር ውስጥ ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በእኩልነት፣ በነፃነት እና በሰላም ከወንድም የኦሮሞ ሕዝብ ጋር እንዲኖሩ ለማድረግ ሁላችንም ከፍተኛ ኃላፊነት አለብን፤ በተለይ ደግሞ እናንተ ልዩ ኃላፊነት አለባችሁ" ሲሉ ለተመራቂዎቹ መልእክት አስተላልፈዋል።

ተመራቂ ፖሊሶቹ ኃላፊነታችውን ሕግ እና ሥርዓትን እንዲሁም የሕዝብ ፍላጎትን መሠረት አድርገው ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።የኦሮሚያ ፖሊስ የኦሮሚያን ሰላም ከማስጠበቅ ባሻገር ማንኛውንም በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጣ አደጋን መመከት ይገባዋልም ብለዋል። ኦሮሚያን ለመገንባት እና ኢትዮጵያን ለማሻገር የድርሻቸውን እንዲወጡ ለተመራቂዎቹ ጥሪ አስተላልፈዋል።

Via ETV/OBN
@YeneTube @FikerAssefa
All women functioned flight ceremony in pictures
ዛሬ በአዲስ አበባ የስብሰባ አዳራሽ እናት ፓርቲ ተመስርቷል

በጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡ የእናት ፓርቲ አመሬሮች

የፓርቲው አመራሮች⬇️

-ፕሬዝደንት፡ ዶ/ር ኃ/ኢየሱስ ሙሉቀን

-ም/ፕሬዝደንት፡ ዶ/ር ሠይፈሥላሴ አያሌው

-ጠቅላይ ፀሐፊ፡ አቶ ጌትነት ወርቁ

መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል።
@Yenetube @Fikerassefa
የዓለም የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በካፒቴን አምሳለ ጓሉ አብራሪነት ከአዲስ አበባ የተነሳው አውሮፕላን በዋሺንግተን ዳላስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በደረሰበት ወቅት ሞቅ ያለ አቀባበል ጠብቆታል።

Via VOA
@YeneTube @FikerAssefa
ባይብል ኮድ

ስለ እያንዳንዳችን ዕጣ ፈንታ ጨምሮ በአለም ላይ ያሉ መሪዎች ስለሚገደሉበት ቦታ፣ ስለሚገድሏቸው ሰዎች ስም…

በአለም ላይ ስለተከናወኑ ነገሮችና ወደፊትም ስለሚከናወኑ ነገሮች ሁሉ በስም፣ በቀንና በቦታ ሳይቀር ከዛሬ ሶስት ሺ አመት በፊት…

በየቤታችን በሚገኘው መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ በኮድ ተቀጧል!!

በአንድ ምሽት ሽያጭ ብቻ ሪከርድ የያዙት ባይብል ኮድ ቁጥር 1፣ ቁጥር 2 እና የመጨረሻው ቁጥር 3 ኮዶቹን እየፈቱ ያስደምሙናል፡፡

ሶስቱንም መጽሐፎች በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኟቸዋል፡፡
@teklutilahun
ግራ አጋቢው ዘመን
አዲስ መፅሐፍ በገበያ ላይ

የወባ ትንኞችን ከመግደል ሀሳቦችን ወደ መግደል፤
ከስራ አጥነት ወደ ስራ አልባነት እያመራን ነው… ምን ይሻላል?

ግራ አጋቢው ዘመን መፅሐፍ መፍትሄ አለው፡፡

መፅሐፉ እንዴት ከጀግንነት ወደለየለት ብሔርተኝነት፣
ከኃይማኖተኝነት ደግሞ ወደ ሽብርተኝነት እያመራን እንዳለን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ መጨረሻችንስ?

መልሱ ግራ አጋቢው ዘመን መፅሐፍ ውስጥ ይገኛል፡፡

እንኳን ወደ ግራ አጋቢው ዘመን መፅሐፍ ግራ ተጋብተው መጡ!!

የእውነት ይሄ መፅሐፍ አስተሳሰባችሁን ያሰፋዋል!!

በየመፅሀፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል!!
Forwarded from YeneTube
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEmpJPx72XxnzEFGQg

🔖እናስተዋዉቅዎ! AmAzON BrAnD® ገበያ
ሱቅ ለሱቅ መሄድ ሳይጠበቅቦት ባሉበት ቦታ ሆነው ውስን እቃዎችን በማይታመን ዋጋ ሚገኙበትን ማወቅ ይፈልጋሉ እንግዲያውንስ ይሄን የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ በመጫን የፈለጉትን ይምረጡ ይዘዙ
.
ብራንድ ጫማዎች የወንድም የሴትም
ብራንድ ልብሶች የወንድም የሴትም
ብራንድ ሸሚዞች ቲሸርቶች
ብራንድ ቱታዎች ሹራቦች እንዲሁም ጃኬቶች በወንድም በሴትም
ብራንድ ቦርሳዎች
የእጅ ጌጣጌጦች
ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
ሀገር ውስጥ ውስን የሆኑ መዋብያ እቃዎች ሽቶዎች
.
እንዲሁም በግል የቴሌግራም አካውንት ማዘዝ የምትፈልጉ እቺን ሊንክ በመጫን ያናግሩን @KALID67 እንዲሁም በስልክ ቁጥራችን +251954833467 ደውለው ይዘዙን
.
በተጨማሪም አዲስ አበባ ለምትገኙ ደንበኞቻችን ይዘዙን ያሉበት ድረስ እናመጣለን ክፍለ ሀገር ለምትገኙ ደንበኞቻችን ባዘዙን በ48ሰአት ውስጥ በፖስታ ቤት ወይም በሹፌር እናደርሳለን ታማኝነት መገለጫችን AmAzON BrAnD® ገበያ
online shopping is always a good idea!!
Forwarded from HEY Online Market
Acer predator (i7, 9th gen)
Ram: 16 GB
Hard disk: 1tb+256gb ssd
Graphics: 6 GB NVDIA Graphix 1660ti
Price : 55,500 birr

Acer predator (i7, 8th gen)
Ram: 16 GB
Hard disk: 256gb ssd
Graphics: 6 GB NVDIA Graphix
Price : 47,500 birr

Contact us @heymobile
0953964175
0925927457
0910695100