YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአዲስ አበባ የከባድ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሰዓት ማሻሻያ ተደረገ።

በአዲሱ ማሻሻያም ከባድ ተሽከርካሪዎች ጠዋት ከ1-3 ሰአት እንዲሁም ከሰዓት ከ 10:30-12:00 ውጪ ባሉ ሰዓቶች እንዲንቀሳቀሱ መወሰኑን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።ማሻሻያው የተደረገው የተለያዩ ተቋማት በሰዓት ገደቡ ምክኒያት በተለይም የግንባታ ስራዎቻቸውን ለማከናወን መቸገራቸውን ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።በመሆኑም የትራፊክ እንቅስቃሴውን ጫና ውስጥ በማይከት መልኩ ማሻሻያው ተደርጓል።እስካሁን በነበረው ህግ በከተማዋ የሚገኙ ከባድ ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ብቻ ነበር መንቀሳቀስ የሚፈቀድላቸው።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የቻይናው ፕሬዝደንት ኢትዮጵያን አመሰገኑ!

በቻይና በተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር የነበራትን የቀደመ ግንኙነት በማሰብ፣ በዓለም የጤና ድርጅት ምክር መሠረት ግንኙነቷን ባለማቋረጧ ያለኝን አድናቆት ለመግለፅ እፈልጋለሁ ሲሉ የቻይናው ፕሬዝደንት ዢ ጂንፒንግ ተናገሩ፡፡‹‹የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት የቻልነውን ሁሉ እያደረግን ባለንበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያው ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ሁለት ጊዜ መልዕክት በመላክ እንዲሁም ስልክ በመደወል የአብሮነት ተምሳሌትነታቸውን አሳይተውናል›› ብለዋል።

ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጎናችን መሆን በቻይና እና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን መደጋገፍ እና ትብብር ያሳያል ያሉት ፕሬዝደንት ዢ ጂንፒንግ፣ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር የነበራትን የቀደመ ግንኙነት በዓለም ጤና ድርጅት ምክር መሠረት ባለማቋረጧ ያለኝን አድናቆት ለመግለፅ እፈልጋለሁ ሲሉ አብራርተዋል፡፡ በመጨረሻም፣ የአፍሪካ አገራት እና ህዝቦቻቸው ቻይና በኮሮና ቫይረስ ጋር በምታደርገው ትግል ወንድማዊ ግንኙነታቸው በደስታችንም ሆነ በሀዘናችን ከጎናችን በመሆን አሳይተውናል ብለዋል፡፡

ምንጭ፡- ሺንዋ/ዋልታ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር ወስደው ያልመለሱ እና የጠፉ 71 ባለሃብቶች እና ሰራተኞቹን በሕግ ለመጠየቅ እንዲሁም ያለአግባብ የባከነ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ግንዘብን ለማስመለስ ምርመራ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ።ምርመራው ሲጠናቀቅ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ የባንኩ ፕሬዝዳንት ኃይለየሱስ በቀለ ዛሬ ጠዋት በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል። ከዚህ በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረ ግጭት ከዚኅ ቀደም ከባንኩ ብድር የወሰዱ 38 ፕሮጅክቶች መውደማቸውንም ኃይለየሱስ ተናግረዋል። ምርመራ እየተደረገባቸው ያሉትን ድርጅቶች እና ባላሃበቶች ስም ዝርዝር ከመናገር ግን ተቆጥበዋል።

ምንጭ:አዲሰ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢራኑ ምክትል ፕሬዘዳንት በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ተገለጸ።

ፖፕ ፍራንሲስም በዚሁ ቫይረስ ተጠቅተዋል የሚል ጥርጣሬ ታይቶባቸዋል።

ከሁለት ቀናት በፊት የኢራን ምክትል የጤና ሚኒስትር በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው ወደ ለይቶ ማከሚያ ክፍል መግባታቸው ይታወሳል።

ከደቂቃዎች በፊት ዳይሊ ሜይል ይዞት በወጣው ሰበር ዜናው የኢራን ምክትል ፕሬዘዳንት በዚሁ ቫይረስ ተጠቅተው ሆስፒታል ገብተዋል።

በተጨማሪም የኢራን የቤተሰብ እና የሴቶች ጉዳዮች ምክትል ፕሬዘዳንት በዚሁ ቫይረስ መጠቃታቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ሜትሮ የተሰኘው የእንግሊዙ ተነባቢ ጋዜጣ ደግሞ በጣልያን በሽተኞችን ሲጠይቂ የዋሉት የካቶሊክ ቄሱ ፖፕ ፍራንሲስ ምልክት ታይቶባቸዋል።

ይሁንና ፖፕ ፍራንሲስ የተጠቁት በዚሁ ቫይረስ ይሁን አይሁን እስካሁን በምርመራ አልተረጋገጠም።

በኢራን በዚህ ገዳይ ቫይረስ የተጠቁ ዜጎች ቁጥር ወደ 254 የደረሰ ሲሆን በጣልያን ደግሞ ከ450 በላይ ደርሷል።

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
ህንፃ ተከራይተው ለሚገኙ 77 የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶች ኪራይ በዓመት 1 ቢሊዮን ብር እየተከፈለ መሆኑ ተገለጸ። በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ስር የተደራጀው ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ ተክለፃዲቅ ተክለአረጋይ እስካሁን 30 ለሚሆኑ መስሪያ ቤቶች ቢሮ መገንባቱን ጠቁመዋል። በዚህም በየወሩ መንግሥት በትንሹ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን መቻሉን ገልጸዋል።

ምንጭ:አሐዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ሱዳን መንግሥት በጎረቤት ሀገራት የሚገኙ ስደተኛ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማድረጉን የሀገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ስደተኞች በኢትዮጵያ ጋምቤላ ክልል ተጠልለው ይገኛሉ፡፡ ሀገሪቱ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የሽግግር አንድነት መንግሥት ካቋቋመች ወዲህ ዘላቂ ሰላም አንደሚሰፍን ተስፋ ተደርጓል።

ምንጭ:- ዋዜማ ራዲዮ
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ ቴሌኮም በቀጣዩ ወር ለግል ባለሃብቶች ሊያወጣቸው የነበሩትን ሁለት የቴሌኮም አገልግሎት ፍቃድ ጨረታዎች እንደገና ማራዘሙን ሮይተርስ ዘግቧል። ተጨማሪ ጊዜ የጠየቁት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ኩባንያዎች ናቸው። ለጨረታው በሁለት ሳምንት ውስጥ አዲስ የጊዜ ሰሌዳ ይወጣል።

Via:- Wazema Radio
@YeneTube @Fikerassefa
Forwarded from የሀ Digital Art
Taking place over two days Saturday 7th & Sunday 8th March. https://www.facebook.com/events/848716598903708/

Brought to you in partnership with Noah Real Estate, Rainbow Bed Foam and Beyond, British Council Ethiopia, Eternal Media & Communication, @artsmailinglist @saryanevents, EthioCrypto, @yenetube, @Yegarawebhost @johnnyvideoproduction, @officialkuriftuwaterpark, Bored Cellphone Addis Ababa, @woinidigitalart, @jayineedarts— At Noah Plaza, Addis Ababa, Ethiopia.

@yehadigitalart
የሕዳሴን ግድብ ግንባታና የዉኃ ቀሞላልን በተመለከተ ሱዳን ግብፅና ኢትዮጵያ በሚያካሂዱት ድርድር ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ላይ እያሳረፈች ያለዉን ጫና ታንሳ ሲሉ በዋሽንግተን እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን በአሁኑ ሰአት በዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፊት ለፊት የተቃዉሞ ሰልፍ ወጥተዋል።

ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ጥበቡ አሰፋ ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት የአባይ ጉዳይ የኢትዮጵያዉያን ሁሉ ህልዉና ነዉ። በዩናይትድ ስቴትስ የምንገኝ ኢትዮጵያዉያን የአባይ ጉዳይ ያገባናል፤ ጉዳዩን ችላ ብለን አንተዉም ያሉት ሰልፈኞቹ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል።

ሰልፈኞቹ አሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ይህንኑ ጥያቄያቸዉን በደብዳቤ መልክ አዘጋጅተዉ በእጅ እንደሚሰጡ የሰልፉ አስተባባሪ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

Via :- DW Photo :- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች

Video :- Al alin
ከሲዳማ ህዝብ የክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ታስረው የቆዩና የጠቅላይ አቃቤ ህግን የክስ ስረዛ ተከትሎ የተፈቱ ግለሰቦች ዛሬ በርካታ ህዝብ በተገኘበት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
ናይጄሪያ ኮሮና ቫይረስ የገባባት ሶስተኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ሆናለች።

ሰላም እደሩ ቸር ወሬ ያሰማን!!
@YeneTube @Fikerassefa
Forwarded from HEY Online Market
#ኦሪጂናል ሞባይል ስልኮች ዋስትና

🔸SAMSUNG
#GALAXY A SERIES 
A10S 2019 /32 GB/ 5,599ብር
A20S 2019 /32 GB/ 7,199ብር
A30S 2019 /64 GB/ 8,499 ብር
A50 2019 /64 GB/ 9,499 ብር
A50 2019 /128 GB/ 10,499 ብር
A50S 2019 /128 GB/ 4GB 11,199
A50S 2019 /128 GB/ 6GB 11,999
A51 2020 /128 GB/ 6GB 12,799 ብር
A70 2019 /128 GB/ 6GB 13,899 ብር

🔸SAMSUNG #GALAXY M SERIES 
M10 (2019) /32 GB/ 5,699 ብር
M10S (2019) /32 GB/ 6,200 ብር
M30S (2019) /36 GB/ 9,200ብር

አድራሻ :- ከቦሌ መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ ብራስ የሚወስደው መንገድ ላይ

Contact US
0953964175
0925927457
0910695100
@Roviii

@HEYOnlinemarket
ብልፅግና ፓርቲ ትግራይ ክልል ቢሮ ሊከፍት ነው።

የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አወሉ አብዲ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ብልጽግና አገር አቀፍ ፓርቲ በመሆኑ ከትግራይ ክልል ጋር በሚኖረው ሕገ መንግሥታዊ ግንኙነት መሠረት አደረጃጀቱን በማስፋት በቅርቡ በክልሉ በሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ጽሕፈት ቤቶችን ይከፍታል፡፡ብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ክልል ነባራዊ ሁኔታ እስካሁን ትርጉም ባለው መልኩ እንቅስቃሴ እንዳልተደረገ የገለጹት አቶ አወሉ፤ ነገር ግን አሁን በአዲስ መልክ የትግራይ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ተቋቁሞ ሥራውን እየሰራ ስለሆነ በቅርብ ጊዜ በክልል፣ በዞኖች፣ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ እንቅስቃሴ ይደረጋል ብለዋል።

Via:- EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮና ቫይረስ አስጊ የሚባል ደረጃ ላይ ደርሷል - ዶ/ር ቴድሮስ

የኮሮና ቫይረስ አስጊ የሚባል ደረጃ ላይ እና ዓለም አቀፍ ስጋት ሊሆን የሚችልበት አቅም ላይ መድረሱን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገለፁ።የዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አስተያየት የተሰማው በተለያዩ የዓለም ሀገራት እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት ነው።ባለፉት ሁለት ቀናት ከቻይና በበለጠ በሌሎች ሀገራት አዳዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች መገኘታቸውም ተጠቁሟል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa