ትራምፕ ለምክትላቸው ማይክ ፔንስ 'የኮሮና ተከላካይ' ሹመት ሰጧቸው
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ምክትላቸውን ማይክ ፔንስ መንግሥትን ወክለው ኮሮና ቫይረስን እንዲከላከሉላቸው ሾሟቸው።
ትራምፕና ምክትላቸው ፔንስ በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ኮሮናቫይረስ የአሜሪካ ሕዝብ ላይ የሚደቅነው አደጋ ዝቅ ያለ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ሁለቱ ባለሥልጣናት መግለጫ የሰጡት ኮቪድ-19 የተሰኘ ስያሜ የተሰጠው ኮሮናቫይረስ ከቻይናዋ ዉሃን ግዛት ተነስቶ በዓለም ዙሪያ በፍጥነት መዛመቱን ተከትሎ ነው።
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እስካሁን 60 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተዘግቧል። ባለሥልጣናቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ከሰጡ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ አንድ ግለሰብ በኮሮና መያዙ ተዘግቧል።
በራስ መተማመን የሞላቸው ትራምፕ፤ ዩኤስ ኮሮናቫይረስን የመከላከል ብቃቱ እንዳላት ጠቁመዋል።
«እኛ በጣም፣ በጣም ዝግጁ ነን» ያሉት ትራምፕ አጥኚዎች ለበሽታው ክትባት ለማግኘት ቀን ተሌት እየተጉ እንደሆነ አሳውቀዋል።
ነገር ግን የአሜሪካ ብሔራዊ አለርጂና ተላላፊ በሽታዎች ኃላፊ አንቶኒ ፎኪ የኮሮናቫይረስ ክትባት ቢያንስ በአንድ ዓመት ወይም አንድ ዓመት ተኩል ካልሆነ በቀላሉ እንደማይገኝ ይናገራሉ።
ትራምፕ ጋዜጣዊ መግለጫ ከመስጠታቸው በፊት መገናኛ ብዙሃን ኮሮናቫይረስን አካብደው እያዩት ነው፤ አላስፈላጊ ጩኸት እያሰሙ ነው ሲሉ ትዊተር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።
ቢሆንም ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ አሜሪካ ለቫይረሱ ዝግጁ መሆን አለባት ሲሉ አስጠንቅቀዋል። አልፎም ወደ አንዳንድ ሃገራት የሚደረገው ጉዞ መሰረዙ አግባብ ነው ሲሉ ውሳኔውን አድንቀዋል።
የአሜሪካው ጤና ሚኒስትር አሌክስ አዛር መንግሥታቸው የሚጠበቅበትን ሁሉ እያደረገ እንደሆነ ባይክዱም በአሜሪካ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አልካዱም።
Via:- BBC

በቢሾፍቱ በሚገኘው የኢፌዴሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በዛሬው ዕለት 106 ለሚሆኑ ከፍተኛ መኮንኖች ሹመት እንደሚሰጥ ታውቋል።
በተጨማሪም በዛሬው ዕለት ላለፉት 6 ወራት በስልጠና ላይ የቆዩ የአየር ኃይል ወታደራዊ ፖሊስ አባላት ምረቃ እንደሚኖር ተገልጿል።የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ ሹመቱን እንደሚሰጡ ተጠቁሟል።
የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ በስፍራው ተገኝተው ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።ባለፉት 6 ወራት በተቋሙ ከፍተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሰራተኞችም ሽልማት ይበረከታል ነው የተባለው።
Via OBN
@YeneTube @FikerAssefa

ጃፓን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የደገሰችዉን ኦሎምፒክ እንደምታቆም አስታወቀች።
አገሪቱ በቀጣዩ ክረምት ልታስተናግድ የነበረዉን የኦሎምፒክ ዝግጅቷን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ልታራዝም አልያም ለመተዉ እንዳሰበች ተነግሯል፡፡የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ እንዳስታወቁት የቶክዮ ኦሎምፒክ ለጊዜዉ መራዘም አለበት ካልሆነም ሊሰረዝ ይገባል ብለዋል፡፡
አሁን ላይ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በመላዉ አለም እየተሰራጨ መምጥቱን የዘገበዉ አልጄዚራ በጃፓንም በቫይረሱ የሚያዙት ሰዎች ቁጥር እጨመረ ነዉ ተብሏል፡፡
ጃፓን በኮሮና ቫይረስ የተጠረጠሩ ዜጎችን በመርከብ ላይ እንዲቆዩ ማድረጓም የሚታወስ ነዉ፡፡የዓለም የጤና ድርጅት ኮሮና ቫይረስ የዓለም ስጋት መሆኑን አውጆ የቫይረሱ ስርጭት በዚሁ ከቀጠለ ከዓለም ሀዝብ እስከ 70 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ ሊያጠቃ ስለሚችል አገራት ዝግጅት እንዲያደርጉ ማሳሰቡ ይታወሳል።
Via Ethio FM

በአዲስ አበባ ለሚገነባው የአማራ ባህል ማዕከል ግንባታ 50 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡ ተገለጸ፡፡
የአማራ ሕዝብ ራሱን ለማልማት ከሚያደርገው ጥረት በተጨማሪ ያለውን ቱባ ባህል እና ማንነቱን ለሌሎች ለመሸጥ እና ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኝዎች ክልሉን እንዲጎበኙ ለማስተዋዎቅ ታሳቢ ተደርጎ በአዲስ አበባ የባህል ማዕከል ለመገንባት መታቀዱን የአማራ ልማት ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዓለማየው ሞገስ ተናግረዋል፡፡
አቶ ዓለማየው እንዳሉት አማራ ያሉትን ባህል፣ ወግ እና ሥርዓት በማስተዋወቅ ራሱን በኢኮኖሚ ማደራጀት እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ያለው አካባቢን ለመፍጠር አካባቢውን ለቱሪስቶች በስፋት እያስተዋወቀ መሸጥ አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋናው የባህል ማዕከል ነው፡፡ ይህንንም ታሳቢ ተደርጎ ነው የባህል ማዕከሉን ዋና ከተማዋ ላይ መገንባት እንዳስፈለገም ተናግረዋል፡፡የባህል ማዕከሉን መላው የአማራ ሕዝብ ተወላጆች እና ወዳጆች በሚያደርጉት ድጋፍ ለመገንባት ነው ታሳቢ ተደርጎ እንቅስቃሴ እየተደረገ ያለው፡፡
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አዲስ አበባ ከሚኖሩ የአማራ ተወላጆች የባህል ማዕከሉን ለማስገንባት የሚውል 50 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል፡፡ የባህል ማዕከሉን ለመገንባት የሚያስችል ቦታ ለመስጠት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈቃደኛ መሆኑንና በቀጣዩ ሳምንት የመሬት ርክክብ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአማራ ልማት ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዓለማየው ሞገስ ለአብመድ ተናግረዋል፡፡፡
Via AMMA

ኢትዮ ቴሌኮም የብሮድባንድ ኢንተርኔት የታሪፍ ቅናሽ አደረገ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬሀይወት ታምሩ ተቋሙ በመደበኛ ብሮድባንድ ማሻሻያ ላይ ሲያደርገው የነበረውን ስራ ማጠናቀቁን አስታውቋል።
ይሄን የብሮድባንድ ኢንተርኔት ማሻሻያ ይፋ ማድረጊያ መርሀ ግብር ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ለተሻለ ምርታማነት በሚል መሪ ቃል በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው።
ተቋሙ ማሻሻያውን ማጠናቀቁን አስመልክቶም የብሮድባንድ ኢንተርኔት የታሪፍ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።
በማሻሻያው መሰረትም ለመኖርያ ቤት 69 በመቶ ቅናሽ ፣ ለድርጅቶች 65 በመቶ፣ VPN ደግሞ 72 በመቶ ቅናሽ መደረጉ ተገልጿል።
ማሻሻያው በዋጋ ብቻ ሳይሆን በፍጥነትም ጭምር መሆኑን ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል።
ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም የኢንተርኔት አገልግሎቱ ለመኖርያ ቤት የ 3 በመቶ ፍጥነት ፣ ለ ድርጅቶች 4 በመቶ ፍጥነት ይጨምራል ሲሉ ተናግረዋል።
በመርሀግብሩ ላይ እንደተገለጸው በአንድ ሀገር የ 10 በመቶ የብሮድባንድ ኢንተርኔት እድገት ወይም ስርፀት የ 1 ነጥብ 38 በመቶ አጠቃላይ ምርታማነትና እድገት ያመጣል።
Via:- Ethio FM

ኤርሚያስ አመልጋ ከአስር አልተፈቱም - Ethio FM
ኤርሚያስ አመልጋ ከአስር እንዲፈቱ የሚያዘው ደብዳቤ እስካሁን እንዳልደረሰው የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን አስታወቀ።
መንግስት የአገሪቱን የፖለቲካ ምህዳር ለማስፋት በሚል የ63 ተከሳሾችን ክስ አቋርጫለሁ ማለቱ ይታወሳል።
ክሳቸው ከተቋረጠላቸው ሰዎች ውስጥ እስካሁን 62ቱ ከእስር መለቀቃቸውን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።
ኤርሚያስ አመልጋ ምህረት ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል አንዱ ቢሆኑም እስካሁን ከእስር አልተፈቱም።
ያልተፈቱበት ምክንያት ደግሞ የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ለቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ኤርሚያስ አመልጋ ከአስር እንዲፈቱ ደብዳቤ ባለመጻፉ ምክንያት መሆኑን በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገረመው አያሌው ነግረውናል።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ በበኩላቸው የአቶ ኤርሚያስ አመልጋ ጉዳይ በመንግስት በኩል ለውጥ የለም፣ይፈታሉ ብሏል ደብዳቤውም ለማረሚያ ቤቱ ይላካል እስካሁንም የዘገየው የሚጣሩ ጉዳዮች ስላሉ ብቻ ነው እንጂ መፈታታቸው አይቀርም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ምንጭ:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa

ለ106 የአየር ኃይል ከፍተኛ መኮንኖች ሹመት ተሰጠ። ሹመቱን የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ ሰጥተዋል።
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
ከየካቲት 30 በኋላ ለመመዝገብ የሚመጡ አዳዲስ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመጪው ምርጫ መሳተፍ እንደማይችሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡
አዲስ ምስረታ ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በመከታል መደገፍና በአዲሱ አዋጅ የተቀመጠውን መስፈርት አሟልተው እንደአዲስ መመዝገብ የሚገባቸውን ፓርቲዎች እያጣራ ሰነዳቸውን መርምሮ ምዝገባ መከወን እየሰራ የሚገኘው ቦርዱ ሥራወ ጊዜ የሚፈጅ ነው ብሏል፡፡
በመሆኑም ‹‹ለመመዝገብና ለምርጫ ለመወዳደር የሚፈልግ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የግለሰቦች ስብስቦች እንዲሁም ግንባርና/ቅንጅት መፍጠር የሚፈልጉ ፓርቲዎች፣ አስፈላጊ ሰነዶቻችሁን እስከ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለቦርዱ እንድታስገቡ›› ሲል አስታውቋል፡፡
ይህ ሳሆን ቀርቶ ‹‹ከየካቲት 30 በኃላ የሚመጡ የምዝገባ ማመልከቻዎች በተለመደው አግባብ የሚስተናገዱ ቢሆንም ያለው የአሰራር ሂደት ከሚወስደው ጊዜ አንጻር መጪው ብሔራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ የማይችሉ መሆኑን እንገልጻለን›› ሲልም ቦርዱ አሳስቧል፡፡
Via:-Ahadu

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጋምቤላ ክልል በኑዌር ብሔረሰብ ዞን የአንድ የቀበሌ ሊቀመንበር መገደልን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ግጭት የ12 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡
በተጨማሪም 24 ሰዎች ቆስለዋል፣ ከ400 በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ከ7,000 በላይ የ5 ቀበሌ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል እንዲሁም ከ300 በላይ እንስሳት ተዘርፈዋል።
🎥ETV
@YeneTube @Fikerassefa
በተጨማሪም 24 ሰዎች ቆስለዋል፣ ከ400 በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ከ7,000 በላይ የ5 ቀበሌ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል እንዲሁም ከ300 በላይ እንስሳት ተዘርፈዋል።
🎥ETV
@YeneTube @Fikerassefa
ከመርከብ ግዥ ጋር ተያይዞ በእነ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ላይ በተመሰረተው ክስ ሁለት ምስክሮች ውድቅ ተደረጉ!
የግዥ መመርያን በመተላለፍ እና የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ከተቋቋመበት አላማ ውጭ 2 የንግድ መርከቦችን በመግዛት ከ544 ሚሊዮን ብር በላይ በህዝብ እና በመንግበስት ላይ ጉዳት አድርሰዋል ሲል በ14 የቀድሞ የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች ላይ አቃቤ ህግ በከፍተኛ ፍርድ ቤት የሙስና ወንጀል ክስ መመስረቱ ይታወቃል፡፡
ከእነዚህም 3ቱ በዚህ ሳምንት ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ክሳቸውን ካቋረጠላቸው መሀከል ናቸው፡፡የኮርፖሬሽኑ የቀድሞ ዋና ስራ አስኪያጅ ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና ቀሪ ተከሳሾች ደግሞ አቃቤ ህግ ያስቆጠረባቸውን ቀሪ 3 ምስክሮች ለመስማት ረቡዕ ረፋድ ላይ ጉዳያቸውን በሚመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ተሰይመው ነበር፡፡
ሆኖም 2 ምስክሮች በተመለከተ ፖሊስ አፈላልጎ ማግኘት እንዳልቻለ 3ኛው ምስክር ደግሞ ባስመዘገበው አድራሻ ማይኖር መሆኑን ለፍርድ ቤቱ በደብዳቤ ገፅዋል፡፡ይህን ተከትሎም ከሳሽ አቃቤ ህግ በወንጀለኛ መቅጫ የስነስርዓት ህጉ አንቀፅ 145(2) መሰረት ምስክሮች ከዚህ ቀደም ለፖሊስ የሰጡትን ቃል ፍርድ ቤቱ ይያዝልኝ ጠበቆችም ግልባጩን ወስደው አስተያየት እንዲሰጡበት ይሁን ሲል ጠይቋል፡፡ጠበቆች በበኩላቸው ለተከሳሾች ህግመንግስቱ የሰጣቸውን ምስክሮች እና ማስረጃዎችን የማየት እና የማወቅ መብት የሚፃረር ነው ሲሉ ተከላክለዋል፡፡
አክለውም በፖሊስ ጣቢያ ያለ ከባቢ ምስክሮች ላይ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል የሚገመት ነው ያሉ ሲሆን በፍርድ ቤት ቀርበው በቃለ መሀላ መመስከራቸው እውነታ እንዳለ ያሳያል የእነሱ ቃል ስለመሆኑ ማረጋገጫ በሌለበት ከዚህ ቀደም የሰጡት ቃል ተያይዞ መምጣቱ ግን ፍትህን እና የተከሳሾችን የመከላከል መብት የሚጋፋ ነው በማለት ውድቅ እንዲሆንላቸው ጠይቀዋል፡፡
ችሎቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ ትዕዛዙን መክሮ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ተፈልገው ያልተገኙት ሁለት ምስክሮችን ውድቅ አድርጓል፡፡ ባስመዘገበው አድራሻ ነዋሪ አይደለም የተባለው ምስክር ከዚህ ቀደም ለፖሊስ የሰጠው ቃል ግን በማስረጃነት እንዲያያዝ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡ጠበቆች ግልባጩን ወስደው አስተያየት ስጡበት የተባለ ሲሆን ችሎቱ በማስረጃዎች ላይ ብይን ለመስጠት ለሚያዝያ 2 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
[ዋዜማ ራዲዮ]

ግብፅ የህዳሴው ግድብ ድርድሩን ለመቀጠል ቁርጠኛ ነኝ አለች!
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በአሜሪካ ሊካሄድ ታስቦ የነበረውን ድርድር ኢትዮጵጵያ አልሳተፍም ማለቷን ተከትሎ፣ ግብፅ ድርድሩን ለመቀጠል ቁርጠኛ ነኝ አለች፡፡
የኢትዮጵያ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በስምምነቱ ዙሪያ በሀገር ውስጥ የሚደረጉ ምክክሮች ባለማለቃቸው በድርድሩ ላይ ኢትዮጵያ እንደማትሳተፍ ባሳወቀ በሰዓታት ልዩነት ውስጥ ነው ግብፅ ይህን ያለችው፡፡
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫን የዘገበው አል-አህራም፣ ሚኒስቴሩ በአሜሪካ እና በአለም ባንክ አሸማጋይነት የሚደረገው ድርድር ላይ ግብፅ ለመቀጠል ቁርጠኛ ነች ብሏል፡፡ ይሄም ግብፅ ድርድሩን ከዳር ለማድረስ ያላትን ፍላጎት የሚያሳይ ነው ሲል መግለጫው አክሏል፡፡ግብፅ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ከስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችላቸውን ሰነድ በመሪዎች ደረጃ ይፈርማሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡
Via Asham TV

በአዲስ አበባ የከባድ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሰዓት ማሻሻያ ተደረገ።
በአዲሱ ማሻሻያም ከባድ ተሽከርካሪዎች ጠዋት ከ1-3 ሰአት እንዲሁም ከሰዓት ከ 10:30-12:00 ውጪ ባሉ ሰዓቶች እንዲንቀሳቀሱ መወሰኑን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።ማሻሻያው የተደረገው የተለያዩ ተቋማት በሰዓት ገደቡ ምክኒያት በተለይም የግንባታ ስራዎቻቸውን ለማከናወን መቸገራቸውን ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።በመሆኑም የትራፊክ እንቅስቃሴውን ጫና ውስጥ በማይከት መልኩ ማሻሻያው ተደርጓል።እስካሁን በነበረው ህግ በከተማዋ የሚገኙ ከባድ ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ብቻ ነበር መንቀሳቀስ የሚፈቀድላቸው።

የቻይናው ፕሬዝደንት ኢትዮጵያን አመሰገኑ!
በቻይና በተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር የነበራትን የቀደመ ግንኙነት በማሰብ፣ በዓለም የጤና ድርጅት ምክር መሠረት ግንኙነቷን ባለማቋረጧ ያለኝን አድናቆት ለመግለፅ እፈልጋለሁ ሲሉ የቻይናው ፕሬዝደንት ዢ ጂንፒንግ ተናገሩ፡፡‹‹የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት የቻልነውን ሁሉ እያደረግን ባለንበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያው ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ሁለት ጊዜ መልዕክት በመላክ እንዲሁም ስልክ በመደወል የአብሮነት ተምሳሌትነታቸውን አሳይተውናል›› ብለዋል።
ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጎናችን መሆን በቻይና እና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን መደጋገፍ እና ትብብር ያሳያል ያሉት ፕሬዝደንት ዢ ጂንፒንግ፣ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር የነበራትን የቀደመ ግንኙነት በዓለም ጤና ድርጅት ምክር መሠረት ባለማቋረጧ ያለኝን አድናቆት ለመግለፅ እፈልጋለሁ ሲሉ አብራርተዋል፡፡ በመጨረሻም፣ የአፍሪካ አገራት እና ህዝቦቻቸው ቻይና በኮሮና ቫይረስ ጋር በምታደርገው ትግል ወንድማዊ ግንኙነታቸው በደስታችንም ሆነ በሀዘናችን ከጎናችን በመሆን አሳይተውናል ብለዋል፡፡
ምንጭ፡- ሺንዋ/ዋልታ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር ወስደው ያልመለሱ እና የጠፉ 71 ባለሃብቶች እና ሰራተኞቹን በሕግ ለመጠየቅ እንዲሁም ያለአግባብ የባከነ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ግንዘብን ለማስመለስ ምርመራ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ።ምርመራው ሲጠናቀቅ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ የባንኩ ፕሬዝዳንት ኃይለየሱስ በቀለ ዛሬ ጠዋት በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል። ከዚህ በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረ ግጭት ከዚኅ ቀደም ከባንኩ ብድር የወሰዱ 38 ፕሮጅክቶች መውደማቸውንም ኃይለየሱስ ተናግረዋል። ምርመራ እየተደረገባቸው ያሉትን ድርጅቶች እና ባላሃበቶች ስም ዝርዝር ከመናገር ግን ተቆጥበዋል።
ምንጭ:አዲሰ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ:አዲሰ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
የኢራኑ ምክትል ፕሬዘዳንት በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ተገለጸ።
ፖፕ ፍራንሲስም በዚሁ ቫይረስ ተጠቅተዋል የሚል ጥርጣሬ ታይቶባቸዋል።
ከሁለት ቀናት በፊት የኢራን ምክትል የጤና ሚኒስትር በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው ወደ ለይቶ ማከሚያ ክፍል መግባታቸው ይታወሳል።
ከደቂቃዎች በፊት ዳይሊ ሜይል ይዞት በወጣው ሰበር ዜናው የኢራን ምክትል ፕሬዘዳንት በዚሁ ቫይረስ ተጠቅተው ሆስፒታል ገብተዋል።
በተጨማሪም የኢራን የቤተሰብ እና የሴቶች ጉዳዮች ምክትል ፕሬዘዳንት በዚሁ ቫይረስ መጠቃታቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ሜትሮ የተሰኘው የእንግሊዙ ተነባቢ ጋዜጣ ደግሞ በጣልያን በሽተኞችን ሲጠይቂ የዋሉት የካቶሊክ ቄሱ ፖፕ ፍራንሲስ ምልክት ታይቶባቸዋል።
ይሁንና ፖፕ ፍራንሲስ የተጠቁት በዚሁ ቫይረስ ይሁን አይሁን እስካሁን በምርመራ አልተረጋገጠም።
በኢራን በዚህ ገዳይ ቫይረስ የተጠቁ ዜጎች ቁጥር ወደ 254 የደረሰ ሲሆን በጣልያን ደግሞ ከ450 በላይ ደርሷል።