YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ምርጫ ቦርድ ኢዜማ እየተገለገለበት ያለውን ጽኀፈት ቤቶች ለኢዴፓ እንዲመልስ ጠየቀ!

የኢትየጵያ ምርጫ ቦርድ በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እየተገለገለባቸው የሚገኙትን ሦስት ጽኀፈት ቤቶች እንዲመልስ ለፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስለመጠየቁ የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።ምርጫ ቦርድ የሦስቱ ጽኀፈት ቤቶች ባለቤትነት የኢዴፓ መሆኑን ጠቀሶ፣ ለፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በየካቲት 17/2012 በጻፈው ደብዳቤ ላይ ከኢዜማ በማስመለስ ለፓርቲያችን እንዲያስረክብ ተጠይቋል ሲሉ የኢዴፓ ፕሬዝዳንት አዳነ ታደሰ ገልጸዋል።

አዳነ፣ ምርጫ ቦርድ አስቀድሞ ይህን ነገር መፍታት ሲኖርበት ዘግይቶም ቢሆን ተገቢ እርምጃ መውሰዱን በመልግለፅ ቀጣዩ ስራችን የቤቶች ኮርፖሬሽን አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወስድ መጠየቅ ነው ብለዋል።ኢዴፓ በኢዜማ ላይ መስርቶት የነበረውን ክስ ጽኅፈት ቤቶቹ መመለሳቸውን እርግጠኛ ሲሆን ክሱን ሊያቋርጠው እንደሚችል ጠቁሟል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ!

በዚህ አንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ በተለያዩ ሀገርቱ ክፍሎች በሕገ ወጥ መንገድ ስንቀሳቀስ የነበረው ገቢና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ግሚታዊ ዋጋቸው 45 ሚሊዮን 880 ሺህ 799 ብር የሚያወጣ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉ የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹም ኤሌክትሮኒክስ፣ ጎማ፣ ማዕድን፣ ስጋራ፣ ጀነሬተሮች፣ አልባሳት፣ ዘመናዊ መገናኛ ሬዲዮዎች፣ የተለያዩ ሀገራት ገንዝብ፣ አደንዛዥ ዕፅ (አሽሽ)፣የጦር መሣሪያዎች፣ ተሸከርካሪዎች እንዲሁም ብዛት ያላቸው የተለያዩ ዓይነት ዕቃዎች ናቸው፡፡

እነዚህ ሕገ-ወጥ ዕቃዎች በጅግጅጋ፣ ሞያሌ፣ አዋሽ፣ ኮምቦልቻ፣ አዋሳ፣ ሞጆ፣ ጅማ፣ ባህር ዳር፣ ድሬ ደዋ እና በሌሎች የኬላ ጣብያዎች አካባቢ በጉምሩክ ሠራተኞች፣ የጸጥታ አካላት እና በአካባቢው ህብረተሰብ ድጋፍ በተደረገው ከፍተኛ ቁጥጥርና ፍተሻ ነው እንዲያዙ የተደረገው፡፡

ምንጭ: የገቢዎች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from HEY Online Market
#ኦሪጂናል ሞባይል ስልኮች ዋስትና

🔸SAMSUNG
#GALAXY A SERIES 
A10S 2019 /32 GB/ 5,599ብር
A20S 2019 /32 GB/ 7,199ብር
A30S 2019 /64 GB/ 8,499 ብር
A50 2019 /64 GB/ 9,499 ብር
A50 2019 /128 GB/ 10,499 ብር
A50S 2019 /128 GB/ 4GB 11,199
A50S 2019 /128 GB/ 6GB 11,999
A51 2020 /128 GB/ 6GB 12,799 ብር
A70 2019 /128 GB/ 6GB 13,899 ብር

🔸SAMSUNG #GALAXY M SERIES 
M10 (2019) /32 GB/ 5,699 ብር
M10S (2019) /32 GB/ 6,200 ብር
M30S (2019) /36 GB/ 9,200ብር

አድራሻ :- ከቦሌ መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ ብራስ የሚወስደው መንገድ ላይ

Contact US
0953964175
0925927457
0910695100
@Roviii

@HEYOnlinemarket
🇬🇧🇬🇧ወደ UK ሄደው መማር ይፈልጋሉ?🇬🇧🇬🇧
Sky Education Consultancy Ltd is licensed education consultancy firm that will be based in UK-London.

👉 Providing college selection
👉 Educational guidance and support

#Partial_Scholarship_to_UK
የትምህርት እና የኑሮ ወጪዎን እርሶ ይሸፍናሉ፡፡
#For_full_Scholarship_to_UK
👉 a high level academic achievements in order to be competitive

#Branch_office: Bole Atlas
📞 0977202020
@secethiopia
#Invest_in_your_knowledge
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ አቶ ግርማ ብሩን የኢትዮ-ቴሌኮም ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አድርገው እንደሾሟቸው ፎርቹን ዘግቧል፡፡ ትናንት ደሞ አምባሳደር አዲስ ዐለም ባሌማን የፖሊሲ ጥናት እና ምርምር ዋና ዳይሬክተር አድርገው እንደሾሙ ፋና ብሮድካስት ዘግቧል። ተሹዋሚው ቀደም ሲል የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነበሩ።

T.me/YeneTube @FikerAssefa
አቶ ዮሃንስ ቧያለው የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዘዳንትነት ሹመትን እንደማይቀበሉት አስታወቁ።

@YeneTube @Fikerassefa
YeneTube
አቶ ዮሃንስ ቧያለው የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዘዳንትነት ሹመትን እንደማይቀበሉት አስታወቁ። @YeneTube @Fikerassefa
‹‹አሁን ተቋሙ ባለው የሕዝብ አመለካከት በተቋሙ መሥራት የምችልበት ሁኔታ ሥለሌለ የቀረበውን ሹመት ለመቀበል ያስቸግረኛል፡፡›› አቶ ዮሃንስ ቧያለው

አዲሱን ምደባ በዜና እንደሰሙ የተናገሩት የቀድሞው የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ቧያለው በዜና ከመስማታቸው በፊት በፌደራል ደረጃ ኃላፊነት እንደሚሰጣቸው እንጅ የትኛው መስሪያ ቤት እንደሚመደቡ እውቅናው እንዳልነበራቸው ለአብመድ ገልጸዋል፡፡

‹‹በአሁኑ ጊዜ እራሴን ሳዳምጠው እና ስመረምረው በዚያ ተቋም መሥራት ቢኖርብኝ እንኳ አሁን ተቋሙ ባለው የሕዝብ አመለካከት በተቋሙ መሥራት የምችልበት ሁኔታ ሥለሌለ የቀረበውን ሹመት ለመቀበል ያስቸግረኛል፤ ስለሆነም የሕዝቡን ትግል በተለያየ መልኩ አስተዋጽኦ በማድረግ ፓርቲው ጉዞው እንዲጠናከር በማድረግ በሌላ አግባብ ላገለግል እችላለሁ እንጅ የተመደብኩበት ተቋም አሁን ባለው ስያሜ እና ሥዕል በተቋሙ ለማገልገል እንደማልችል ገልጫለው፡፡ ምደባውን ከሰማሁ በኋላም ምደባውን እንደማልቀበለው ሪፖርት አድርጌአለው›› ብለዋል አቶ ዮሃንስ ቧያለው፡፡

Via AMMA
T.me/YeneTube @FikerAssefa
የአቶ ንዋይ ገብረአብ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ!

ለረዥም ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የየቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው ያገለገሉት አቶ ንዋይ ገብረአብ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ።አቶ ንዋይ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የሚታወስ ነው።

የቀብር ሰነ ስርዓታቸው ቤተሰቦቻቸው ፣ የቀድሞ የስራ ባልደረቦቻቸው ፣ አድናቂዎቻቸው በተገኙበት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል።ከ1970ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና በፕላን ኮሚሽን ውስጥም ለረዥም ዓመታት አገልግለዋል።አቶ ንዋይ ከኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪነታቸው ባለፈ የኢትዮጵያ የልማት ጥናት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ብልጽግና ፓርቲ የህዝብና የመንግስት ሃብትን ለምርጫ ቅስቀሳ እየተጠቀመ መሆኑን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ አስታወቀ።

T.me/YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ረፋድ ላይ በሀዋሳ ከተማ በቱላ ክ/ከተማ በተለምዶ ኩቤ ካባ ተብሎ በሚጠራው የድንጋይ ማምረቻ የድንጋይ ካባ ተደርምሶ የ2 ሰዎች ህይዎት ማለፉንና በ3 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማው አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ አስታወቀ።

ሟቾቹ በስራ ላይ የነበሩ የስካባተር ኦፕሬተር እና አንድ ሰራተኛ ነበሩ።
@YeneTube @Fikerassefa
የብሮድካስት ባለስልጣን ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ የሰጠው ማስጠንቀቂያ (የኢኦተ ቤተክርስቲያን ቴሌቪዝን)
@YeneTube @Fikerassefa
Audio
በደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት ያለፋቸውን የትምህርት ክፍለ-ጊዜ ለማካካስ ዩኒቨርሲቲው ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑን ገለፁ።

ተማሪዎቹ ከተቋረጠ ከወር በላይ የሆነው የኢንተርኔትና ስልክ አገልግሎት እንዲመለስላቸውም ጠይቀዋል።

የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ለታ ተስፋዬ “ዩኒቨርሲቲው ወደ ቀድሞ መረጋጋቱ ተመልሶ በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን ለማስመረቅ እየሰራን ነው” ብለዋል።

ታገቱ የተባሉ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ጉዳይ በተመለከተም “ተማሪዎቹን የማፈላለግ ጥረት ቀጥሏል፣ ተገኝተው ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ እየሰራን ነው" ብለዋል።
ታገቱ የተባሉ ተማሪዎችን በተመለከተ ይገኙ አይገኙ እስካሁን ከቤተሰብም ሆነ ከመንግሥት የተሰጠ መግለጫ የለም።

Via:- VOA
@YeneTube @Fikerassefa
Forwarded from HEY Online Market
#ኦሪጂናል ሞባይል ስልኮች ዋስትና

🔸SAMSUNG
#GALAXY A SERIES 
A10S 2019 /32 GB/ 5,599ብር
A20S 2019 /32 GB/ 7,199ብር
A30S 2019 /64 GB/ 8,499 ብር
A50 2019 /64 GB/ 9,499 ብር
A50 2019 /128 GB/ 10,499 ብር
A50S 2019 /128 GB/ 4GB 11,199
A50S 2019 /128 GB/ 6GB 11,999
A51 2020 /128 GB/ 6GB 12,799 ብር
A70 2019 /128 GB/ 6GB 13,899 ብር

🔸SAMSUNG #GALAXY M SERIES 
M10 (2019) /32 GB/ 5,699 ብር
M10S (2019) /32 GB/ 6,200 ብር
M30S (2019) /36 GB/ 9,200ብር

አድራሻ :- ከቦሌ መድሃኔአለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ ብራስ የሚወስደው መንገድ ላይ

Contact US
0953964175
0925927457
0910695100
@Roviii

@HEYOnlinemarket
Forwarded from YeneTube
🇬🇧🇬🇧ወደ UK ሄደው መማር ይፈልጋሉ?🇬🇧🇬🇧
Sky Education Consultancy Ltd is licensed education consultancy firm that will be based in UK-London.

👉 Providing college selection
👉 Educational guidance and support

#Partial_Scholarship_to_UK
የትምህርት እና የኑሮ ወጪዎን እርሶ ይሸፍናሉ፡፡
#For_full_Scholarship_to_UK
👉 a high level academic achievements in order to be competitive

#Branch_office: Bole Atlas
📞 0977202020
@secethiopia
#Invest_in_your_knowledge