የክልል ልዩ ሃይል እና ሚሊሻ በፌደራል ስር እንዲጠቃለሉ የሚመክር ጉባኤ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።
ውይይቱን ጽናት ኢትዮጵያ የተሰኘው የበጎ አድራጎት ማህበር ያዘጋጀው ሲሆን የክልል ልዩ ሃይልና ሚሊሻዎች ለአገራችን ሰላም ያላቸው ሚና በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይግኛል። በኢትዮጵያ የዜጎች መፈናቀል፣ የማምለኪያ ቦታዎች መቃጠል እና ሌሎች እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮች እንዲቆሙ እና የህግ የበከላይነት እንዲረጋገጥ መፍትሔዎቹ ምን ምን ናቸው በሚል ላይ እንደሚያተኩር የውይይቱ አዘጋጆች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይ የህግ ምሁራን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የሃይማኖት አባቶች፣የአገር ሽማግሌዎች፣ የጸጥታ እና የፍትህ ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል።የክልል ልዩ ሃይሎች እና ሚሊሻዎች አሁን ካሉበት ፉክክር ወጥተው እንዴት ለአገር ግንባታ እናውለው በሚልም የመፍትሔ ሃሳቦች እንደሚነሱበትም ይጠበቃል።
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa

የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ያለዕድሜ ጋብቻንና የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም የተዘጋጀዉን ፍኖተ ካርታ በኦሮሚያ ክልል ማስተዋወቅ ጀመረ!
ያለዕድሜ ጋብቻንና የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም የተዘጋጀዉን ፍኖተ ካርታ በኦሮሚያ ክልል ማስተዋወቅ በዛሬዉ ዕለት በጅማ ዞን ተጀምሯል፡፡ይህንንኑ ፍኖተ ካርታ አጠር ባለ መልኩ ያስተወወቁት አቶ ሰሎሞን አሰፋ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የሚኒስቴር ጽ/ቤት ሀላፊ ሲሆኑ በገለጻቸዉም ፍኖተ ካርታዉ ከሌሎች መሰል አስትራተጂዎች በተለየ መልኩ ለስራዉ አስፈላጊ የሆነ በጀት በዉስጡ እንዳካተተና ያለዕድሜ ጋብቻንና የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም በከፍተኛ ፍጥነት መሰራት እንዳለበት አጽንኦት የሰጠ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በማስተዋወቂያ መድረኩ ላይ ከጅማ ዞን የተዉጣጡ በሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ላይ የሚሰሩ ሴክተር መ/ቤት ተወካዮች፣ የሀይማኖት ተቋማት ተወካዮችና ሌሎች ጉዳዮ ከሚመለከታቸዉ አካላት የተዉጣጡ ከ 250 በላይ የሚገመቱ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ምንጭ: የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር

#COVID-2019_update
የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከስድሳ ስድስት ሺህ ያለፈ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 1526 ደርሷል።
Via AFP
@YeneTube @FikerAssefa
የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከስድሳ ስድስት ሺህ ያለፈ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 1526 ደርሷል።
Via AFP
@YeneTube @FikerAssefa
"ከ350 በላይ የሚሆኑ አባላቶቻችን እና ደጋፊዎቻችን ለእስር ተዳርገውብናል" ኦ.ነ.ግ
“27 አባላት እና ደጋፊዎቻችን ለእስር ተዳርገዋል” ኦ.ፌ.ኮ
"በክልላችን የፖለቲካ ፓርቲ አባል ስለሆነ ብቻ ማንም ሰው አይታሰርም መታሰርም የለበትም።” ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት
Via Sheger Times
@YeneTube @FikerAssefa
“27 አባላት እና ደጋፊዎቻችን ለእስር ተዳርገዋል” ኦ.ፌ.ኮ
"በክልላችን የፖለቲካ ፓርቲ አባል ስለሆነ ብቻ ማንም ሰው አይታሰርም መታሰርም የለበትም።” ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት
Via Sheger Times
@YeneTube @FikerAssefa
በጅግጅጋ ከተማ ነገ የድጋፍ ሰልፍ ይደረጋል።
በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅጋ በነገው እለት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ እንደሚደረግ ከአዘጋጆቹ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።በነገው እለት ከማለዳው አንስቶ በሚካሄደው ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በጅግጅጋ እና በአከባቢው የሚገኙ በርካታ ነዋሪዎች የሚሳተፉበት ሲሆን "በህብር ወደ ብልፅግና!" እንዲሁም " ብልፅግና ለሁሉም ሁሉም ወደ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃልም እንደሚካሄድ ታውቋል።

በተቀማጭ ገንዘብ ማነስ ምክንያት ከባንኮች የሚገኘው ብድር እጅግ ቀንሷል!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ በሀገሪቱ ያሉ የግል ባንኮች በተቀማጭነት ያስቀመጡት ገንዘብ ከሰጡት ብድር ጋር ስላልተጣጣመ ለደንበኞቻቸው የሚሰጠው ብድር ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ እጅግ መቀነሱን የባንክ ሰራተኞች ለፊደል ፓስት ተናግረዋል።አብዛኞቹ ባንኮችም ካላቸው ተቀማጭ ገንዘብ ከ70 እሰከ 90 ከመቶ ብድር ላይ በማዋላቸው የገንዘብ እጥረት ገጥሟቸዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለላኪዎች፣ መድሀኒትና ዘይት አቅራቢዎችእንዲሁም ሌሎች ለሀገሪቱ የግድ አስፈላጊ ከሆኑ ምርቶች በስተቀር ለሀገር ውስጥ እቃዎች ግዢም ይሁን ለሌሎች እቃዎች የሚሰጠውን ብድር እንዳቆመ ስማቸው እንዳይገለፅ ያልፈለጉ የባንኩ ሰራተኞች ለፊደል ፓስት ተናግረዋል። ንግድ ባንክ ለሰራተኞቹ የሚሰጠውን ብድር በተቀማጭ ገንዘብ ማነሱ ምክንያት እንዳቆመ ተናግረዋል።
በዳሽን ባንክ የምትሰራ አንዲት ሰራተኛም ብድሮች እንደድሮ እየተለቀቁ እንዳልሆ ተናግራለች ።እንደሰራተኞቹ ገለፃ ባንኮች የብድር አለቃቀቃቸውን ካላቸው ተቀማጭ ገንዘብ ጋር አመጣጥኖ አለመሄድ፣ የኢኮኖሚው መቀዝቀዝ ፣የዋጋ ንረት ባንኮችን ተቀማጭ ገንዘባቸው እንዲቀንስ አድርጎ የብድር አገልግሎታቸው እንዲቀነስ አድርጎታል።ይሄም ችግርን ለመፍታት ኢኮኖሚውን ማቅናትና የሰጡትን ብድር የመመለስ ረጅም ስራ ይጠብቃል በማለት የባንክ ሰራተኞቹ አስተያየታቸውን ገልፀዋል።
Via Fidelpost

41 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ እንደማይስማሙ ድምጽ ሰጡ።
ዛሬ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት ፓርቲዎች በጊዜ ሰሌዳው ላይ ድምጽ እንዲሰጡ ባሰናደው መድረክ ከተገኙ ፓርቲዎች 41ዱ በጊዜ ሰሌዳው እንደማይስማሙ የገለጹ ሲሆን፣ ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ 6 ፓርቲዎች የጊዜ ሰሌዳውን ደግፈዋል።
6 ፓርቲዎች በበኩላቸው ድምጽ ተሃቅቦን መርጠዋል። የጋራ ምክርቤቱ የፓርቲዎችን አቋም ለምርጫ ቦርድ እንደሚያቀርብ አስታውቋል።
Via:- ELU
@Yenetube @Fikerassefa

ዩናይትድ ስቴትስ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ አንድ ግዙፍ መርከብ ውስጥ ተገልለው የሚገኙ ዜጎቿን ወደ ሀገሯ ልትመልስ ነው።
ቶኪዮ የሚገኘው የዩ ኤስ ኤምባሲ እንዳስታወቀው አንድ አይሮፕላን ወደ ጃፓን በመላክ ዜጎቹን ወደ ካሊፎርኒያ እሁድ ዕለት ለመመለስ አቅዷል።
ዲያመንድ ፕሪንሰስ የተባለችው ትልቅ መርከብ ውስጥ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጠ አንስቶ መርከቧ ፎኮሹማ ወደብ አቅራቢያ ካለፈው ወር አንስቶ እንዳንትቀሳቀስ ታግታ ትገኛለች። በርካታ አገር ጎብኚዎች በተሳፈሩባት በዚችው መርከብ ውስጥ ዛሬ ብቻ 67 ሰዎች ቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በዚህም የተነሳ የተያዙት ሰዎች ቁጥር ወደ 285 አሻቅቧል። በመርከቧ ላይ በጠቅላላው 3500 የሚሆኑ ሰዎች የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 380 የሚሆኑት አሜሪካውያን ናቸው።
Via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa

የቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ኮንሰርት ቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ የካቲት 14 መስቀል አደባባይ ይካሄዳል።
ቴዲ በመድረክ ላይ የ3 ሰዓት ቆይታ የሚያደርግ ሲሆን የመግቢያ ዋጋ ቪ.አይ.ፒ 500ብር መደበኛ 200 ብር ሲሆን ትኬቶቹም ከማክሰኞ ጀምሮ በሁሉም ዳሽን ባንክ ቅርንጫፎች ይሸጣሉ ተብሏል።
Via:- ዳሰሳ አዲስ
@yeneTube @Fikerassefa

የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተር ግርማ ጉተማ አርቲስት ልጅ ያሬድ በቡራዩ ከተማ መታሰሩን አስታውቋል።
በተጨማሪም በዜግነት ኖርዌያዊ የሆነች ሀዊ የተባለች አርቲስት ለጊዜው ባልታወቀ የፀጥታ አስከባሪ ክፉኛ ተጎድታ ሆስፒታል መግባቷን በግርማ ጉቱማ ገፅ እና ከOMN ሚዲያ የፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
OMN ለብራዩ ከተማ ከንቲባ ስልክ ቢሞክርም እንዳልተሳካለት አስነብቧል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ነገ በሰፊው የምንመለስበት ይሆናል።

ሀይቲ ውስጥ በአንድ የልጆች ማሣደጊያ ጣቢያ ውስጥ በደረሰ ቃጠሎ የ15 ልጆች ህይወት ማለፉን ባለስልጣናት አስታወቁ።
የሁለቱ ልጆች ህይወት እዛው ማሣደጊያ ጣቢያው ውስጥ ሲያልፍ የሌሎች 13 ደግሞ ሀኪም ቤት ከደረሱ በኋላ በቃጠሎው ጭስ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ ተዘግቧል።
በዚሁ መንግስታዊ ባልሆነው የልጆች ማሳደጊያ ጣቢያ ውስጥ 66 ህፃናት ይኖሩ ነበር። አንድ የጣቢያው ሰራተኛ ለፈረንሳይ ዜና ምንጭ እንደገለፁት እሳቱ የተነሳው ሀሙስ ዕለት በሀገሪቱ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ሶስት ሰአት አካባቢ ሲሆን የእሳት አደጋ ሰራተኞች ስፍራው እስኪደርሱም 90 ደቂቃ ያህል ፈጅቷል።
በዚሁ ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆች ማሳደጊያ ጣቢያ ውስጥ መብራት ስላልነበረ ሻማ ይጠቀሙ እንደነበርም ሰራተኛዋ ተናግረዋል። ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ ገና ጨቅላዎች እንደነበሩ ተዘግቧል።
የካረቢክ ደሴቷ ሀገር ሀይቲ እኢአ በ 2010 ዓ ም ከደረሰባት ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ አሁንም አላገገመችም። በዚሁ አደጋ ከ 200 ሺ በላይ ሰዎች ህይወት የጠፋ ሲሆን ከ 1,5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ቤት አልባ ሆኗል።

የአየር መንገድ ሰራተኞች በነፃ ትኬት ተጉዘው ለሚያመጡት እቃ ሶስት እጥፍ ቀረጥ መጣሉ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጠረ
የገቢዎች ሚኒስቴር አየር መንገድ ለሰራተኞቹ በሚሰጠው ነፃ ትኬት የንግድ እቃዎችን በብዛት እየመጡ ሰለሆነ ማንኛውም በነፃ ትኬት ውጭ የሚሄድ የአየር መንገድ ሰራተኛ ይዞ በሚመጣው እቃ ላይ ሶስት እጥፍ ቀረጥ እጥላለው ማለቱ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል።
ገቢዎች በዚህ አሰራሩ ለሌላውም መንገደኛ እንደሚያደርገው በቁጥር 60 በአይነት አራት ከቀረጥ ነፃ የሚፈቅደውን አልባሳት ለአየር መንገዱ ሰራተኞች ከልክሎ አንድም ልብስ ከውጭ ቢያመጡ እንደሚቀርጥ አስታውቋል።
ሚኔስቴሩ ከሳምንት በፊት ዱባይ በተጓዙ የአየር መንገዱ ሰራተኞች ላይ ተግባራዊ አርጎ ከዛም በተቃውሞ የጣለውን የሶስት እጥፍ ቀረጥ ያነሳ ቢሆንም አሰራሩ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ መልሶ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ይሄ አዲስ አሰራር በሁለት ሻንጣ ልብስ ላይ እሰከ መቶ ሺ ብር ድረስ ሊቀርጠን ይችላል በማለት የአየር መንገዱ ሰራተኞች ተቃውሞ አሰምተል።
በስልክ ለፊደል ፓስት ቅሬታዋን የገለፀቸው ሄለን የተባለች የአየር መንገዱ ሰራተኛ እንዳለችው ” እኛ ነፃ ትኬት አገኘን እንጂ ውጭ ስንሄድ ልብስ በነፃ አናመጣም ።እንድ መንገደኛ ከቀረጥ ነፃ የሚፈቀድ ነገረ ሊፈቀደልን ይገባል። ከዛ በላይ በሆነ ነገር ደግሞ እንደመንገደኛው ልንቀረጥ ይገባል። አዲሱ አሰራር አድሏዊ ነው።
የአየር መንገድ ሰራተኛ ለሀገሪቷ ትልቅ ገቢ እያስገባ ገና ለገና በነፃ ትኬት ሄደሀልና አንድም ልብስ ብታመጣ ትቀረጣለህ ማለት ለእኛ ክብር አለመስጠት ነው ” ብላለች ።
የአየር መንገዱ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር ለሚኒስቴር መሰርያቤቱ በፃፈው ደብዳቤ በአመት ከሁለት ጉዞ በላይ በነፃ ትኬት ውጭ ደርሰው የሚመጡትን የአየር መንገዱን ሰራተኞች እንደ ነጋዴ ማየት ተገቢ አይደለም እንደከዚ በፊቱ መንገደኞች በሚቀረጡበት አይን ሊታዩ ይገባል በማለት አዲሱ መመርየ እንዲቀር ጠይቋል ።
Via:- FidelPost.com

ሰባተኛው ከተማ አቀፍ የብዙሃን ስፖርት በዛሬው ዕለት በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የቶክዮ ኦሎምፒክ የበላይ ጠባቂ አቶ አባ ዱላ ገመዳ ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራሮች ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ አትሌቶች ፣ የተለያዩ የስፖርት ማህበራት እንዲሁም በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡በመድረኩ ላይ የ2020 የቶክዮ ኦሎምፒክ ችቦ የማብራት መርሃ ግብርም ተከናውኗል፡፡
Via Mayor office

ክልሎች ለስኳር ፋብሪካዎች የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ታወቀ!
የክልሎቹ አቋም ስኳር ፋብሪካዎቹን ለመሸጥ የተያዘውን ዕቅድ እንዳይስተጓጎል ሥጋት ፈጥሯል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ መፍትሔ እንዲያሰጡ ተጠይቋል።በፌዴራል መንግሥት ለተቋቋሙ ነባርና በግንባታ ላይ ለሚገኙ አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎች የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ እንዲሰጡ ተደጋጋሚ ጥያቄ ለሚመለከታቸው ክልሎች ቢቀርብም፣ ክልሎች ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ሪፖርተር አገኘሁት ያለው መረጃ አመለከተ፡፡
የተገኘው የሰነድ መረጃ እንደሚያመለክተው የፌዴራል መንግሥት ከበርካታ ዓመታት በፊት ላቋቋማቸው ነባር የስኳር ፋብሪካዎችም ሆነ፣ በአሁኑ ወቅት በግንባታ ላይ ለሚገኙት የስኳር ፋብሪካዎች የይዞታ ማረጋገጫ ማግኘት ባለመቻሉ መንግሥት ፋብሪካዎቹን ወደ ግል ለማዘዋወር እያደረገ ያለውን ጥረት እንዳያስተጓጉል ሥጋት ፈጥሯል፡፡
ሙሉውን ዝርዝር 👇👇👇
https://telegra.ph/projects-02-16

በአዲስ አበባ የተተከሉ አበቦች እና ሀገር በቀል ዛፎች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር በከተማው ዋና ዋና መንገዶች ቅኝት በማጠናከር ህጋዊ ርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሰታወቀ፡፡
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
በኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የምዕራብ ዕዝ በደቡብ ጎንደር ዞን ክምር ድንጋይ ከተማ ያስገነባውን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ አስመርቋል፡፡
በ"ጉና ቤጌምድር 2ኛ ደረጃ ትምርት ቤት" የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የታደሙት የምዕራብ ዕዝ መከላከያ ሰራዊት አዛዥ ሜጀር ጀነራል መሠለ መሠረት ሰራዊቱ የሀገርን ሉዓላዊነት ከመጠበቅ ባሻገር የሕዝብን ችግሮች የሚቀርፉ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ለአብነትም በመስኖ ልማት፣ በችግኝ ተከላ እና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ ጠቅሰዋል። ለሕዳሴው ግድብም ከ999 ሚሊዮን ብር በላይ የቦንድ ግዥ መፈጸማቸውን ገልፀዋል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ እንደተናገሩት ሰራዊቱ ለሀገር ውስጣዊ አንድነት መጠበቅና ለሉዓላዊነቷ እየሠራ ነው። ትምህርት ቤቱ ሰራዊቱ ቋሚ ሀውልት ለሕዝቡ ያስቀመጠበት እንደሆነም ጀነራል አደም ገልፀዋል።
ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ትምህርት ቤቱ በ10 ወራት እንደተጠናቀቀም ታውቋል። የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ በበኩላቸው ሰራዊቱ ላደረገው አስተዋጽዖ አመሥግነዋል። የሀገርን ዳር ድንበር ከማስከበር ባለፈ በማኅበራዊ አገልግሎትና በተቋማት ግንባታ እያደረገው ያለው ተግባር የሚያስመሰግን መሆኑንም ተናግረዋል።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ በሱዳን የገዳሪፍ ግዛት የሁለተኛ ክፍለ ጦር አዛዥን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ታድመዋል፡፡ ስምንተኛው የኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን "የሀገራችንን ሉዓላዊነትና የሕዝባችንን ሰላም በጽናት እንጠብቃለን" በሚል መሪ መልዕክት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል። በዓሉ በጉና በጌምድር ወረዳ ክምር ድንጋይ ከተማም ከትምህርት ቤቱ ምረቃ ጎን ለጎን ተከብሯል።
ምንጭ: አብመድ

በቡራዩ ከተማ የተከሰተው ምንድን ነው?
በትናትና ዕለት ቅዳሜ የካቲት 7/2012 ዓ.ም በቡራዩ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆቴል ምረቃ ላይ በፀጥታ ኃይሎች ድብደባ ደርሶብናል በማለት አርቲስቶች ለቢቢሲ ገልፀዋል።ድብደባ ደርሶባቸዋል ከተባሉት መካከል አንዷ ሃዊ ኤች ቀነኒ ፊቷ በተደም ተለውሶ እንዲሁም እጇ የተሰበረበት ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር ነበር።ሃዊ ኤች ቀነኒ በፀጥታ ኃይሎች ተደበደበች የተባለው እውነት መሆኑን አረጋግጣ በአሁኑ ወቅት ሃያት ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳለች ለቢቢሲ አስረድታለች።የቡራዩ ፖሊስ በበኩሉ ችግሩ የተፈጠረው ለሆቴሉ ምርቃት የተጠሩ እንግዶች ጎራ ለይተው የዘፈን ምርጫ ላይ ባለመስማማታቸው መሆኑን ገልጿል።
ተጨማሪ 👇👇👇👇
https://telegra.ph/Burayue-02-16