YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በፌደራል ፍርድ ቤቶች ብቻ እንዲታይ ተደርጎ የነበረው የጊዜ ቀጠሮና የዋስትና ጉዳዮች በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች እንዲታዩ ተደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት የስራ ክንውን ሪፖርት እንደሚያሳየው ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ የጊዜ ቀጠሮና የዋስትና ጉዳዮች በፌደራል ፍርድ ቤቶች እንዲታዩ ተደርጎ ቆይቷል፡፡ይህ ተግባር ግን የህጋዊነት መርህን የጣሰና የከተማዋን ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን መሸርሸር በመሆኑ የተጠቀሰው የዳኝነት ስልጣን ለአዲስ አበባ ፍርድ ቤቶች እንዲመለስ ተደርጓል ይላል ሪፖርቱ፡፡

ከፌደራል ፍርድ ቤቶች የስራ ሀላፊዎች እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመነጋገርና መግባባት ላይ በመድረስ ውሳኔ ላይ ተደርሷል ተብሏል። በመሆኑም ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ ስልጣኑ ለአዲስ አበባ ፍርድ ቤቶች ተመልሶ የጊዜ ቀጠሮና የዋስትና ጉዳዮችን ዳግም ማየት ጀምረዋል ተብሏል፡፡

Via Sheger Radio
@YeneTube @FikerAssef
የሆላንዱ ጠ/ሚኒስትር በአይሁዶች ጅምላ ጭፍጨፋ ወቅት ሀገሬ ለነበራት ሚና ይቅርታ እጠይቃለሁ አሉ።

በአለም አቀፍ ደረጃ በሁለተኛ የአለም ጦርነት ወቅት ጅምላ ጭፍጨፋ የተፈፀመባቸው አይሆዶችና ሌሎች አናሳዎች የሚታሰቡበት ቀን ነው ዛሬ፡፡ የፈረንጆቹ ጥር 27 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተመረጠው ደግሞ ትልቁ የናዚ የማጎርያና የሞት ካምፕ ኦሽዊትዝ ፤ በሩሲያ ቀዩ ጦር ተወሮ ፍፃሜ ያገኘበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ይሄንን ቀን በማስመልከት ነው የሆላንዱ ጠ/ሚኒስትር ማርክ ሩቴን አይሁዶችን ይቅርታ የጠየቁት ፤ ይፋዊ ይቀርታ የጠየቁ የመጀመርያው የሆላንድ መሪም ሆነዋል፡፡ከዚህ ቀደም የነበሩ የሆላንድ መንግስታት ከማጎርያ ካምፖች የተረፉ አይሁዶች ወደ መኖርያ ቤታቸው ሲመለሱ ለተስተናገዱበት መንገድ ይቅርታ ቢጠይቁም በሁለተኛው የአለም ጦርነት አይሁዶችና ሌሎች አናሳዎች ላይ ናዚ ላደረሰው ጭፍጨፋ የሆላንድ መንግስት የነበረውን መጥፎ ሚና አንስተው አያውቁም ነበር፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ማስታወቂያ!!

ለአዲስ ቅጥር ተፈታኞች በሙሉ

የፈተኛችሁ ውጤት ከዚህ በፊት የመፈተኛ ቦታችሁን ለማወቅ የተጠቀማችሁበትን የቢሯችን ዌብ ሳይት ማለትም www.addis.gov.et ተጠቅማችሁ ማለፍ እና አለማለፋችሁን ማወቅ የምትችሉና ካለፋችሁም የሚከተሉትን ዝርዝር ተግባራት እንታከናውኑ እናሳውቃለን፡፡

• በፈተናው ማለፍዎንና አለማለፍዎን (Passedor Failed) እንዲሁም ምደባን ለማወቅ ስልክ ቁጥር ወይም ሙሉ ስም በማስገባት መጠቀም ይችላሉ፤
• ፈተናውን ያለፋችሁ ተፈታኞች ከቀን 18/05/2012 ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታተይ የስራ ቀናት የተመደቡበት መስሪያ ቤት (Work Place) ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅብዎታል፤

• ወደ ተመደቡበት መስሪያ ቤት ሲሄዱ ኦሪጂናል እና ፎቶ ኮፒ የትምህርት ማስረጃ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት መታወቂያ ይዘው በመቅረብ የቅጥር ፎርማሊቲዎች ማሟላት ይጠበቅብዎታል፤

• ፈተናዉን አልፋችሁ ምደባ የተሰጣችሁ አመልካቾች በተጠቀሰው ቀን ቀርባችሁ ሪፖርት ማድረግ አለባችሁ :: ሪፖርት ያላደረጋችሁ አመልካቾች በምትካችሁ ተጠባባቂ አመልካቾች የሚተኩ መሆናቸዉን እንገልጻለን፤
• ፈተናውን ያላለፋችሁ ተፈታኞች በቀጣይ ቢሮው በሚያሳውቀው መረጃ መሰረት እንድትከታተሉ እናሳውቃለን፡፡

ምንጭ:- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
@YeneTube @Fikerassefa
በምዕራብ ጎንደር ዞን በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ በአማራ እና በቅማንት ማህበረሰቦች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት ያለመ የዕርቀ ሰላም ኮንፈረንስ ተካሄደ። በኮንፈረንሱ ከ5 ሺህ በላይ የወረዳው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ላለፉት ሁለት አመታት በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ በተከሰቱ ግጭቶች የበርካታ ሰዎች ህይዎት ማለፉ ይታወሳል።

በመድረኩ የተገኙት የ33ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮ/ል ደስታ ተመስገን ወደ ጫካ ወጥተዉ የነበሩ አካላት በአካባቢው በታወጀው የይቅርታ እና የምህረት አዋጅ መመለሳቸው ገልጸው፣ "ከአሁን በኅላ በብሄር ስም የሚነግድ ቡድን ካለ ሊታረም ይገባዋል" ብለዋል።

ምንጭ:- ELU
@YeneTube @Fikerassefa
ሰበር ዜና ❗️❗️

ንብረትነቱ የ #አፍጋን_አሪና_ኤርላይን የሆነ አውሮፕላን ከህርታ ተነስቶ በመብረር ላይ ሳለ አፍጋኒስታን ውስጥ የመከስከስ አደጋ እንደገጠመው የተለያዩ የውጪ ሚዲያዎች ቢያበስሩም #አፍጋን_አሪና_ኤርላይንስ ምንም አይነት የመከስከስ አደጋ አላጋጠመንም ሲል በofficial ፌስቡክ ገፁ አስተባብሏል።

ተጨማሪ መረጃዎች ይዘን እንመለሳለን....
@YeneTube @Fikerassefa
ትናንት ምሽት አመታዊው የግራሚ ሽልማት ስነስርዓት ተካሂዷል!

በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው የአካዳሚ ግራሚ ሽልማት ስነስርዓት ትናንት ምሽት የተካሄደ ሲሆን በትናንትናው እለት በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወቱን ያጣውን የቅርጫት ኳስ ኮከብ ኮቤ ብሪያንን በማሰብ የተጀመረው ፕሮግራም ወጣቷ የፖፕ አቀንቃኝ ቤሊ ኤሊሽ ዋና ዋና በሚባሉት ዘርፎች አሸናፊ አርጓታል ።ከዚህ በታች ዋና ዋና በሚባሉት ዘርፎች ያሸነፉትን ዘፋኞች ዝርዝር እንደሚከተለው አቅርበናል:

📌የአመቱ ምርጥ አልበም: ቢሊ ኤሊሽ "When we all fall asleep, Where do we go?"

📌ምርጥ ጀማሪ አርቲስት: ቤሊ ኤሊሽ

📌ምርጥ የራፕ ፔርፎርማንስ: ዲጄ ካሊድ በኒፕሲ ሃስል እና ጆን ሌጀንድ ታጅቦ "Higher"

📌ምርጥ ዘፈን: ቤሊ ኤሊሽ "Bad Guy"

📌ምርጥ የራፕ አልበም: ታይለር ዘ ክሪኤተር "IGOR"

📌ምርጥ ኮሜዲ አልበም: ዴቭ ቻፔል "Sticks and Stones"

📌ምርጥ የጣምራ ፔርፎርማንስ:ዳን እና ሻይ "Speechless"
.
.
.
ስነስርዓቱ በኮቤ ብሪያን ያልተጠበቀ ህልፈት ብዙ ትኩረት ማግኘት ባይችም አሪያና ግራንድ፣ አሸር፣ እንዲሁም ዲጄ ካሊድ ስራቸውን መድረክ ላይ በማቅረብ አድምቀውታል።የመድረክ መሪዋ ደግሞ አሊሻ ኪስ ነበረች።

@YeneTube @FikerAssefa
"የኮሮና ቫይረስ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ ለመከላከል በቦሌ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ የተሟላ ምርመራ እየተደረገ ነው " የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ
በቻይና የተከሰተው "የኮሮና" ቫይረስ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ቀድሞ ለመከላከል የተለየ የምርመራ ክፍል ተዘጋጅቶ በተሟላ የምርመራ መሳሪያ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡

በቻይና የተከሰተው "የኮሮና" ቫይረስ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ለመከላከል በቦሌ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ ወደ አገር ውስጥ ለሚገቡ ተጓዦች ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የማህበረሰብ ጤና ቁጥጥር ባለስልጣን ከኢትዮጵያ የማህበረሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ጋር በመተባበር ከቻይና እና የበሽታው ምልክት ከታየባቸው አገራት የሚመጡ ተጓዦች ምርመራ የሚደረግበት የተለየ ክፍል ተዘጋጅቶ የተሟላ የምርመራ አገልግሎት እየተከናወነ እንደሚገኝ ምክትል ከንቲባው አመልክተዋል፡፡

ምንጭ:- ከንቲባ ፅ/ቤት
@YeneTube @Fikerassefa
በሀረሪ ክልል በጥምቀት በዓል አከባበር ላይ ተፈጥሮ ከነበረው ሁከት ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ 87 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።

ከበአሉ አከባበር ጋር የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ከሐይማኖትም ሆነ ከብሔር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ቢሮ አያይዞ ገልጿል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ናስር ዩያ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ባሳለፍነው ሳምንት ከጥምቀት በአል አከባበር ጋር ተያይዞ ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

ድብቅ የፖለቲካ አላማ ያላቸው አካላት በፈጠሩት የፀጥታ ችግር ምክንያትም የአንድ ሰው ህይወት ማለፉንና ሰባት ሰዎች መቁሰላቸውን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የ11 ህንፃዎች መስታወት የተሰባበረ ሲሆን አንድ የኮካኮላ ማከፋፈያና አንድ ተጨማሪ ህንፃ መቃጠላቸውን ገልጸዋል።

ሁለት መኪኖች እና አራት ባጃጆች ጭምር በሀከቱ መቃጠላቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።

Via:- EBC
@YeneTube @FikerAssefa
በአፍጋኒስታን የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ

በምሥራቅ አፍጋኒስታን አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን መከስከሱን ባለስልጣናት ገለጹ።
ከዋና ከተማዋ ካቡል ደቡብ ምዕራብ በምትገኘው የጋዝኒ ግዛት ውስጥ ደህ ያክ በተባለ ቦታ አውሮፕላኑ መከስከሱን የአካባቢው ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም አውሮፕላኑ በቴክኒክ ችግር ምክንያት መከስከሱንና በእሳት መያያዙን ገልጸዋል።

መጀመሪያ ላይ አውሮፕላኑ ዘ አሪያና የተባለው አየር መንገድ ንብረት እንደሆነ ቢነገርም በኋላ የወጡ መረጃዎች ደግሞ አየር መንገዱ አውሮፕላኑ የእኔ አይደለም ማለቱን የሚያትቱ ናቸው።

"የአሪያና አውሮፕላኖች ሁሉም በሰላም ደርሰዋል። ይህ ማለት የተከሰከሰ የአሪያና አውሮፕላን የለም ማለት ነው" ይላል ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በወጡ መረጃዎች።
አውሮፕላኑ በእሳት መያያዙም እየተነገረ ነው። ለጊዜው የተጎጂዎች ማንነትም ሆነ ቁጥር አልተገለጸም።

ምንች:- ቢቢሲ
@YeneTube @Fikerassefa
“የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና የፌደራል መንግስት በታገቱ ሴት ተማሪዎች ዙሪያ ቸልተኝነት አሳይተዋል” የምዕራብ ጎጃም ዞን ዞኑ ከደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ በታገቱ ተማሪዎች ዙሪያ ዛሬ ከስዓት መግለጫ ሰጥቷል።

ከታገቱት ተማሪዎች ውስጥ 5ቱ የዞኑ ተወላጆች መሆናቸውን ከወላጆቻቸው ማረጋገጥ መቻሉን ያስታወቀው የምዕ/ጎጃም ዞን፣ የአማራ ክልላዊ መንግስት በፌደራልና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ላይ ጫና እንዲፈጥር ግፊት እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡

Via:- ELU
@YeneTube @Fikerassefa
የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ደምቢዶሎ ዩንቨርስቲ እየመከሩ ይገኛሉ።

በሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል የተመራው የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ እና ከአካባቢው ማኅበረሰብ፣ ከጸጥታ አካላት እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር እየተወያየ መሆኑን አማራ ማስ ሚዲያ ዘግቧል።

ጋዜጠኞችም አብረው እንደተጓዙ ከELU ተመልክተናል።
@YeneTube @Fikerassefa
የታገቱ ተማሪዎችን በተመለከተ 5 በሰብዐዊ መብቶች እንዲሁም በሴቶች ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች መግለጫ አውጥተዋል።

#Bringbackourhgirls
#Bringbackourhgirls
#Bringbackourhgirls
#Bringbackourhgirls
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት ጠየቀ።

ዓለም አቀፍ የአማራ ኅብረት የአደረጃጀት ጉዳይ ተጠሪ አቶ ደህናሁን እምሩ እንደገለጹት በፀጥታ ስጋት ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ የታገቱ የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉዳይ እልባት ሊሰጠው እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡ ዓለም አቀፍ የአማራ ኅብረት ድርጊቱን እንደሚያወግዘውም ነው የተናገሩት፡፡ የተማሪ ወላጆችና ሕዝቡ እየተጨነቁ ባሉበት በዚህ ወቅት መንግሥት ዝምታን መምረጡ ተገቢነት የለውም ብሏል ኅብረቱ፡፡

ስለ ጉዳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ማብራሪያ ሊሰጡ እንደሚገባም ጠይቋል፡፡ መንግሥት ተማሪዎቹ ተለቅቀዋል ብሎ ከዚህ ቀደም መግለጫ ስለሰጠበት ጉዳይም በአደባባይ ለሕዝብ ማሳወቅ እንዳለበት አቶ ደህናሁን ተናግረዋል፡፡ ኅብረቱ በታገቱ ተማሪዎችና እየደረሱ ባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ በዋሽንግተን ዲሲ ትናንት ሲመክር መቆየቱንም አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ:- አብመድ
@YeneTube @Fikerassefa
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የነባር ተማሪዎች የ1ኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን እና የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች መደበኛ የመማር ስራ ለጊዜው የተቋረጠ መሆኑን አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮምያ በተለያዩ ዞኖች ቅዳሜና እሁድ ብቻ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ደጋፊዎች የሆኑ ቢያንስ 75 የሚጠጉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አረጋግጧል፡፡

⬇️⬇️ዘገባውን ይመልከቱ ⬇️⬇️


https://www.amnesty.org/en/latest/news/2020/01/ethiopia-authorities-crack-down-on-opposition-supporters-with-mass-arrest
የተጠራው ሰልፍ ፍቃድ አግኝቷል...

በኦሮምያ ክልል ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የታገቱን የዩንቨርስቲ ተማሪዎችን ድርጊት ለማውገዝ የተጠራው ሰልፍ ተፈቅዷል።

#ሼር #Share
#Amharapolicecommission
@YeneTube @Fikerassefa