#ሹፌሩ_ነው_በስልክ_ተደዋውሎ_አሳልፎ_የሰጠን
በደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር ተከትሎ ወደ ጋምቤላ በመጓዝ ላይ የነበሩ 18 የተማሪዎችን ለአጋቾች አሳልፎ የሰጠው የአውቶቡስ አሽከርካሪ እንደነበረ ከእገታው ያመለጠችው ተማሪ ተናገረች፡፡
ተሳፍረውበት የነበረው የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ምን ያህል ሰው እንደሚጭን ባታስታውስም፤ ሌሎች ተማሪዎችን ጨምሮ የአካባቢውን ህብረተሰብ ያሳፈረ መኪና ነበር፡፡ መኪናው ከጫናቸው ሰአት ጀምሮ ስልክ ቢያወራም ቋንቋ ባለማወቃቸው ከጥርጣሬ ያለፈ እርምጃ እንዳይወስዱ እንዳደረጋቸውም ትናገራለች፡፡
ከዛም ሱድ አካባበ ሲደርሱ በቁጥር ከሃያ የሚበልጡ አካለቸው በጣም ግዙፍ ከሆኑ ወጣቶች ጋር ሲደርስ ሹፌሩ ውረዱ ብሎ እንዳስወረዳቸውና ጥሏቸው እንደሄደ ገልፃለች፡፡
በወቅቱ አንድ ሰውዬ እያለቀሰ አትውሰዷቸው ብሎ እንደለመነላቸው እና ነገር ግን ወጣቶቹ በጣም ስላስፈራሩት ተስፋ ቆርጦ እንደሄደ ተናግራለች፡፡
ሌሎች የኦሮሚያ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ወጥተው ሱድ እስኪደርሱ ባለው ግዜ አደጋ እንዳይደርስባቸው ሲጠብቋቸው እንደነበረ የምትናገረው ወጧቷ ‹‹አጋቾች ሊወስዱን ሲሉም እነዚህ ጓደኞቻችን ለምነውልናል›› ብላለች፡፡
ነገር ግን ምን እንደተባባሉ ባለውቅም በሃይለ ቃል የሆነ ነገር ካሏቸው በኋላ ደንግጠው ጥለውን ሄዱ›› ስትል ለአዲስ ማለዳ ተናግራለች፡፡
ከታገገቱት ጓደኞቿ ጋር እስከተለያየችበት ግዜም በጫካው አካባቢ የተወሰኑ ትናንሽ መንደሮች እንዳጋጠሟቸው ተናግራ ምንም እርዳታ ሊያደርግላቸው የፈለገ አካል እንዳልነበረ ግን ገልፃለች፡፡
Via:- Addis Maleda
@YeneTube @Fikerassefa