YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአማራ ዴሞክራሲዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) በመጪው ምርጫ እንደሚሳተፍ አስታወቀ፡፡

የአዴኃን ሊቀመንበር አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ በዛሬዉ ዕለት ለዶቼ ቬለ (DW)እንደገለፁት ንቅናቄው በመጭዉ ምርጫ ለመሳተፍና በምርጫው ብቁ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የቅድመ ዝግጅት ሥራ እያከናወነ ነዉ።ንቅናቄዉ እስካሁን በጎንደር፣ በወልዲያና በጎጃም አንዳንድ አካባቢዎች ዓላማና ፕሮግራሙን ማስተዋወቁንም አቶ ተስፋሁን ገልፀዋል።ሊቀመንበሩ አያይዘውም በምርጫ ሊወዳደሩ የሚችሉ አባሎቻችንን ለይተን በመምረጥ የማብቃት ሥራ እየተሰራን ነዉ ብለዋል።

ለዚህም «የተሸለ ግንዛቤ ያላቸውን፣ የተሻለ ተሰሚነት ላቸውን፣ የኅብረተሰቡን ጥያቄ ሊመልሱ የሚችሉና በኅብረተሰቡ ዘንድ ተሰሚነት ያላቸውን አባሎቻችንን እየመረጥን ሰፊ እንቅስቃሴ እደረግን እንገኛለን” በማለት ተናግረዋል፡፡« ሊበራል» የፖቲካ ፍልስፍና እከተላለሁ የሚለው አዴኃን የኢትዮጵያን መንግስት በትጥቅ ትግል ለማስወገድ ለ8 ዓመታት በኤርትራ የቆየ ሲሆን በአገሪቱ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ ከአንድ ዓመት በፊት ወደ አገር ውስጥ የገባ ድርጅት ነው፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
“የሽግግር መንግስት” ይመስረት ያሉ 3 ፓርቲዎች በጋራ ሊሰሩ ነው።

Via:- Al Ain
@Yenetube @Fikerassefa
ኅብረት ባንክ የብድር ወለድ ምጣኔውን ቀነሰ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግል ባንኮች በአስገዳጅነት ሲተገብሩት የነበረውን የ27 በመቶ የቦንድ ግዥ መመርያ ካነሳ በኋላ፣ ባንኮች ለብድር ያስከፍሉ የነበረውን የወለድ ምጣኔ እየቀነሱ ሲሆን፣ ኅብረት ባንክም እስከ 4.5 በመቶ የብድር ወለድ ምጣኔውን መቀነሱን አስታውቋል፡፡ባንኩ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ ከሚያደርገው ከዚህ ውሳኔ ጎን ለጎን ከሌሎች ባንኮች በተለየ ከ27 በመቶ መመርያ ጋር ተያይዞ ተግባራዊ አድርጎ የነበረውን የሦስት በመቶ የብድር ቅጣት አብሮ ማንሳቱንም አስታውቋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
በኢራቅ አንድ ከፍተኛ የሚሊሻ መሪ አሜሪካ ለወሰደችው የአየር ጥቃት በኢራቅ በሚገኙ ወታደሮቿ ላይ ከባድ አፀፋ ሊወሰድ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡

Via:- Al Ain
@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ በመጭው ግንቦት አክሲዮን ገበያ ልትጀምር እንደምትችል ብሄራዊ ባንክን ጠቅሶ ካፒታል ጋዜጣ አስነብቧል፡፡ ብሄራዊ ባንክ አክሲዮን ገበያው የሚመራባቸውን ደንቦች እያዘጋጀ ነው፤ ደንቦቹ በቅርቡ ለሚንስትሮች ምክር ቤት ይቀርባሉ፡፡ ገበያው በአዋጅ እንዲመራ መንግሥት ከወሰነ ግን ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ የሚያወጣ ይሆናል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በአርባምንጭ oilibya ነዳጅ ማደያ ድንገት ቤንዚል ወደ ታንከር በመገልበጥ ላይ እያለ የተነሳ እሳት በድርጅቱ ሠራተኞች ርብርብ fire extinguisher/ በእሳት ማጥፊያ ዱቄት በመጠቀም በቁጥጥር ውሏል።

አደጋው ሊነሳ የነበረው ከነተጎተታቹ ቤንዚል የጫነ ቦቲ መኪና 10 ሠዓት ከ37 አካባቢ ነዳጅ በማራገፍ ላይ እያለ የተነሳ እሳት በድርጅቱ ሰራተኞች ጠፍቷል።

የድርጅቱ ሠራተኞች በፍጥነት የእሳት ማጥያ ኬሚካል ባይጠቀሙ ኖሮ የሚደርሰው አደጋ ከፍተኛ ነበር።

Via:- Gamo Zone Administration public Relation office
@Yenetube @Fikerassefa
ወለጋ ዩንቨርስቲ አስቸኳይ ማስታወቂያ

ለአራት ሳምንታት የተቋረጠው ትምህርት እስከ ረቡዕ ታህሳስ 22 /04/2012 ድረስ ትምህርት የማይጀመር ከሆነ :-

የክሪላንስ ፎርም በመሙላት እጃችሁ ላይ ያለውን ማንኛውንም የዩንቨርስቲ ንብረት በመመለስ ግቢውን ለቃችሁ መውጣት ትችላላችሁ።

- ሙሉውን ከፎቶው ላይ ያንብቡ
@Yenetube @FikerAssefa
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአምባሳደር ማይክል ራይነር ጋር ተወያዩ!

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑትን ሚስተር ማይክል ራይነር ዛሬ ታህሳስ 20 ቀን 2012 ዓ. ም በጽ/ ቤታቸው ተቀብለው በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። አቶ ገዱ በዚህ ወቅት እንደገለፁት በኢትዮጵና በአሜሪካ መካከል ያለው ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሁለቱን አገራት የጋራ ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር ለዘመናት የዘለቀ መሆኑ አንስተዋል። አሜሪካ በኢትዮጵያ በትምህርት፣ በጤና፣ በሰብአዊ ልማት እና በሌሎች ዘርፎች እያደረገችው ያለውን ድጋፍ ክቡር አቶ ገዱ አድንቀዋል።

ሁለቱ አገሮች በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን በበርካታ ጉዳዮች በትብብር እየሰሩ መሆኑን አስታውሰው፤ ይህንኑ አጠናከሮ ለማስቀጠል በሁሉም ወገን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።ክቡር አምባሳደር ማይክል ራይነር በበኩላቸው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሁሉን አቀፍ ለውጥ አድንቀዋል። ኢትዮጵያ በቀጠናው እያደረገች ያለውን አስተዋጽኦ አሜሪካ ታደንቃለችም ብለዋል። አሜሪካ በኢትዮጵያ የተጀመረው ለውጥ ግቡን እንዲመታ ድጋፏን አጠናከራ እንደምትቀጥልም ገልጸዋል። የሁለቱን አገሮች ህዝቦች ጥቅም ለማስጠበቅ የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉም አምባሳደሩ አረጋግጠዋል።

ምንጭ: ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
ጀዋር መሀመድን በመተካት አቶ ግርማ ጉተማ የOMN ስራ አስኪያጅ ሆነዋል።

ይህ ሹመት በቀጥታ ጃዋር መሀመድ ወደ ኦፌኮ መግባትን ተከትሎ የተደረገ እንደሚሆን ተገምቷል።
@Yenetube @Fikerassefa
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
መልካም ቀን ይሁንላችሁ !!
«አቶ ጀዋር መሐመድ ኦፌኮን በአባልነት መቀላቀላቸው ዛሬ የተፈጠረ ሳይኾን ለረዥም ጊዜ ፓርቲውን ሲደግፉ ከቆዩ በኋላ የተፈጸመ ነው»

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለOBN Oromiyaa ከተናገሩት የተወሰደ
@YeneTube @FikerAssefa
ታህሳስ 9 ቀን ከጠገዴ ወረዳ ከብት በመጠበቅ ላይ በነበሩበት ወቅት በታጣቂዎች ከታገቱ 8 ታዳጊዎች መካከል 6ቹ በአጋቾቻቸው መገደላቸው ተነገረ። ታዳጊዎቹ የተገደሉት አጋቾች በአንድ ሰው የጠየቁትን 100ሺህ ብር ወላጆች መክፈል ባለመቻላቸው ነው።

ከ8-15 ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት ታደጊዎች ከጠገዴ ወረዳ ዳውጨና ቀበሌ ወደ ታች አርማጭሆ ወረዳ ከተወሰዱ በኅላ በትናንትናው ዕለት ነበር በጥይት ተመተው የተገደሉት። ከሟቾቹ መካከል የ4ቱ አስከሬን አሰሳ በሚያደርጉ የመንግስት ሚኒሻዎች ተገኝቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
አንጀሊና ጆሊ ከፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ጋር ውይይት አድርጋለች፡፡

እሁድ አዲስ አበባ የገባችው አንጀሊና ጆሊ በብሄራዊ ቤተመንግስት ከፕሬዝደንቷ ጋር በልማት፣ በሴቶች እና በስደተኞች ጉዳይ ላይ የሀሳብ ልውውጥ አድርጋለች፡፡በዚህም ወቅት ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ "የአንጀሊና ጆሊ ጉብኝት ኢትዮጵያ በአስገራሚ የለውጥ ጎዳና ላይ ባለችበትና የሴቶችን ጉዳይ ጨምሮ በሁሉም መስኮች አዲስ ምዕራፍ እየተከፈተ ባለበት ወቅት የተደረገ በመሆኑ ጉብኝቱ ስለ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ስለ አፍሪካ ያለውን አተያይና አስተሳሰብ ለመለወጥ የማይናቅ አስተዋፅዎ አለዉ፡፡" ብለዋል በሰብዐዊ ስራዎቿ የምታወቀው አንጀሊና በበኩሏ "ወደኢትዮጵያ የመጣሁት በህጻናትና ሴቶች እንዲሁም ጤና ላይ መስራት የሚቻልባቸውን እድሎች ለማየት ነው" ብላለች::አንጀሊና ወደ ኢትዮጵያ የመጣችዉ ከልጆቿ ጋር ሲሆን ከእነርሱም መካከል የ14 አመቷ ዘሃራ በትውልድ ኢትዮጵያዊት ነች።

ምንጭ: የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
era vacancy.pdf
91 KB
ዛሬ የወጣ የስራ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የውጭአመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል ።

91ኪሎ ባይት ናት download አድርጋችሁ በውስጡ ብዙ የዝራ ዝርዝር አለ ተመልከቱት።

@YeneTube @fikerassefa
በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ጉዳት ደረሰ!

በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉን ተከትሎ በአምቦ ዩኒቨርሲቲም በተማሪዎችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት አሥር ተማሪዎችና ሦስት የፀጥታ አካላት መቁሰላቸውን የዩኒቨርሲቲው ሪፈራል ሆስፒታል ገለፀ። የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴር "አለመረጋጋት ተፈጥሮባቸው ከነበሩ 22 ዩኒቨርስቲዎች ከ7 ውጭ ሌሎቹ ተረጋግተዋል" ብሏል።የቀሩትም ተረጋግተው ወደ ቀድሞ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲመለሱ የኅብረተሰቡን ትብብር ጠይቋል።

Via VOA
@YeneTube @FikerAssefa
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ትምህርት እንደሚጀምር የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከሰሞኑ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አንድ የሶስተኛ አመት ተማሪ ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲው ከትናነት ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የመማር ማስተማር ስራውን ማቋረጡን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ይህንን ውሳኔ ተከትሎም ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው እንዲወጡ ሁነዋል፡፡ኢትዮ ኤፍ ኤም ለመሆኑ የዩኒቨርሲቲው የመዘጋት ውሳኔ እስከ መቼ ድረስ ሊቀጥል ይችላል ሲል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል፡፡የሚኒስትሩ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ደቻሳ ጉርሙ በአሁኑ ሰዓት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በስተቀር ሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማስተማር ስራቸው ላይ ናቸው፤ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲም እንዲዘጋ የወሰነው ጊዜያዊ ችግሮች እስከሚፈቱ ድረስ እንጂ አመቱን ሙሉ አይደለም ብለዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ተማሪዎች እስከ ነገ ረቡዕ ድረስ ትምህርት የማይጀምሩ ከሆነ ተቋሙ ሊዘጋ እንደሚችል ወለጋ ዩኒቨርስቲ አስታወቀ።

@YeneTube @FikerAssefa
ለስልኮች የፊት ገጽ ማጠንከሪያ ተብሎ አገልግሎት ላይ እየዋለ ያለው የናኖ ቴክኖሎጂ ፈሳሽ ተፈትሾ ችግር አልተገኘበትም ብሏል የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን

ለስልኮች የፊት ገጽ ማጠንከሪያ ተብሎ አገልግሎት ላይ እየዋለ ያለው የናኖ ቴክኖሎጂ ፈሳሽ ተፈትሾ በሰው፣ በአካባቢ እና በንብረት ላይ ጉዳት የማያስከትል ስለመሆኑ መረጋገጡን የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ አቶ አወቀ ሺፈራው በተለይ ለኢቲቪ እንደገለፁት መሥሪያ ቤታቸው በደረሰው ጥቆማ መሠረት ለስልኮች የፊት ገጽ ማጠንከሪያ ተብሎ አገልግሎት ላይ እየዋለ ያለው የናኖ ቴክኖሎጂ ፈሳሽ ላይ ፍተሻ አድርገዋል።

በመሥሪያ ቤቱ ባለሞያዎች በተደረገ ምርመራ ስልኮች ላይ የሚቀባው ፈሳሽ ምንም ዓይነት ጨረራ የማያመነጭ እና ችግር የማያስከትል ስለመሆኑ አመልክተዋል።የናኖ ፈሳሽ ቴክኖሎጂውን የተለያዩ አስመጪዎች ወደ አገር ውስጥ እንደሚያስገቡት የጠቆሙት፣ አቶ አወቀ መሥሪያ ቤታቸው አስመጪዎች ማናቸውም ዕቃዎች ከውጭ ማስገባታቸውን ለተቋማቸው ሲያሳውቁ ብቻ ፍተሻ የሚያደርጉ መሆኑን ከዚህ ባለፈ ግን ወጪ እና ገቢ ዕቃዎችን የሚመለከተው ገቢዎች ባለሥልጣን እንደሆነ በአጽንኦት ተናግረዋል።

ምንጭ: ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
አባይ ባንክ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የዲጂታል ክፍያ መላዎችን ጀመርኩ አለ፡፡

ባንኩ ከአየር መንገዱ ጋር የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት መላዎችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ሀላፊዎች ጋር ተፈራርሟል፡፡ለዚሁ መላ የባንኩ ደንቦች በኦንላይን ባንኪንግ በመጠቀም ትኬት መቁረጥ ይችላሉ፡፡ ሌሎችም አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላሉ መባሉን ሰምተናል፡፡አባይ ባንክ አገልግሎቱን በጀመረ በአንድ ሳምንት ውስጥ 1 ሚሊየን ገደማ ጥሪት መንቀሳቀሱን የስራ ሀላፊዎች ተናግረዋል፡፡በተያያዘም፣ ይህንኑ አገልግሎት ከአማርኛ በተጨማሪ በሁለት የአገር ቤት ቋንቋዎች ማግኘት ይቻላል ተብሏል፡፡ የባንኩ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች 125 000 የደረሰ ሲሆን አጠቃላይ የደንበኞቹ ቁጥርም 700 000 እንደደረሰ ሰምተናል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa