በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ በተሰማሩ አካላት እስከሞት ቅጣት የሚያደርስ ህግ እየረቀቀ መሆኑን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብት ኮሚሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በሰው የመነገድና ሕገ-ወጥ ድንበር የማሻገር ወንጀል ለመከላከል ረቂቅ ሕጉ አስፈላጊ ቢሆንም፤ የሞት ቅጣት መያዙ ግን ስህተት ነው፡፡ የሞት ፍርድ ጨካኝና ኢሰብዓዊ የሆነ ሊመለስ የማይችል ቅጣት በመሆኑ ተፈጻሚነቱ ሊታቀብና ለወደፊቱም ሊቀር ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
👎1
ምርጫ ቦርድ ለብልፅግና ፓርቲ የእውቅና ሰርተፊኬት ለመስጠት ወሰነ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእውቅና ጥያቄ እና፣ የፓርቲ መለያ ሰንደቅ አላማ የማጸደቅ ጥያቄን ያቀረቡ ፓርቲዎችን ጉዳይ አይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በዚህም መሰረት
1.የኢህአዴግ አባል የነበሩ ሶስት ፓርቲዎች እና ሌሎች አምስት ፓርቲዎች በጋራ ራሳቸውን በማክሰም ብልጽግና ፓርቲን መመስረታቸውን በማሳወቅ የእውቅና ሰርተፍኬት እንዲሰጣቸው ህዳር 24 ቀን 2012 ዓ.ም በጽሁፍ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረቡ ሲሆን ቦርዱም ጥያቄያቸውን በፓለቲካ ፓርቲዎችና ምርጫ አዋጅ 1162/2011 መሰረት መርምሮ ውሳኔውን ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት ቦርዱ የእውቅና ጥያቄ ከቀረበለት በኋላ በተጨማሪ መሟላት ያለባቸውን ሰነዶች በታህሳስ 01 ቀን 2012 ዓ.ም በመጠየቅ በጥያቄውም መሰረት ታህሳስ 06 ቀን 2012 ዓ.ም የጥያቄዎቹ ምላሾችና ማብራሪያዎች ተሟልተው መቅረባቸውን በማረጋገጡ ብልጽግና ፓርቲን ለመመስረት
1. የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ( ኦዴፓ)፣
2.የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች
ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን)፣
3.የሃረሪ ብሔራዊ ሊግ (ሐብሊ)፣
4.አማራ ዴሞክራያዊ ፓርቲ ( አዴፓ) ፣
5. የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶህዴፓ)፣
6. የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ፣
7.የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ (ጋህአዴን)
8.የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ( ቤጉህዴፓ)
በተናጠል በጠቅላላ ጉባኤያቸው ውሳኔ መሰረት አድርገው ውህደቱን ለመቀላቀልና ፓርቲያቸውን ለማክሰም የወሰኑት ውሳኔዎች እንዲሁም ውህደቱን ለመመስረት ያደረጉትን ስምምነት በሙሉ ህጉን ተከትሎ የተፈጸመ በመሆኑ ቦርዱ ፓርቲዎቹ ተሰርዘው ብልጽግና ፓርቲ የእውቅና ሰርተፍኬት እንዲሰጠው ወስኗል፡፡በዚህም መሰረት ውህዱ ፓርቲ በአዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 92/2 መሰረት በተመዘገበ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ውህደቱ ያስገኘውን ሃብትና ንብረት እና እዳ የሚያሳይ የሂሳብ ሪፓርት ለቦርዱ እንዲያቀርብ በውሳኔው ውስጥ ተካቷል፡፡
2.የኦሮሞ ብሔራዊ ፓርቲ በምዝገባ ወቅት ያቀረበው ሰንደቅ አላማ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ጋር ይመሳሰላል በሚል በቦርዱ የቀረበለትን ጥያቄ እንደማይመሳሰል በመግለጽ ልዮነቱን አብራርቶ ቦርዱ እንዲቀበለው ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ቦርዱ በሁለቱ ሰንደቅ አላማዎች መካከል አለ የተባለውን ልዩነት መርምሮ የኦሮሞ ብሔራዊ ፓርቲ የጠቀሳቸው ልዮነቶች ለማስተዋል የሚያስቸግሩ በመሆናቸው እና ድምጽ ሰጭዎችን የሚያምታቱ ሆነው ስለሚገኙ ሰንደቅ አላማውን ቀይሮ በማቅረብ ምዝገባውን እንዲያጠናቅቅ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
3.እናት ፓርቲ በሚል አገር አቀፍ ፓርቲ ለማቋቋም በሂደት ላይ ያለ ፓርቲ በአዋጅ 1162/ 2011 መሰረት ጊዜያዊ የእውቅና ሰርተፍኬት እንዲሰጠው ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ በአዋጁ ላይ የተቀመጠውን ጊዜያዊ ሰርተፍኬት መውሰጃ መስፈርት በማሟላቱ እናት ፓርቲ የጊዜያዊ እውቅና ሰርተፍኬት እንዲሰጠው ቦርዱ ወስኗል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ነገ ሐሙስ ታህሳስ 16 ቀን 2012 ዓ.ም በመላው ኢትዮጵያ ከፊል የፀሀይ ግርዶሽ (ፓርሻል ሶላር ኢክሊፕስ) እንደሚታይ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ አስታወቀ፡፡
የፀሀይ ግርዶሹ ከጠዋቱ 12፡37 እስከ ጠዋቱ 1፡26 የሚቆይ እንደሆነ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ቤዛ ተስፋዬ አስታውቀዋል፡፡የፀሀይ ግርዶሹ ለኳታር፣ ህንድ፣ ፊሊፒንስ፣ ማሌዥያ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ እስከ 94 በመቶ ፀሀይ እንደምትሸፈን ታውቋል፡፡በዓለማችን የፀሀይ ግርዶሽ በየሁለት አመቱ ሊከሰት የሚችል ክስተት ሲሆን ሰው በትክክል ሊያይበት በሚችለው ቦታ የሚከሰተው በአራት መቶ አመት አንድ ጊዜ ነው፡፡ከፊል የፀሀይ ግርዶሹን ለመመልከት ወደ ፀሀይ ያለ መከላከያ ፊልተር እንዳይመለከቱ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ማሳሰቡን ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡
Via Walta

የአማራ ወጣቶች ማህበር በሞጣ በታቀጠለው መስጊድ መልሶ ግንባታ እሳተፋለው ብሏል።
ማህበሩ ዛሬ ባህርዳር ባደረገው ስብሰባ በሞጣ በተቃጠለው መስጊድ ተቃውሞውን ገልፆ መስጆዶችን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ስራም እገዛ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል።
Via Tesfaye Getinet
@YeneTube @FikerAssefa
ማህበሩ ዛሬ ባህርዳር ባደረገው ስብሰባ በሞጣ በተቃጠለው መስጊድ ተቃውሞውን ገልፆ መስጆዶችን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ስራም እገዛ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል።
Via Tesfaye Getinet
@YeneTube @FikerAssefa
ለሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ማሰባሰቢያና ለሲ ኤን ኤን የዓመቱ ጀግና ፍሬወይኒ የአቀባበል መርሃ ግብር ሊካሄድ ነው!
በአዲስ አበባ ከተማ በመንግስት ትምህርት ቤት ለሚማሩ ሴት ተማሪዎች ሞዲስ እና ሌሎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በነጻ ለማቅረብ የከተማ አስተዳደሩ ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል። በዚሁ መሰረት የፊታችን ታህሳስ 28 ቀን 2012ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የቁሳቁስ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር መዘጋጀቱን አስተባባሪዎቹ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።በመርሃ ግብሩ 700 ሺህ ሞዴስ…
Via FBC

"ድርጅታችን ብልፅግና ፓርቲ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የእውቅና ሰርተፊኬት በማግኘቱ የድርጅታችን አባላት እና ደጋፊዎች" እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን"
--- ብልፅግና ፓርቲ---
@Yenetube @Fikerassefa
--- ብልፅግና ፓርቲ---
@Yenetube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በዓለም ተፅዕኖ ከፈጠሩ 50 ግለሰቦች አንዱ ሆኑ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ በፋይናንሺያል ታይምስ ጋዜጣ ከፈረንጆቹ 2010-2019 በነበሩት 10 ዓመታት በዓለም ላይ ለውጥ በማምጣት ከተጠቀሱት 50 ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ዝርዝር ተካትተዋል።
1ኛ) በፖለቲካው መስክ፦
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ቱኒዚያዊው ሞሃመድ ቡአዚዝ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜሪከል የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሳዑዲው አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሃመድ ቢን ሳልማን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቻይናው መሪ ዢ ዥንፒንግ እና ሌሎችም ተካትተዋል።
2ኛ) በምጣኔ ሀብት፣ በቢዝነስና በቴክኖሎጂ፦
የአማዞን ኩባንያ ባለቤት ጄፍ ቤዞስ የአፕል ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቲም ኩክ ቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ የአውሮፓ ማዕከላዊ ባንክ ፕሬዚዳንት ክርስቲን ላጋርድ ቻይናዊው ስራ ፈጣሪ ባለሃብት ጃክ ማ የፌስቡክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ እና ሌሎችም ተካትተዋል።
3ኛ) በባህል፣ በሚዲያ፣ በስፖርት እና በሳይንስ ዘርፍ፦
ሊዮኔል ሜሲ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ
አሜሪካዊቷ ሙዚቀኛ ቴይለር ስዊፍት የሜዳ ቴኒስ ንግስቷ ሴሬና ዊሊያምስ እና ሌሎችም ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ተካትተዋል።
ምንጭ፡-ኢፕድ

የዶክተር አምባቸው ፋውንዴሽን ሊቋቋም ነው፡፡
በሰኔ 15 ጥቃት ሕይወታቸው ያለፉ የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች 6ኛ ወር መታሰቢያ በአዲስ አበባ ማምሻውን ተካሂዷል፡፡ በመታሰቢያ መርሀ ግብሩም በቀድሞው የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አምባቸው መኮንን (ዶክተር) ሥም ፋውንዴሽን ለማቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩ ይፋ ተደርጓል፡፡በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የዶክተር አምባቸውን ራዕዮች እውን ለማድረግ ፋውንዴሽኑ መቋቋሙ አስፈላጊ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ ‹‹በማንኛውም ሰዋዊ ተግባር መልካም የሠራን ማስታወስና ሥራውን መዘከር ተገቢ ነው፡፡ይህንንም ሐሳብ ለማሳካት ለፋውንዴሽኑ እውን መሆን የሚያስፈልጉ ድጋፎችን ማድረግ ይገባናል›› ብለዋል፡፡
ፍትሕንና እውነትን እስከ መጨረሻው የመፈለግ ጉዳይ፣ የዶክተር አምባቸው ራዕዮች እውን እንዲሆኑ የመደገፍና በሐዘኑ ወቅት ቃል እንደተገባው ቤተሰቦቻቸውን ለትልቅ ዓላማና ወግ ማዕረግ ማብቃት ከሁሉም እንደሚጠበቅም አቶ ደመቀ አስገንዝበዋል፡፡የዶክተር አምባቸው ልጅ መዓዛ አምባቸውም በመተሳቢያው ላይ መልዕክት አስተላልፋለች፡፡ ‹‹የአባቴን ዓላማ ለማሳካት ፋውንዴሽኑ ይቋቋማል፤ አባቴ ለተልዕኮና ዓላማ ተገዥ ነበር›› ያለችው መዓዛ ፋውንዴሽኑም ለመሠል ተልዕኮ እንደሚቋቋም አስታውቃለች፤ ለፋውንዴሽኑ እውን መሆን እየለፉ ያሉ አካላትንም አመሥግናለች፡፡ፋውንዴሽኑ እንደሚመሠረት በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል በተዘጋጀው የ6ኛ ወር መታሰቢያ ላይ ዛሬ ይፋ ይደረግ እንጅ ዝርዝር የፋውንዴሽኑ ተግባራትና ሌሎች ጉዳዮች በ1ኛ ዓመት መታሰቢያቸው ላይ እንደሚገለጹ ነው መዓዛ አምባቸው የተናገረችው፡፡
Via AMMA

👍1
ዶክተር አሚር የኢትዮጵያን ህዝብ አመሰግነዋል። በቀጣይ ሀገሬን በአቅሜ እደግፋለው ሲሉ በፌስ ቡክ ገፃቸው አሳውቀዋል።
"በቅድሚያ ሀገሬንና ሕዝቤን በጤና ሚኒስትርነት እንዳገለግል ለሰጡኝ እድል፣ የተሰጠኝን ኃላፊነት ማሳካት እንድችል ላሳዩኝ ያላሰለሰ ድጋፍና ጽኑ ዕምነት እንዲሁም ያቀረብኩትን የሥራ መልቀቂያ ስለተቀበሉኝ ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድን ከልብ አመሰግናለሁ።
በጤና ሚኒስቴር በተለያዩ ኃላፊነቶች በቆየሁባቸው ዘጠኝ አመታት፣ በተለይም ከሚያዝያ 2010 ዓ.ም ጀምሮ በሚኒስትርነት ባገለገልኩባቸው አንድ ዓመት ከስምንት ወር በፍጹም መከባበርና ለስራ ቅድሚያ በመስጠት በጋራ ስላከናወናቸው ተግባራት የስራ ባልደረቦቼን ፣ጓደኞቼንና የልማት አጋር ድርጅቶችን በሙሉ በእጅጉ ማመስገን እወዳለሁ:: በእነዚህ አመታት የተቀዳጀናቸው ስኬቶች ሁሉ የጋራ ጥረት ውጤቶች እንደመሆናቸው በእኩል ልንኮራባቸው ይገባል::ያላሟላናቸው ነገሮችን በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ወደ ስኬት እንደሚመጡ እርግጠኛ ነኝ::
ገና በወጣትነት እድሜ የህክምና ትምህርቴን ጨርሼ ስራ ከጀመርኩበት ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ፣ በሙያዬና በተለያዩ የመንግስት የሀላፊነት ዘርፎች ሳገለግል ያለኝን እውቀት፣ ጉልበትና የስራ ልምድ ያልሰስት ደስ ብሎኝ በስራ ላይ ለማዋል ጥሬያለሁ።
አሁን ወደ ኋላ ስመለከተው ግን በቆይታዬ ወቅት ከሰራሁት ይልቅ የተማርኩት፣ ከሰጠሁትም የተቀበልኩት እጅግ የላቀ እንደሆነ ተረድቻለሁ። "ተማሪ ካስተዋለ አስተማሪ ሁልጊዜም አለ" እንዲሉ ጥሩ ስሰራ በማበረታታት ሳጠፋም በማረም የዛሬ ማንነቴን በመቅረጽ በማንነቴ ላይ የማይጠፋ አሻራውን ላስቀመጠው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንደበቴ ከማመስገን በተጨማሪ በቀጣይ የሥራ ዘመኔ ሁሉ አቅሜ በፈቀደ መጠን ሀገሬንና ያደኩበትን ቤቴን የጤና ሚኒስቴርን ለመድጋፍ ቃል እገባለሁ:: "
አመሰግናለሁ
አሚር አማን

ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ - EBC
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች በተገለፀው ክፍት የስራ መደብ ለይ ተፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በኮርፖሮሽናችን ድህረ-ገፅና ፌስቡክ እንዲሁም የሬዲዮና የቴሌቪዥን ቻናሎች እና በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የውጭ ሰሌዳ ቦርድ ላይ ከወጣበትና ከተገለፀበት ከታህሳስ 20 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሰው ሃይል ምልመላና መረጣ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1020 በመቅረብ ወይም በተወካይ ተገቢውን የስራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት ዋናውንና የማይመለስ ኮፒ በማቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የትምህርትደረጃ እና የስራ ልምድ
በአካውንቲንግ፤ማርኬቲንግ፤ፐርቸዚንግ ፕሮኪዩርመንት ወይም ቢዚነስ ማናጅመንት፤በሎጀስቲክ
የመጀመሪ ዲግሪ---------------- 4 ዓመት
ዲፕሎማ/10+3/ ወይም ደረጃ III- 6 ዓመት
ቴክኒክና ሙያ------------------- 8 ዓመት
በአካውንታንትነት፤በኦዲተርነት፤በግዢና ንብረት አስተዳደር ስራ፤በፐርቸዚንግነት፤በፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ የሰሩ፤በትራንዚትና በተመሳሳይ የስራ ዘርፍ የሰሩ ፤ስራ ማቀድ፤የመተንተን፤የማደራጀት የማስተባበር፤የመከታተልና የመደገፍ እንዲሁም ጊዜውን ለተቋሙ ስራ ለማዋል ቁርጠኛ የሆኑ፤የለውጥ አስተሳሰብና ተነሳሽነት ያላቸው፤በስራቸው መልካም ባህሪ ያላቸው፤ታማኝና በስራመስኩ የስራ ልምድ የሚየቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡
ማሳሰቢያ፤
1. ከዚህ በላይ የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ከላይ በተገለፁ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እየቀረባችሁ ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 1020 እየቀረባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
2. አመልካቾች ለምዝገባ ሲቀርቡ ከስራው ጋር አግባብነት ያለው የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃቸውን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
3. ከደረጃ 3------5 የተጠቀሱት የትምህርት ማስረጃዎችለምዝገባ የሚያገለግሉት ለቀረበው ደረጃ ከሙያ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (ሲኦሲ) ጋር ሲቀርብ ብቻ ነው፡፡
4. የከፍተኛ የትምህርት ተቋም ወጪ መጋራትየሚመለከታቸው አመልካቾች ለምዝገባ ሲቀርቡ ከተማሩበት ተቋም የተሰጣቸውን የእዳ መግለጫና ተቀጥረው ሰርተው ከሆነ የከፈሉትን መጠን የሚያሳይ ማስረጃ ይዘው መቅረብ የጠበቅባቸዋል፡፡
5. ከውጭ አገር የተገኙ የትምህርት ማስረጃዎች በአገር ውስጥ ከሚመለከተው አካል የአቻ ግመታ ያገኙና ማስረጃ የሚቀርብባቸው መሆን ይገባቸዋል፡፡
6. አመልካቾች ለምዝገባ ሲቀርቡ ዋናውን የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃቸውን ከማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. አመልካቾች ምዝገባቸውን ለማካሄድ በአካል ቀርበው ወይም ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማስረጃቸውን በተወካይ በመላክ የተዘግጀውን ፎርም መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
8. ቀጥታ አግባብነት የለው የትምህርት ዝግጅት እና የስራ ልምድ ውጭ ለምዝገባ የሚቀርቡ ሌሎች ማስረጃዎች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
9. ለምዝገባ በአመልካቾች የሚቀርቡ የስራ ልምድ ማስረጃዎች የስራ ልምዱ የተገኘበት የስራ መደብና ደመወዝ፤ ከመቼ እስከ መቼ እንደሰሩና የስራ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን መግለፅ አለባቸው፡፡
10. የፈተና ጊዜ በውስጥ ማስታወቂያ ውይም በሬዲዮና በቴሌቪዥን አማካኝነት የሚገለፅ ይሆናል፡፡
11. አመልካቾች ተጨማሪ መረጃ ማግኝት ከፈለጉ በቢሮ ቁጥር 0115172556 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

የጤና ሚንስትሩ ሥልጣን መልቀቅ
የኢትዮጵያ ጤና ሚንስትር የነበሩት ዶክተር አሚር አማን ከኃላፊነታቸው ለቀቁ።
ከወራት በፊት የሥራ መልቀቂያን አስገብተው የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር)ን ምላሽ ሲጠባበቁ የከረሙት ዶክተር አሚር ጥያቄቸው ተቀባይነት ማግኘቱን ይፋ አድርገዋል።
በህክምና ሙያ ትምህርት የተመረቁት የቀድሞው ሚንስትር ከ2001 ጀምሮ ወደ ሥራው ዓለም የተቀላቀሉ ሲሆን ለዓመታት በጤና ጥበቃ ሚንስትር ዴኤታነትም አገልግለዋል።
ከሚያዚያ 2010 ጀምሮ ደግሞ የጤና ሚንስትር ሆነው እስከዛሬ ሰርተዋል።
በቀጣይ በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኝ ዓለም ዓቀፍ የጤና ተቋም ሥራን ሊጀምሩ እንደሚችሉ እየተነገረላቸው የሚገኙት ዶክተር አሚር የኢትዮጵያን ሕዝብ በቻሉት ሁሉ እያለገሉ እንደሚኖሩ ቃል ገብተዋል።
@Yenetube @FikerAssefa

በጃፓን ኦሎምፒክ ወቅት የጠፋው የአበበ ቢቂላ ቀለበት ከ55 ዓመታት በኋላ ለቤተሰቦቹ ተመለሰ
እኤአ 1964 በተካሄደው በጃፓን ኦሎምፒክ ወቅት አበባ ቢቂላ የቶኪዮ ማራቶን ውድድርን ባሸነፈበት ውድድር ወቅት የጠፋው ቀለበት ለቤተሰቦቹ ተመለሰ፡፡
የጠፋው የአበበ ቀለበት በወቅቱ በፅዳት ስራ ላይ በነበረች ጃፓናዊት እጅ እንደነበረ እና ከ55 ዓመታት በልጇ አማካኝነት ለአበበ ቤተሰቦች መመለሱ ነው የተገለፀው፡፡
በወቅቱ አበበ ቢቂላ ቀለበቱን በእስታዲዮም መታጠቢያ ክፍል ውስጥ ረስቶት መውጣቱ ስታዲየሙን በማጽዳት ስራ ላይ የነበሩት ባረክ እናት አግኝተውት ለአበበ ቢቂለ እንዲሰጠው ለልጃቸው እንዳስረከቡት ሚስተር ባረክ ተናግሯል፡፡
በወቅቱ የ19 ዓመት ልጅ የነበረው ሚስትር ባረክ ለግማሽ ክፍለ ዘመን የዘለለ አደራ ይዞ በዕድለኝነት ስሜት የአበበን ቤተሰብ ይቅርታ በመጠየቅ ቀለበቱን አስረክቧል፡፡
የአበበ ቤተሰብም ይቅርታውን በመቀበል ቀለበቱን ተቀብለዋል፡፡

በአማራ እና ትግራይ የሀገር ሽማግሌዎች መካከል የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው
የአማራ እና ትግራይ ክልል ህዝቦችን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር ዋነኛ አላማው ያደረገ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
"ህብረ—ብሄራዊ አንድነታችንን ለማጠናከር ውስጣዊ ችግሮቻችንን በምክክር እንፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ባለው የምክክር መድረክ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡
የምክክር መድረኩ በኢትዮጵያ የሀገር ሽማግሌዎች መማክርት ጉባኤ፣ በሰላም ሚኒስቴር እና በጀስትስ ፎር ኦል ፒ. ኤፍ. ኢትዮጵያ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የሁለቱ ክልል ህዝቦች እየገጠሟቸው ያሉ ችግሮች እና የመፍትሄ ሀሳቦች ይጠቁሙበታል ተብሎ ይጠበቃል።
Via:- EBC

ሩዋንዳ ሁለት ተከታታይ የኢትዮጵያ ድራማዎችን በትርጉም በቴሌቪዥን ማሳየት ልትጀምር ነው!
በሩዋንዳ ብሄራዊ ቴሌቪዝን ጣብያ በሆነው አር ቲቪ ሰው ለሰው እና ዘመን ድራማ በትርጉም ሊቀርቡ መሆኑ ተሰምቷል። በቅድሚያ ሰው ለሰው ለእይታ የሚቀርብ ሲሆን ለዚህ ይረዳ ዘንድ የሩዋንዳ ሃገር ተዋንዎች የሰው ለሰው ድራም ትርጉም ድምጽ ቀረጻ ላይ መሆናቸውን ታዲያስ አዲስ ዘግቧል።
@Yeneyube @Fikerassefa

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የአዳማ የኢንዱሰትሪ ፓርክን እየጎበኙ ነው
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እና በኢትዮጵያ ጉበኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የአዳማ የኢንዱሰትሪ ፓረክን በመጎብኘት ላይ ናቸው።
መሪዎቹ ለጉብኝቱ አዳማ ሲደርሱ የኦሮሚያ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትናንት ነበር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት።
Via:- FBC

የኢትዮጵያ ሳተላይት ከህዋ ያነሳችውን የመጀመሪያ ምስል ላከች!!
ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት ወደ ህዋ ያመጠቀቻት ሳተላይት ከህዋ ያነሳቸውን የመጀመሪያ ምስል ልካለች።
ምድርን እየቃኘች እና በፎቶ እየመዘገበች መረጃ የምትሰበስበውና “ETRSS-1” የሚል ስያሜን የተሰጣት የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሳተላይት የመጀመሪያ ፎቶን ከህዋ እንደላከች ነው የተገለፀው።
ሳተላይቷ ቻይና ከሚገኘው የሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ባለፈው አርብ ነበር የመጠቀቸው።
የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር፣ ከግብርና ጋር የተያያዙ ጥናት እና ምርምሮችን ለመሥራት እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ የመሠረተ ልማት ተግባራትን ለማከናወን ታስችላለች ነው የተባለው።
በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ይህን የመጀመሪያ ምስል ይፋ አድርገዋል፤ ሆኖም ምስሉ የት አከባቢን የሚያሳይ እንደሆነ አልተመለከተም።

ዳሽን ባንክ በ100 ሚሊየን ብር የስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ።
የኢትዮጵያ ታለንት ፓወር ሲሪየስ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ ፕሮጀክት፥ ስራ ፈጠራን ማበረታታት፣ ክህሎት ላላቸው ዜጎች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግና የስራ አጥነትን ለመቅረፍ ያግዛል ነው የተባለው።
ከዚህ ባለፈም ለሃገራዊው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እቅድ ትግበራ የራሱን ሚና ይወጣል ተብሎም ይጠበቃል።
ፕሮጀክቱ በዚህ አመት በተመረጡ ስድስት ከተሞች ተግባራዊ እንደሚደረግም ባንኩ አስታውቋል።
በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ዜጎችም የስራ ፈጠራ ክህሎትና የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚያገኙ ሲሆን፥ ስራ መጀመር የሚያስችል ድጋፍም ከባንኩ ያገኛሉ።
ፕሮጀክቱ የስራ ፈጠራ ስልጠና፣ የጥቃቅን እና አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ግንባታ፣ የከፍተኛ ትምህርት የፋይናንስ ድጋፍ መርሃ ግብር፣ የፋይናንስ ተደራሽነት መርሃ ግብር፣ የቢዝነስ ክለብ ምስረታ፣ የገበያ ትስስር እና የእሴት ሰንሰለት የፋይናንስ ድጋፍ ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።