YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
ዲጅታል የኤሌክትሮኒክስ መሸጫ
DIGITAL ELECTRONICS - SHOPPING
___________________________
የተወደዳቹ የኢትዬጵያ ቤተሰቦች እና ውድ የፈጠራ ስራ ባለሞያዋች
🤖ኣዳዲስ ግኝቶች
🇨🇦አለም አቀፋና ኣገር ኣቀፍ ውድድሮች
ለፈጠራ ስራ ምትፈልጓቸው ማንኛውም እቃ ለመግዛት
🛰 ARDUINO, SENSOR ለመግዛት ይቀላቀሉን
#ኣድራሻችን፡ 4 ኪሎ: ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ህንፃ፡ 105ሀ

join @Ethioinvention
@Ethioinvention
Forwarded from YeneTube
ታላቅ ቅናሽ!!!
ወብ የሆኑ የወንዶች አልባሳትን ከRJ FASHION በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ.
ጂንስ ሱሪ,ቱታ,ሸሚዞች አሉን
ለበለጠ መረጃ
:0900628132
TELEGRAMPAGE:-
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
Forwarded from FERES ፈረስ
ስራ ጀምረናል አሁኑኑ ፈረስ ይዘዙና የፈለጉበት ቦታ ይሂዱ

ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም መተግበሪያውን ያውርዱ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.feres.user
በምድር ባቡር የሚገኙት የኑጉሳውያን ባቡሮች ወደ እዮቤልዩ ቤተመንግሥት አመሩ።

ንጉሥ ሃ/ስላሴ በ1924ዓ.ም በፈረንሳይ መንግስት እና በ1950ዎቹ በእንግሊዝ መንግስት በስጦታ የተበረከቱላቸው 4 የባቡር ፈረፋንጎዎች ትላንት (9-4-2012ዓ.ም ) ወደ አስገነቡት ቤተ መንግስት አምርተዋል ።ከፍልውሃ ከፍ ብሎ በሚገኘውና በአሁን ወቅት የክብርት ፕሬዚዳንትዋ መቀመጫ ወደ ሆነው ያመሩት ቤተመንግሥቱን ወደሙዚየምነት ለመለወጥ በሂደት ላይ ስለተኮነ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ። ለገሀር ባቡር ጣብያ ሙዚየም ውስጥ የነበሩት ባቡሮቹ ካዲላክ መኪኖች ወደሚገኙበት ቤተ መንግስት አምርተዋል።

Via HuluAddis on Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
ሰሞኑን መነጋገሪያ የሆነው የ1ኛ ዐመት ከፍተኛ ትምህርት መማሪያ ሰነድ በአስተያየት እንዲዳብር ያሰራጨሁት ረቂቅ እንጅ ያለቀለት አይደለም- ብሏል የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ዛሬ በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መግለጫ፡፡ ለማስተማሪያት ለትምህርት ተቋማት የተላከ በማስመሰል የሚሰራጨው ወሬ ሐሰት ነው፡፡ እስከ ታህሳስ 16 ከትምህርት ተቋማት አስተያየቶች ከተሰበሰቡ በኋላ ረቂቁ የታሪክ መምህራን እና ሌሎች አካላት ለሚሳተፉበት ሀገር ዐቀፍ ጉባዔ ይቀርባል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
💥ማስታወቂያ💥
School of American English

📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ

አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን

አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022


💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥

ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል

T.me/SCHOOLOFAMERICAN
ዋልታ አራት የተቋሙን ሰራተኞች ከስራ አገደ!!

በድርጅታችን ዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽ ኮርፖሬት የፌስቡክ ገፅ waltainfo.com በ03/04/12 ዓ.ም ከትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካዔል ጋር በተያያዘ ከተቋማችን እውቅና ውጪ ሀሰተኛ መረጃ መለቀቁ ይታወሳል፡፡

ይህንን ተከትሎም ተቋማችን ወዲያውኑ ለተፈጠረው ክስተት ይቅርታ መጠየቁ እና ጉዳዩን አጣርቶ እንደሚገልፅ አስታውቆ ነበር፡፡

በዚህም መሰረት ተቋማችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ሲሰራ ቆይቷል፡፡

በመሆኑም ሁኔታውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲና ፖሊስ እየመረመሩት ይገኛል፡፡

የምርመራ ውጤቱን መጨረሻ እንደምንገልፅ የተጠበቀ ሆኖ ተቋማችን ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው ብሎ በጠረጠራቸው አራት የተቋሙ ሰራተኞች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል፡፡

ዛሬ የዋልታ የስራ አመራር ቦርድና ማኔጅመንት አባላት ክስተቱ ከተፈጠረበት ዕለት ጀምሮ የተደረገውን ማጣራት መነሻ በማድረግ ውይይት ካካሄዱ በኋላ ሰራተኞቹ ላልተወሰነ ጊዜ ከስራ እንዲታገዱ ወስነዋል፡፡

በቀጣይም ከአስተዳደራዊ እርምጃ ባለፈ የፍትህ አካላት ድርጊቱን በፈፀሙት አካላት ላይ አጣርቶ በሀገሪቱ ህግ መሰረት የሚወስዱትን እርምጃ ተከታትለን ይፋ የምናደርግ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ድርጅታችን በሀገሪቱ የሚዲያ ኢንዱስትሪ ውስጥ እየፈጠረ ያለውን በጎ ተፅዕኖ በእውነትኛ መረጃ እና የህዝብን ድምፅ ባከበረ መልኩ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እናረጋግጣለን!!

Via ዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት
@YeneTube @FikerAssefa
ደም ሳይቃቡ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መገንባት ያስፈልጋል - ጠ/ሚ ዐቢይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው የአማራ እና የኦሮሞ ባለሃብቶች ኮሚቴ በተዘጋጀው የሰላም ኮንፈረስ ላይ ንግግር አድርገዋል።
በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደዚህ አይነት መድረኮች እንዲዘጋጁ ድጋፍ ላደረጉ ምሁራን፣ አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ባለሀብቶች ምስጋና አቅርበዋል።እንዲሁም በሀገሪቱ የሰላም አየር እንዲመጣ እና ሰዎች ሀሳባቸውን በነፃነት ማንሸራሸር እንዲችሉ ድጋፍ ያበረከቱ ቄሮዎችና ፋኖዎችን አመስግነዋል።

የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች በርካታ ቁጥር ያላቸው ህዝቦች መሆናቸውን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በጋራ ሲሆኑና ሲተባበሩ ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ እና በተቃራኒው ሲለያዩ የሚለውጡት ነገር እንደማይኖር ገልፀዋል።ሁለቱ ብሄሮች በሃገሪቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው ህዝቦች መሆናቸውን ጠቅሰው፥ መዋደድ፣ መከባበር እና መፋቀር እንደሚገባቸውም አውስተዋል።
በቀጣይነት ሁለቱም ህዝቦች በሁሉም አቅጣጫ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ጋር በጋራ በመሆን የተለያዩ ውይይቶችን እንደሚያዘጋጁ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።

በኢትዮጵያ ያለው ልዩነት ፀጋ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሻለና የተለያየ ነገር ያስፈልጋልም ብለዋል በንግግራቸው።
አብሮ ለመኖርም የአብሮ መኖር ጥቅምን መገንዘብ፣ የሌሎችን እሴት ማወቅ እና ሳይጠፋፉ አብሮ መኖር እንዴት ይቻላል የሚለውን መመለስ ያስፈልጋል ሲሉም ገልፀዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብሮ ሲኖር የሃሳብ ግጭት አይኖርም ማለት ሳይሆን በዚህ የሀሳብ ልዩነት መገዳደልና መጠፋፋት አያስፈልግም ማለት መሆኑንም አስረድተዋል።ወጣቶች የታገሉት፣ የደሙት እና የደከሙት ተጨማሪ ወጣት እንዳይሞት እንጅ ሊማር የሄደ በወጣበት እንዲቀር ባለመሆኑ የአማራና የኦሮሞ ወጣቶች ተቀራርበው መስራት እንደሚገባቸው አስታውሰዋል።

ዩኒርሲቲዎችን በተመለከተም ባስተላለፉት መልዕክት ዩኒቨርሲቲ የሚኬደው ለመገዳደል ሳይሆን ለመማር መሆኑን ጠቅሰው፥ እነዚህን ወጣቶች ለግጭት የሚጠቀሙ አካላት እንደማይጠፉ አንስተዋል።በአሁኑ ወቅት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ጠንካራ ጥበቃ የማደራጀት ስራ መከናወኑን እና በጥፋተኞች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም ጠቅሰዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለዴሞክራሲያ ሽግግር ባደረጉት ንግግር ሰላም እንዲሰፍንና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ደም መቀባባት እንደማያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።ወጣቶችም አሁን ካሉበት ቦታ በላይ እንዲያስቡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁከት የተጠረጠሩ 16 ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማስታወቁን ኢትዮ ኤፍኤም ዘግቧል፡፡ በጥቅምቱ የኦሮሚያ ክልል ግድያ ወንጀሎች ከሚፈለጉት 337 ተጠርጣሪዎች ደሞ 250ዎቹ ተይዘዋል፡፡ ይህ የተገለጸው የዐቃቤ ሕግ ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዝናቡ ቱኑ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ከልል ዎላይታ ሶዶ ከተማ ሁከትና ረብሻ ይነሳል በሚል ሥጋት የከተማይቱ የወትሮ እንቅስቃሴ ዛሬ ተስተጎጉሎ ዋለ።

የከተማይቱ ነዋሪዎችና ባለስልጣናት እንዳረጋገጡት ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ የመንግስት አገልግሎት መስጪያ ተቋማት፣ የንግድ መደብሮችና መዝናኛ ተቋማት ተዘግተዉ ነዉ የዋሉት።የትራንስፖርት አገልግሎትም የለም።ፀጥታ አስከባሪዎች በዞኑ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን፣ የዎላይታ ዞን በክልል እንዲደራጅ የሚጠይቁ የፖለቲካ አቀንቃኞችና ተባባሪዎቻቸዉ ያሏቸዉን ሰዎች ማሰራቸዉም ተነግሯል።የእስረኞቹ ማንነት፣ ቁጥርና የታሰሩበት ስፍራ ግን በዉል አልተገለጠም።ዞኑን የሚቆጣጠረዉ ወታደራዊ ዕዝ ወይም ኮማንድ ፖስት በበኩሉ የዎላይታ ሶዶ ከተማን ጨምሮ በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎች የተቃውሞ ሰልፎች እንዳይደረጉ፣ የሞተር ብስክሌቶች ጉዞዎችንና እንቀስቃሴዎችንም አግዷል።ሁከት ይነሳል በሚል ሥጋት እንቅስቃሴዎች ከመገደባቸዉ ባለፍ እስከ ዛሬ አመሻሽ ድረስ የአደባባይ ተቃዉሞ፣ ሁከትም ሆነ ግጭት የለም።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በቀን 10/04/2012ዓ.ም በባ/ዳር ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ብዛቱ 1,702 የሆነ ህገ ወጥ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

በባ/ዳር ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ምድረ ገነት ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሠራተኞች እና የፊደራል ፖሊስ አባላት በቅንጅት በጥናት ተለይቶ በነበረ ቀንደኛ ኮንትሮባንዴስት ቤት በደረሰ የህብረተሰብ ጥቆማ መሠረት በተደረገ ብርበራ /ኦፕሬሽን/በቀን 10/04/2012 ዓ.ም ብዛቱ 1288 የክላሽ ጥይት እና 414 የብሬን ጥይት በድምሩ 1702 ህገ ወጥ ጥይት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ከጉዳዪ ጋር በተያያዘ 02 ተጠርጣሪ ተይዘው ጉዳያቸው በህግ አግባብ እየታየ ይገኛል።

Via Ministry of Revenue
@YeneTube @FikerAssefa
IMF ለኢትዮጵያ የ2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር ብድርና ድጋፍ አጸደቀ!

የአለም አቀፉ የፋይናንስ ተቋም (IMF) ስራ አስፈጻሚ ቦርድ በሶስት አመታት ተግባራዊ የሚሆን የብድርና የእርዳታ የሚውል 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር ይፋ አድርጓል።ይህም በቅርቡ በመንግስት ይፋ ለተደረገው ‘’የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ’’ ማስፈጸሚያ እንደሚውል ይጠበቃል።ድጋፉ ተግባራዊ ከሚሆንባቸው ዘርፎች ዋና ዋናዎቹ

1ኛ) የውጭ ምንዛሬ እጥረት ጫናን ማቃለል

2) በገቢና ወጭ ምርቶች ያለውን አለመጣጠን መቀነስ

3) የብድር ጫናን ለመቋቋም/ተጋላጭነትን ማስቀረት

4) የአገር ውስጥ የሃብት ምንጮችን የማሰባሰብ አቅምን ማጎልበት ይገኙበታል።

ድጋፉ በጥቅሉ ሲታይ በኢኮኖሚው ውስጥ ቀጣይነት ላለው እድገት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማበረታታትና ለማሳደግ፣ ስራ አጥነትን ለመቀነስ፣ በዝቅተኛ የገቢ ምንጭ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማዕከል ያደረገ የልማት ትልምን የመተግበሪያ ማዕቀፍ ተድርጎ ሊወሰድ ይችላል።

ምንጭ: በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
‹‹ሕዝቡ የሚፈልገውን መርጦ በሚፈልገው ፓርቲ ይመራ ዘንድ ምርጫው በሠላማዊ ሁኔታ እንዲካሄድ ነው ምንፈልገው፡፡›› የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ መጭው ሀገራዊ ምርጫ በሠላም እንዲካሄድ ለማድረግ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ለሠላም እየተሠራ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ሕዝቡ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የሚፈልገውን መርጦ በሚፈለገው ፓርቲ ይተዳደር ዘንድ የክልሉ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ነው ያስታወቁት ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡የክልሉ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች እንዲጠበቁ ሠላም አስፈላጊ መሆኑንም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

‹‹አሁን ባለው የክልሉ ነባራዊ ሁኔታ አንፃራዊ ሠላም ሰፍኗል›› ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ከዚህ በፊት መረጋጋት ባልነበረባቸው አካባቢዎች ከሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋርም በሠላም አስፈላጊነት ዙሪያ ተደጋጋሚ ውይቶች ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህን ተከትሎም በክልሉ ለማልማት ፍላጎት ያላቸው የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ባለሀብቶች ፍላጎት እያሳዩ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ ከቅማንትና አማራ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በተደረገው ውይይት አበረታች ውጤቶች መታየቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ ከቅማንት ኮሚቴ ጋር በተደረሰው ስምምነት መሠረትም የአካባቢውን እንቅስቃሴ ሠላማዊ ማድረግ እንደተቻለ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጠቁመዋል፡፡

አሁን ባለው የክልሉ ነባራዊ ሁኔታ አንጻራዊ ሠላም እንደታየና ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ በየትኛውም የክልሉ አካባቢ ያለምንም ችግር መድረክ ፈጥሮ አባላቱን ማወያየት የሚችል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ይህን ጉዳይ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ራሳቸው ምስክርነት እየሰጡበት እንደሆነም ገልጸዋል፡፡ ‹‹ከሁከትና አለመረጋጋት የሚገኝ ነገር የለም፤ ምርጫው በሠላማዊ ሁኔታ እንዲካሄድ ነው ምንፈልገው፤ በምርጫም ሆነ በሌሎች ነገሮች አሳብቦ ወደ ግጭት የምናመራ ከሆነ የነበርንበትን ችግር ማስቀጠል ነው›› ሲሉም የተጀመረው ሠላም እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የክልሉ ኢንቨስትመንት እድገት እንዲያንሠራራ፣ የሥራ እድል ፈጠራ እንዲስፋፋ የክልሉ ሕዝብ አሁን ያለውን አንጻራዊ ሠላም መጠበቅ እንደሚገባው ርዕሰ መስተዳድሩ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ አካባቢ ትናንት ማምሻውን የፀጥታ መደፍረስ አጋጥሞ ነበር፤ ብሏል የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት። አሁን ላይ ሁኔታዎች ወደ መረጋጋት እየተመለሡ ነውም ብሏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ በመልካም ወጣት ፕሮጀክት ስም የከተማ አስተዳደሩ ለጀመረው የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ የከተማ አስተዳደሩ ለጀመረው የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር በመልካም ወጣት ፕሮጀክት ስም የአስር ሚሊዮን ብር ድጋፍ ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በተገኙበት አስረክቧል፡፡የመልካም ወጣት ፕሮጀክት የከተማ አስተዳደሩ የጀመረውን የህጻናት ምገባ በመደገፍ ለሚቀጥሉት አምስት አመታት በጠቅላላው የ 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንደሚያደርግም አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ተናግሯል፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ በበኩላቸው አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ለተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ላደረገው ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ህግ እና ተቋማዊ ይዘት እንዲኖረው እና በዘላቂነት እንዲተገበር መወሰኑና የተማሪዎች የምገባ ኤጀንሲ መቋቋሙም ይታወሳል፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ አስተዳደር ትናንት አመሻሽ የበሃይማኖት ተቋማት ላይ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደርሷል፡፡ የፀጥታ አካላትና ሕዝቡ ባደረጉት ጥረት እሳቱ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር እንደዋለም ታውቋል፡፡
ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ ያኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው አሁን ሁኔታዎች እየተረጋጉ ነው፤ ተጠርጣሪዎችንና የችግሩን መንስኤዎች የመለዬት ሥራም እየተከናወነ ነው፡፡ የጉዳት መጠኑ በውል አለመታወቁም ተመላክቷል፡፡

ምንጭ: አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸህ ሰኢድ አሕመድ በሞጣ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ አራት መስጂዶች መቃጠላቸዉንና የሙስሊም ሱቆችና ድርጅቶች ላይ ዝርፊያ መፈጸሙን ገልጸዋል።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
ሞጣ ከተማ አስተዳደር በቤተ እምነት ተቋማት ላይ የደረሰው የቃጠሎ አደጋ በተመለከተ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ትናንት ታኀሣሥ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡20 አካባቢ በሞጣ ከተማ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የእሳት ቃጠሎ መከሰቱን ተከትሎ በሌሎችም የሃይማኖት ተቋማት ላይ የእሳት ቃጠሎ መፈጸሙን ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ ያገኙትን መረጃ ጠቅሰው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ማኅበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል መምሪያ ኃላፊ ጀማል መኮንን ተናግረዋል፡፡በቡድን በመሰባሰብ መስጂዶች ላይ ጥቃት እንደተፈፀመ ነው ኮማንደር ጀማል የተናገሩት፡፡በድርጊቱ በሞጣ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 03 የሚገኝ መስጂድ ሙሉ በሙሉ ሲቃጠል፣ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን እና ቀበሌ 05 እና 06 የሚገኙ መስጂዶች ደግሞ በከፊል እንደተቃጠሉና አንድ የገበያ ማዕከል በቃጠሎና በመሰባበር ጉዳት እንደደረሰበት ኮማንደር ጀማል መኮንን ለአማራ ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ሪፖርት እንዳልተደረገም አመላክተዋል፡፡ ፖሊስ ችግሩን በማስቆም የማረጋጋት ሥራ እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ በቀጣይ ተጠርጣሪዎችን አፈላልጎ በመያዝ እርምጃ እንደሚወሰድም አስታውቀዋል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ሃይማኖትንና ማንነትን መሠረት አድረገው የሚነሱ ችግሮችን ኅብረተሰቡ ከማባባስ ይልቅ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር የማርገብና የማረጋጋት ልምድ ሊዳብር እንደሚገባ ኮማንደር ጀማል መኮንን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
"በብልጽግና ጎዳና ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ የሀገራችንን የቆየ የሃይማኖቶችን የመቻቻልና አብሮ የመኖር ባህል የሚፃረሩ ጽንፈኛ አካሄዶች ቦታ የላቸውም:: እንዲህ ያሉ የፈሪ አካሄዶችን አጥብቄ አወግዛለሁ:: መላው ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያንም የመከባበርና አብሮ የመኖር ጥልቅ ዕውቀታችሁን እንድታጋሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ:: ከፋፋይ አጀንዳዎችን መረዳትና መጠየፍ የጋራ ዕድገታችንን ለማረጋገጥ ያስችላል::"

-ጠ/ሚ አብይ አህመድ
@YeneTube @FikerAssefa
140.2 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የጎሬ-ማሻ-ቴፒ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ!

በመንገዱ ጅማሮ መርሃ ግብር ላይ ከፍተኛ የክልሉ እና የፌደራል የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል። የጎሬ-ማሻ-ቴፒ ፕሮጀክት የደቡብ ፣ የጋምቤላ እና የኦሮሚያ ክልሎችን በአቋራጭ የሚያገናኝ ነው። የመንገድ ፕሮጀክቱን በ4.5 ቢሊዮን ብር ለመገንባት ጨረታዉን አሸንፎ ወደ ስራ የገባዉ የደቡብ ኮሪያው ሃዮንዳይ ዴቨሎፕመንት ካምፓኒ ነው።

የፕሮጀክቱን የማማከርና የቁጥጥር ስራ ደግሞ ሱሶንግ ኢንጂነሪንግ ከሃገር በቀሉ ኔት ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በጋራ ያከናውናሉ፡፡ የግንባታዉ ሙሉ ወጪ የሚሸፈነዉም በኢትዮጵያ መንግስት እና በኮሪያው ኤግዚም ባንክ ነው፡፡ የመንገዱ መገንባት ከአዲስ አበባ ተነስቶ በጅማ አድርጎ በመቱ ወደ ጋምቤላ የሚዘልቀው ዋና መንገድ እና ከአዲስ አበባ ተነስቶ በጅማ በኩል ወደ ሚዛን ቴፒ የሚሄደውን ሌላ ዋና መንገድ በአቋራጭ የሚያስተሳስር ነው።

የመንገዱ ስራ በአራት ዓመት ከስድስት ወራት ዉስጥ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ መርሃ ግብር ተይዞለታል ። የመንገዱ የጎን ስፋት ትከሻን ጨምሮ በገጠር 10 ሜትር ፣ በቀበሌ 12 ሜትር ፣ በወረዳ 19 ሜትር እና በዞን ከተማ 21.5 ሜትር ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የመንገድ ዘርፉ የግብርና ፣ የማዕድን ፣ የባህልና ቱሪዝም ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፣ የብሄራዊ ሎጂስቲክስ እና ሌሎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎችን በሚደግፍ መልኩ እንዲተገበር ለማስቻል የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ይህ መንገድ እነዚህን ዘርፎች በሚደግፍ መልኩ ታስቦ የሚገነባ ነው፡፡

ምንጭ:ERA
@YeneTube @FikerAssefa